Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

 • January 2023
  M T W T F S S
   1
  2345678
  9101112131415
  16171819202122
  23242526272829
  3031  
 • Archives

 • Categories

 • Recent Posts

Posts Tagged ‘ካራማራ’

ዐቢይ አህመድ እስክንድር ነጋን በረሃብ ቀጥቶ አሰደበደበው

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on July 4, 2020

ወገኖቼ፡ እጅግ በጣም የከፋ ግፍ በሃገራችን እየተፈጸመ ነው። ኦሮሚያ በተባለው ሲዖል በናዚዎች ጊዜ እንኳን ታይቶና ተሰምቶ በማይታወቅ መልክና እጅግ ዘግናኝ በሆነ የግድያ ዘመቻ ወገኖቻችን አካላቸው ተቆራርጦ፣ ተጠብሶና ተሰቅሎ እየታየ እንደሆነ ምንጮች ጠቁመዋል። ባካችሁ ወገኖች እያንዳንዷን ነገር መዝግቡልን፣ ቅረጹልን!

በሌላ በኩል የባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ከፍተኛ አመራሮች አቶ እስክንድር ነጋ እና አቶ ስንታየሁ ቸኮል መታሰራቸው የሚታወስ ነው ነገር ግን በአሁን ሰአት ከፍተኛ ድብደባ እና እንግልት እየደረሰባቸው ነው። ከውስጥ የወጡ መረጃዎች እንደሚያሳዩት ለ ሁለት ቀናት ምንም አይነት ምግብ እንዳልቀረበለት እና በረሀብም ጭምር እየቀጡት ነው። ልብ በሉ፦ እንድ እምነስቲ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች ነንየሚሉት ግብዝ ድርጅቶች ጸጥ ብለዋል። ኢትዮጵያውያን የሚፈተኑበት ወቅት አሁን ነው!

“…ጦርነት ውስጥ እንገባለን!” ብሏል እኮ ገዳይ አብይ አስቀድሞ። እስካሁን የተናገራቸውን ጽንፈኛ ንግግሮች ሁሉ በተግባር ላይ እያዋላቸው ነው። ከጀግናው ኢንጂነር ስመኘው እስከ ጽንፈኛው አጫሉ ሁሉንም የገደላቸው ዐቢይ አህመድ አሊ ነው። 100%! እርግጠኛ ነኝ።

የበሻሻ ቆሻሻን የባሌ ንግግር እናስታውስ፦

ኦሮሞ እስኪነቃ ነው እንጂ፣ እስኪነሳ ነው እንጂ ሲነሳ ሚዳቋ አትበላንም፤ እኛ ዝሆን ነን፤ እንሰብራለን፤ እንበላለን፤ እንገዛለን። ሃሳብ አለን፤ ድርጅት አለን፤ ከአለም ጋር ግንኙነት አለን፤ ህዝባችን በስራ ያውቀናል፤ እኛም ህዝባችንን እናውቃለን፤ ሽማግሌዎቻችንን እናውቃለን፤ ተያይዘን መላውን አፍሪካን ለመለወጥ፣ ይሄ ዘመን የእኛ ስለሆነ፣ ይህን ዘመን የሰጠን እግዝያብሄር በመሆኑ አሳልፈን ሰጥተን ዳግም ወደ ባርነት ለመመለስ አንፈልግም፤ ያ ደግሞ ተመልሶ አይመጣም። እጃችሁ የገባውን ነገር ጠብቁ፤ ቆጥቡ፤ አጠንክሩ፤ ጉድለት (ስህተት) ካለ ምከሩ። ያለበለዚያ ይህን ከጅ ካወጣን አጥር ውስጥ ተቀምጠው እንደሚያለቅሱት ዓይነት ለቅሶ ስለሚሆን፣ ከዚህ በኋላ ለኦሮሞ ለቅሶ የማይሆንለት ስለሆነ፣ ያገኘነውን ይዘን፣ የቀረውን ሞልተን፣ ወደ ፊት መሄድ እንድንችል”

_________________________________________

Posted in Conspiracies, Ethiopia, Infos | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

አብዮት አህመድ አንድ ትውልድ የቀጠፈውን ኦሮሞውን መንግስቱን ለመመለስ “ካራማራን” አነሳ

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on March 6, 2020

ያውም በአድዋ መታሰቢያ በዓል ማግስት። እያየን ነው? እባቡ አብዮት የመስቀል ደመራን በዓል በኢሬቻ፣ የአድዋን ደግሞ በካራማራ ለመተካት ሰውን ቀስ በቀስ በማለማመድ ላይ ይገኛል።

ሞኙ ኢትዮጲያዊ ባለፈው ታሪክ ሂደት ላይ እንዲጠመድና ለፉት ነገሥታት ስለሠሩት እንዲጨቃጨቅ ይደረጋል፤ እነዚህ የኢትዮጵያ ጠላቶች ግን በጀት ፍጥነት ሃገራችንን በመሸጥ እና በመቋረስ ላይ ይገኛሉ። እነዚህ ታሪክ የሌላቸው ወሮበሎች ታሪክህን በመስረቅ ታሪክ ለመስራት ቆርጠው ተነስተዋል። ወጣቱ ያለቸው አንዲት ሃገ ር ኢትዮጵያ ብቻ ናት፤ ነገር ግን አባቶቹ ያቆዩለትን ይህችን ሃገር ከጥፋት ከማዳንና እራሱንም ከመከላከል ይልቅ እንደተመቸው ድብ የሦስት ወር እንቅልፍን መርጧል፤ ይህን ወጣት ምን እንዳደረጉት፣ በምን በክለው እንዳስተኙት ለማወቅ ከባድ ነው። ዲያስፐራ ባለው ሃገርወዳድ ከበስተጀርባ አንድ ኢትዮጵያዊ የጥላ መንግስት (Shadow Government) በይፋ ተመሥርቶ ህዝቡና ኢትዮጵያዊ የሆነው የሠራዊቱ አባል ለአመፅ እስካልተቀሰቀሰ ድረስ እንደምናየው የኢትዮጵያ ልጆች የወሮበሎቹ የጠላት ቅጥረኞች መጫወቻ መሆኑን ይቀጥላሉ።

እስኪ ተመልከቱ ወገኖቼ 20 ልጃገረድ ተማሪዎች ለ80 ቀናት ያህል ታግተዋል፤ የነርሱን ጉዳይ በማስመልከት ተቃውሞ ሰልፍ ለማድረግ የማይገባቸውና ብቃት የሌላቸው፤ ወይንም ህን ተብለው የተመረጡ የግራኝ አህመድ ደጋፊዎች አንድ የዝግጅት ኮሜቴ እንዲያቋቁሙ ተደረጉ፤ በጥቂት ሰዓታት ውስጥ የተቃውሞ ሰልፉ እንዳይካሄድ ተወሰነ፤ ልክ እንደ መስከረም ፬ቱ። በሌላ በኩል ግን ወጣቱ ልክ ሆዱ እንደሞላና እንቅልፍ እንደጠገበ ሰው በአደባባይ ወጥቶ እንዲጨፍርና በዓላትን ጸጥ ብሎ እንዲያከብር ፈቅደውለታል፤ በዚህም አንገብጋቢ የሆኑት ጉዳዮች እንዲረሱና ሁሉም ነገር ኖርማል እንደሆነ ተደርጎ እንዲቆጠር ለማድረግ እየተሞከረ ነው። በአደዋ መታሰቢያ ሆነ በካራማራው በዓላት ላይ የታገቱትን ምናልባትም የተገደሉትን እህቶቻችንን የሚያስታውስ

አንድ መፈክር እንኳን ይዞ የወጣ ሰው የለም። በየጎዳናው እየዞሩ የበዓሉን ተሳታፊዎች ሲጠይቁ የነበሩት “ገለልተኛ” የሚባሉት ሜዲያዎች እንኳን በዓላትን ለማክበር እድሉን ያላገኙትን የታገቱት እህቶቻችን ጉዳይ አስመልክቶ ጥያቄዎችን ሲጠይቁ አልተሰሙም? ይህ ምን ዓይነት ደካማ ትውልድ ቢሆን ነው?

_______________________________

Posted in Ethiopia, Infos, Life | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

የግራኝ አህመድ መንግስታዊ ሽብር በ እስክንድር ነጋ ላይ

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on March 6, 2020

29ኛ ጊዜ እንዲሰለጥኑ ከተደረጉት የኦሮሚያ ልዩ ሃይል ውርንጭላዎች አንዱ ዛሬ በአዲስ አበባ እስንድርን በድጋሚ ተተናኮለው። ለመጭው “ምርጫ” እየተለማመዱ ነው … ጦርነት ውስጥ እንገባለን ብሏል ገዳይ አብይ…

____________________________

Posted in Ethiopia, Infos | Tagged: , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

 
%d bloggers like this: