የቡልጋሪያ ጠቅላይ ሚንስትር ቦይኮ ቦሪሶቭ ከቡልጋሪያ ኦሮቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ፓትርያርክ ኒዖፊት ጋር ከተገናኙ በኋላ መንግስት በኮሮና ሳቢያ ለ ሆሣዕና ፣ ለሕማማት / ቅዱስ ሳምንት እና ለፋሲካ ዓብያተ ክርስቲያናት መዝጋት እንደማይችልና እንደማይዘጋም በድጋሚ ገልጸዋል፡፡
ጠቅላይ ሚንስትሩ የሚከተለውን ተናግረዋል፦
“እንዴት የዚህችን ቤተ ክርስቲያን በሮች ለመዝጋትና ካህናቱን ለማባረር እናስባለን? የማይታሰብ ነው፡፡”
“ይህች ቤተ ክርስቲያን እኮ እኛን ቡልጋሪያውያንን ከኦቶማን ቱርኮች ባርነት ነፃ አውጥታናለች፡፡ ፖሊስ ልኬ አብያተ ክርስቲያናት እንዲዘጉ ለማድረግ የማይሆን ነው፤ አላስበውም።”
“የኦርቶዶክስ ሃይማኖታችን ፣ እንደምናነበውና እንደምናየው እጅግ በጣም ብልህ ፣ ለሁሉም ነገር መልስ ያላት ፣ ብዙ ማስተማር የምትችል ሃይማኖት ናት። ቅዱሱ መጽሐፋችን “ያለ ጌታ ምንም ማድረግ አንችልም” ይላል ፡፡ ስለሆነም ያለ እርሱ ምንም ማድረግ የማንችል ከሆነ ወደ እርሱ የምንጸልይባቸውን ዓብያተ ክርስቲያናትን እንዴት መዝጋት እችላለሁ? አይሆንም!” በማለት አክለዋል፡፡”
ቡልጋሪያ በክርስቶስ ተቃዋሚዎቹ ኦቶማን ቱርኮች መሀመዳውያን እ.አ.አ. ከ 1396–1878 ዓ.ም ለ፭ መቶ ዓመታት ያህል የቆየ አስከፊ ባርነት(የጨለማው ዘመን ይሉታል)፤ ከዚያ ደግሞ ከ 1944–1990 ዓ.ም ድረስ በብልሹውና ጨካኙ የኮሙኒዝም ሥርዓት የተሰቃየች ሃገር ነበረች። ዛሬ የኦርቶዶክስ ክርስትናን ጣፋጭ የነፃነት ጣዕም ስላዩት ካለፉት የእስልምና እና ኮሙኒዝም ከንቱ ሥርዓቶች ጋር እያነጻጸሩ በበጎ መኖር ጀምረዋል። ተመስገን! በሃገራችን ደግሞ መደረግ የሌለባቸውን ለውጦችን በማድረግና በጭራሽ መመረጥ የሌለባቸውን ከሃዲ ፖለቲከኞች ስልጣን ላይ በማስቀመጥ ከእነ ቡልጋርያ ተቃራኒ የሆኑ አሳዛኝ ክስተቶች እየታዩ ነው።