[የማቴዎስ ወንጌል ምዕራፍ ፳፬፥፴፯]
“የኖኅ ዘመን እንደ ነበረ የሰው ልጅ መምጣት እንዲሁ ይሆናልና።”
ድንቅ ነው፤ እግዚአብሔር በደመናዎች ላይ ብዙ ምልክቶችን እያሳየን ነውና ወደ ታች ሳይሆን ወደላይ መመልከቱን ማዘውተር ሊኖርብን ነው።
በእኛ በኢትዮጵያውያን ዘንድ “ሰባቱ ኪዳናት” ተብለው የሚታወቁትና የቅዱሱ ኪዳን አካላት የኾኑት፡ የኢትዮጵያዊነት ተዋህዶ ሃያማነኖታችን መሠረቶች፡ መደበኛ ስማቸውና መለያ ምልክታቸው ተለይቶና ተዘርዝሮ ይገኛል። እነዚህም፦
-
ኪዳነ አዳምና ሔዋን፥
-
ኪዳነ ኖኅ፥
-
ኪዳነ መልከ ጼዴቅ፥
-
ኪዳነ አብርሃም፥
-
ኪዳነ ሙሴና
-
ኪዳነ ዳዊት፥ በመጨረሻም፡
-
በድንግል ማርያምና በኢየሱስ ክርስቶስ የተገኘው “ኪዳነ ምሕረት”
የሚባሉት ናቸው።