Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • June 2023
    M T W T F S S
     1234
    567891011
    12131415161718
    19202122232425
    2627282930  
  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

Posts Tagged ‘ኦርቶዶክስ’

Axum, Ethiopia: ‘Ghosts’ at Emperor Kaleb’s Tomb?

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on May 28, 2023

የአፄ ካሌብ መቃብር፣ አክሱም | ሰውዬው በአፄ ካሌብ መቃብር ‘መናፍስት አየሁ’ ይለናል

❖❖❖ እንኳን ለታላቁ መናኝ ንጉሥ ቅዱስ አፄ ካሌብ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል/ መታሰቢያ አደረሰን።❖❖❖

👑 ቅዱሱን ንጉሥ አፄ ካሌብን በዓለም ያሉ አብያተ ክርስቲያናት በትልቁ ያከብሩታል። ኢትዮጵያ ውስጥ ግን አክሱም አካባቢ ካልሆነ ከነ ስም አጠራሩ እንኳ እየተዘነጋ ይመስላል።

ነገር ግን ጀግንነቱ፣ ውለታው፣ ምናኔውና ቅድስናው የማይረሳ ነውና እንኳን በእምነት የሚመስሉን ይቅርና የማይመስሉን ምሥራቅ ኦርቶዶክሶችና ካቶሊኮች ዓመታዊ በዓሉን በወርኀ ጥቅምት ያከብራሉ።

ከአክሱም ነገሥታት በኃይሉም ሆነ በሃይማኖታዊ ቅድስናው አፄ ካሌብ ዋናው ነው። ቅዱሱ የነገሠው በ485 ዓ/ም አካባቢ ሲሆን እስከ 515 ዓ/ም ድረስ በዙፋኑ ላይ ቆይቷል። ከመልካም ትዳሩ አፄ ገብረ መስቀልን ጨምሮ ልጆችን ወልዷል።

😇 ስለ ቅዱስ አፄ ካሌብ የሚከተሉትን ነጥቦች ብቻ እናንሳ፦

  • ፩ኛ. በንግሥና ዙፋን ከመቀመጡ በፊት የሚገባውን መንፈሳዊ ትምሕርት ጠንቅቆ ተምሯል።
  • ፪ኛ.ሃይማኖቱ የጠራና እጅግ የሚደነቅ ነበር። በእርሱ ዘመን ሃይማኖት ለነገሥታቱ የፖለቲካ ማስፈጸሚያ ነበር። እርሱ ግን እግዚአብሔርን በፍጹም ልቡ አምልኳል።
  • ፫ኛ.ለእመቤታችንና ለቸር ልጇ የነበረው ጥልቅ ፍቅር የተገለጠና የሚያስቀና ነበር።
  • ፬ኛ.ገና በዙፋኑ ሳለ ጸሎትን ያዘወትር ነበር።
  • ፭ኛ.ዛሬም ድረስ ሁሉም ክርስቲያኖች የማይረሱትን መንፈሳዊ ቅንዓትን አሳይቷል።

ይሕስ እንደ ምን ነው ቢሉ:-

*በወቅቱ ዐመፀኛው የአይሁድ መሪ ፊንሐስ በሃገረ ናግራን(የዛሬዋ የመን) ውስጥ የነበሩ ክርስቲያኖችን ክርስቶስን ካዱ በሚል ጨፈጨፋቸው። ከተማዋንም ለአርባ ቀናት በእሳት አነደዳት። ዜናው በመላው ዓለም ሲሰማ በርካቶቹ ቢያዝኑም የተረፉትን ለመታደግ የሞከረ አልነበረም።

😇 ቅዱስ አፄ ካሌብ ግን የሆነውን ሲሰማ ወደ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ገብቶ በግንባሩ ሰገደ። ወደ ፈጣሪም ጸለየ:- “ጌታዬ ሆይ! የክርስቲያኖችን ደም እመልስ ዘንድ እርዳኝ? እኔ በጦሬ ብዛት አልመካም። እኔ ተሸንፌ ክርስትና ከሚናቅ እዚሁ ግደለኝ” ብሎ በበርሃ ላሉ መነኮሳት እንዲጸልዩ ላከባቸው።

ጊዜ ሳያጠፋ በመርከብና በፈረስ : በበቅሎና በግመል ናግራን (የመን) ደረሰ። ፊንሐስን ገድሎ ሠራዊቱንም ማርኮ ክርስቲያኖችን ነጻ አወጣ። ደምና እንባቸውንም አበሰ። አብያተ መቅደሶችን አንጾላቸው ወደ ኢትዮጵያ ተመለሰ።

ወዲያው እንደተመለሰ ወደ አክሱም ጽዮን ገብቶ “ጌታየ ኢየሱስ ክርስቶስ ስላደረክልኝ የምሰጥህ ሰውነቴን እንጂ ሐብቴን አይደለም” ብሎ መንግስቱን ለልጁ ገብረ መስቀል አውርሶ ከዙፋኑ ወጣ። የወርቅ አክሊሉን ወደ ኢየሩሳሌም ልኮ እርሱ በአባ ጰንጠሌዎን እጅ መንኩሶ መነነ።

ከዚሕች ዓለም ከአንዲት ረዋት(ኩባያ)፣ ከአንዲት ሰሌንና ከአንዲት ቀሚስ በቀር የወሰደው አልነበረም። ከዚያም በበዓቱ ውስጥ በጾምና በጸሎት ተወስኖ አንድም ሰው ሳያይ በሰባ ዓመቱ (በ፭፻፳፱/529 ዓ/ም) ዐርፏል። 😇 ጌታችንም በሰማይ ክብርን አጐናጽፎታል።

ንጉሥ ካሌብን ሳስብ ዛሬ በመላዋ ሃገራችን ሥልጣኑን ይዘው ኢትዮጵያን እየበደሏት ያሉት የኦነግ/ብልጽግና፣ የሻዕቢያ፣ የሕወሓት፣ የብአዴን፣ የኢዜማ፣ የአብን መስለ ወንጀለኛ ፓርቲዎች መሪዎች በደብረ ዘይት ሆራ ሐይቅ የተፈለፈሉ ተባዮች/ቁንጫዎች ሆነው ነው የታዩኝ።

እንደ ንጉሥ ካሌብ ያለ ምርጥ የዓለም መሪ ለሃገራችን ያምጣልን። ለቅዱስ አፄ ካሌብ የተለመነ አምላክ ለእኛም ይለመነን። በጻድቁም ጸሎት ከመከራ ይሠውረን።

On May 28, we commemorate Saint Elesbaan (Kaleb), King of Ethiopia.

The sixth-century King Kāleb is one of a few African historical characters that have left a visible trace in European art and literature. Venerated by the Catholic Church as Saint Elesbaan, he is frequently present in pre-modern and modern literature and iconography.

👑 King Kaleb of Ethiopia’s Axum — St. Elesbaan(አፄ ካሌብ) : The Black Saint Who Embodied Christianity for the African Masses

The Kingdom of Axum flourished for many years with a succession of powerful rulers, but one stood out as being the most important.

Axum at the time was enjoying the wealth and business of Christian Byzantines that were heavily engaged in trade within their region.

King Kaleb of Axum (520 c) also known by his throne name Ella Asbeha/Atsbeha is well known for his invasion and conquest of Yemen in southern Arabia.

King Kaleb is believed to have launched an attack against the Jewish King Yusuf Asar Yathar because of his ruthless persecution of Christians.

King Kaleb is said to have rented about 60 ships from ports ran by the Byzantines in the Erythrean Sea, or the modern day Red Sea.

His forces were in the range of 100,000 to 120,000 which he sent to combat the king in Yemen.

After a bloody war that tested both sides to the extreme, King Kaleb emerged victorious and proceeded to kill King Yusuf.

In his place he appointed a Christian called Sumuafa Ashawa as his viceroy.

Due to his willingness to protect Christians, the 16th century Cardinal Cesare Baronio named him Saint Elesbaan.

He was also referred to by the Greeks as Hellesthaeus or “the one who brought about the morning or the one who collects tribute”.

Some historians believe that the Axumite kingdom over extended itself by conquering Yemen, and it eventually led to their demise.

______________

Posted in Ethiopia, Faith, Saints/ቅዱሳን | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

The Freedom of The Enemy Will Be Granted | የጠላት ነፃነት ይሰጣል

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on May 28, 2023

መንፈሳዊ ጦርነት ሊሟላ አይችልም – ለአባታችን ቃለ ሕይወት ያሰማልንና፤ አባ ማር ማሪ አማኑኤል እንዲህ በማለት ይመክሩናል፤

የዘመናችን ልዕለ ኃያል የሆነች ሀገር መንፈሳዊውን ጦርነትን ተዋግታ ማሸነፍ አትችልም። ከኑክሌር የጦር መሳሪዎች መንፈሳዊውን ውጊያ ማሸነፍ አይችሉም። በጭራሽ!

አያችሁ መንፈሳዊው ጦርነት ፍፁም ነው፣ የተለየ ደረጃ ነው፣ በጣም ኃይለኛ ነው፣ በጣምም ግዙፍ ነው። እና ጌታ አሁን ልቦናችሁን ለአፍታ ከከፍተ እመኑኝ፤ አሁን የሰማይ መላእክት ሲጋደሉልን ማየት ትችላላችሁ።

መላእክቱ ጠላትን እና ርኩስ መናፍስቱን ሁሉ ያለማቋረጥ እየተዋጓቸው ነው። በቀላሉ እንድንሄድ እና እንድንመጣ እና በነጻነት እንድንጓዝ፣ መኪና ውስጥ እንድትገቡ፤ ታውቃላችሁ፤ ወደ ሥራ ወደ ትምህርት ቤት፣ ወደ ቤተ ክርስቲያን፣ ወደ ገባያ በሰላም ለመሄድ የቻለነው በመልአክቱ እርዳታ ነው።

የምታደርጉትን ሁሉ አስታውሱ። ጌታችን ሁሌ እየጠበቃችሁ ነው። ለዚህም ነው ኑሮ በጣም ቀላል የሆነው። ግን ጌታ እጁን የሚያነሳበትና ለዲያብሎስ ጠላት ሙሉ ነፃነት የሚሰጥበት ቀን ይመጣል።

አሁን ጠላት ሙሉ ነፃነት የለውም። ሙሉ ነፃነት ሲኖረው ምን እንደሚሰራ ተመልከቱ፤ በዓለም ውስጥ ብቻ ሳይሆን ቤተ ክርስቲያን ውስጥም ሳይቀር ምን እንደሚሰራ ተመልከቱ፤ ቤተ ክርስቲያን ከፋፍሏታል።

በክርስቶስ ወንድማማቾች መሆን ያለባቸውን ቤተ ክርስቲያን እና የቤተ ክርስቲያን መሪዎችን እርስበርስ እንዲጠላሉ አድርጓቸዋል።

በጣም የማይታመን ነገር ነው!

ግን ይህ የምታዩት ጠላት ሙሉ የማጥፊያ ነፃነት ገና አልተሰጠውም። ሆኖም ግን እኛ ትግል ላይ ነን።

አንድ ጉድጓድ ውስጥ ወድቀን እንወጣለን፣ ከዚያም ወደ ትልቅ እና ጥልቅ መውደቁን እንቀጥልበታለን።

እና በቃን ዳግም ሃጢዓት አንሰራም እንላለን ፥ ግን ከዚያ የከፋ ሃጢዓት እንሰራለን፣ ከእንግዲህ አልመለስም እንላለን፤ ግን ከዚህ የከፋ መጥፎ ነገር እናደርጋለን፣ ዕፅ አልወስድም እንላለን ግን በይበልጥ መውሰዱን እንገፋበታለን።

ይባስ ብሎ፤ ቁማር አልጫወትም እንላለን ፥ ግን ደጋግመን እንጫወታለን።

ወንዶች ከልጃገረዶች ጋር አልወጣም እንላለን ፥ ግን የባሰውን ዝሙት እንፈጽማለን።

ሴቶች ከወንዶች ጋር አልወጣም እንላለን ፥ ግን ይባስ ብለን ከባዱን ሃጢአት ለመፈጸም እንወስናለን። ያንን አላደርግም እላለሁ ግን አሁንም ደግሜ ደጋግሜ አደርገዋለሁ።

አዎ! ጠላት እየተቃጠለ ነው። ሆኖም እስከዚህ ቅጽበት ድረስ ሙሉ ነፃነት ገና አልተሰጠውም።

ግን በጊዜው ይመጣል። ሦስት ዓመት ተኩል ጌታ ያንን ጠላት ይፈታዋል እና ይላል።

ልክ እኔ ኢየሱስ ክርስቶስ የጠፉ ነፍሳት ለማዳን፣ ለመውሰድ እና ወደ እግዚአብሔር ለማምጣት ሦስት ዓመት ተኩል ጊዜ እንደነበረኝ፣ እኔ ፍትሃዊ ነኝ፤ ስለዚህ የትግሉን ድርሻ እሰጥሃለሁ። አዎ! ለመግደል እና ለማጥፋት የሦስት ዓመት ተኩል ነፃነት ተሰጥቶሃል፤ ከዚያ ነፃ ትወጣለህ!

እግዚአብሔር ይመስገንና ዛሬም ሰላምታ የሚሰጧችሁ ሰዎች አሉ። አሁንም ስለእናንተ የሚያስቡና የሚቆረቆሩ ሰዎች አሉ።

እግዚአብሔር ይመስገን አሁንም አፍቃሪ ሰዎች አሉ። እግዚአብሔርን አመሰግናለሁ፤ ትግል ነው ግን አመሰግነዋለሁ።

ማንም የማይኖርበት ጊዜ ግን ይመጣል። ለምን? ምክንያቱም ሰይጣን ቦታውን ይሞላልና ነው፤ ነፃነትን ይበላልና ነው። መላው ዓለም ከምስራቅ እስከ ምዕራብ፣ ከሰሜን እስከ ደቡብ ማንም ሰው ዓይኑን ከመግለጡ በፊት በሰይጣን ይበላል። እና አሁን ሰይጣንን የሚያመልኩትን ሳይቀር ያቃጥላቸዋል።

አያችሁ፤ ሰይጣን ሁሉንም ሰው እርሱን የሚያመልኩትን ጨምሮ ይጠላቸዋል። ምስኪኖች አላፊውን ሰው እያመለኩ ነው። በመጨረሻ እነርሱንም ያቃጥላቸዋል

አያችሁ፤ ሰይጣን ሁሉንም በስሜታዊነት ይጠላል፤ በተለይ ጌታን የሚወዱትን በይበልጥ ይጠላል።

ለእርሱ የሚገዙለትንም ግን ይጠላቸዋል።

ያ ነፃነት ሲሰጠው ይህን ያደርጋል፤ እነዚህን ምስክሮች ይገድላቸዋል። ምን ያህል ኃይል እንዳላቸው ተመልከቱ። ሙሴ ውሃውን ወደ ደም ለወጠው። ኤልያስ ከሰማይ እሳት አወረደ። ሔኖክ ወደ ዓለም ፍርዱን አሳለፈ። ብዙ ኃይል እነሱ አላቸውና ምድርን በቀላሉ ማጥቃት ይችላሉ፤ ብዙ መቅሰፍቶችን እንደፈለጉ ማውረድ ይችላሉ። ለሚመጣው ማንም ሰው ስልጣን ይሰጣቸዋል። እና እነሱን ለመጉዳት የሚሞከር ሁሉ ይቃጠላታል፣ ይሞታታል፤ ሰይጣን ተፈትቶ ሙሉ ስልጣን ሲሰጠው ግን ይገድላቸዋል።

መላውን ዓለም በኮንክሪት ማደባለቂያ ውስጥ አስገብቶ ያሽከረክረዋል። እና ሁሉንም በአንድ ላይ ያደበለቃቅለዋል፤ አዲስ ኮንክሪት ያወጣል። ምናልባት በጥቂት ሰከንድ ውስጥ ሁሉም ይደርቃል

ፍትሃዊ እንደሆነ ይፈቅድለታል። አዎ! ፍትሃዊ፤ ግን ጌታ ለምን ለሰይጣን እንኳን ፍትሃዊነት እንደሚሰጠው ታውቃላችሁን? ምክንያቱም፤ በጊዜው የነበሩ ሰዎች ከጌታ ርቀው በመሄዳቸው ነበርና ነው።

ምንም እንኳን ለሰይጣን ሙሉ ነፃነት ቢሰጠውም ግን አሁንም ሁለት ምስክሮች አሉት። ‘ለመመስከር ሰዎች ተመልሰው ይምጡ’ለማለትና ንስሐ መግባት ይችሉ ዘንድ ነው።

የዚህ ዓለም የመጨረሻ ሰከንድ ቢሆንም ግእና ጌታ ግን ሁልጊዜ የእሱ የሆኑ ምስክሮች አሉት። ምንም ቢሆን ለራሱ ምስክሮች አሉት። በየትኛውም ጊዜ እና በየትኛውም ቦታ ክርስቶስ እራሱን ያለ ምስክር አይተውም። በገሃነም ልብ ውስጥ እንኳን ሁለት ምስክሮች አሉት።

ስለዚህ በእነዚህ ሦስት ዓመታት ተኩል ውስጥ ዓለምን ለማጥፋት ለሰይጣን እድል ይሰጠዋል።

______________

Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

በውኑ ኢትዮጵያዊ መልኩን ወይስ ነብር ዝንጕርጕርነትን ይለውጥ ዘንድ ይችላልን?

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on May 28, 2023

ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን

~ በዐቢይ ኀይል ወሥልጣን

አሰሮ ለሰይጣን

~ አግአዞ ለአዳም

ሰላም

~ እምይእዜሰ

ኮነ

~ ፍሥሐ ወሰላም።

❖❖❖[ትንቢተ ኤርምያስ ምዕራፍ ፲፫]❖❖❖

  • ፩ እግዚአብሔር እንዲህ ይለኛል። ሂድ፥ ከተልባ እግር የተሠራችን መታጠቂያ ለአንተ ግዛ፥ ወገብህንም ታጠቅባት፤ በውኃውም ውስጥ አትንከራት።
  • ፪ እንደ እግዚአብሔርም ቃል መታጠቂያን ገዛሁ ወገቤንም ታጠቅሁባት።
  • ፫-፬ ሁለተኛም ጊዜ። የገዛሃትን በወገብህ ያለችውን መታጠቂያ ወስደህ ተነሥ፥ ወደ ኤፍራጥስም ሂድ፥ በዚያም በተሰነጠቀ ዓለት ውስጥ ሸሽጋት የሚል የእግዚአብሔር ቃል መጣልኝ።
  • ፭ እግዚአብሔርም እንዳዘዘኝ ሄድሁ በኤፍራጥስም አጠገብ ሸሸግኋት።
  • ፮ ከብዙ ቀንም በኋላ እግዚአብሔር። ተነሥተህ ወደ ኤፍራጥስ ሂድ፥ በዚያም ትሸሽጋት ዘንድ ያዘዝሁህን መታጠቂያ ከዚያ ውስጥ ውሰድ አለኝ።
  • ፯ እኔም ወደ ኤፍራጥስ ሄድሁ ቆፈርሁም፥ ከሸሸግሁበትም ስፍራ መታጠቂያይቱን ወሰድሁ። እነሆም፥ መታጠቂያይቱ ተበላሽታ ነበር፥ ለምንም አልረባችም።
  • ፰ የእግዚአብሔርም ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ፤
  • ፱ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል። እንዲሁ የይሁዳን ትዕቢት ታላቁንም የኢየሩሳሌምን ትዕቢት አበላሻለሁ።
  • ፲ ቃሌን ይሰሙ ዘንድ እንቢ የሚሉ፥ በልባቸውም እልከኝነት የሚሄዱ፥ ያመልኩአቸውና ይሰግዱላቸው ዘንድ ሌሎችን አማልክት የሚከተሉ እነዚህ ክፉ ሕዝብ አንዳች እንዳማትረባ እንደዚች መታጠቂያ ይሆናሉ።
  • ፲፩ መታጠቂያ በሰው ወገብ ላይ እንደምትጣበቅ፥ እንዲሁ ሕዝብና ስም ምስጋናና ክብር ይሆኑልኝ ዘንድ የእስራኤልን ቤት ሁሉ የይሁዳንም ቤት ሁሉ ከእኔ ጋር አጣብቄአለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር፤ ነገር ግን አልሰሙም።
  • ፲፪ ስለዚህ።የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል። ማድጋ ሁሉ የወይን ጠጅ ይሞላል ብለህ ትነግራቸዋለህ፤ እነርሱም። ማድጋ ሁሉ የወይን ጠጅ እንዲሞላ በውኑ እኛ አናውቅምን? ይሉሃል።
  • ፲፫ አንተም እንዲህ ትላቸዋለህ። እግዚአብሔር እንዲህ ይላል። እነሆ፥ በዚህች ምድር የሚኖሩትን ሁሉ፥ በዳዊት ዙፋን የሚቀመጡትን ነገሥታት ካህናቱንም ነቢያቱንም በኢየሩሳሌምም የተቀመጡትን ሁሉ በስካር እሞላቸዋለሁ።
  • ፲፬ ሰውንም በሰው ላይ፥ አባቶችንና ልጆችን በአንድ ላይ፥ እቀጠቅጣለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር፤ አጠፋቸዋለሁ እንጂ አልራራም፥ አላዝንም፥ አልምርም።
  • ፲፭ ስሙ፥ አድምጡ፤ እግዚአብሔር ተናግሮአልና አትታበዩ።
  • ፲፮ ሳትጨልም እግራችሁም በጨለመችው ተራራ ላይ ሳትሰናከል፥ በተስፋ የምትጠባበቁትን ብርሃን ለሞት ጥላና ለድቅድቅ ጨለማ ሳይለውጠው ለአምላካችሁ ለእግዚአብሔር ክብርን ስጡ።
  • ፲፯ ይህን ባትሰሙ ነፍሴ ስለ ትዕቢታችሁ በስውር ታለቅሳለች፤ የእግዚአብሔርም መንጋ ተማርኮአልና ዓይኔ ታነባለች፥ እንባንም ታፈስሳለች።
  • ፲፰ ለንጉሡና ለንጉሥ እናት ለእቴጌይቱ። የክብራችሁ አክሊል ከራሳችሁ ወርዶአልና ተዋርዳችሁ ተቀመጡ በል።
  • ፲፱ የደቡብ ከተሞች ተዘግተዋል፥ የሚከፍታቸውም የለም፤ ይሁዳ ሁሉ ተማርኮአል፥ ፈጽሞ ተማርኮአል።
  • ፳ ዓይናችሁን አንሥታችሁ እነዚህን ከሰሜን የሚመጡትን ተመልከቱ፤ ለአንቺ የተሰጠ መንጋ፥ የተዋበ መንጋሽ፥ ወዴት አለ?
  • ፳፩ ወዳጆችሽ እንዲሆኑ ያስተማርሻቸውን በራስሽ ላይ አለቆች ባደረጋቸው ጊዜ ምን ትያለሽ? እንደ ወላድ ሴት ምጥ አይዝሽምን?
  • ፳፪ በልብሽም። እንዲህ ያለ ነገር ስለ ምን ደረሰብኝ? ብትዪ፥ ከኃጢአትሽ ብዛት የተነሣ የልብስሽ ዘርፍ ተገልጦአል ተረከዝሽም ተገፍፎአል።
  • ፳፫ በውኑ ኢትዮጵያዊ መልኩን ወይስ ነብር ዝንጕርጕርነትን ይለውጥ ዘንድ ይችላልን? በዚያን ጊዜ ክፋትን የለመዳችሁ እናንተ ደግሞ በጎ ለማድረግ ትችላላችሁ።
  • ፳፬ ስለዚህ እንደሚያልፍ እብቅ በምድረ በዳ ነፋስ እበትናቸዋለሁ።
  • ፳፭ ረስተሽኛልና፥ በሐሰትም ታምነሻልና ዕጣሽ የለካሁልሽም እድል ፈንታ ይህ ነው፥ ይላል እግዚአብሔር።
  • ፳፮ ስለዚህም የልብስሽን ዘርፍ በፊትሽ እገልጣለሁ እፍረትሽም ይታያል።
  • ፳፯ አስጸያፊ ሥራሽን፥ ምንዝርናሽን፥ ማሽካካትሽን፥ የግልሙትናሽንም መዳራት በኮረብቶች ላይ በሜዳም አይቻለሁ። ኢየሩሳሌም ሆይ፥ ወዮልሽ! ለመንጻት እንቢ ብለሻል፤ ይህስ እስከ መቼ ነው?

______________

Posted in Ethiopia, Faith, War & Crisis | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

ዐረገ በስብሐት ዐረገ በእልልታ | The Feast of the Ascension of Jesus Christ

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on May 26, 2023

ዕርገት› በግእዝ ቋንቋ ማረግ፣ ከታች ወደ ላይ መውጣት ማለት ሲኾን የጌታችን ትንሣኤ በተከበረ በዐርባኛው ቀን የሚውለው ዐቢይ በዓልም ‹ዕርገት› ይባላል (ኪዳነ ወልድ ክፍሌ፣ ገጽ ፯፻፷)፡፡ በዓለ ዕርገት ጌታችን አምላካችንና መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከሙታን ከተነሣ በኋላ ለዐርባ ቀናት በግልጽም በስውርም ለቅዱሳን ሐዋርያትና ለቅዱሳት አንስት መጽሐፈ ኪዳንን፣ ትርጓሜ መጻሕፍትን፣ ምሥጢራትን፣ ሕግጋትንና ቀኖናተ ቤተ ክርስቲያንን ሲያስተምር ቆይቶ ወደ ቀደመ ዙፋኑ ወደ ሰማይ በክብር በምስጋና ማረጉን በደስታ የምንዘክርበት ዐቢይ በዓል ነው፡፡ በዓለ ዕርገት በቤተ ክርስቲያናችን በየዓመቱ በድምቀት ይከበራል፡፡ በዓሉ የሚውልበት ዕለት ሐሙስን ባይለቅም ቀኑ ግን የአጽዋማትና በዓላት ማውጫ ቀመርን ተከትሎ ከፍ እና ዝቅ ይላል፡፡

በዚህ መሠረት የዘንድሮው በዓለ ዕርገት ግንቦት ቀን ፳፻፲ ዓ.ም ይውላል ማለት ነው፡፡ ከጌታችን የዕርገት በዓል ጀምሮ (ከበዓለ ትንሣኤ ዐርባኛው ቀን) እስከ በዓለ ጰራቅሊጦስ ዋዜማ (ዐርባ ዘጠነኛው ቀን) ድረስ ያለው ወቅትም ‹ዘመነ ዕርገት› ተብሎ ይጠራል፡፡ በዘመነ ዕርገት ውስጥ በሚገኘው እሑድ (ሰንበት) ሌሊት ሊቃውንቱ የሚያደርሱት መዝሙርም ‹‹በሰንበት ዐርገ ሐመረ›› የሚል ሲኾን ይኸውም ጌታችን በሰንበት ወደ ታንኳ በመውጣት ባሕርንና ነፋሳትን እንደ ገሠፀ፤ ሐዋርያቱንም ‹‹ጥርጥር ወደ ልቡናችሁ አይግባ፤ አትጠራጠሩ›› እያለ በሃይማኖት ስለ መጽናት እንዳስተማራቸው፤ እንደዚሁም ወንጌልን ይሰብኩ፣ ያስተምሩ ዘንድ በመላው ዓለም እንደሚልካቸው፤ በሰማያዊ መንግሥቱ ይኖሩ ዘንድም ዳግመኛ መጥቶ እንደሚወስዳቸው የሚያስገነዝብ መልእክት አለው (ሉቃ.፰፥፳፪-፳፬፤ ዮሐ.፲፬፥፪፤ ፳፥፳፩)፡፡

በበዓለ ዕርገት ሊቃውንቱ ሌሊት በማኅሌት፣ በዝማሬ እግዚአብሔርን ሲያመሰግኑ ያድራሉ፡፡ ሥርዓተ ማኅሌቱ እንዳበቃ የሚሰበከው የነግህ ምስባክም፡- ‹‹ዘምሩ ለእግዚአብሔር ዘዐርገ ውስተ ሰማይ ሰማይ ዘመንገለ ጽባሕ ናሁ ይሁብ ቃሎ ቃለ ኃይል›› የሚለው የዳዊት መዝሙር ሲኾን፣ ቀጥተኛ ትርጕሙ፡- ‹‹በምሥራቅ በኩል ወደ ሰማየ ሰማያት ለወጣ (ላረገ) ለእግዚአብሔር ዘምሩ፤ የኀይል የኾነውን ቃሉን እነሆ ይሰጣል፤›› ማለት ነው (መዝ.፷፯፥፴፫)፡፡ ምሥጢራዊ ትርጕሙ ደግሞ ‹‹ነፍሳትን ይዞ ከሲኦል ወደ ገነት ለወጣ፤ አንድም በደብረ ዘይት በኩል ላረገ ለእግዚአብሔር ምስጋና አቅርቡ›› የሚል መልእክት አለው፡፡ እንደዚሁም ጌታችን በዐረገ በዐሥረኛው ቀን ‹የኀይል ቃል› የተባለ መንፈስ ቅዱስን ለሐዋርያት እንደ ላከላቸው፤ በተጨማሪም ጌታችን በሕያዋን እና በሙታን (በጻድቃን እና በኃጥአን) ላይ ለመፍረድ ዳግም እንደሚመጣ፤ እኛም ይህንን የጌታችንን የማዳን ሥራ እያደነቅን ለእርሱ ምስጋና፣ ዝማሬ ማቅረብ እንደሚገባን ያስረዳናል – ምስባኩ፡፡

በነግህ (ከቅዳሴ በፊት የሚነበበው) ወንጌል ደግሞ ሉቃስ ፳፬፥፵፭ እስከ መጨረሻው ድረስ ያለው ኃይለ ቃል ነው፡፡ ቃሉም ጌታችን አምላካችንና መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከሰማየ ሰማያት እንደሚወርድ፣ የሰውን ልጅ ለማዳን ሲል መከራ እንደሚቀበል፣ እንደሚሞት፣ ከሙታን ተለይቶ እንደሚነሣ፣ ወደ ሰማይ እንደሚያርግና ዳግም እንደሚመጣ በነቢያት የተነገረው ትንቢት መፈጸሙን፤ ለዚህም ቅዱሳን ሐዋርያት ምስክሮች መኾናቸውን ማለትም በመላው ዓለም እየዞሩ ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ የማዳን ሥራ እንዲሰብኩና በሰማዕትነት እንዲያልፉ፤ እንደዚሁም ሰማያዊ ሀብትንና ዕውቀትን እስኪያገኙ ድረስ በኢየሩሳሌም እንዲቆዩ መታዘዛቸውን ያስረዳል (ትርጓሜ ወንጌል)፡፡ ይህ ምሥጢር ለጊዜው የሐዋርያትን ተልእኮ የሚመለከት ይኹን እንጂ ለፍጻሜው ግን ዅላችንም ቅዱሳት መጻሕፍት የተናገሩትን ቃል አብነት አድርገን የእግዚአብሔርን ሰው መኾንና የማዳኑን ሥራ አምነን፣ ሌሎችንም በማሳመን በሃይማኖታችን ጸንተን መኖር እንደሚገባን፤ እግዚአብሔር አምላካችን ኃይሉን፣ ጸጋውን፣ ረድኤቱን እንዲያሳድርብንም ከቅድስት ቤተ ክርስቲያን መለየት እንደሌለብን የሚያስገነዝብ መልእክት አለው፡፡

በቅዳሴ ጊዜ የሚነበቡ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎችም ከቅዱስ ጳውሎስ መልእክት ዕብራውያን ፩፥፩ እስከ ፍጻሜው ድረስ፤ ከሌሎች መልእክታት ደግሞ ፩ኛ ጴጥሮስ ፫፥፲፰ እስከ ፍጻሜው፤ የሐዋርያት ሥራ ፩፥፩-፲፪ ሲኾኑ፣ ምስባኩም ‹‹ዐርገ እግዚአብሔር በይባቤ ወእግዚእነ በቃለ ቀርን ዘምሩ ለአምላክነ ዘምሩ›› የሚለው ነው፡፡ ትርጕሙም ‹‹በዕልልታና በመለከት ድምፅ ላረገ ለአምላካችን፣ ለጌታችንና ለመድኀኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ ምስጋና አቅርቡ›› ማለት ነው (መዝ.፵፮፥፭-፮)፡፡ ወንጌሉ ደግሞ፣ ማርቆስ ፲፮፥፲፬ እስከ ፍጻሜ ድረስ ሲኾን ቃሉም በነግህ ከተነበበው የወንጌል ክፍል ቃል ተመሳሳይነት አለው፡፡ ቅዳሴውም ቅዳሴ ዲዮስቆሮስ ሲኾን ይህ ቅዳሴ ከሦስቱ አካላት አንዱ የኾነውን የእግዚአብሔር ወልድን (የኢየሱስ ክርስቶስን) ዘለዓለማዊነት የሚያስረዳ፤ ሥጋዌዉን፣ ሕማሙን፣ ሞቱን፣ ትንሣኤዉን፣ ዕርገቱንና ዳግም ምጽአቱንም የሚናገር በመኾኑ በዘመነ ትንሣኤ፣ በዘመነ ዕርገትና በበዓለ ኀምሳ ሰሙን ይቀደሳል፡፡

ቅዱስ ዲዮስቆሮስ በቅዳሴዉ መጀመሪያ ላይ ሀልዎተ እግዚአብሔርንና ምሥጢረ ሥላሴን መሠረት በማድረግ ለእግዚአብሔር ምስጋና ካቀረበ በኋላ፣ ቍጥር ፴፩ ላይ ‹‹… ወበ፵ ዕለት አመ የዐርግ ሰማየ አዘዞሙ እንዘ ይብል ጽንሑ ተስፋሁ ለአብ፤ … ከሙታን ተለይቶ በተነሣ በዐርባኛው ቀን በብርሃን፣ በሥልጣን፣ በይባቤ ወደ ሰማይ በሚያርግበት ጊዜ አብ የሚሰድላችሁ መንፈስ ቅዱስን እስክትቀበሉ ድረስ ከዚህ ቆዩ ብሎ አዘዛቸው፤›› በማለት መጽሐፍ ቅዱሳዊ በኾነ ቋንቋ የጌታችንን ወደ ሰማይ ማረግና ለሐዋርያት የሰጠውን አምላካዊ ትእዛዝ ይናገራል (ሉቃ.፳፬፥፵፱)፡፡

______________

Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

Ethiopia Silenced! The Truth About Early Church History in Africa

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on May 21, 2023

❖ ኢትዮጵያ ታፍናለች! በአፍሪካ የቀደመችዋ ቤተክርስቲያን ታሪክ እውነት ❖

✞ ከአንጾኪያ፣ እስክንድርያ፣ እየሩሳሌም፣ ሮም እና ባይዛንቲየም፣ ጋር መካተት ያለበት ሌላ ከተማ ወይም አገር ቢኖሩ ኖሮ ከጎናቸው መሆን ያለባት ኢትዮጵያ ናት። ዛሬ የኒቆሚዲያው ዩሴቢየስ የቤተክርስቲያን ታሪክ ፪ ኛን መጽሐፍ ከዘኍልቍ ምዕራፍ ፲፪፣ የሐዋርያት ሥራ ምዕራፍ ፰ እና ከኢትዮጵያ ታሪክ ጋር ሲወሰዱ፣ ኢትዮጵያ በክርስትና እምነት ውስጥ እጅግ በጣም አስፈላጊ የሆነች አገር እንደነበረች የሚገልጹትን አንዳንድ ጠቃሚ እውነታዎችን ይዞ ይጀምራል።

አዎ! መምህር ኒክ ጃሬት ትክክል ናቸው፤ ግን ይህችኛው ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ ዘ-መንፈስ ናት። በአክሱማዊቷ ኢትዮጵያ ላይ ከጠላት አህዛብ ጋር አብራ የዘመተውን፡ የልፍስፍሱን፣ እራሱን የሚጠላውንና የዳግማዊ ምንሊክ ተረት ተረት ‘ብሔረ ብሔረሰብ’ የመጨረሻ ትውልድ የሆነውን’ኢትዮጵያ ዘ-ስጋን አይመለከትም። ለዚህም ነው ርዕሱ እንደሚጠቁመን ይህች በሰይጣን የምትመራዋ ዓለም ተገቢውን ትኩረት ልትሰጠው ያልፈለገችው። ላለፉት ሁለት ዓመታት እንኳን ከሚሊየን በላይ የተጨፈጨፈው ኢትዮጵያዊ ኦርቶዶክስ ክርስቲያኑ ሆኖ ሳለ፤ ይህ ጭፍጨፋ ሃይማኖታዊ ግብ እንዳለውና በሕዝበ ክርስቲያኑ ላይ ያነጣጠረ እንደሆነ ለመናገር የደፈረ አንድም ‘ኢትዮጵያዊ’ የለም።

ለዚህም እኮ ነው፡ እንኳን የተቀረው ዓለም፡ የኦርቶዶክስ ክርስቲያኑ ዓለም ሳይቀር ድጋፉን እንዲነፍገን የተደረገው። ከዚህ ጨፍጫፊ የጋላ-ኦሮሞ አገዛዝ ጋር ጎን እንደ ግብጽና ሩሲያ ያሉ የኦርቶዶክስ ክርስቲያን ሃገራት ሳይቀሩ የተሰለፉት። በኢትዮጵያ እየተፈጸመ ያለው ግፍና ጥቃት በኦርቶዶክስ ተውሕዶ ክርስቲያን ኢትዮጵያውያን ላይ መሆኑን እያንዳንዳችን እስካላሳወቅን ድረስና፣ “የዘር ማጥፋት ወንጀል በትግሬ ላይ፣ በአማራ ላይ፣ በጉራጌ ወዘተ ላይ ነው የተፈጸመው” ማለቱን፣ ብሎም ክቡር መስቀሉን እና ታቦተ ጽዮንን በመሸከም ፈንታ የሉሲፈርን/ቻይናን ባንዲራ ማውለብለቡን ከቀጠልን እግዚአብሔር አምላክም ፈጽሞ አይሰማንም፣ ከገባንበት መቀመቅም አያወጣንም። ምክኒያቱም ይህ ሃቁ አይደለምና ነው፤ ምክኒያቱም ፈጣሪያችን ‘ትግሬ’፣ ‘አማራ’፣ ጉራጌ ወዘተ የተሰኙትን የስጋ ማንነትና ምንነት ያላቸውን ብሔሮችን ወይንም ነገዶችን አያውቃቸውምና ነው።

ለምሳሌ ያ ዘምድኩን በቀለ የተባለው ግብዝ ሰው፤ “የአማራ አምላክ” “አማራ እንደ ኢየሱስ ክርስቶስ የሚሰቃየው ኢትዮጵያን ለማዳን ነው” እያለ ሲቀባጥር ስሰማው፤ እያቅለሸለሸኝ፤ “እንዴ ይህ ፍዬል ምን ያህል ጸያፍና እጅግ የሚያስኮንን ነገር እያስታወከ መሆኑን አይገነዘበውምን? የቀበሩለት ቺፕስ ነው ወይንስ ዋቄዮ-አላህ እንዲህ የሚያስቀባጥረው?!” ለማለት ነበር የተገደድኩት። እግዚዖ! አቤት ድፍረት! አቤት ውድቀት፤ እንደው ይህን ግለሰብ የሚመክረው ወገን የለምን?

✞ If there were another city or country that should be included with Antioch, Alexandria, Jerusalem, Rome, and Byzantium, Ethiopia, should be right along side them. Today Eusebius of Nicomedia kicks off book 2 of his Church history with some important facts that when taken with Numbers chapter 12, Acts chapter 8, and the history of Ethiopia, reveal it was a much more important Country in the Christian faith.

______________

Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

A Word on The End of The World | ስለ አለም መጨረሻ አንድ ቃል

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on May 21, 2023

😇 የቭላድሚር ቅዱስ ሴራፒዮን († 1275)

የቭላድሚር ቅዱስ ሴራፒዮን እ.አ.አ ከ 1247 እስከ 1274 ባለው ጊዜ ውስጥ የኪየቭ ዋሻዎች ገዳም ሊቀ ጳጳስ ነበሩ ። ከዚያ በኋላ የቭላድሚር ፣ ሱዝዳል እና የኒዝኒ ኖቭጎሮድ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ሆነው ተሾሙ ፣ እስከ ቀጣዩ የእረፍታቸው ዓመት ድረስ አስተዳደሩ። በወቅቱ የሀገረ ስብከቱ ግዛት የቭላድሚር ግራንድ ዱቺ እና የጎሮዴት ፣ ኮስትሮማ ፣ ሞስኮ ፣ ፔሬስላቭል ፣ ስታሮዱብ ፣ ሱዝዳል ፣ ኒዝኒ ኖቭጎሮድ እና ዩሪየቭ ርእሰ መስተዳድሮችን ያካተተ ነበር። የቅዱስ ሱራፒዮን አምስት ስብከቶች ተጠብቀው ቆይተዋል፣ አብዛኞቹ እንደ ተዋረዳዊው ዘመን እንደሆነ ይታመናል።

ወንድሞች ሆይ፣ የሚያስፈራው ቀን በድንገት ይመጣል፤ የኃጢአታችን ፅዋ ሞልቶ እጅግ አስፈሪ የሆነ የቅዱሱ የእግዚአብሔር ፍርድ ይጠብቀናልና የእግዚአብሔርን ፍርድ ፍሩ። በበጎ ምግባር ራሳችንን ካላዘጋጀን ራቁታችንን ቀርተንና እና ተቸግን በማይጠፋ እሳት እንቀጣለን።

ወንድሞች ሆይ ፣ እግዚአብሔርን በመፍራት ኑሩ ፣ የዚህ ሕይወት ጊዜ አጭር ነው እና እንደ ጭስ ይጠፋል። ከኃጢአታችን የተነሣ ብዙ መከራ ደረሰብን፥ ትንሽም ሐዘን አይደለም፥ የአሕዛብ ወረራ፥ በሰዎች መካከል መነሣሣት፥ የአብያተ ክርስቲያናት ረብሻ፥ በመኳንንት መካከል አለመረጋጋት፥ ሥጋን ብቻ የሚያስደስቱት አመፀኞቹ ካህናት ለነፍስ ደንታ የሌላቸው ናቸው። የመነኮሳት አለቆችም እንዲሁ። እናም መነኮሳቱ ስለ በዓላት መጨነቅ ይጀምራሉ፣ ግልፍተኛ እና ለፉክክር የተጋለጡ ይሆናሉ፣ እናም ለቅዱሳን አባቶች የማይመች ህይወት ይመራሉ። ሹማምንቱ በባለሥልጣናትና ኃያላን ፊት ይፈራሉ፣ በግል ጥቅማቸው ላይ ተመስርተው ይፈርዳሉ፣ ወላጅ አልባ ልጆችን ያሰናክላሉ፣ ለመበለቶችና ለድሆች አይማልዱም። በምእመናንም ውስጥ፣ አለማመን እና ዝሙት አለ፤ እና እውነትን ትተው ውሸት መፍጠር ይጀምራሉ።

በዚህ ዘመን ግን ማንም የሚፈልግ ቢኖር ይድናል፣ በመንግሥተ ሰማያትም ታላቅ ይባላል። በኖኅ ዘመንም እንዲሁ ነበርና፡ ይበሉም ይጠጡም፣ ያገቡም ያመነዝሩም ነበር ስለዚህ የጥፋት ውኃም መጣ ሁሉንም ስለ በደሉ አጠፋቸው። እንደዚህ ያለ አስፈሪ ክስተት ማየት እንዴት አሳዛኝ ነው! ኖህ ጌታ እንዳዘዘው መርከብን ሲሰራ ከህንድ የመጡ ዝሆኖች እና የፋርስ አንበሶች በጎች እና ፍየሎች ሳይጎዱ አብረው ተጓዙ; የሚሳቡ እንስሳትና አእዋፍ ኖኅ መርከቡን ወደሚሠራበት ቦታ አመሩ። ኖኅም አለቀሰ ሕዝቡንም “ንስሐ ግቡ! ጎርፉ እየመጣባህ ነው” አለው። እናም ይህን ሁሉ ሲያዩ፣ ቃሉን አልሰሙም እናም ትምህርቱን አልሰሙም የጥፋት ውሃ እስኪሸፍናቸው እና አስከፊ ሞት እስኪደርስባቸው ድረስ።

ወንድሞች ሆይ፣ እንፍራ፣ እነሆ፣ የተጻፈው ሁሉ ወደ ፍጻሜው እየመጣ ነው፣ እናም የተተነበዩት ምልክቶች እየፈተጸሙ ነውና። እና ከህይወታችን እና ከእድሜያችን ትንሽ የቀረ ነገር አለ።

ስለዚህ፣ መዳን የሚፈልግ፣ በትህትና፣ በመታቀብ እና በምጽዋት አሁን ይሥራ። ወዳጆች ሆይ፥ ማንም በወንበዴዎች እጅ ቢወድቅ ነፍሱ እንዲተርፍ ንብረቱንም በእነርሱ ፋንታ እንዲወስዱ እንዴት አዝኖ እንደሚለምን ተመልከቱ። ወንድሞች፣ ለመጥፎ ሕይወት ስንል ሁሉንም ነገር መጠቀማችን መጥፎ አይደለም፣ ነገር ግን ለመንፈሳዊ ጥቅማችን ግድ አንሰጥም? ለድሆች ስንሰጥ ለምን እንቆጫለን? ለምን ክፉውን ስራን አንተወውም እና ልባችንን ወደ ንስሃ ሕይወት ለምን አንመልስም?

😇 St. Serapion of Vladimir

St. Serapion of Vladimir (†1275) was archimandrite of the Kiev Caves Monastery from 1247 to 1274. He was then consecrated bishop of the Diocese of Vladimir, Suzdal, and Nizhny Novgorod, which he ruled until his repose the following year. At the time, the territory of the diocese consisted of the Grand Duchy of Vladimir and the principalities of Gorodets, Kostroma, Moscow, Pereslavl, Starodub, Suzdal, Nizhny Novgorod, and Yuriev. Five sermons from St. Serapion have been preserved, most believed to date from his time as a hierarch.

Brethren, fear the terrible and dread judgment of God, for that fearful day will come suddenly. If we don’t prepare ourselves with virtues, then naked and destitute we shall be condemned to unquenchable fire.

O brethren, live in the fear of God, for the time of this life is short and vanishes like smoke; and many calamities befall us for our sins, and no small sorrow: invasions of the heathen, agitation between people, the disorder of churches, unrest between princes, the lawlessness of priests who please only the flesh, taking no care for the soul. And abbots too. And the monks start to care about feasts, they become irascible and prone to rivalry, and they lead a life unbecoming of the Holy Fathers. The hierarchs cower before the powerful, they judge based on personal gain, they offend orphans and don’t intercede for widows and the poor. In the laity, there is unbelief and fornication; and abandoning the truth, they begin to create untruth.

But in such days, if anyone so desires, he will be saved and will be called great in the Kingdom of Heaven. For so it was in the days of Noah: They ate, they drank, they married, they fornicated, and the flood came and destroyed everyone for their iniquity. How awful to see such a fearful phenomenon! When Noah was building the ark as the Lord commanded him, then the elephants from India and lions from Persia traveled together with sheep and goats without harming each other; the reptiles and birds headed to where Noah was building the ark. And Noah wept and told the people: “Repent! The flood is coming for you.” And even seeing all this, they didn’t heed his words and didn’t listen to his teachings until the flood waters covered them and they suffered a wretched death. O brethren, let us be afraid, for behold, all that is written is coming to an end and the signs foretold are coming true. And there is already little left of our life and age.

Thus, whoever wants to be saved, let him labor now in humility, abstinence, and alms. For if anyone falls into the hands of robbers, beloved, then see how tenderly he entreats that his life be spared and that they take his property instead. How, brethren, is it not bad that for the sake of a bad life we are divested of everything, but we take no care for our spiritual benefit? Why do we regret giving to the poor? Why don’t we abandon evil deeds and why don’t we incline our hearts towards repentance?

👉 Courtesy: Orthochristian.com

______________

Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

አንተም የዘንዶውን ራሶች ቀጠቀጥህ፤ ለኢትዮጵያ ሰዎችም ምግባቸውን ሰጠሃቸው

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on May 21, 2023

❖❖❖[መዝሙረ ዳዊት ምዕራፍ ፸፫]❖❖❖

  • ፩ አቤቱ፥ ስለ ምን ለዘወትር ጣልኸኝ? በማሰማርያህ በጎች ላይስ ቍጣህን ስለ ምን ተቈጣህ?
  • ፪ አስቀድመህ የፈጠርሃትን ማኅበርህን፥ የተቤዤሃትንም የርስትህን በትር፥ በእርስዋ ያደርህባትን የጽዮንን ተራራ አስብ።
  • ፫ ጠላት በቅዱሳንህ ላይ እንደ ከፋ መጠን፥ ሁልጊዜም በትዕቢታቸው ላይ እጅህን አንሣ።
  • ፬ ጠላቶችህ በበዓል መካከል ተመኩ፤ የማያውቁትንም ምልክት ምልክታቸው አደረጉ።
  • ፭ እንደ ላይኛው መግቢያ ውስጥ በዱር እንዳሉም እንጨቶች፥ በመጥረቢያ በሮችዋን ሰበሩ።
  • ፮ እንዲሁ በመጥረቢያና በመዶሻ ሰበሩአት።
  • ፯ መቅደስህን በእሳት አቃጠሉ፤ የስምህንም ማደሪያ በምድር ውስጥ አረከሱ።
  • ፰ አንድ ሆነው በልባቸው በየሕዝባቸው። ኑ፥ የእግዚአብሔርን በዓሎች ከምድር እንሻር አሉ።
  • ፱ ምልክታችንን አናይም ከእንግዲህ ወዲህም ነቢይ የለም፤ እስከ መቼ እንዲኖር የሚያውቅ በኛ ዘንድ የለም።
  • ፲ አቤቱ፥ ጠላት እስከ መቼ ይሳደባል? ስምህን ጠላት ሁልጊዜ ያቃልላልን?
  • ፲፩ ቀኝህንም በብብትህ መካከል፥ እጅህንም ፈጽመህ ለምን ትመልሳለህ?
  • ፲፪ እግዚአብሔር ግን ከዓለም አስቀድሞ ንጉሥ ነው፥ በምድርም መካከል መድኃኒትን አደረገ።
  • ፲፫ አንተ ባሕርን በኃይልህ አጸናሃት፤ አንተ የእባቦችን ራስ በውኃ ውስጥ ሰበርህ።
  • ፲፬ አንተም የዘንዶውን ራሶች ቀጠቀጥህ፤ ለኢትዮጵያ ሰዎችም ምግባቸውን ሰጠሃቸው።
  • ፲፭ አንተ ምንጮቹንና ፈሳሾቹን ሰነጠቅህ፤ አንተ ሁልጊዜ የሚፈስሱትን ወንዞች አደረቅህ።
  • ፲፮ ቀኑ የአንተ ነው ሌሊቱም የአንተ ነው፤ አንተ ፀሓዩንና ጨረቃውን አዘጋጀህ።
  • ፲፯ አንተ የምድርን ዳርቻ ሁሉ ሠራህ፤ በጋንም ክረምትንም አንተ አደረግህ።
  • ፲፰ ይህን ፍጥረትህን አስብ። ጠላት እግዚአብሔርን ተላገደ፥ ሰነፍ ሕዝብም ስሙን አስቈጣ።
  • ፲፱ የምትገዛልህን ነፍስ ለአራዊት አትስጣት፤ የችግረኞችህን ነፍስ ለዘወትር አትርሳ።
  • ፳ ወደ ኪዳንህ ተመልከት፥ የምድር የጨለማ ስፍራዎች በኅጥኣን ቤቶች ተሞልተዋልና።
  • ፳፩ ችግረኛ አፍሮ አይመለስ፤ ችግረኛና ምስኪን ስምህን ያመሰግናሉ።
  • ፳፪ አቤቱ፥ ተነሥ በቀልህንም ተበቀል፤ ሰነፎች ሁልጊዜም የተላገዱህን አስብ።
  • ፳፫ የባሪያዎችህን ቃል አትርሳ፤ የጠላቶችህ ኵራት ሁልጊዜ ወደ አንተ ይወጣል።

______________

Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

1,100-Year-old Hebrew Bible Sells at Auction for US$38 Million

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on May 20, 2023

💭 የአንድ ሺህ አንድ መቶ/ 1,100 አመት እድሜ ያለው የዕብራይስጥ መጽሐፍ ቅዱስ በ38 ሚሊየን ዶላር በጨረታ ተሸጠ። ይህ የመጀመሪያው በጣም የተሟላየዕብራይስጥ መጽሐፍ ቅዱስ እንደሆነ ይነገርለታ።

💭 ‘Earliest most complete’ Hebrew Bible gets winning bid of $38 million

A Hebrew Bible has attracted a $38 million winning bid in an auction at Sotheby’s.

Sotheby’s auctioned off what it describes as “the earliest most complete Hebrew Bible” in New York on Wednesday.

The Codex Sassoon is believed to have been written around 900 A.D. by Jewish scholars living in modern-day Israel or Syria. The text vanished for centuries before re-emerging in 1929, when it was acquired by collector David Solomon Sassoon, who owned the world’s largest private collection of Hebrew manuscripts.

The Sotheby’s auction house describes the Codex Sassoon as “the earliest surviving example of a single codex containing all the books of the Hebrew Bible.”

Former U.S. Ambassador to Romania, Alfred H. Moses won the auction on behalf of the American Friends of ANU. The Codex will be given to the ANU Museum of the Jewish People in Tel Aviv, where it was previously displayed between March 23 and March 29.

The text’s seller, Jacqui Safra, obtained the Codex in 1989 for $3.19 million, which is equivalent to $7.7 million when adjusted for inflation.

______________

Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

Largest Turkish Overseas Military Base & Embassy Are Located in Somalia

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on May 14, 2023

💭 ትልቁ የቱርክ የባህር ማዶ ወታደራዊ ቤዝ እና ኤምባሲ በሶማሊያ ይገኛሉ

☪ የክርስቶስ ተቃዋሚዎች ሶማሊያ እና ቱርክ በጂሃዳዊ ትግል እህትማማቾች ናቸው። ምስጋና ለሰሜን አትላንቲክ የጦር ቃልኪዳን ‘ኔቶ’

ሶማሌዎች ልክ እንደ ጋላ-ኦሮሞዎች ለቱርኮች ያላቸው ‘ፍቅር’ በጣም ልዩ ነው። ከአምስት መቶ ዓመት በፊት የጀመረ የያኔው ግራኝ ቀዳማዊ እና የአሁኑ ዳግማዊ ግራኝ ግኑኝነት መርዛማ ፍሬ መሆኑ ነው። አዎ! ቱርክ ያሉ ሶማሌዎች ግን ከፍተኛ አድሎ ይፈጸምባቸዋል።

አዎ! ሶማሌዎችና ጋላኦሮሞዎች የአክሱማዊቷ ኢትዮጵያን የአፍሪቃ ቀንድ ግዛቶችን ለመጀመሪያ ጊዜ የረገጡት በ፲፮/16ኛው ክፍለ ዘመን በክርስቶስ ተቃዋሚዎቹ ቱርኮችና በፕሮቴስታንቶች እንዲሁም ካቶሊክኢየሱሳውያን ምኞት፣ ተልዕኮና እርዳታ ነበር። ሶማሌዎችና ጋላኦሮሞዎች በማደጋስካር፣ በታንዛኒያ፣ በቡሩንዲ እና ኬኒያ ያገሬዎችን ነገዶችና ጎሳዎች ከጨፈጨፏቸው በኋላ ነበር ወደ ኢትዮጵያ ግዛቶች ሰተት ብለው እንዲገቡ መሀመዳውያኑ ቱርኮችና ሉተራን ፕሮቴስታንቶች እንዲሁም ካቶሊክኢየሱሳውያን የፈቀዱላቸው። ሶማሌዎቹና ጋላኦሮሞዎቹ ኢትዮጵያም እንደገቡ ከሃያ ስምንት በላይ ጥንታውያን የኢትዮጵያን ነገዶችና ጎሣዎች ከምድረ ገጽ ለማጥፋት በቅተዋል። ዋናውን ተልዕኳቸውን በዚህ በእኛ ዘመን በመተገበር ላይ ይገኛሉ። ያነጣጠረውም በጥንታውያኑን ኦርቶዶክስ ተውሕዶ ክርስቲያኖች ላይ መሆኑን እየየነው ነው።

በኅዳር ጽዮን ቀናት በኦርቶዶክስ ክርስቲያኖች ላይ ጭፍጨፋው እንዲካሄድ የተደረገው በቱርኮች፣ አረቦች፣ አይሁዳውያን እና ፕሮቴስታንቶች ፍላጎትና በሻዕቢያ፣ በሕወሓት፣ በኦነግ/ብልጽግና እና በብአዴን አቀነባባሪነት ነበር። በጭፍጨፋው የተሳተፉትም የኤርትራ ቤን አሚር እና የሶማሌ ታጣቂዎች መሆናቸው የሚነሶታዎቹ ጂሃዳውያን የእነ፣ ጃዋር መሀመድ/Jawar Mohammad ፣ ኢልሃን ኦማር/Ilhan Omar፣ ኪት ኤሊሰን/ Keith Ellison አካሄድ በግልጽ ጠቁሞን ነበር። ፍኖተ ካርታው፤ ሕወሓቶች ወደ ትግራይ እንዲገቡ፣ ግራኝ አብዮት አህመድ እና ኢሳያስ አፈወርቂ/አብደላ-ሃሰን በአስመራ እንዲገናኙ፣ እነ ኢልሃን ኦማር ወደ አስመራ እንዲጓዙ፣ የኖርዌይ የኖቤል ኮሚቴ የሰላም ሽልማቱን ለግራኝ እንዲሰጥ፣ የአሜሪካው ድምጽ (VOA) በበኦባማ አስተዳደር የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት ዋና ፀሀፊ በነበሩት በእነ አምባሳደር ጆኒ ካርሰን/ Johnny Carson በኩል፣ በእነ ጃዋር መሀመድ፣ አሉላ ሰለሞን፣ አቻምየለህ ታምሩ፣ ዶር ደረሰ ጌታቸው በኩል ጋላ-ኦሮሞን በአዲስ አበባ ለማንገስና ተጋሩን ለማራቅ ቅስቀሳዎችን አደረጉ። ሁሉም የሲ.አይ.ኤ ወኪሎች ናቸውን ይህን ስክሪፕትም ሲ.አይ.ኤ ነበር የሰጣቸው።

የሶማሌዎቹን፣ የኢሳያስ ቤን አሚርንና ራሻይዳን፣ የኢዜማን፣ አብንን፣ ፋኖንን፣ የሕወሓትን፣ የብአዴንን እንዲሁም የጋላኦሮሞ ጂሃዳውያኑን ዛሬም ድጋፍ እየሰጧቸው ያሉት መሀመዳውያኑ አረቦች፣ ቱርኮች፣ የማርቲን ሉተር ፕሮቴስታንቶችና የፖፕ ፍራንሲስኮ ካቶሊክኢየሱሳውያን ናቸው።

በትናንትናው ዕለት በጋላ-ኦሮሞዋ: በአቴቴ ብርቱካን ሜድቀሳ የሚመራው የይስሙላው የምርጫ ቦርድ “ሕወሓትን አናውቀውም!” ሲለን፤ እነ ግራኝና ጌታቸው ረዳ + አርከበ እቍባይ ያውጠነጠኑት ሌላ ማለቂያ የሌለው አሰልቺ ድራማ መሆኑን መረዳት አለብን። ለምን? አዎ! ሕወሓት በትግራይ ሕዝብ ዘንድ እየተተፋ ስለመጣ ጽዮናውያን “በእልህ” ከሕወሓት ጋር ተጣብቀው እንዲቀሩ ለማድረግ ሲባል ነው፤ ይህን ሁሉ ሕዝባችንን ጨፍጭፈውና አስጨፍጭፈው እንዲሁም ለረሃብና ስደት አብቅተው ዛሬም ያለሃፍተትና ይሉኝታ ዲያብሎሳዊ ጨዋታቸውን መቀጠል የሚሹት። (Thesis-Antithesis-Synthesis(ተሲስ ፣ ፀረ-ፀረስታ እና ውህደት/መደመር)

ያኔ ወደ ትግራይ የተመለሱት ከሃዲዎቹ ሕወሓቶች በትግራይ ሕዝብ ዘንድ ተቀባይነት ሊያገኙ የቻሉት ከፍተኛ ፀረ-ሕወሓት ቅስቀሳ እንዲደረግና በኋላም በአክሱም ጽዮን ላይ የዘር ማጥፋት ጦርነት እንዲከፈት ከተደረገ በኋላ ነው። የምንሊክ የመጨረሻው ትውልድ የሆኑት ከሃዲዎች በሰሜኑ ሕዝብ ላይ የመዘዙት ካርድ ‘የእልህ ካርድን” ነው። ሕወሓት ከእነ ርዝራዦቹና ሉሲፈር ባንዲራው ባፋጣኝ መወገድ አለባቸው፤ አሊያ የሕዝባችን ስቃይና መከራ ማቆሚያ አይኖረውም።

Antichrist Somalia & Turkey are Sisters in Arms / in Jihad – Courtesy of NATO

🔥 World War III | For the past 500 years, Anti-Christ Turkey is Bombing The World’s Most Ancient Christian Nations: Armenia & Ethiopia

🔥 Ottoman-Portuguese War in Africa – Ethiopian–Adal /Turkish War 🔥

______________

Posted in Ethiopia, News/ዜና, War & Crisis | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

☪ Antichrist Somalia & Turkey are Sisters in Arms / in Jihad

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on May 14, 2023

💭 በመቶዎች የሚቆጠሩ የሶማሊያ ሴቶች የቱርክን መንግስት ለመደገፍ የቱርክን ባንዲራ እያውለበለቡ ሰልፍ ወጡ ፣ መፈንቅለ መንግስት ሙከራውንም አወገዙ።

የክርስቶስ ተቃዋሚዎች ሶማሊያ እና ቱርክ በጂሃዳዊ ትግል እህትማማቾች ናቸው።

አሁንስ? የቱርክ ምርጫ በመጨረሻ የአምባገነኑን ሬሴፕ ጣይብ ኤርዶጋንን መጨረሻ ያሳይ ይሆንን? በአክሱማዊቷ ኢትዮጵያ ክርስቲያኖች ላይ ለደረሰው የዘር ማጥፋት ወንጀል ተጠያቂ ከሆኑት ወንጀለኞች መካከል አንዱ የሆነው ኤርዶጋን ስልጣኑን በፈቃዱ ያስረክባልን? በፍፁም አይመስለኝም። እነዚህ እባቦች በክርስቲያኖች ደም ገና በደንብ አልረኩም!

ሶማሌዎች ልክ እንደ ጋላ-ኦሮሞዎች ለቱርኮች ያላቸው ‘ፍቅር’ በጣም ልዩ ነው። ከአምስት መቶ ዓመት በፊት የጀመረ የያኔው ግራኝ ቀዳማዊ እና የአሁኑ ዳግማዊ ግራኝ ግኑኝነት መርዛማ ፍሬ መሆኑ ነው። አዎ! ቱርክ ያሉ ሶማሌዎች ግን ከፍተኛ አድሎ ይፈጸምባቸዋል።

Antichrist Somalia & Turkey are Sisters in Arms / in Jihad

💭 Hundreds of Somali Women March to Support Turkey Government- Condemn Coup Attempt

How about today, will Turkey’s elections finally spell the end of dictator Recep Tayyip Erdogan? One of the people responsible for the genocide against the Christians of Axumite Ethiopia, will Erdogan willingly hand over his power? I don’t think so at all. These serpents are not quite satisfied with the blood of Christians yet!

______________

Posted in Ethiopia, News/ዜና, War & Crisis | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

 
%d bloggers like this: