Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • March 2023
    M T W T F S S
     12345
    6789101112
    13141516171819
    20212223242526
    2728293031  
  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

Posts Tagged ‘እግዚአብሔር አብ’

ጽዮናዊው ንጉሥ አጽበሃ የመሠረቱት የ የካ ሚካኤል ዋሻ ቤተ ክርስቲያን | እርስቴን ለኦሮሞ ወራሪዎች አሳልፌ አልሰጥም

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on November 22, 2021

St. Michael Church was in use from 320 to 1878 AD

💭 ይህን የአባቶቻችንን ታሪክ የምትሰሙ እና የምታነቡ ጽዮናውያን፤ ወራሪዎቹ ኦሮሞዎች አዲስ አበባን እና ደቡብ ኢትዮጵያን “ኬኛ” ሲሉ ስትሰሟቸው ደማችሁ አይፈላምን?፣ “ከላይ ሆነው የሚያዩን አባቶቻችን ይቆጣሉ፣ ያለቅሳሉ!” ብላችሁ አትደነግጡምን? በጣም የሚያሳዝነው ደግሞ ባለ ወቃማ ታሪክ የሆኑ የትግራይ ወገኖች እንደ ሕወሓት በመሳሰሉ ተዳጋጋሚና አላስፈላጊ የሆነ ስህተት በሚሠሩ ቡድኖች ማንነታቸውን እና ምንነታቸውን፣ ታሪካቸውን፣ ሃይማኖታቸውንና ምልክቶቻቸውን ሁሉ ልክ እንደ ዔሳው እንዲከዱ/እንዲተው/እንዲሸጡ እና ለጠላቶቻቸው እንዲያስረክቡ እየተደረጉ መሆኑ ነው። እስኪ ይታየን፤ እኔ መኪናየን ከእነ ቁልፉ ወይንም ጫማዬን መንገድ ላይ ትቼ ብሄድ እኮ መንገደኛው “የኔ ነው/ኬኛ” ብሎ ይወርሰዋል። አይደል?!

እንግዲህ ፳፯/ 27 ጥንታውያን የኢትዮጵያ ነገዶችን ጨፍጭፈው ከምድረ ገጽ ያጠፏቸው ወራሪዎቹ የዋቄዮ-አላህ አርበኞች የሆኑ ኦሮሞዎች/ ጋሎችም ወደ አብርሃ ወአጽበሐ እና ንጉሥ ዳዊት ከተማ ወደ አዲስ አበባ መጥተው ከመስፈራቸውና “ፊንፊኔ ኬኛ” የሚለውን የእባብ ገንዳ መዝሙራቸውን ከመጻፋቸው ከሺህ ዓመታት በፊት የታነጸውን ታሪካዊውን የየካ ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን / ዋሻን፤ አንድ ጽዮናዊ፤ እንደ አቶ ጌታቸው፤ “አይ እኛ ሥልጣን አንፈልግም፣ ግዛት ለመቀማት አይደለም ቅብርጥሴ” ማለት ሳይሆን የሚጠበቅበት፤ በቀጥታ እና በድፍረት፤ “አይ! ይሄ እኮ የአባቶቻችን እርስት ነው! እኛ ነን የሠራነው፣ ይህን እርስታችንን ለማንም ወራሪ አሳልፈን አንሰጥም፤ አርፈህ ትኖር ከሆነ ኑር አልያ ተጠራርገህ ትወጣ ዘንድ ግድ ይሆናል ወዘተ” የሚል ወገን ነው ዛሬ የሚያስፈልገው።

ዛሬ የእግዚአብሔር አብ ዕለት ነው፣ ወደ ጸሎት በምንገባበት ወቅት የወገኖቻችንን ሰቆቃና ለቅሶ በይበልጥ እየሰማን ነው፤ የአቤል ደም እየጮኸ ነው፤ የጽዮን ጠላቶች እየተርበተበቱ ነው፤ ግን የትም አያመልጧትም፤ ለዓመታት ስናስጠነቅቅ ቆይተናል፤ አሁን አንድ በአንድ በመለኮታዊ ሰይፍ የሚጠረጉበት ጊዜ ተቃርቧል፤ ቀጣዮቹን ቀናት በጥሞና እንከታተላቸው፤ የጽዮናውያን ድልና የዋቄዮአላህ አህዛብ ሽንፈት ወቅት በጣም እየተቃረበ ነው!

ቅድስት በኾነች በጽርሐ ጽዮን በሐዋርያት ላይ የወረደው የእግዚአብሔር አብ ጸጋ፣ የእግዚአብሔር ወልድ ፍቅር፣ የእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ አንድነት በዅላችን ላይ ይደር፤ እጽፍ ድርብም ይኹን።

❖❖❖ ታሪካዊው የካ ደብረ ሳህል ቅዱስ ሚካኤል ዋሻ ቤተክርስቲያን ❖❖❖

በ፬/4ኛው ክፍለ ዘመን በአክሱም ንጉሥ በአጽበሃ ተመሠረተ

❖❖❖ የአንጋፋው ቀደምት እና ባለ ታሪክ የካ ደብረ ሳህል ቅዱስ ሚካኤል ዋሻ ቤተክርስቲያን ታሪክ ❖❖❖

ዋሻ ሚካኤል ከአዲስ አበባ በስተምስራቅ በኩል የካ ከፍለ ከተማ ውስጥ ያለ ጥንታዊ እና በከፊል ወጥ ከሆነ ዓለት ተፈልፍሎ የተሰራ ቤተክርስቲያን ነው። አዲስ አበባ ከሚገኘው የእንግሊዝ ኢምባሲ በስተጀርባ ትንሽ ራቅ ብሎ በሚገኘው ከፍታማ ቦታ ላይ ይገኛል። ምንም እንኳ የአካባቢው የቀደሙት ካህናት በ፬/4ኛው ክፍለ ዘመን እንደተሰራ ቢናገሩም በአብዛኛው ሊሆን ይችላል ተብሎ የሚገመተው ግን በ፲፪/12ኛው ክፍለ ዘመን እንደተሰራ ነው።

👉 ታሪካዊ ተደራሽነቱ

የአክሱም መንግስትና የዋሻ ሚካኤል ውቅር ቤተክርስቲያን:- አብርሃና አጽብሃ የአክሱም መንግስትን በጋራ ይገዙ እንደነበር የተለያዩ መጽሃፍት ይገልፃሉ፡፡ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ጽሁፍም ይሄንን በተለያዩ መረጃዎች ይጠቅሳል፡፡ ክርስትናን ከተቀበሉ በኋላ እንደተፃፈ በሚነገረው የድንጋይ ላይ ፅሁፍ አብርሃና አፅብሃ የሚያስተዳድሩት አገር ግዛት ዝርዝር ተጠቅሷል፡፡ ከዚህ ዝርዝር እንደምንረዳው ግዛታቸው ሳባን /የመንን/፣ ኑባ /ሱዳንን/ እና ቤጃ /ደቡብ ግብጽ/ ድረስ ይደርሳሉ፡፡ ይህም እጅግ ሰፊ ግዛት እንዳላቸው ያስረዳል፡፡ ከየካ ሚካኤል የተገኘው /ያልታተመ/ መረጃ ይህንን ሀሳብ እንደሚከተለው ያጠናክራል።

በዚያን ጊዜ የኢትዮጵያ ወሰን በጣም ሰፊ ስለነበር ሁሉቱ ወንድማማቾች አክሱም ላይ ሆነው ሕዝባቸውን በቅርብ ለማስተዳደር ስለተቸገሩ እጣ ተጣጥለው ንጉስ አብርሃ አክሱም ላይ በመሆን ሰሜን ኢትዮጵያን፣ ንጉስ አጽብሃ ደግሞ ደቡብ ኢትዮጵያን ለማስተዳደር ሸዋ ውስጥ የረር ተራራ ላይ ቤተ መንግሥቱን ሰራ፡፡ በወቅቱ ቤተመንግሥቱን ለመሥራት ሲመጣ ማዕቀበ እግዚእ በሚባል ካህን ታቦት ሚካኤልን አሸክሞ አስመጥቶ ነበር፡፡ ይህንን አሸክሞ ያስመጣውን ታቦት ከየረር ተራራ በስተ ሰሜን አቅጣጫ ባስፈለፈለው ዋሻ ውስጥ እንዳስገባው ይገልፃል፡፡”

በትግራይ ክልል በአብርሃና አፅብሃ ቤተ ክርስትያን ውስጥ ከጅማ የአፅብሃ ሬሳ የመጣበት ነው የሚባለው የጠፍር አልጋ ይገኛል፡፡ ከዚህ የምንረዳው ደቡብ ኢትዮጵያን የሚያስተዳድረው አፅብሃ እስከ ጅማ መድረሱን ነው፡፡ ውቅር ቢተክርስቲያን መስራት ለአጽብሃ አዲስ አይደለም፡፡ በትግራይ ከውቁሮ ከተማ ፳/20 .. ርቀት ላይ ገረአልታ ውስጥ ገማድ በተባለ ስፍራ አብርሃና አጽብሃ ያሰሩት ነው የሚባል አብርሃ አጽብሃ በመባል የሚታወቅ ውቅር ቤተክርስቲያን ይገኛል፡፡ ቤተክርስቲያኑ ገዳም ነው፡፡

ከየካ ሚካኤል የተገኘው/ያልታተመ/ መረጃ እንደሚገልፀው በትግራይ ውቅሮ አካባቢ የሚገኘው የአብርሃና አፅብሃ ውቅር ቤተክርስቲያን ከዋሻ ሚካኤል ውቅር ቤተክርስቲያን ጋር ተመሳሳይነት እንዳለው በመግለጽ ታሪኩን እንደሚከተለው ዘርዝሯል፡-

ከንጉስ አጽብሃ ጋር የመጣው ታቦት የገባበት ዋሻ የተፈጥሮ ዋሻ ሳይሆን በሰሜን ኢትዮጵያ እንደሚገኙት ከአንድ ቋጥኝ ድንጋይ ተፈልፍለው ከታነፁት ጥንታዊ ቤተክርስቲያን ዓይነት በኢትዮጵያ ፊደል “ሀ” ቅርጽ የታነፁ ሲሆን በቤተክርስቲያን የፊደል ትርጉም “ሀ” ማለት “ህልዎቱ ለአብ እምቅድም ይትፈጠር ዓለም” ወይም “የአብ መኖር ከአለም አስቀድሞ ነው” ማለት ነው የሚለውን አባባል ለማስረዳት ተብሎ የታነፀ ነው ይላል፡፡” በሌላ በኩል አንዳንድ የታሪክ ተመራማሪዎች የዋሻ ሚካኤል ውቅር ቤተክርስቲያን በደቡብ ሸዋ ከአዲስ አበባ በስተ ምዕራብ በአለምገና ቡታጅራ መንገድ አቅጣጫ ከአዲስ አበባ ፷፮/66 ኪሎ ሜትር አካባቢ ከምትገኘው አዳዲ ማሪያም ውቅር አብያተ ክርስቲያን ጋር በመመሣሠሉና ይህ ደግሞ በንጉስ ላሊበላ ዘመን እንደ ላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት በዚያ ዘመን የተሰራ ነው ይላሉ፡፡

በአዳዲ ማርያም የሚገኘው የታሪክ ማስታወሻ ንጉስ ላሊበላ የአዳዲ ማሪያምን ከቋጥኝ ድንጋይ እንደፈለፈለውና ሥራውን ሲጨርስ በራዕይ ተመርቶ ወደ ላሊበላ እንደተመለሰና እዚያ ሲደረሰ እንደሞተ ይተርካል፡፡

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በየሶስት ወሩ በሚያሳትመውና ሰላምታ ተብሎ በሚጠራው ቋሚ የበረራ መፅሄት ዊሊያም ዴቪድሰን የተባሉ የታሪክ ተመራማሪ የዋሻ ሚካኤል ውቅር ቤተክርስትያን የ፯፻/700 ዓመት እድሜ እንዳለውና አሰራሩም ከላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት አሰራር ጋር እንደሚመሳሰል ይገልፃሉ፡፡

በየትኛው ዘመን እንደተሰራ ለማወቅ የአርኪዎሎጂ ጥናት መደረግ ስላለበት የነሱን የወደፊት የጥናት ውጤት መጠበቁ ወሳኝ ቢሆንም ከየካ ደብረሳህል ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስትያን ያገኘነው ያልታተመ ፅሁፍ የዋሻ ሚካኤል ውቅር ቤተክርስትኑ ከላሊበላ ጋር በማመሳሰል ማቅረብ የኢትዮጵያን ሀይማኖት ጥንታዊነት በሚፃረሩ ሀይሎች የሚወራ ነው በማለት ይቃወማሉ፡፡

አብርሃና አፅብሃ ከአባታቸው ታዜር ከእናታቸው ሶፍያ (አይዋል) ታህሳስ ፲፱/19ቀን ፫፻፲፪/312 .. ተወለዱ፡፡ አባ ሰላማ (አባ ከሣቴ ብርሃን) በ፳፰/28ኛ ዓመታቸው አጠመቁዋቸው፡፡ አብርሃና አጽብሃ ከአባ ሰላማ ጋር በመሆን ክርስትናን በግዛታቸው አስፋፍተዋል፡፡ በዘመናቸው ፷/60 አብያተ ክርስቲያናትን እንዳሳነፁና ከዚህም ውስጥ ፵፬/44 ቤተክርስቲያናት ፍልፍል ቤተክርስቲያናት ናቸው፡፡ በስማቸው ቤተክርስቲያን ታንፃል፡፡ በየወሩ በ፬/4ኛው ቀንና በየዓመቱ ጥቅምት ፬/4 በአክሱም ፅዮንና መርጦ ለማርያም ቤተክርስትያናት በዓላቸው ይከበራል፡፡

እንደ ነገሥታቱ ገድል በ፴፪/32ዐዎቹ ንጉሥ አጽብሃ በየረር ተራራ ላይ የገነባው ቤተ መንግሥትና ከቤተመንግሥቱ በስተ ሰሜን አቅጣጫ የተገነባው ውቅር ቤተክርስቲያን በአባ ከሣቴ ብርሃን የመጀመሪያው ጳጳስ ተባርኮ ተመረቀ፡፡

አብርሃና አጽብሃ የጀመሩትን ክርስትናን የማስፋፋት ሥራ በተከታዮችም ነገሥታት የቀጠለ ሲሆን በ፮/6ተኛው ክፍለ ዘመን በአፄ ካሌብና በአፄ ገ/መስቀል የንግስና ዘመን በበለጠ ተስፋፍቷል፡፡ በ፮/6ተኛው ክ/ዘመን በተለይ ዘጠኙ ቅድሳን ከመጡ በኋላ ክርስትናን የማሠራጨቱ ሥራ ይበልጥ ተስፋፍቷል፡፡

በአክሱም ዘመነ መንግስት ዮዲት ጉዲት የተባለች በአክሱም ግዛት ያሉትን አብያተ ክርስቲያናትና ቄሶችን ማጥፋት በጀመረች ጊዜ የአክሱም ፅዮንን ጨምሮ አንዳንድ ታቦታት ወደተለያዩ ቦታዎች ተሰደዋል፡፡ ምናልባት እነዚህ የፀረ ክርስትና ሰዎች አጽብሃ ወዳሰራው ውቅር ቤተክርስቲያን ቢመጡም ታቦቱን የእምነቱ ተከታዮች እስከ ፲፰፻፴፰/1838 ዓ.ም ድረስ ይዘው ሲሰደዱ እንደቆዩና በመጨረሻ ቡልጋ ውስጥ ከሚገኘው ኢቲሳ ተ/ሃይማኖት ገዳም የቅዱስ ሚካኤልን ጽላት እንዳመጡት ይነገራል፡፡

__________________

Posted in Ethiopia, Faith, War & Crisis | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

እግዚአብሔር አብ ፥ የአጽናፈ ዓለሙ ፈጣሪ እና ገዥ ተዓምሩን በቅርቡ ያሳየናል

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on November 22, 2021

💭 በአስደናቂ ልዩ ጥበብ የተሠራውና “አዲሱ ገበያ” ተብሎ በሚጠራው ሠፈር የሚገኘው ውቡ የእግዚአብሔር አብ ቤ/ክርስቲያን ሕንፃ፤ አዲስ አበባ ፳፻፲ ወ ፩ ዓ.ም።

💭 እንዲሁም ፳፯/ 27 ጥንታውያን የኢትዮጵያ ነገዶችን ጨፍጭፈው ከምድረ ገጽ ያጠፏቸው ወራሪዎቹ የዋቄዮ-አላህ አርበኞች የሆኑ ኦሮሞዎች/ ጋሎች ወደ አብርሃ ወአጽበሐ እና ንጉሥ ዳዊት ከተማ ወደ አዲስ አበባ መጥተው ከመስፈራቸውና “ፊንፊኔ ኬኛ” የሚለውን የእባብ ገንዳ መዝሙራቸውን ከመጻፋቸው ከሺህ ዓመታት በፊት የታነጸው ታሪካዊው የካ ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን / ዋሻ

ዛሬ የእግዚአብሔር አብ ዕለት ነው፣ ወደ ጸሎት በምንገባበት ወቅት የወገኖቻችንን ሰቆቃና ለቅሶ በይበልጥ እየሰማን ነው፤ የአቤል ደም እየጮኸ ነው፤ የጽዮን ጠላቶች እየተርበተበቱ ነው፤ ግን የትም አያመልጧትም፤ ለዓመታት ስናስጠነቅቅ ቆይተናል፤ አሁን አንድ በአንድ በመለኮታዊ ሰይፍ የሚጠረጉበት ጊዜ ተቃርቧል፤ ቀጣዮቹን ቀናት በጥሞና እንከታተላቸው፤ የጽዮናውያን ድልና የዋቄዮ-አላህ አህዛብ ሽንፈት ወቅት በጣም እየተቃረበ ነው!

ቅድስት በኾነች በጽርሐ ጽዮን በሐዋርያት ላይ የወረደው የእግዚአብሔር አብ ጸጋ፣ የእግዚአብሔር ወልድ ፍቅር፣ የእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ አንድነት በዅላችን ላይ ይደር፤ እጽፍ ድርብም ይኹን።

___________________

Posted in Ethiopia, Faith, War & Crisis | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

መንፈስ ቅዱስ በሰው ላይ አድሮ ጥበብን ይገልጣል

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on June 7, 2020

እንኳን ለበዓለ ጰራቅሊጦስ በሰላም አደረሰን!

ጰራቅሊጦስ› የሚለው ቃል ከሦስቱ አካላት አንዱ የኾነው የእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ መጠሪያ ስም ሲኾን፣ ትርጕሙም በጽርዕ (ግሪክ) ቋንቋ

  • 👉 ናዛዚ (የሚናዝዝ)
  • 👉 መጽንዒ (የሚያጸና)
  • 👉 መስተፍሥሒ (የሚያስደስት) ማለት ነው።

መንፈስ ቅዱስ ለሐዋርያት በወረደበት ዕለት በቤተ ክርስቲያን የሚከበረው ይህ በዓል ‹በዓለ ጰራቅሊጦስ› ወይም ‹በዓለ ጰንጠቆስጤ› በመባል ይታወቃል። ‹ጰንጠቆስጤ› በግሪክ ቋንቋ በዓለ ኀምሳ፣ የፋሲካ ኀምሳኛ ዕለት፣ በዓለ ሠዊት (የእሸት፣ የመከር በዓል) ማለት ነው (ኪዳነ ወልድ ክፍሌ፣ ገጽ ፱፻፮፱፻፯)

ጌታችን አምላካችንና መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ካረገ በኋላ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም፣ ዐሥራ ሁለቱ ደቀ መዛሙርት፣ ሰባ ሁለቱ አርድእት፣ አምስት መቶው ባልንጀሮች እና ሠላሳ ስድስቱ ቅዱሳት አንስት በኢየሩሳሌም ከተማ በአንድነት ኾነው በጸሎት ይተጉ ነበር።

ጌታችን በሚያርግበት ጊዜ እነሆ አባቴ የሰጠውን ተስፋ እኔ እልክላችኋለሁ፤ እናንተ ግን ከላይ ኃይል እስክትለብሱ ድረስ በኢየሩሳሌም ከተማ ቆዩ፤ሲል ለሐዋርያቱ በሰጣቸው የተስፋ ቃል መሠረት በዐረገ በዐሥረኛው ቀን መንፈስ ቅዱስን ልኮላቸዋል (ሉቃ. ፳፬፥፵፱)። ዅሉም በአንድ ቦታ ተሰባስበው ሳሉ በበዓለ ጰራቅሊጦስ ማለዳ እንደ ዐውሎ ነፋስ ያለ ድምፅ ድንገት ከሰማይ ወርዶ የነበሩበትን ቤት ሞላው። ከዚያም የተከፋፈሉ የእሳት ላንቃዎች በዅሉም ላይ አረፉባቸው። በዚህ ጊዜ ዅላቸውም መንፈስ ቅዱስ ባደላቸው መጠን በየአገሩ ቋንቋዎች ዅሉ ተናገሩ (ሐዋ.፪፥፩)

ጌታችን መንፈስ ቅዱስን ለሐዋርያት የላከበት ይህ ዐቢይ በዓል ዐሥራቱን፣ በኵራቱን፣ ቀዳምያቱን ካህናተ ኦሪት ስለሚቀበሉበት በብሉይ ኪዳን በዓለ ሠዊት ተብሎ ይከበር ነበር። በሐዲስ ኪዳን ደግሞ ቅዱሳን ሐዋርያት መንፈስ ቅዱስን ስለ ተቀበሉበት በበዓለ ሠዊት ምትክ በዓለ ጰራቅሊጦስ ገብቶበታል። የበዓለ ትንሣኤ መነሻው የአይሁድ የፋሲካ በዓል ማለትም በግብጽ፣ እስራኤል ከሞት የዳኑበት የመታሰቢያ በዓል እንደ ኾነው ዅሉ፣ ለበዓለ ጰራቅሊጦስም መነሻው ይኸው የአይሁድ የፋሲካ በዓል ነው። የአይሁድ ፋሲካ ከተከበረ ከሰባት ሳምንታት በኋላ በኀምሳኛው ቀን የሩቆቹ ከከተሙበት ወጥተው፣ የቅርቦቹ ከተሰባሰቡበት ተገናኝተው ለበዓሉ ፍጻሜ የሚኾነውን በዓለ ሠዊት (የእሸት በዓል) ያከብሩ ነበር።

ሐዋርያት በጽርሐ ጽዮን ተሰባስበው ሳሉ መንፈስ ቅዱስ በእሳት አምሳል ወርዶ ሰማያዊ ሀብትን፣ ዕውቀትና ጸጋን አድሏቸዋል መንፈስ ቅዱስ ከወረደላቸው በኋላም በአእምሮ ጐልምሰዋል፤ ጥቡዓን (ቈራጦች)፣ ጽኑዓን ኾነዋል፤ ለስብከተ ወንጌል የሚፋጠኑበትንና ለሰማዕትነት የሚዘጋጁበትን ልቡና ታድለዋል

ቅድስት በኾነች በጽርሐ ጽዮን በሐዋርያት ላይ የወረደው የእግዚአብሔር አብ ጸጋ፣ የእግዚአብሔር ወልድ ፍቅር፣ የእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ አንድነት በዅላችን ላይ ይደር፤ እጽፍ ድርብም ይኹን

___________________________________

Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , | Leave a Comment »

ጰራቅሊጦስ | መንፈስ ቅዱስ በሰው ላይ አድሮ ጥበብን ይገልጣል

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on June 15, 2019

እንኳን ለበዓለ ጰራቅሊጦስ በሰላም አደረሰን!

እግዚአብሔር መንፈስ በሰው ላይ አድሮ ጥበብን ይገልጣል

ጰራቅሊጦስ› የሚለው ቃል ከሦስቱ አካላት አንዱ የኾነው የእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ መጠሪያ ስም ሲኾን፣ ትርጕሙም በጽርዕ (ግሪክ) ቋንቋ

  • ናዛዚ (የሚናዝዝ)
  • መጽንዒ (የሚያጸና)
  • መስተፍሥሒ (የሚያስደስት) ማለት ነው።

መንፈስ ቅዱስ ለሐዋርያት በወረደበት ዕለት በቤተ ክርስቲያን የሚከበረው ይህ በዓል ‹በዓለ ጰራቅሊጦስ› ወይም ‹በዓለ ጰንጠቆስጤ› በመባል ይታወቃል። ‹ጰንጠቆስጤ› በግሪክ ቋንቋ በዓለ ኀምሳ፣ የፋሲካ ኀምሳኛ ዕለት፣ በዓለ ሠዊት (የእሸት፣ የመከር በዓል) ማለት ነው (ኪዳነ ወልድ ክፍሌ፣ ገጽ ፱፻፮፱፻፯)

ጌታችን አምላካችንና መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ካረገ በኋላ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም፣ ዐሥራ ሁለቱ ደቀ መዛሙርት፣ ሰባ ሁለቱ አርድእት፣ አምስት መቶው ባልንጀሮች እና ሠላሳ ስድስቱ ቅዱሳት አንስት በኢየሩሳሌም ከተማ በአንድነት ኾነው በጸሎት ይተጉ ነበር።

ጌታችን በሚያርግበት ጊዜ ‹‹እነሆ አባቴ የሰጠውን ተስፋ እኔ እልክላችኋለሁ፤ እናንተ ግን ከላይ ኃይል እስክትለብሱ ድረስ በኢየሩሳሌም ከተማ ቆዩ፤›› ሲል ለሐዋርያቱ በሰጣቸው የተስፋ ቃል መሠረት በዐረገ በዐሥረኛው ቀን መንፈስ ቅዱስን ልኮላቸዋል (ሉቃ. ፳፬፥፵፱)። ዅሉም በአንድ ቦታ ተሰባስበው ሳሉ በበዓለ ጰራቅሊጦስ ማለዳ እንደ ዐውሎ ነፋስ ያለ ድምፅ ድንገት ከሰማይ ወርዶ የነበሩበትን ቤት ሞላው። ከዚያም የተከፋፈሉ የእሳት ላንቃዎች በዅሉም ላይ አረፉባቸው። በዚህ ጊዜ ዅላቸውም መንፈስ ቅዱስ ባደላቸው መጠን በየአገሩ ቋንቋዎች ዅሉ ተናገሩ (ሐዋ.፪፥፩)

ጌታችን መንፈስ ቅዱስን ለሐዋርያት የላከበት ይህ ዐቢይ በዓል ዐሥራቱን፣ በኵራቱን፣ ቀዳምያቱን ካህናተ ኦሪት ስለሚቀበሉበት በብሉይ ኪዳን በዓለ ሠዊት ተብሎ ይከበር ነበር። በሐዲስ ኪዳን ደግሞ ቅዱሳን ሐዋርያት መንፈስ ቅዱስን ስለ ተቀበሉበት በበዓለ ሠዊት ምትክ በዓለ ጰራቅሊጦስ ገብቶበታል። የበዓለ ትንሣኤ መነሻው የአይሁድ የፋሲካ በዓል ማለትም በግብጽ፣ እስራኤል ከሞት የዳኑበት የመታሰቢያ በዓል እንደ ኾነው ዅሉ፣ ለበዓለ ጰራቅሊጦስም መነሻው ይኸው የአይሁድ የፋሲካ በዓል ነው። የአይሁድ ፋሲካ ከተከበረ ከሰባት ሳምንታት በኋላ በኀምሳኛው ቀን የሩቆቹ ከከተሙበት ወጥተው፣ የቅርቦቹ ከተሰባሰቡበት ተገናኝተው ለበዓሉ ፍጻሜ የሚኾነውን በዓለ ሠዊት (የእሸት በዓል) ያከብሩ ነበር።

ሐዋርያት በጽርሐ ጽዮን ተሰባስበው ሳሉ መንፈስ ቅዱስ በእሳት አምሳል ወርዶ ሰማያዊ ሀብትን፣ ዕውቀትና ጸጋን አድሏቸዋል መንፈስ ቅዱስ ከወረደላቸው በኋላም በአእምሮ ጐልምሰዋል፤ ጥቡዓን (ቈራጦች)፣ ጽኑዓን ኾነዋል፤ ለስብከተ ወንጌል የሚፋጠኑበትንና ለሰማዕትነት የሚዘጋጁበትን ልቡና ታድለዋል

ቅድስት በኾነች በጽርሐ ጽዮን በሐዋርያት ላይ የወረደው የእግዚአብሔር አብ ጸጋ፣ የእግዚአብሔር ወልድ ፍቅር፣ የእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ አንድነት በዅላችን ላይ ይደር፤ እጽፍ ድርብም ይኹን።

___________________

Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , | Leave a Comment »

እግዚሐርአብ-ሰርግ-እርግብ = ሰእርግብ | ቅዱስ ጋብቻ በተዋሕዶ ብቻ እንደሚገኝ እርግቦቹ መሠከሩ

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on May 21, 2019

ይህን ባየንበት ወቅት የሁላችንም እምባ መጥቶ ነበር። ዛሬ ማክሰኞ ነው፤ እግዚአብሔር፦ የምድር አራዊትንና የሰማይ ወፎችን ሁሉ፦ ሕያው ነፍስ ላለውም ሁሉ ስም ያወጣላቸው ዘንድ ወደ አዳም አመጣቸው። እግዚአብሔር ሰኞ ማክሰኞ አዕዋፋትን አመጣለት፤ ነገር ግን ለአዳም እንደ እርሱ ያለ ረዳት አልተገኘለትም ነበርና አጭቶ፥ ወድዶ፥ ፈቅዶ እንዲገባበት ሔዋንን ከጎኑ አንዲት አጥንት ወስዶ ሴት አድርጎ ሠራለት። አዳምም፦ “ይህች አጥንት ከአጥንቴ ናት ፥ ሥጋም ከሥጋዬ ናት፤ እርስዋ ከወንድ ተገኝታለችና ሴት ትባል። ስለዚህ ሰው አባቱንና እናቱን ይተዋል፥ ከሚስቱም ይጣበቃል፤ ሁለቱም አንድ ሥጋ ይሆናሉ።” ብሎ እግዚአብሔር የሰጠውን በጸጋ ተቀበለ።

አዳምና ሔዋን በጋብቻ አንድ አካል መሆናቸው፦ ሔዋን ከአዳም የጎን አጥንት በመፈጠሯ ብቻ አይደለም። አንድ ክብር በመውረስም ነው። ሐዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስ፦ “እናንተ ባሎች ሆይ ፥ ደካማ ፍጥረት ስለሆኑ ከሚስቶቻችሁ ጋር በማስተዋል አብራችሁ ኑሩ፤ ጸሎታችሁ እንዳይከለከል አብረው ደግሞ የሕይወትን ጸጋ እንደሚወርሱ አድረጋችሁ አክብሩ አቸው።” ያለው ለዚህ ነው። ፩ኛ ጴጥ ፫፥፯። ከዚህም ሌላ አንድነታቸው አንድ ልብስ በመልበስ ነው። ፈቃደ ሥጋቸው በጠ የቃቸው ጊዜም በግብር አንድ ይሆናሉ። ወንድ ቢወለድ ያንተ ነው፥ ሴት ብትወለድ ያንቺ ነው አይባባሉም። ሁለት ሆነው አንድ ልጅ ያስገኛሉ። አንድም፦ ከእናት ደም ፥ ከአባት ዘር ተከፍሎ አንድ ሰው ሁኖ ይወለዳል።

የጋብቻ ዓላማዎች ሦሰት ናቸው፦

የመጀመሪያው። “የሚመቸውን ረዳት እንፍጠርለት” እንዲል፦ ለመረዳዳት ነው። መረዳዳት ሲባልም በሥጋ ብቻ አይደለም በነፍስም ጭምር ነው። ለሥጋቸው በሥራ ሲረዳዱ ለነፍሳችው ደግሞ በጸሎት ይረዳዳሉ። ለምሳሌ፦ ይስሐቅ፦ ሚስቱ ርብቃ ለሃያ ዓመታት መክና ልጅ አልወለደችለትም ነበር። በዚህም ምክንያት ስለ ርብቃ ወደ እግዚአብሔር ጸለየ ፥ እግዚአብሔርም ተለመነው፥ ርብቃም መንታ ፀነሰች ይላል። ዘፍ ፳፭ ፥፳፩። ሁለተኛው በፍትወተ ሥጋ ላለመቸገር ነው። ሦስተኛው ደግሞ፦ “ወንድና ሴት አድርጎ ፈጠራቸው ፥እግዚአብሔርም ባረካቸው ፥እንዲህም አላቸው፦ ብዙ ተባዙ ፥ምድርንም ሙሉአት።” እንዲል፦ ዘር ለመተካት ነው። ዘፍ ፩፥፳፰። እነዚህም እንደ ሦስት ጉልቻዎች የሚቆጠሩ ናቸው።

አዎ! እግዚአብሔርን ስንቀርበው ፥ ይቀርበናል፤ ስንረቀው ይርቀናል። እግዚአብሔርን በቀረቡ ተዋሕዶዎች ዘንድ ፩ + = ፩ ሲሆኑ እግዚአብሔርን በራቁት በሌሎች ዘንድ ግን ፩ + = ፪ ናቸው። ስለዚህ ቅዱስ ጋብቻ በሌሎች ዘንድ የለም ለማለት ያስደፍራልበሌሎች ዘንድ ሁሉም ነገር ሂሳብ ነው፡ ዓለማዊ ነው፤ ከጋብቻ በፊት “መልአክ” የተባለ የትዳር ጓደኛ ከጋብቻ በኋላ “ሰይጣን” ይባላል። በመላው ዓለም እንደምናየው ወንዱ ወንድነቱን ሴቷ ሴትነቷን በማጣት ፍቅርአልቦች፣ አመጸኞች እና ጨካኞች ለልጆቻቸው ነፍስ የማይቆረቆሩ ግድየለሾች ይሆናሉ፤ ትዳራቸውም የሲዖል ነው። ይህ ክስተት ዛሬ “ለዘብተኞች”፣ “ፌሚኒስቶች” ፣ “ሰዶማውያን”፣ “መሀመዳውያን” በሚባሉት ዘንድ በደንብ እየተንጸባረቀ ይታያል።

ኢትዮጲያዊ ሲፋቀር አቤት ሲያምር ፥ ኢትዮጵያውያን በራሳቸው ጎዳና ሲራመዱ ሁሉም መዋደዱ! የምንጓዝበት መንገድ መንፈሳዊ ከሆነ በሁሉም በኩል ሰላም፣ ፍቅር፣ ብልጽግና እና ደስታ ሲነግሱ እናያለን፤ እርግቦቹ (መንፈስ ቅዱስ) እንደሚያሳዩን።

ታላቋ አገራችን ከተዋሕዶ ውጭ የሚገኙትን ትርኪምርኪ መጤ የምዕራባውያንን (ዔሳው)እና የአርቦችን(እስማኤል)አምልኮቶችን፣ ርዕዮተ-ዓለሞችንና ባሕሎችን አስገብታ መቀበል ስትጀምር ነው ፍቅር እየቀዘቀዘ፣ ሰላም እየጠፋባት፣ እንስሳቱ፣ አራዊቱ እና አዕዋፋት እየራቁባት፣ ድርቅ፣ ረሃብ እና በሽታ እየሰፈኑባት፤ ባጠቃላይ እያነሰችና እየወደቀች የመጣችው።

__________________

Posted in Ethiopia, Faith, Love | Tagged: , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

ሙሽሪት ኢትዮጵያ ጠላትሽ ይንቀጥቀጥ ይሁን እያሪኮ፤ በነገድ በዘርም የእልፍነሽ አንቺኮ

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on May 19, 2019

[ወደ ኤፌሶን ሰዎች ፭፥፲፱]

በመዝሙርና በዝማሬ በመንፈሳዊም ቅኔ እርስ በርሳችሁ ተነጋገሩ፤ ለጌታ በልባችሁ ተቀኙና ዘምሩ”

__________________

Posted in Ethiopia, Faith, Love | Tagged: , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

 
%d bloggers like this: