Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • March 2023
    M T W T F S S
     12345
    6789101112
    13141516171819
    20212223242526
    2728293031  
  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

Posts Tagged ‘እንጦጦ’

የእግዚአብሔርን ፍጹም አንድነትና ልዩ ሦስትነት ማመን ከሁሉ ይቀድማል

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on January 15, 2022

❖ ❖ ❖

ያለምንም ጉድለት በሥላሴ ስም ይህን ሦስትነት አምናለሁ፤ ወዳጅ መስለው ጽዮናውያንን በመጠጋት፣ እያታለሉና በየዋሕ እንግዳ ተመስለው አክሱም ጽዮንን ያጠቋትን የጽዮን ጠላቶች የሆኑትንና በጽዮን ልጆች ላይ በጣም ብዙ ግፍ ያደረሱትን የዋቄዮ-አላህ-አቴቴ አጋንንቶችን እነ ግራኝ አብዮት አህመድ አሊ እና ተከታይ አህዛብ፣ እባብ ገንዳ (አባ ገዳ) መንጋውን 😈 ሁሉ የእግዚአብሔር ቃል መቅ ያውርዳቸው፣ በተሣለ የመለኮት ሠይፍ አንገታቸውን ይረደው። አሜን! አሜን! አሜን!

✞✞✞ምስጢረ ሥላሴ፡ የእግዚአብሔርን ፍጹም አንድነትና ልዩ ሦስትነት ማመን ከሁሉ ይቀድማል✞✞✞

በዐይነ ሥጋ የማይታይና የማይመረመር፣ ሁሉን ማድረግ የሚችል፣ የሰው ህሊና አስሶ የማይደርስበት፣ ሁሉን የፈጠረ፣ መጀመሪያና መጨረሻ የሌለው፣ ለዘላለም የሚኖር አምላክ መኖሩን እናምናለን፡፡ እርሱም በአካል፣ በስም፣ በግብር ሦስት፤ በባሕርይ፣ በመለኮት፣ በሕልውና፣ በፈቃድ አንድ ነው፡፡ ከዚህም ባሻገር በመስጠት በመንሳት፣ በመፍጠር በማሳለፍ፣ በመግዛትና በአኗኗር አንድ ነው፡፡

ሥላሴ” የሚለው ቃል “ሠለሰ” ሦስት አደረገ ካለው የግዕዝ ግሥ የተገኘ ሲሆን ትርጉሙም ሦስትነት ማለት ነው፡፡ ቅድስት ሥላሴ ስንል ለሥላሴ ቅድስት ብለን እንቀጽላለን፡፡ ቅድስት ሥላሴ ማለት ልዩ ሦስትነት ማለት ነው፡፡ ይህም ሦስት ሲሆኑ አንድ፣ አንድ ሲሆን ሦስት ስለሚሆኑ ልዩ ሦስትነት ተብሏል፡፡ ሥላሴ የሚለውን ቃል ለመጀመሪያ ጊዜ ያለና የሚኖረውን አምላክ ለመግለጽ የተጠቀመው የአንጾኪያው ቴዎፍሎስ በ169 ዓ.ም ነው፡፡ኋላም በኒቅያ ጉባዔ 318ቱ ሊቃውንት አጽንተውታል፡፡ እነዚህ ሊቃውንት በቅዱሳት መጻሕፍት የተመሰከረውን የእግዚአብሔርን ፍጹም አንድነትና ልዩ ሦስትነት ለእኛ በሚረዳ ቋንቋ ገለጡት እንጂ አዲስ ትምህርት አላመጡም፡፡ ይልቁንም ነገረ ሥላሴን ሳይረዱ በሥላሴ መካከል የክብርና የተቀድሞ ልዩነት ያለ አስመስለው በክህደት ትምህርት የተነሱ መናፍቃንን ክህደት ለማስረዳት፣ የሐዋርያዊት ቤተክርስቲያንን የቀናች ሃይማኖት ለመግለጥ ምሥጢረ ሥላሴን አብራርተው አስተምረዋል፡፡

ምስጢረ ሥላሴ ማለት የአንድነት የሦስትነት ምስጢር ማለት ነው፡፡ ምሥጢር መባሉም በእምነት የተገለጠ፣ ያለ እምነትም የማይመረመር ስለሆነ ነው፡፡ ይኸውም አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ በስም፣ በአካል፣ በግብር ሦስት ሲሆኑ በባሕርይ በሕልውና፣ በመለኮት ደግሞ አንድ ናቸው፡፡ እንደዚህ ባለ ድንቅ ነገር አንድ ሲሆኑ ሦስት፣ ሦስት ሲሆኑ አንድ ይባላሉና፣ ይህም ልዩ ሦስትነት ረቂቅ እና በሰው አእምሮ የማይመረመር ስለሆነ ምስጢር ይባላል፡፡ ስለዚህም በአንድ አምላክ፣ በሦስቱ አካላት እናምናለን፡፡

የክርስትና ዶግማ (መሠረተ እምነት) በምስጢረ ሥላሴ ላይ የተመሠረተ ነው፡፡ ምስጢረ ሥላሴ የእምነታችን ዋነኛው ምሰሶ ነው፡፡ በመዳን ትምህርት ውስጥ የመጀመሪያውን ደረጃ የሚይዘው ምስጢረ ሥላሴ ነው፡፡ ለመዳናችንም መሠረት ነው፡፡ ክርስቲያኖች ሁላችን የተጠመቅነው በሥላሴ (በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ) ስም ነው (ማቴ 2819)፡፡ የሥራችን ሁሉ መጀመሪያም አድርገን በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ስንልም በሥላሴ ማመናችንን እየመሰከርን ነው፡፡ በሥራችን መጨረሻም “ምስጋና ይሁን አንድ አምላክ ለሚሆን ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ ዛሬም ዘወትርም ለዘላለሙ አሜን” ብለን ሥራችንን በሥላሴ ስም ጀምረን በሥላሴ ስም እንፈጽማለን፡፡ሆኖም ግን ምስጢረ ሥላሴ ለሰው አእምሮ እጅግ የረቀቀ ስለሆነ የሰው አእምሮ ሊያውቅ የሚችለው እግዚአብሔር በገለጠለት መጠን ብቻ ነው፡፡

የአንድነት ምስጢር – አንድ አምላክ

ስለ ሥላሴ አንድነትና ሦስትነት ስናነሳ ቀድመን የምንመለከተው ”አንድነትን” ነው። ይህም የሆነበት ምክንያት ለአንድነታቸውና ለሦስትነታቸው መቀዳደም ኑሮበት ሳይሆን የቁጥር መሠረት አንድ ስለሆነ በዝያው ለመጀመር ነው /እንዘ አሐዱ ሠለስቱ ወእንዘ ሠለስቱ አሐዱ/፡፡ ሥላሴ ሦስት ናቸው ስንል እንደ አብርሃም፣ እንደ ይስሐቅ እንደ ያዕቆብ የተነጣጠለና በክብርም ሆነ በዘመን የሚበላለጥ የሚቀዳደም ማለታችን አይደለም፡፡ ሦስት ሲሆኑ አንድ ናቸው እንጂ፡፡ አንድ ናቸውም ስንል ከሰው ሁሉ ቀዳሚ ሆኖ እንደተፈጠረው እንደ አዳም ሦስትነትን የሚጠቀልል መቀላቀል ማለታችን አይደለም፡፡ አንድ ሲሆኑ ሦስት ናቸው እንጂ፡፡ /ቅዳሴ ማርያም/፡፡ ሥላሴ ቅድስት ተብሎ በሴት አንቀጽ መጠራታቸው ወላድያነ ዓለም (ዓለምን ያስገኙ) መሆናቸውን ለማጠየቅ ነው፤ እናት ለልጇ ስለምታዝንና ስለምትራራ ሥላሴም ለፍጥረታቸው ምሕረታቸው ዘለዓለማዊ ነውና ቅድስት ይባላሉ፡፡

ባህርይ ማለት ምንነትን የሚያሳይ ሲሆን የእግዚአብሔር ባህርይ የሚባሉትም የመለኮትነቱ ባህርያት ናቸው፡፡ አካል የምንለው ደግሞ ማንነትን የሚገልጽ ሲሆን ሦስቱ አካላት የምንላቸው የአምላክን ማንነት የሚገልጹ ናቸው፡፡ ባሕርይ ማለት “ብሕረ ተንጣለለ፥ ሰፋ፥ ዘረጋ” ከሚለው ግስ የወጣ ነው። በቲኦሎጂ /በነገረ መለኮት/ ቋንቋ ሲፈታም ባሕርይ ማለት ሥርው፥ ነቅዕ አዋሃጅ /የሚያዋሕድ/ አስተገባኢ ማለት ነው። ባሕርይ አካል ሥራውን የሚሠራበት መሣሪያ ነው። ባሕርይና አካል እንደ አጽቅና እንደ ሥር አንድ ናቸው፤ አይለያዩም፣ አንዱ ያለ አንዱ መኖር አይችልም። እግዚአብሔር በአንድነቱ የሚታወቅበት ስሞች ፈጣሪ፣ አምላክ፣ ጌታ፣ መለኮት፣ እግዚአብሔር፣ ጸባኦት፣ አዶናይ፣ ኤልሻዳይ የመሳሰሉት ናቸው፡፡ ሥላሴ በባሕርይ ረቂቅ ናቸው፡፡ ርቀታቸውስ እንዴት ነው? ቢሉ ከፍጥረት ሁሉ ነፋስ ይረቃል፡፡ ከነፋስ የሰው ነፍስ ትረቃለች፡፡ ከነፍስ መላእክት ይረቃሉ፡፡ ከነፍሳትና ከመላእክት ደግሞ ኅሊናቸው ይረቃል፡፡ ይህ የኅሊናቸው ርቀት በሥላሴ ዘንድ እንደ አምባ እንደ ተራራ ነው፡፡ በዚህም ርቀታቸው በፍጥረት ሁሉ ምሉዓን፣ ኅዱራን ናቸው፡፡ ባሕርያቸውም የማይራብ፣ የማይጠማ፣ የማይደክም፣ የማይታመም፣ የማይሞት ሕያው ነው፡፡ «ስምከ ሕያው ዘኢይመውት ትጉህ ዘኢይዴቅስ ፈጣሪ ዘኢይደክም» እንዳለ /ቅዲስ ባስልዮስ በማክሰኞ ሊጦን/፡፡

እግዚአብሔር አንድ መለኮታዊ ባህርይ፣ ዘላለማዊ የሆነ አምላክ ነው፡፡ መለኮት ማለት “መለከ – ገዛ” ከሚለው የግእዝ ግስ የወጣ ሆኖ ”ግዛት” ማለት ነው። መለኮት (ወይም ማለኹት) በዕብራይስጥ ቋንቋ መንግሥት ማለት ነው፡፡ በግዕዝ ግን ባሕርይ፣ አገዛዝ፣ ሥልጣን ማለት ነው፡፡ እንግዲህ አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ በመለኮት ይህም ማለት በግዛት በመንግስት አንድ ናቸው። አብ አልተፈጠረም፣ ወልድም አልተፈጠረም፣ መንፈስ ቅዱስም አልተፈጠረም፡፡ ሦስቱም አካላት ከዚህ ጀምሮ ነበሩ የማይባልላቸው ዘላለማዊ ናቸው፡፡ አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ የሚለው የተለያዩ ክፍሎች ስም አይደለም የአንድ አምላክ ስም እንጂ፡፡ ሦስቱ አካላት በህልውና ተገናዝበው ይኖራሉ እንጂ አይከፋፈሉም አይነጣጠሉም፡፡ እያንዳንዳቸው አካላት በመለኮታዊ ባህርይ አንድ ናቸው፡፡ ሐዋርያው ይህንን ሲያስረዳ ‹‹ከአንዱም በቀር ማንም አምላክ እንደሌለ እናውቃለን›› በማለት ገልጾታል (1ኛ ቆሮ 84)። በአጠቃላይ ሥላሴ አንድ ሲሆኑ ሦስት፣ ሦስት ሲሆኑ አንድ ናቸው፡፡ አንድነቱ ሦስትነቱን ሳይጠቀልለው፣ ሦስትነቱ አንድነቱን ሳይከፋፍለው በሕልውና ተገናዝበው የሚኖሩ ናቸው፡፡ ሥላሴ በአካላት ሦስት ሲሆኑ በባሕርይ በመለኮት አንድ ናቸው፡፡ አንድ እግዚአብሔር፤ አንድ አምላክ ናቸው፡፡ ይህን ሲያስረዱ መጻሕፍት እንዲህ ይላሉ፤ እስራኤል ሆይ ስማ እግዚአብሔር አምላካችን አንድ እግዚአብሔር ነው፡፡ ዘጸ.6÷4 እግዚአብሔር አንድ ነው፡፡ ኤፌ. 4÷5 ሦስት ስም አንድ እግዚአብሔር ነው፡፡

ሥላሴ በሕልውና አንድ ናቸው፡፡ ሕልውና ማለት “ነዋሪነት፥ ኑሮ፥ አነዋወር” ማለት ነው። በነገረ መለኮት ቋንቋ አፈታት ግን አብ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ኅልው ሆኖ፣ ወልድም በአብና በመንፈስ ቅዱስ ኅልው ሆኖ፣ መንፈስ ቅዱስም በአብና በወልድ ኀልው ሆኖ በመኖር አንድ ናቸው ማለት ነው። በሌላ አባባልም ህልውና ሦስትነታቸውን ሳይጠቀልለው፣ ሦስትነትም አንድነታቸውን ህልውናውን ሳይከፍለው አንዱ ከአንዱ ጋራ ተገናዝቦ ባንድነት መኖር ነው። ይህም በኲነት የበለጠ ይብራራል፡፡ የኩነት /የሁኔታ/ ሦስትነታቸውን በተመለከተም በህልውና /በአኗኗር/ እያገናዘቡ በአንድ መለኮት የነበሩ፣ ያሉ፣ የሚኖሩ ናቸው፡፡

የሦስትነት ምስጢር -ሦስት አካላት

ሥላሴ በግብር ሦስት ናቸው፡፡ የአብ ግብሩ መውለድ፣ ማስረጽ ሲሆን የወልድ ግብሩ መወለድ፣ የመንፈስ ቅዱስ ግብሩ መስረጽ ነው፡፡ አብ ወላዲ፣ ወልድ ተወላዲ፣ መንፈስ ቅዱስ ሠራፂ /የወጣ፣ የተገኘ/ ነው፡፡ አብ አባት ነው፣ ወልድ ልጅ ነው፣ መንፈስ ቅዱስ ከአብ ብቻ የሠረፀ ነው፡፡ /ዮሐ.14-26/፡፡ ሦስቱ አካላት አንድ መለኮት ናቸው፡፡ ሠለስቱ ስም አሐዱ እግዚአብሔር እንዳለ /አባ ሕርያቆስ በቅዳሴው/፡፡ አብ ወልድን የወለደ መንፈስ ቅዱስን የሚያሰርጽ (አስገኛቸው) ነው፡፡ እንዲህ ቢሆንም ግን አይቀድማቸውም፤ አይበልጣቸውምም፡፡ መጀመሪያና መጨረሻ የሌለው መጀመሪያውና መጨረሻው እርሱ የሆነ ዘላለማዊ ነው፡፡ አብ ይወልዳል እንጂ አይወለድም፣ ያሰርጻል እንጂ አይሰርጽም፡፡ አብም ‹‹ከእኛ በላይ ያለው አምላክ›› ተብሎ ይታወቃል፡፡ ወልድ የእግዚአብሔር (የአብ) ልጅ፣ ቃል ተብሎ ይጠራል፡፡ ሊቃውንትም ‹‹የአብ ክንዱ/እጁ›› ይሉታል፡፡ ቅድመ ዓለም ከአብ የተወለደ ነው፡፡ ተወለደ ሲባልም አብ ቀድሞት የነበረበት ጊዜ አለ ማለት አይደለም፡፡ ከእኛ ጋር ያለው አምላክ ይባላል፡፡ መወለዱም እንደሰው መወለድ ሳይሆን ‹‹ከብርሃን የተገኘ ብርሃን›› ነው፡፡ መንፈስ ቅዱስም አምላክ ጌታ ነው፡፡ ሕይወትን የሚሰጥ አምላክ ነው፡፡ ከአብ የሠረፀ ከአብ ከወልድ ጋራ በአንድነት የምንሰግድለትና የምናመሰግነው አምላክ ነው፡፡ እርሱም በነቢያት አድሮ የተናገረ ነው። መንፈስ ቅዱስ እስትንፋስ ይባላል፡፡ ሊቃውንት አባቶችም ‹‹የአብ ምክሩ›› ብለውታል፡፡ መንፈስ ቅዱስ የሚሰርጸውም ከአብ ብቻ ነው፡፡ የሚሰርጸውም ከዚህ ጊዜ ጀምሮ ነው አይባልለትም፡፡ ከአብ ቢሰርጽም አብ ከእርሱ ቀድሞ የነበረበት ጊዜ የለም፡፡ መንፈስ ቅዱስ ‹‹በውስጣችን ያለው አምላክ›› ይባላል፡፡

የአካል ሦስትነታቸውም ለአብ ፍጹም አካል፣ ፍጹም መልክ፣ ፍጹም ገጽ አለው፤ ለወልድም ፍጹም አካል፣ ፍጹም መልክ፣ ፍጹም ገጽ አለው፤ ለመንፈስ ቅዱስም ፍጹም አካል፣ ፍጹም መልክ፣ ፍጹም ገጽ አለው፡፡ነገር ግን አይከፋፈሉም፣ አይነጣጠሉም፣ ፍጹም አንድ ናቸው፡፡ አካል የተባለውም ምሉእ ቁመና ነው፤ ገጽ ከአንገት በላይ ያለው ፊት ነው፤ መልክዕ ልዩ ልዩ ሕዋሳት ዓይን ጆሮ፣ እጅ፣ እግር ከዚህም የቀሩት ሕዋሳት ሁሉ ናቸው፡፡ እንዲህ ሲባል ግን የሥላሴ አካል አንደ ሰው አካል ውሱን፣ ግዙፍ፣ ጠባብ አይደለም፡፡ ምሉዕ፣ ስፉሕ፣ ረቂቅ ነው እንጂ፡፡ ምሉዕነታቸውና ስፋታቸው እንዴት ነው? ቢሉ ከአርያም በላይ ቁመቱ፣ ከበርባኖስ በታች መሠረቱ፣ ከአድማስ እስከ አድማስ ስፋቱ ተብሎ አይነገርም፣ አይመረመርም፡፡ ምክንያቱም ሥላሴ ዓለሙን ይወስኑታል እንጂ ዓለሙ ሥላሴን አይወስናቸውምና፡፡

በኩነትም የአብ ከዊንነቱ ልብነት ነው፤ የወልድ የመንፈስ ቅዱስ ልባቸው እርሱ ነው፤ የወልድ ከዊንነቱ ቃልነት ነው፤ ለአብ ለመንፈስ ቅዱስ ቃላቸው እርሱ ነው፤ የመንፈስ ቅዱስ ከዊንነቱ ሕይወትነት ነው፡፡ የአብ የወልድ ሕይወታቸው እርሱ ነው፡፡ ይህም በአብ መሠረትነት ለራሱ ለባዊ /አዋቂ/ ሆኖ ለወልድ፣ ለመንፈስ ቅዱስ ልብ፣ ዕውቀት መሆን ነው፡፡ ወልድ በአብ መሠረትነት ለራሱ ነባቢ /ቃል/ ሆኖ ለአብ፣ ለመንፈስ ቅዱስ ቃል መሆን ነው፡፡ መንፈስ ቅዱስም በአብ መሠረትነት ለራሱ ሕያው ሆኖ ለአብ፣ ለወልድ ሕይወት መሆን ነው፡፡ ስለዚህ በአብ ልብነት ወልድ፣ መንፈስ ቅዱስ ህልዋን ናቸው ያስቡበታል፤ በወልድ ቃልነት አብ፣ መንፈስ ቅዱስ ህልዋን ናቸው ይናገሩበታል፤ በመንፈስ ቅዱስ እስትንፋስነት አብ፣ ወልድ ህልዋን ናቸው ሕያዋን ሆነው ይኖሩበታል፡፡

ሥላሴ (3ቱ አካላት) በአንድ ልብ በአብ ያውቃሉ፣ በአንድ ቃል በወልድ ይናገራሉ፣ በአንድ ሕይወት በመንፈስ ቅዱስ ሕያዋን ሁነው ይኖራሉ፡፡ ጌታችን ይህን ምስጢር “እኔ በአብ እንዳለሁ አብም በእኔ እንዳለ”፤ ሲል ለሐዋርያት አስተምሯል (ዮሐ. 1411)፡፡ ወንጌላዊ ቅዱስ ዮሐንስ ቃልም በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረ፤ እግዚአብሔርም ቃል ነበረ፤ ይህ አስቀድሞ በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረ ሲል ገልጾልናል (ዮሐ. 11-2)፡፡ቅዱስ ዮሐንስ በወንጌሉ ቃል በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረ በማለቱ ወልድ በቃልነቱ በአብ ህልውና መኖሩን ያስረዳል፡፡ ይህ አስቀድሞ በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረ በማለቱ በመንፈስ ቅዱስ ህልው ሆኖ መኖሩን ያስረዳል፡፡ ዮሐንስ ከሦስቱ አካላት አንዱ ወልድ ቃልን በቃልነት በአብና በመንፈስ ቅዱስ አለ በማለቱ ሁለቱን አብ በልብነት በወልድ በመንፈስ ቅዱስ እንዳለ፤ መንፈስ ቅዱስ በሕይወትነት በአብና በወልድ እንዳለ ይታወቃል፡፡ እግዚአብሔር በሦስትነቱ የሚታወቅባቸው ስሞች ደግሞ አብ፣ ወልድ፣ መንፈስ ቅዱስ ናቸው፡፡ እግዚአብሔር በግብር ሦስትነቱ የሚታወቀው አብ ወላዲ፣ አሥራፂ በመባል፣ ወልድ ተወላዲ በመባል፣ መንፈስ ቅዱስ ሠራፂ በመባል ነው፡፡

የእግዚአብሔርን አንድነት የምናምነው በፈጣሪነት፣ በአምላክነት፣ በአገዛዝ፣ በፈቃድ፣ በሥልጣን እነዚህን በመሳሰሉት የመለኮት ባሕርያት ነው፡ ሦስትነቱን የምናምነው ደግሞ በስም፣ በግብር /በኩነት/ በአካል ነው፡፡ «እንዘ አሐዱ ሠለስቱ ወእንዘ ሠለስቱ አሐዱ፣ ይሤለሱ በአካላት ወይትዋሐዱ በመለኮት» እንዳለ /ቅዱስ ባስልዮስ ዘቂሣርያ/፡፡ ታላቁ ሐዋርያ ብርሃነ ዓለም ቅዱስ ጳውሎስ በሮሜ 10-17 ላይ «እምነት ከመስማት ነው፣ መስማትም ከእግዚአብሔር ቃል ነው» ብሎ እንደተናገረው ከላይ የተጠቀሱትን መጠነኛ ማስረጃዎች በሙሉ ለመገንዘብ እንዲቻል የእግዚአብሔር እስትንፋስ የሆኑትን የቅዱሳት መጻሕፍት ማስረጃዎችን መመልከት ያስፈልጋል፡፡ ሥላሴ የሚለው ስም እንዲያው የመጣ አይደለም፡፡ እግዚአብሔር በአንድነቱና በሦስትነቱ የሚጠራበት የከበረና ከስም ሁሉ በላይ የሆነ ስም ነው፡፡ ለዚህም የመጽሐፍ ቅዱስ /ዐሥራው ቅዱሳት መጻሕፍት/ ማስረጃዎችን በዝርዝር እንመለከታለን፡፡

ምስጢረ ሥላሴ በብሉይ ኪዳን

እግዚአብሔር ሰውን ሲፈጥር፡ እግዚአብሔርም አለ፡– «ሰውን በመልካችን እንደምሳሌአችን እንፍጠር» ዘፍ.1-26 እዚህ ላይ «እግዚአብሔርም አለ» ሲል አንድነቱ፣ «እንፍጠር» ሲል ከአንድ በላይ መሆኑን ግሱ /ቃሉ/ ያመለክታል፡፡ በዚህ ንባብ እግዚአብሔር የሚለው ሥመ አምላክ ከአንድ በላይ የሆኑ አካላትን የሚመለከት መሆኑን ከተረዳን ስለ ሥላሴ ኃልወት በሌሎች የቅዱሳት መጻሕፍት ከተጻፉት ምንባባት ጋር በማገናዘብ ይህ ጥቅስ ፍጹም አንድነቱንና ልዩ ሦስትነቱን እንደሚመሰክር በግልጽ መረዳት ይቻላል፡፡ በዚህ አንቀጽ እንፍጠር በመልካችን እንደምሳሌያችን የሚለው ንግግር የሦስት ተነጋጋሪዎች ነው እንጂ ያንድ ተናጋሪ ቃል አይደለም፡፡ ስለዚህ እግዚአብሔር፤ ሰውን እንፍጠር በመልካችን እንደምሳሌያችን፤ ሲል ሦስትነቱን ማስተማሩ ነው፡፡ ሙሴም ይህን የእግዚአብሔርን ነገር ሲጽፍልን ሰውን እንፍጠር በመልካችን እንደ ምሳሌያችን ያለውን የብዙውን አነጋገር ለአንድ ሰጥቶ፤ እግዚአብሔር አለ፤ ብሎ መጻፉ በአካል ሦስት ሲሆን በባሕርይ በህልውና አንድ ስለሆነ በአንድ ቃል መናገሩን ከእግዚአብሔር ተረድቶ ለእኛ ሲያስረዳን ነው፡፡

እግዚአብሔርም ለሰው ልጅ ቃል ኪዳን ሲሰጥ፡ እግዚአብሔር አምላክ አለ፡– «እነሆ አዳም መልካሙንና ክፉውን ለማወቅ ከእኛ እንደ አንዱ ሆነ» ዘፍ.3-22 በማለት ባለቤቱን አንቀጽን አንድ፣ አሳቡን ዝርዝሩን የብዙ አድርጐ ይናገራል፡፡ «እግዚአብሔር አለ» ሲል አንድነቱን፣ «ከእኛ እንደ አንዱ ሆነ» ሲል ደግሞ ከአንድ በላይ መሆኑን ያመለክታል፡፡ እግዚአብሔር ከእኛ እንደ አንዱ ሆነ በማለቱ ሦስትነቱን ያስረዳል፡፡ ምንአልባትም እግዚአብሔር አለ፤ አዳም ከእኛ እንደ አንዱ ሆነ፤ የሚለው ቃል ሦስት ተነጋጋሪዎች በአንድ ቦታ ቢኖሩ አንዱ ሁለቱን ከእኛ እንደ አንዱ ሆነ ብሎ ሲነገር ከአንድ የበዙ ተናጋሪዎች ቃል መሆኑን ነው የሦስትነት ተነጋጋሪዎች መሆኑን ስለሚያስረዳ እግዚአብሔር ሦስት አካል መሆኑ በዚህ አነጋገር ግልጽ ነው፡፡

በባቢሎን ግንብ ወቅት፡ እግዚአብሔርም አለ፡– «ኑ እንውረድ አንዱ የአንዱን ነገር እንዳይሰማው ቋንቋቸውን በዚያ እንደባልቀው፡፡» ዘፍ.11.6-8፡፡ «እግዚአብሔር አለ» ብሎ አንድነቱን፣ «ኑ እንውረድ» ብሎ ደግሞ ከአንድ በላይ መሆኑን ያመለክታል፡፡በዚህ አንቀጽ እግዚአብሔር ኑ እንውረድ ብሎ በመናገሩ ከሁለትነት የተለየ ሦስትነቱን ያስረዳል፡፡ መረጃውም ሦስት ተነጋጋሪዎች በአንድ ቦታ ሁነው ሲነጋገሩ ሦስተኛው ሁለቱን ኑ እንውረድ ሊላቸው ይችላል፤ ምክንያቱም ሁለት ሆነው ግን አንዱ ሁለተኛውን ና እንውረድ ቢለው እንጂ ኑ እንውረድ ሊለው ስለማይችል ነው፡፡ ከዚህ በላይ የተጠቀሱት የእግዚአብሔር ቃላት ተገልጸው ሲተረጐሙ፤ አካላዊ ልባቸው አብ አካላዊ ቃሉ ወልድንና አካላዊ ሕይወቱ (እስትንፋሱ) መንፈስ ቅዱስን፤ ሰውን እንፍጠር በመልካችን እንደ ምሳሌያችን፤ እነሆ አዳም ከእኛ እንደ አንዱ ሆነ፤ እንዲሁም ኑ እንውረድ፤ ብሎ እንዳነጋገራቸው ይታወቃል፡፡

ለአብርሃም በተገለጠለት ጊዜ፡ የአንድነቱና የሦስትነቱ ማስረጃ ሁነው የታመኑ እነዚህ ሦስቱ ቃላት ከአንድ የበዙ የሁለት ተነጋጋሪዎች፤ ከሁለትም የበዙ ተነጋጋሪዎች ቃላት መሆናቸው ይታወቃል እንጂ ከሦስት ያልበለጡ የሦስት ብቻ ተነጋጋሪዎች ቃላት እንደ ሆኑ ቃላቶቹ በማያሻማ ሁኔታ ስለማያስረዱ፤ እግዚአብሔር በእነዚህ አነጋገሮች ከሦስት ያልበዛ ሦስት አካላት ብቻ መሆኑ አይታወቅም የሚል አሳብም ቢነሳ፤ መጽሐፍ ቅዱስ ከዚህም በሌላ አንቀጽ ይመልሳል፡፡ «በቀትርም ጊዜ እግዚአብሔር ለአብርሃም ተገለጠለት አብርሃም ሦስት ሰዎችን በፊቱ ቆመው አየ» ዘፍ.18.1-15 በማለት እግዚአብሔር አንድ መሆኑንና ሦስት አካል ያለው መሆኑን ወስኖ ያስረዳናል፡፡

የነቢያት ምስክርነት፡ እግዚአብሔር ለሙሴ በተገለጠለት ጊዜ «እኔ የአብርሃም አምላክ፣ የይስሐቅም አምላክ፣ የያዕቆብም አምላክ እግዚአብሔር ነኝ» ዘጸ.3-6 ሲል «አምላክ፣ አምላክ፣ አምላክ» ብሎ ሦስትነቱን፣ «እኔ እግዚአብሔር ነኝ» ብሎ ደግሞ አንድነቱን ገልጾ ተናግሯል፡፡ ነቢየ እግዚአብሔር ክቡር ዳዊትም «የእግዚአብሔር ቸርነት ምድርን ሞላች፣ በእግዚአብሔርም ቃል ሰማዮች ጸኑ፣ ሠራዊታቸውም ሁሉ በአፉ እስትንፋስ» በማለት የሥላሴን ምስጢር ተናግሯል (መዝ.32-6)፡፡ ነቢዩ ኢሳይያስም «ንጉሡ ዖዝያን በሞተበት ዓመት እግዚአብሔርን በልዑል ዙፋኑ ላይ ተቀምጦ አየሁት… ሱራፌልም ቅዱስ፣ ቅዱስ፣ ቅዱስ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ምድር ሁሉ ከክብሩ ተሞልታለች እያሉ ይጨሁ ነበር፡፡» ኢሳ.6.1-8 በማለት ቅዱስ፣ ቅዱስ፣ ቅዱስ ብሎ ሦስትነቱን፣ የሠራዊት ጌታ እግዚአበሔር ብሎ ደግሞ አንድነቱን አይቶ መስክሯል፡፡ እንዲሁም “የጌታንም ድምፅ ‘ማንን እልካለሁ? ማንስ ወደዚያ ሕዝብ ይሄድልናል’ ሲል ሰማሁ” (ኢሳ. 6፡8) በማለት ፍጹም አንድነቱንና ልዩ ሦስትነቱን አመልክቷል፡፡ የእግዚአብሔር ቀራቢዎች አገልጋዮች ሱራፌል በምስጋናቸው ሦስት ጊዜ ብቻ ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ ማለታቸው የሦስትነቱን አካላት መጥራታቸው ነው፤ እግዚአብሔር የሠራዊት ጌታ በማለት በአንድ ስም ጠርተው ምድር ሁሉ ምስጋናህን መልታለች በማለት ያንድ ተመስጋኝ ምስጋናን መስጠታቸው ሦስቱ አካላት አንድ ሕያው እግዚአብሔር፤ አንድ ገዥ፤አንድ አምላክ፤ አንድ ተመስጋኝ አምላክ መሆኑን መመስከራቸው ነው፡፡ ሱራፌልም በዚህ ምስጋናቸው እግዚአብሔር በአካል ከሦስትነት ያልበዛ ሦስት ብቻ እንደ ሆነ በባሕርይ በህልውና ከአንድነት ያልበዛ ሦስት አካል አንድ አምላክ ብቻ መሆኑን ይመሰክሩልናል፡፡

ምስጢረ ሥላሴ በሐዲስ ኪዳን

በሐዲስ ኪዳንም የእግዚአብሔር አንድነትና ሦስትነት /ምስጢረ ሥላሴ/ በምስጢረ ሥጋዌ (በጌታችን በተዋህዶ ሰው መሆን) በሚገባ ታውቋል፡፡

በብስራት ጊዜ፡ መልአኩ ቅዱስ ገብርኤልም እመቤታችንን ባበሠራት ጊዜ «መንፈስ ቅዱስ በአንች ላይ ይመጣለ፣ የልዑልም ኃይል ይጸልልሻል ስለዚህ ደግሞ ከአንች የሚለደው ቅዱሱ የእግዚአብሔር ልጅ ይባላል፡፡» ብሎ የሥላሴን ሦስትነት በግልጽ ተናግሯል፡፡ሉቃ.1-35፡፡

በጥምቀት ጊዜ፡ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በተለየ አካሉ /ሰው ሆኖ/ በዮርዳኖስ ሲጠመቅ፣ አብ በደመና ሆኖ «የምወደው ልጄ ይህ ነው የሚላችሁን ስሙት» ሲል፣ መንፈስ ቅዱስ ደግሞ በራሱ ላይ በርግብ አምሳል ሲወድቅበት ታይቶአል፡፡ /ማቴ.3.16-17፣ ማር.1.9-11፣ ሉቃ.3.21-22፣ ሉቃ.1.32-34/ በዚህም እግዚአብሔር በአካል ሦስት እንደሆነ ተገልጿል፡፡

በደብረ ታቦር፡ ጌታችን ብርሃነ መለኮቱን በገለፀበት በደብረ ታቦር ተራራም ምስጢረ ሥላሴ ተገልጿል፡፡ ወልድ በተለየ አካሉ ሥጋን ተዋህዶ በደብረ ታቦር ተገኝቶ፣ አብ በሰማያት ሆኖ “በእርሱ ደስ የሚለኝ ልጄ እርሱ ነው፤ እርሱን ስሙት” የሚል ቃል ተናግሮ፣ መንፈስ ቅዱስ ደግሞ በደመና ጋርዷቸው ተለግጠዋል፡፡ (ማቴ 171-10)

ሐዋርያዊ ተልዕኮ ሲሠጥ፡ እራሱ ባለቤቱ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም የማዳን ሥራውን ፈጽሞ ከማረጉ በፊት ለደቀመዛሙርቱ ቋሚ ትዕዛዝ ሲሰጥ «እንግዲህ ሂዱና አሕዛብን ሁሉ በአብ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችኋቸው ደቀመዛሙርት አድርጓቸው» ብሏል ማቴ.28.19-20፡፡ በዚህም ‹‹ስም›› ብሎ አንድነታቸውን ‹‹አብ ወልድና መንፈስ ቅዱስ›› ብሎ ሦስትነታቸውን ገልጿል፡፡ ስለመንፈስ ቅዱስም ሲናገር «ዳሩ ግን እኔ ከአብ ዘንድ የምልክላችሁ አጽናኝ እርሱም ከአብ የሚወጣ የእውነት መንፈስ በመጣ ጊዜ እርሱ ስለ እኔ ይመሰክራል፡፡» በማለት አንድነትና ሦስትነቱን በግልፅ ተናግሯል (ዮሐ.15.2614.16-1725-26)፡፡

በሐዋርያት አንደበት፡ ብርሃነ ዓለም ቅዱስ ጳውሎስ ለቆሮንቶስ ክርስቲያኖች በጻፈው መልእክቱ የሥላሴን ሦስትነት ገልጾ «የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ፣ የእግዚአብሔርም ፍቅር፣ የመንፈስ ቅዱስም ኅብረት ከሁላችሁ ጋር ይሁን» (2ኛ ቆሮ.13-14) በማለት ተናግሮአል፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ ዮሐንስ በጻፈው መልእክቱ በማያሻማ ሁኔታ «በሰማይ የሚመሰክሩ ሦስት ናቸው፡፡ እነርሱም አብ፣ ልጁም፣ መንፈስ ቅዱስም ናቸው፡፡ 1.ዮሐ.5-7፡፡ እነዚህ ሦስቱም አንድ ናቸው፡፡» በማለት የሥላሴን አንድነትና ሦስትነት በግልጽ ያስረዳናል፡፡ ወንጌላዊው ቅድስ ዮሐንስም «በራእዩ እነሆም በጉ በጽዮን ተራራ ቆሞ ነበር፣ ከእርሱም ጋር ስሙና የአባቱም ስም የመንፈስ ቅዱስም ስም በግምባራቸው የተጻፈላቸው መቶ አርባ አራት ሺህ ነበሩ» ራእ.14-1፡፡ በማለት በገጸልቡናቸው ስመ ወላዲ፣ ስመ ተወላዲና ስመ ሠራፂ የተጻፈባቸውን የሥላሴን ልጆች አይቷል፡፡ በዚህም የሥላሴን ልዩ ሦስትነት በግልጽ መስክሯል፡፡ ከላይ በዝርዝር የተገለጹትና እነዚህን የመሳሰሉት ሁሉ እግዚአብሔር አንድነቱንና ሦስትነቱን የገለጸባቸው ምስክሮች ናቸው፡፡

የምስጢረ ሥላሴ አስረጂ ምሳሌዎች

ምስጢረ ሥላሴ በሊቃውንትም ትምህርት የአብ ወላዲነት፣ የወልድ ተወላዲነትና የመንፈስ ቅዱስ ሠራፂነት ነው፡፡ አብ ተወላዲ አይባልም፣ ወልድ ወላዲ አይባልም፡፡ ወላዲ፣ ተወላዲ፣ ሠራፂ የሚባሉት ቃላት ሦስት አካላት ለየብቻ የሚታወቁባቸው የግብር ስሞች ናቸው፡፡ ሊቃውንት አባቶቻችን በሃይማኖተ አበው ምሳሌ ሲመስሉ ምሳሌ ዘይሐጽጽ /ጎደሎ ምሳሌ/ በማለት አንዳንድ ምሳሌዎችን ያቀርባሉ፡፡ ምሳሌውንም ጎደሎ የሚሉበት ምክንያት ለምስጢረ ሥላሴ ሙሉ በሙሉ ምሳሌ የሚሆን ሲያጡ ነው፡፡ ይሁንና ምሳሌ ከሚመሰልለት ነገር እንደሚያንስ ቢታወቅም ለማስተማር ግን ይጠቅማልና ቤተክርስቲያን ነገረ ሃይማኖትን በምሳሌ ታስረዳለች፡፡ ይህንንም የሥላሴን ሦስትነትና አንድነት ሐዋርያት ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ በተማሩት መሠረት በሚከተሉት ሦስት ምስሌዎች በሚገባ ገልጸውታል፡፡

የሥላሴ አንድነትና ሦስትነት በሰው ምሳሌ ይገለጻል፡፡ ሰው በነፍሱ ሦስትነት አለው፡፡ የኸውም ልብነት፣ ቃልነት፣ ሕይወትነት ነው፡፡ ስለዚህ በሰው ነፍስ በልብነቷ አብ፣ በቃልነቷ ወልድ፣ በሕይወትነቷ መንፈስ ቅዱስ ይመስላሉ፡፡ የነፍስ ልብነቷ፣ ቃልነቷን፣ ሕይወትነቷን ከራሷ ታስገኛለችና፡፡ ቃልና ሕይወት ከአንዷ ልብ ስለተገኙ በከዊን /በመሆን/ ልዩ እንደሆኑ በመናገርም ይለያሉ፡፡ እንዲሁም አብ ወልድን በቃል አምሳል ወለደው፣ መንፈስ ቅዱስንም በእስትንፋስ አንጻር አሰረጸው፡፡ ነፋስ ስትገኝ በሦስትነቷ በአንድ ጊዜ ተገኘች አንዷ ልብነቷ ቀድሞ ቃልነቷና እስትንፋስነቷ በኋላ አልተገኙም፡፡ ሰው በዚህ አኳኋን በነፍሱ የሚመስለው ስለሆነ እግዚአብሔር «ሰውን በመልካችን እንደ ምሳሌአችን እንፍጠር» ዘፍ.1-26 ብሎ ተናገረ፡፡ ስለዚህ ነፍስ ልብ፣ ቃል፣ እስትንፋስ /ሕይወት/ መሆን የከዊን /የመሆን/ ሦስትነትን ነገር በተናገረበት ድርሳን እንዲህ አለ፡፡ «አምላክ ውእቱ አብ፣ ወአምላክ ውእቱ ወልድ፣ ወአምላክ ውእቱ መንፈስ ቅዱስ ወኢትበሀሉ ሠለስተ አማልእክተ አላ አሐዱ አምላክ ብሏል፡፡ ይህም ማለት አብ አምላክ ነው፣ ወልድም አምላክ ነው፣ መንፈስ ቅዱስም አምላክ ነው ነገር ግን ሦስት አማልክት አይባሉም፣ አንድ አምላክ እንጂ፡፡» ማለት ነው፡፡

የሥላሴ አንድነትና ሦስትነት በፀሐይ ይመሰላል፡፡ ፀሐይ አንድ ሲሆን ሦስትነት አለው፡፡ ይኼውም ክበቡ ብርሃኑ፣ ሙቀቱ ነው፡፡ በክበቡ አብ፣ በብርሃኑ ወልድ፣ በሙቀቱ መንፈስ ቅዱስ ይመሰላሉ፡፡ «አብ ፀሐይ፣ ወልድ ፀሐይ፣ መንፈስ ቅዱስ ፀሐይ አሐዱ ውእቱ ፀሐየ ጽድቅ ዘላዕለ ኩሉ» እንዳለ /ቅዱስ አባ ሕርያቆስ/፡፡ እነዚህ ሦስቱ በአንድ ላይ መኖራቸው አንድ ፀሐይ እንጂ ሦስት ፀሐዮች አያስብላትም፡፡ ከፀሐይ ክበብ ብርሃኗና ሙቀቷ ያለመቀዳደም እንደሚገኝ እንዲሁ ከአብ ወልድ ተወለደ፣ መንፈስ ቅዱስም ሰረጸ፤ ይህም ያለመቀዳደም ያለመበላለጥ ነው፡፡ ከፀሐይ ሦስት ኩነታት ብርሃኗ ብቻ ከዓይናችን ጋር እንደሚዋሀድ ከሥላሴም ብርሃን ዘበአማን (እውነተኛ ብርሃን) የተባለ ወልድ ኢየሱስ ክርስቶስ ብቻ በተለየ አካሉ የሰውን ባህርይ ተዋህዷል፡፡

የሥላሴ አንድነትና ሦስትነት በእሳት ይመሰላል፡፡ እሳት አንድ ሲሆን ሦስትነት አለው፡፡ ይኼውም አካሉ፣ ብርሃኑ፣ ዋዕዩ /ሙቀቱ/ ነው፡፡ በአካሉ አብ፣ በብርሃኑ ወልድ፣ በዋዕዩ መንፈስ ቅዱስ ይመሰላሉ፡፡ «አብ እሳት ወልድ እሳት ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ ውእቱ እሳተ ሕይወት ዘእምአርያም፡፡» እንዳለ /አባ ሕርያቆስ/ «አምላክህ እግዚአብሔር የሚባላ እሳት ቀናተኛም አምላክ ነው፡፡» ዘዳ. 4-24፡፡ሥላሴ በፀሐይና በእሳት መመሰላቸውንም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ራሱ ለሐዋርያት «እኔና አባቴ መንፈስ ቅዱስም እሳትና ነበልባል ፍሕምም ነን» በማለት አስተምሮአቸዋል፡፡ ሐዋርያትም ይህንን ጽፈውት ቀሌመንጦስ በተባለው መጽሐፍ ይገኛል፡፡ /ቅዳሴ ሠለስቱ ምእትን/ ይመልከቱ፡፡

የሥላሴ አንድነትና ሦስትነት በባህር ከዊን ይመሰላል፡፡ ባህር አንድ ባህር ሲሆን ሦስት ከዊን አለው፡፡ ይህም ስፍሐት (Sphere)፣ ርጥበት (Moisture) እና እንቅስቃሴ (Tide) ነው፡፡ በስፍሐቱ አብ፣ በርጥበቱ ወልድ፣ በእንቅስቃሴው መንፈስ ቅዱስ ይመሰላሉ፡፡ ሰው ከባህር ገብቶ ዋኝቶ ሲወጣ በአካሉ ላይ ርጥበት ይገኛል እንጂ ስፍሐትና እንቅስቀሴ አይገኝም፡፡ ወልድም በቃልነቱ ከዊን ከአብና ከመንፈስ ቅዱስ ሳይለይ በተለየ አካሉ ሰው በሆነ ጊዜ በመለኮት አንድ ስለሆነ አብና መንፈስ ቅዱስ ሥጋ ለበሱ አያሰኝም፡፡ ሊቃውንትም ‹‹የሁሉ መገኛ አብን ነፋስ በሚያማታት ባህር ባለች ውኃ እንደመሰሉት እወቅ፡፡ በሁሉ ዘንድ የሚመሰገን ወልድንም በውኃ ርጥበት እንደመሰሉት በሁሉ ዘንድ የሚመሰገን መንፈስ ቅዱስንም በውኃ ባለ ባህር እንቅስቃሴ ይመሰላል›› በማለት አስረድተዋል፡፡

ነገር ግን እነዚህ ሁሉ አንድ ነፍስ፣ አንድ ፀሐይ፣ አንድ እሳት፣ አንድ ባህር እንጂ ሦስት ነፍስ፣ ሦስት እሳት፣ ሦስት ፀሐይ፣ ሦሰት ባህር አይባሉም፡፡ ሥላሴም በአካል፣ በስም፣ በግብር ሦስት ቢባሉ በባሕርይ፣ በሕልውና፣ በፈቃድ፣ በመለኮት አንድ ናቸው አንጂ አማልክት አይባሉም፡፡ የቂሣርያው ሊቀ ጳጳስ ቅዱስ ባስልዮስ «እንዘ አሐዱ ሠለስቱ ወእንዘ ሠለስቱ አሐዱ ይሤለሱ በአካላት ወይትዋሐዱ በመለኮት» እንዳለ፡፡ ይህም ማለት አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ አንድ ሲሆኑ ሦስት ሦስት ሲሆኑ አንድ ናቸው፡፡ በአካል ሦስት ሲሆኑ በመለኮት አንድ ናቸው፡፡ ማለት ነው፡፡ ይህም ሰው በሚረዳው መጠን ለመግለጽ ያህል ነው እንጂ ከፍጥረት ወገን ለሥላሴ የሚሆን በቂ ምሳሌ የለም፡፡ የተመሰለ ቢመስል ሕጹጽ /ጎደሎ/ ምሳሌ ነው፡፡

😈 ምስጢረ ሥላሴ ላይ የሚነሱ የስህተት ትምህርቶች

መለዋወጥ (Modalism): ይህ ስህተት የሰባልዮሳውያን ነው፡፡ ስህተቱም አንድ እግዚአብሔር አለ በማለት የአካል ሦስትነትን አይቀበልም፡፡ በዚያ ፈንታ አንዱ እግዚአብሔር ራሱን በተለያየ መንገድ ይገልጻል በማለት ይናገራል፡፡ አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ የሚባሉት አካላት ሳይሆኑ ራሱን የገለጠባቸው መንገዶች ናቸው ይላል፡፡ ስለዚህም እግዚአብሔር አንድ ጊዜ አብ፣ ሌላ ጊዜ ወልድ፣ ሌላ ጊዜ ደግሞ መንፈስ ቅዱስ ሆኖ ተገለጠ በማለት የሥላሴን ምስጢር አዛብቶ ያቀርባል፡፡ ምሳሌም ሲሰጥ ይህም ውኃ ፈሳሽ፣ በረዶ፣ እንፋሎት እንደሚሆነው ነው በማለት ያቀርባል፡፡ ነገር ግን እግዚአብሔር በባህርይው አይለወጥምና (ሚል 3፡6) ይህ የተወገዘ የስህተት ትምህርት ነው፡፡

መነጣጠል (Tri-theism):ይህ ስህተት የሥላሴን አንድነት ካለመረዳት የሚመጣ ነው፡፡ አመለካከቱም አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ሦስት አማልክት ናቸው ይላል፡፡ ልዩ በሆነ መንገድ የተጣመሩ አማልክት ናቸው በማለትም ኅብረት አላቸው ይላል፡፡ ይህ ስህተት ሦስት አካላት የሚለውን በትክክል ባለመረዳት አንዳንዶች ‹‹ክርስቲያኖች ሦስት አማልክት ያመልካሉ›› የሚሉት አይነት ስህተት ነው፡፡ ነገር ግን ሥላሴ የተለያዩ/የተነጣጠሉ/ አይደሉም፡፡ ሊቃውንት አባቶችም ‹‹አንድ አምላክ እንጂ ሦስት አማልክት አንልም›› ብለው በግልጽ መልስ ሰጥተውበታል፡፡

መከፋፈል (Partialism): ይህ ስህተት ደግሞ አብ ወልድና መንፈስ ቅዱስ አንድ ላይ ሲሆኑ አምላክ ይሆናሉ ይላል፡፡ ይህም ማለት እያንዳንዳቸው የአምላክ ክፍል ናቸው እንጂ ሙሉ አምላክ አይደሉም የሚል ትርጉም አለው፡፡ ሦስቱ በአንድ ላይ ሲሆኑ ብቻ ሙሉ አምላክ ይሆናሉ ማለትም እያንዳንዳቸው አካላት አምላክ ሳይሆኑ ‹‹የአምላክ ክፍል›› ናቸው የሚል ፍጹም የክህደት ትምህርት ነው፡፡ እኛ ግን ሥላሴ ግን አይከፋፈሉም እንላለን፡፡ቅዱስ አትናቴዎስ እንደተናገረውም ‹‹“አብ አምላክ ነው፣ ወልድም አምላክ ነው፤ መንፈስ ቅዱስም አምላክ ነው፡፡››

የአርዮስ ክህደት (Arianism): ይህ ደግሞ የወልድን ፍጹም አምላክነት የሚክድ ትምህርት ነው፡፡ ወልድ በአብ በልዕልና የተፈጠረ ነው ይላል፡፡ ፈጥሮ ፈጠረበት ይላል፡፡ አብ ወልድን ስለፈጠረው አብ ይቀድመዋል ይላል፡፡ስለዚህም ወልድ ያልነበረበት ጊዜ ነበር የሚል ክህደት ነው፡፡ ለዚህም ክህደቱ በምሳ 8፡22-25 ቆላ 1፡15 ዮሐ 14፡28 ያሉትን በተሳሳተ መንገድ በመተርጎም ተጠቅሞባቸዋል፡፡ የአርዮስ ክህደትም በኒቅያ ጉባዔ (በ325 ዓ.ም) የተወገዘ ትምህርት ነው፡፡ እኛም እንደ አባቶቻችን ‹‹ቃልም እግዚአብሔር ነበረ›› የሚለውን መሠረት አድርገን ‹‹የተወለደ እንጂ ያልተፈጠረ›› የሚለውን የኒቅያ ጉባዔ ድንጋጌ እንከተላለን፡፡

የመቅዶንዮስ ክህደት (Mecedonianism): የመቅዶንዮስ ክህደት ከአርዮስ ክህደት የቀጠለ ሲሆን የመንፈስ ቅዱስን ፍጹም አምላክነት የካደ ትምህርት ነው፡፡ ክህደቱም መንፈስ ቅዱስ ፍጡር (ሕፁፅ) ነው ይላል፡፡ መንፈስ ቅዱስ ከአብና ከወልድ ያንሳል ይላል፡፡ እኛ ግን በሦስቱ አካላት መበላለጥ የለም ብለን እናምናለን፡፡ የመቅዶንዮስ ትምህርት በቁስጥንጥንያ ጉባዔ (381 ዓ.ም) የተወገዘ ትምህርት ነው፡፡ የቀናችውን ሃይማኖት ያስተማሩ አባቶችም በዚህ ጉባዔ ‹‹በመንፈስ ቅዱስም እናምናለን፤ እርሱ ጌታ ሕይወትን የሚሠጥ ከአብ የሰረፀ ከአብና ከወልድ ጋር እንሰግድለታለን፤ እናመሰግነለዋለን፤ እርሱም በነቢያት አድሮ የተናገረ ነው›› በማለት የመንፈስ ቅዱስን አምላክነት በተረዳ ነገር መስክረዋል፡፡

የሁለት ሥርፀት ትምህርት (Dual procession): ይህ የስህተት ትምህርት ቆይቶ በምዕራባውያኑ ዘንድ የተጨመረ ነው፡፡ እርሱም መንፈስ ቅዱስ ከአብና ከወልድ ይሰርፃል የሚል የስህተት ትምህርት ነው፡፡ የኒቅያ ጉባዔ ድንጋጌ ላይ ከጊዜ በኋላ የተጨመረ ነው፡፡ በጥንታዊያን አብያተ ክርስቲያናት ዘንድ ያልነበረ ምዕራባዊያኑ ያስገቡት ነው፡፡ መሠረታዊ ነገሩም ከምስጢረ ሥላሴ ጋር ይጣረሳል፡፡ ጌታችንም ያስተማረው መንፈስ ቅዱስ ከአብ እንደሚሰርፅ እንጂ ከአብና ከወልድ እንደሚሰርፅ አይደለም፡፡

ስለ ምሥጢረ ሥላሴ ከቀደሙ ሊቃውንት ምስክርነቶች ጥቂቶቹ

እግዚአብሔር አንድ ነው፤ የማትከፈል የማትፋለስ መንግስትም አንዲት ናት፤ ከሥላሴ ምንም ምን ፍጡር ደኃራዊ የለም፤ በእነርሱ ዘንድ አንዱ ለአንዱ መገዛት የለም፡፡ አብ ከወልድ ተለይቶ የኖረበት ዘመን የለም፣ ወልድም ከመንፈስ ቅዱስ ተለይቶ የኖረበት ዘመን የለም፤ መንፈስ ቅዱስም ከአብ ከወልድ ተለይቶ የኖረበት ዘመን የለም፤ ሥሉስ ቅዱስ በዘመኑ በቀኑ ሁሉ በግብርም በስምም ሳይለወጥ ሳይፋለስ ጸንቶ ያለ ነው እንጂ፡፡” (ሃይማኖተ አበው ዘሠለስቱ ምዕት ምዕራፍ 195-6)

ወንድሞቻችን እኛስ እንዲህ እናምናለን፤ ያልተወለደ እግዚአብሔር አብ በተለየ አካሉ አንድ ነው፤ የተወለደ እግዚአብሔር ወልድ ዋሕድ ኢየሱስ ክርስቶስም በተለየ አካሉ አንድ ነው፤ በወደደው የሚያድር የአብ የወልድ እስትንፋስ እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስም በተለየ አካሉ አንድ ነው እንላለን፡፡…አብ አምላክ ነው፤ ወልድም አምላክ ነው፤ መንፈስ ቅዱስም አምላክ ነው፡፡ ግን ሦስት አማልክት አይባሉም አንድ አምላክ እንጂ፡፡” (ሃይማኖተ አበው ዘቅዱስ አትናቴዎስ ሐዋርያዊ ምዕራፍ 252-4)

ከሦስቱ ፍጡር የለም ፍጡራን አይደሉምና፡፡ ከዕውቀት ከሃይማኖት የተለዩ መናፍቃን ከቅድስት ሥላሴ መለኮት መከፈልን በአካላት መጠቅለልን ሊያመጡ አይድፈሩ ሦስት አማልክት ብለን አንሰግድም አንድ አምላክ ብለን እንሰግዳለን እንጂ፡፡ በስም ሦስት ናቸው እንላለን፤ አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ አንድ ባህርይ አንድ ሥልጣን ናቸው፤ በአንድ መለኮት በባህርይ አንድነት የጸኑ ሦስት አካላት ሲሆኑ ከሦስቱ አንዱ የሚበልጥ አንዱ የሚያንስ አይደለም፤ በማይመረመር በአንድ ክብር የተካከሉ ናቸው እንጂ፡፡” (ሃይማኖተ አበው ዘቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘእንዚናዙ ምዕራፍ 606-7)

ወልድ ሳይኖር አብ ከአዝማን በዘመን ፈጽሞ አልነበረም፤ ወልድም ከመንፈስ ቅዱስ ተለይቶ በዘመን አልነበረም፤ ሳይለወጡ ሳይለዋወጡ በገጽ በመልክ ፍጹማን በሚሆኑ በሦስት አካላት ጥንት ሳይኖራቸው በዘመን ሁሉ የነበሩ፤ ፍጻሜ ሳይኖራቸው የሚኖሩ ናቸው እንጂ፡፡” (ሃይማኖተ አበው ዘቅዱስ ቴዎፍሎስ ምዕራፍ 685)

አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ በአካል ሦስት በባህርይ አንድ ነው ብሎ ማመን ይህ ነው፤ የማይመረመር በቅድምና የነበረ አብ በገጹ በአካሉ ፍጹም ነው፤…የማይመረመር በቅድምና ነበረ ወልድም በገጹ በአካሉ ፍጹም ነው፤….የማይመረመር በቅድምና የነበረ መንፈስ ቅዱስም በገጹ በአካሉ ፍጹም ነው፤ ሐዋርያት ያስተማሩዋት ቅድስት ቤተክርስቲያን የተቀበለቻቸው ቅዱሳት መጻሕፍት እንደተናገሩ፡፡” (ሃይማኖተ አበው ዘቅዱስ ቄርሎስ ምዕራፍ 7014-17)

እኛ ግን በሥላሴ ዘንድ በማዕረግ ማነሥና መብለጥ የለም በመለኮት አንድ ወገን ናቸው እንላለን” (አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ ተግሳጽ ዘሰባልዮስ)

ማጠቃለያ

ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ምስጢረ ሥላሴን በተረዳ ነገር ‹‹ሥላሴ አንድ ሲሆኑ ሦስት፣ ሦስት ሲሆኑ አንድ ናቸው፡፡ አንድነቱ ሦስትነቱን ሳይጠቀልለው፣ ሦስትነቱ አንድነቱን ሳይከፋፍለው በሕልውና ተገናዝበው የሚኖሩ ናቸው፡፡›› ብላ ታምናለች፤ ታስተምራለችም፡፡ ይህም እግዚአብሔር ለሰው ልጆች ራሱን የገለጠበት፣ ነቢያት የመሰከሩት፣ ወልደ እግዚአብሔር በተለየ አካሉ ሰው ሆኖ ያስተማረው፣ ሐዋርያትም በዓለም ዞረው የሰበኩት ምስጢር ነው፡፡ ስለዚህ እኛም እንደ አባቶቻችን “ምንም እንኳን ሥላሴን በስም፣ በአካል በግብር ሦስት ናቸው ብንልም ሦስቱ በባህርይ፣ በመለኮት፣ በህልውና፣ በፈቃድ አንድ ናቸው፡፡ አንድ አምላክ እንጂ ሦስት አማልክት አንልም፡፡ አብ ወልድና መንፈስ ቅዱስ ፍጹም አካል ፍጹም ገጽ አላቸው፡፡ ነገር ግን በህልውና አንድ ናቸው፡፡” ብለን እናምናለን፤ እንታመናለን፡፡

ስብሃት ለአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ፡፡ አሜን፡፡

________________

Posted in Ethiopia, Faith, War & Crisis | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

ቅ. ሥላሴ | እናንተም የክርስቶስ ከሆናችሁ እንኪያስ የአብርሃም ዘር እንደ ተስፋውም ቃል ወራሾች ናችሁ

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on December 16, 2021

💭 እንጦጦ መንበረ ስብሃት ቅድስት ስላሴ ቤተክርስትያን ፲፱፻፴፰ ዓ ም ተመሠረተ

ውብ እና ማራኪ የሆነው የቅድስት ሥላሴ ቤተከርስቲያን ግቢ፤ አዲስ አበባ እንጦጦ/ሽሮ ሜዳ መስከረም ፳፻፲ ወ ፩ ዓ.ም

✞✞✞[ወደ ገላትያ ሰዎች ምዕራፍ ፫፥፳፱]✞✞✞

እናንተም የክርስቶስ ከሆናችሁ እንኪያስ የአብርሃም ዘር እንደ ተስፋውም ቃል ወራሾች ናችሁ”

ጥቅምት ፳፬/24 በፃድቁ አባታችን አቡነ ተክለ ሐይማኖት ዕለት የጀመረውን ይህን በትግራይ ላይ እየተካሄደ ያለውን የዘር ማጥፋት “ዘመቻ ፀረአክሱምጽዮን” ጂሃዳዊ የጥቃት ጦርነትን የደገፉትና የሚደግፉ ከእንስሳ ዘር የተገኙት የዋቄዮአላህዲያብሎስ ጭፍሮችና የተታለሉት “ሃጋር/ አጋሮቻቸው እንዲሁም በመላው ዓለም የሚገኙትና የእባቡ ዘር የሆኑት ኤዶማውያን እና እስማኤላውያን ሁሉ፤ ”ጽዮናውያንን ከምድረ ገጽ ካላጠፋን ብለው ዛሬም ሆነ ለብዙ ዘመናትም በተለያየ መንገድ የዘር ማጥፋት ጦርነቱን የከፈቱበት ዋናው ምክኒያት ጥንታዊውን፣ የመጀመሪያውን የሴቲቱን የሰው ዘር፣ እስራኤል ዘነፍስ የተባለውን የአዲስ ኪዳኑን ኢትዮጵያዊ ሙሉ በሙሉ አጥፍተው ምድርን ሙሉ በሙሉ ለብቻቸው በመቆጣጠር “ኬኛ” እያሉ ዋቄዮአላህዲያብሎስን ለማንገስ ስለሚሹ ነው። ተግባራቸው ፀረ ሥላሴ፣ የክርስቶስ ተቃዋሚ፣ ፀረጽዮን፣ ፀረአቡነ አረጋዊ፣ ፀረአቡነ ተክለ ሃይማኖት፣ ባጠቃላ ፀረቅዱሳን፣ ፀረተዋሕዶ ክርስትና፣ ፀረኢትዮጵያ፣ ፀረሰንደቅ፣ ፀረግዕዝ፣ ፀረሰሜናውያን፣ ፀረተጋሩ፣ ፀረሰላም፣ ፀረፍቅር፣ ፀረፍትህ፣ ፀረእውነት መሆኑን ያለፉ አስራ አራት ወራት ቁልጭ አድርገው አሳይተውናል።

ቅዱስ ዮሐንስ በራዕዩ ”ዲያቢሎስ ጥቂት ዘመን እንዳለው አውቆ በታላቅ ቁጣ ወደ እናንተ ወርዷልና” ብሎ ስለነገረን ወደ ሕይወታችን በቅናት ቁጣ እየመጣ የሚያመሰቃቅለንን፣ ግራ የሚያጋባንን፣ የሚያባክነንን፣ የእኛ የሆነውን የሚነጥቀንን ዲያቢሎስ በሰይፈ ሥላሴ ጸሎት ልናርቀው እና ልንርቀው ይገባል። [ራዕ. ፲፪÷፲፪]

✞✞✞በመለኮት ቅድስት ሥላሴ፤ የሚተነኳኰለን፣ ወንድማማቾችን እርስበር የሚያባለው፣ ቀጣፊው፣ አጭበርባሪው፣ አታላዩ፣ ጠበኛው፣ የዲያብሎስ ጭፍራ አብዮት አህመድ አሊ የተባለው አረመኔ ጠላታችን ይጠፋልን ዘንድ የእግዚአብሔር ቃል ይውጋው፣ በተሳለ የመለኮት ሰይፍ አንገቱን ያጣጋው በአምልኮትና በፍጹም ምስጋና በሥላሴ ስም አሜን!✞✞✞

___________________

Posted in Ethiopia, Faith, War & Crisis | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

ቁሱቋም ማርያም | በፋሺስቱ የኦሮሞ አገዛዝ የተገደሉት የወላይታ ብሔር ወጣቶች

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on November 15, 2021

💭 ያው የፋሺስቱ ኦሮሞ አገዛዝ ገና የሥልጣኑን ወንበር እንደተረከበ ነበር ኦሮሞ ያልሆኑትን ኢትዮጵያውያን አንድ በአንድ መጨፍጨፍ የጀመረው። እኛ በወቅቱ፤ “የግራኝን እባባዊ ዓይን ተመልከቱ! በጣም አደገኛ ሰው ነው ወዘተ” በማለት ቻነሎቻችን እስኪዘጉ ድረስ በተደጋጋሚ ስናስጠነቅቅ ነበር። ጭፍጨፋውን ከአንድ ኦሮሞ ካልሆነ ብሔር ወደሌላው ብሔር በሂደትና በማታለያ ስልት እየተሸጋገረ እየፈጸመ ዛሬ ወደ ትግራይ እና አማራ ክልሎች የተሸጋገረው።

አውሬው የበሻሻ ዲቃላ የግራኝ አብዮት አህመድ አሊ የባሌ ንግግር እንደ አንድ ትልቅ የዘርማጥፋት ጥሪ ተደርጎ በማስረጃነት መቅረብ ይኖርበታል። ከ እነ ለማ መገርሳ፣ ጃዋር እና ሽመልስ አብዲስ “ነፍጠኛን ሰባበረነዋል፣ የክርስቲያኑን አንገት በሜንጫ ነው የምንቆርጠው ወዘተ” ንግግር የከፋውና ዛሬ በደንብ ሲተገበር እያየነው ያለነው ይህን ነው፤፦

ኦሮሞ እስኪነቃ ነው እንጂ፣ እስኪነሳ ነው እንጂ ሲነሳ ሚዳቋ አትበላንም፤ እኛ ዝሆን ነን፤ እንሰብራለን፤ እንበላለን፤ እንገዛለን።” ሃሳብ አለን፤ ድርጅት አለን፤ ከአለም ጋር ግንኙነት አለን፤ ህዝባችን በስራ ያውቀናል፤ እኛም ህዝባችንን እናውቃለን፤ ሽማግሌዎቻችንን እናውቃለን፤ ተያይዘን መላውን አፍሪካን ለመለወጥ፣ ይሄ ዘመን የእኛ ስለሆነ፣ ይህን ዘመን የሰጠን አላህ በመሆኑ አሳልፈን ሰጥተን ዳግም ወደ ባርነት ለመመለስ አንፈልግም፤ ያ ደግሞ ተመልሶ አይመጣም። እጃችሁ የገባውን ነገር ጠብቁ፤ ቆጥቡ፤ አጠንክሩ፤ ጉድለት (ስህተት) ካለ ምከሩ። ያለበለዚያ ይህን ከጅ ካወጣን አጥር ውስጥ ተቀምጠው እንደሚያለቅሱት ዓይነት ለቅሶ ስለሚሆን፣ ከዚህ በኋላ ለኦሮሞ ለቅሶ የማይሆንለት ስለሆነ፣ ያገኘነውን ይዘን፣ የቀረውን ሞልተን፣ ወደ ፊት መሄድ እንድንችል”

በግልጽ ብሎናል።

💭 አረመኔው ግራኝ አብዮት አህመድ አሊ ወደ ስልጣን መምጣቱን ተከትሎ በፋሺስቱ የኦሮሞ አገዛዝ የተካሄዱ ጭፍጨፋዎች፣ ግድያዎች፣ እገታቸው፣ ማፈናቀሎች፣ ቃጠሎዎችና ዝርፊያዎች፦

. ቡራዮ ላይ አራት መቶ የጋሞና የሌሎች ብሔር ተወላጆች ተጨፈጨፉ

. በዶዶላ የሰው ልጅ አካል ተቆራረጠ

. በአርባ ጉጉና በብኖ በደሌ የሰው ሬሳ ተጎተተ

. በሶማሌ ክልል ክርስቲያኖች ታረዱ

. በሲዳማ ዞን የሀይማኖት አባቶች ቤንዚን ተርከፍክፎ ተቃጠሉ

. በለገጣፎ በሰበታና በሰንዳፋ የንጹሃን ቤት በላያቸው ላይ ፈረሰ

. ፵፩/41 ዓብያተ ክርስቲያናት በኦሮሚያ ተቃጠሉ

. በርካታ መስጂድ ተቃጠለ

. ወለጋ ላይ 22 ባንክ ተዘረፈ

. ኦነግ በአጣዬ በካራ ቆሬና በኬሚሴ ንጹሃንን ጨፈጨፈ

፲፩. የአፋር አርሶ አደሮች በኡጋንዳ ታጣቂዎች ተረሸኑ

፲፪. /1 ሚሊዮን የጌድዮ ህዝብ ተፈናቀለ

፲፫. የአማራና የትግራይ ተወላጆች ከመስርያ ቤት እየተለቀሙተ ተባረሩ።

፲፬፣ ኢንጂነር ስመኘው በቀለ ተገደለየአብን, የአማራ ወጣት እና የአማራ ተማሪ ማህበር አባላትና አመራሮች በግፍ በጅምላ ታሰሩ

፲፭. በአዲስ አበባ የወላይታ ተወላጆች በኦሮሞ ፖሊስ ተረሸኑ

፲፮. በቤንሻንጉል ክልል ንጹሃን በቀስት ተገደሉ

፲፯. ጎንደር ላይ ህጻናት ታግተው ተረሸኑ

፲፰. ፵፭/45 ሺህ የአማራ ተማሪዎች ከዩኒቨርሲቲ ተባረሩ

፲፱. አሳምነው ጽጌና ሰዓረ መኮንን ጨምሮ በርካታ የአማራና የትግራይ መሪዎች በኦነጉ አብይ ተረሸኑ

. በሐረርጌ የ ሁለት ወር አራስ ታረደች

፳፩. ወለጋ ላይ ፭/5 ተዋሕዶ ክርስቲያኖች በኦሮሞዎች ተገድለው ሬሳቸው ተቃጠለ

፳፪. ፹፮/86 ንጹሃን በአንድ ቀን ተጨፈጨፉ

፳፫. ፲፯ ሴት ተማሪዎች ከደምቢዶሎ ዩኒቨርሲቲ ታግተው እስከ አሁን ቁጥሩን እርግጠኛ መሆን ባይቻልም በርካታ ተማሪዎች በአሰቃቂ ሁኔታ መገደላቸው ተሰምቷል

፪፬. ሻሸመኔ ላይ ሰው ተዘቅዝቆ ተሰቀለ

፳፭. የኦሮምያ ፖሊስ አዲስ አበባ ገብቶ ቤተክርስትያን በማፍረስ ሁለት ወጣቶች ገድሎ ፲፭/15 ወጣቶችን አቁስሏል

ይሄ ሁሉ የሆነው ራሱን ብልጽግና ብሎ በሚጠራው የኦሮሞው አውሬ ስብስብ ፓርቲ ነው። ይህ ከብዙ ግፎች በጥቂቱ ተጨፍልቆ የተጠቀሰ ነው።

ልብ በሉ ይህ ሁሉ ግፍና መከራ ተፈጽሞ አንድም ወንጀለኛ አልተያዘም፣ ለአንዱም ወንጀል ይቅርታ አልተጠየቀም፣ የሃዘን ቀን አልታወጀም። አረመኔው አብዮት አህመድ አሊ ኢትዮጵያን ያጠፋላቸውና እስላማዊቷን ኦሮሞ ኤሚራትን ይመስርትላቸው ዘንድ የተቀጠረ ጸረ-ጽዮን፣ ጸረ ኢትዮጵያና ጸረ ኦሮቶዶክስ አውሬ ነው።

👉 ይህ ከሦስት ዓመታት በፊት ልክ በዚህ ወቅት የቀረበ መረጃ ነው፤

✞✞✞አዲስ አበባ መስከረም ፱፡ ፪ሺ፲፩ ዓ.ም✞✞✞

የቁስቋም ቅድስት ማርያም ቤተክርስቲያን አውደ ምህረት፤ ጸሎተ ፍትሃት በፋሺስቱ የኦሮሞ አገዛዝ ለተሰውት የወላይታ ብሔረሰብ ወንድሞቻችን።

በመስከረም ወር ላይ የኦሮሞ ሙስሊሞችን እንቅስቃሴ ለመቃወም በሰላማዊ መልክ በአደባባይ ወጥተው ከነበሩት ብዙ ወገኖቻችን መካከል ሁለት ወጣቶች መገደላቸው የሚታወስ ነው። ከዚህ ጋር በተያያዘ በ መስከረም ፱፡ ፪ሺ፲፩ ዓ.ም በታሪካዊው ቁስቋም ማርያም ቤተክርስቲያን አውደ ምህረት ላይ የወጣቶቹን ጸሎተ ፍትሀት እና ጸሎት በማከናወን አስፈላጊ የሆነውን ክብርም ተሰጥቷቸው ነበር።

የኀዘን ሥርዓቱ ላይም ብዙዎች ነጭ ለብሰው ይታያሉ።

በቁስቋም ማርያም ውሎዬ ይህን መሰሉ ታሪካዊ ነገር ይገጥመኛል ብዬ አላስብኩም ነበር፤ ቀደም ሲል ስለ ቀብር ሥርዓቱ ምንም የማውቀው ነገር አልነበረምና። ይህን እታዘብ ዘንድ መንፈስ ቅዱስ ነው ወደዚህች ቅድስት ቦታ የመራኝ። ከቤተ ክርስቲያኗ ስወጣ፤ አንድ የኦሮምኛ ቋንቋ ተናጋሪ የሆነ ሰው ወደ እኔ መጥቶ፤ “ለምንድን ነው ቪዲዮ ስትቀርጽ የነበረው?” ብሎ ሲጠይቀኝ፤ “እርስዎ ማን ነዎት?!” በማለት ሰውዬውን ዝም አሰኝቼው እንደነበር አስታውሳለሁ።

የሰማዕታቱ በረከታቸው ይደርብን!❖

_____________

Posted in Ethiopia, Faith, War & Crisis | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

አዲስ አበባ ሰማይ ስር የሚሠራው ግዙፍ መስቀል

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on September 28, 2020

ይህ ሥራ በጣም በጎ ነገር ነው፤ እንዲያውም አዲስ አበባ ዙሪያዋን በመስቀል ብትከበብ ነዋሪዎቿ ከብዙ መዓት ይድናሉ፤ በአቡነ ኃብተማርያም ገዳምም መሠራት ይኖርበታል።

ነገር ግን ዛሬ በአላጋጮችና ድራማ ሠሪዎች ተከብበናልና “ይህ ዜና በአዲስ ዓመት መግቢያ ላይ እንዲሁም በደመራና መስቀል ወቅት ከመውጣቱ ጀርባ ማን/ ምን ይኖር ይሆን?” የሚለውን ጥያቄ ከመጠየቅ መቆጠብ የለብንም። መቼስ ማጭበርበርና ማታለል ሙያው አድርጎ የያዘው የአውሬው አገዛዝ ቤተ ክርስቲያንን ለመፈታተን እና ለመተናኮል የማይቆፍረው ጉድጓድ የለምና።

ምናልባት፦

👉 የቆፋፈረውን የመስቀል አደባባይ ጉዳይ ለማረሳሳትና ህዝበ ክርስቲያኑን ለመደለል ይሆን?

👉 በጣም ሚስጢራዊ የሆነውን እና መስቀል አደባባይ እና ቅዱስ እስጢፋኖስ ቤተክርስቲያን የሚገኙበትን አካባቢ ሙሉ በሙሉ ለመቆጣጠር አቅዶ ይሆን?

👉 የመስቀል አደባባይን “አንድነት ወይንም ኢሬቻ አደባባይ” ብሎ ለመሰየም ዕቅድ ስላለው ይሆን?

👉 ከ “ሸገር ፕሮጀክት፣ እንጦጦ ፓርክ ቅብርጥሴ” ጋርስ የሚያገናኘው ምን ነገር ይኖራል?

ለማንኛውም በሚቀጥሉት ቀናት የምናየው ይሆናል። የአውሬው አገዛዝ ካድሬዎችና ወኪሎች ተዋሕዷውያንን አወናብዶ ወደካምፑ ለማምጣት የተለያዩ ቅስቀሳዎችን ሲያደርጉ የምንሰማበት አጋጣሚ ይኖራል።

________________________

Posted in Ethiopia, Faith, Infos | Tagged: , , , , , , , | Leave a Comment »

ክቡር መስቀሉን እንጦጦ ላይ አላሰራንም ፥ መስቀል አደባባይንም እንዳይቆፈር አልተጋደልንም

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on September 28, 2020

ስለዚህ አውሬው እንዲህ ቢሳለቅብንና ቢፈነጭብን ሊገርመን ይችላልን?

👉 ከዓመት በፊት አቅርቤው የነበረው ጽሑፍ እና ቪዲዮ

አዲስ አበባን ከጠላቶቿ የሚጠብቃት አንጋፋ መስቀል በእንጦጦ ተራሮች ላይ ሊሠራ ነው”

እንኳን ለበአለ መስቀል አደረሰን!

👉 ደብረ መድኃኒት አቡነ ሀብተማርያም፣ ቅድስት ልደታ እና ቅድስት አርሴማ ገዳም፡ ክፍል ፫

ክቡር መስቀሉ የሚሠራው በደብረ መድኃኒት አቡነ ሃብተማርያም፣ ቅድስት ልደታ እና ቅድስት አርሴማ ገዳም ጫፍ ላይ ነው። ከዚህ ተራራ ጫፍ ሆኖ በመላው አዲስ አበባን አካባቢዋ ሊታይ ይችላል፤ ማታ ላይም በደንብ እንዲታይ መብራት ይኖረዋል።

ይህ የተቀደሰ ሥራ ከሁሉም ሥራዎች ቀድሞ በፍጥነት መከናወን ይኖርበታል እላለሁ። ላለፉት አስራ አምስት ዓመታት “እንጦጦ ማርያም ጫፍ ላይ አንድ ትልቅ መስቀል መተከል አለበት” እያልኩ ብዙ አባቶችን በየጊዜው ስወተውት ነበር፤ አሁን ህልሜ ዕውን ሆነ።

ጻድቁ አባታችን አቡነ ሃብተማርያም ወደ ገዳማቸው መርተውኝ ይህን የመስቀል ሥራ ንድፍ ሳይ፡ ባጋጣሚው፡ ማመን እስኪያቅተኝ ድረስ ተገርሜም ተደስቼም ነበር። እስከ አሁንም ድረስ ብዙ ነገሮች ይታዩኛል፤ ለምሳሌ፡ በአንድ በኩል ቤተ ክህነት ኃላፊነቱን ወስዳ ቶሎ ማሠራት አለባት እላለሁ፤ በሌላ በኩል ደግሞ አዲስ አበባውያን፥ ውጭ ካለነው ኢትዮጵያውያን ጋር በመተባበር ባጭር ጊዜ ውስጥ – እንዲያውም ፻፹ ሜትር ከፍ በማድረግ – ማሠራት እንችላለን ብዬ አስባለሁ። እያንዳንዱ የአዲስ አበባ ተዋሕዶ ልጅ በፍጥነት ተረባርቦ በተግባር ሊያውለው የሚገባው ሥራ ነው።

የአቡነ ሃብተማርያምን የፀሎት መጽሐፍ በብሔረ ፅጌ ቅድስት ማርያም ቤተክርስቲያን ሲያከፋፍል የነበረውን የቤተክርስቲያን አገልጋይ ወንድማችንን፡ “መስቀል አቡነ ሃብተማርያም ገዳም ጫፍ ላይ ሊተከል ነው፤ ምን ይሰማሃል” ስለው፤ ቪዲዮው ላይ የቀረበውን ግሩም ትምህርት በደስታ አካፍሎኝ ነበር። እርሱም እንደ አብዛኛው/መላው አዲስ አበቤ መስቀል እዚያ የመትከል ዕቅድ አልሰማም። ቃለ ሕይወት ያሰማልን!

በመጭዎቹ ወራት አዲስ አበባውያን የተዋሕዶ ልጆች በሚከተሉት ሁለት ነገሮች ይፈተናሉ፦

፩ኛ፦ ለክቡር መስቀሉ ምን ያህል ፍቅር እንዳላቸው በማሳየት

፪ኛ፦ በሊቢያ በሙስሊሞች ለተሰውት ሰማዕታት አስከሬን እንዴት አቀባበል እንደሚያደርጉ

በመቅሰፍት የተመታችው አዲስ አበባ መዳን የምትችለው በፖለቲከኞች የተመሰቃቀለ ጭንቅላት ሳይሆን በክቡር መስቀሉ ነው። ቶሎ እናሠራው! መስቀል ኀይላችን፣ ጽንዓችን፣ ቤዛችን፣ የነፍሳችን መዳኛ ነው!!!

ልዑል እግዚአብሔር በመስቀሉ ኃይል ኹላችንንም ከልዩ ልዩ ዓይነት መከራ ይጠብቀን፡፡

_____________________________

Posted in Ethiopia, Faith, Infos | Tagged: , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

ድንቁ ርዕሠ አድባራት እንጦጦ ደ/ኃ/ቅ ራጉኤል ወ ኤልያስ ቤ/ክርስቲያን

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on September 11, 2020

እንኳን ለሊቀ መላእክት ቅዱስ ራጉኤል አመታዊ መታሰቢያ እለት አደረሳችሁ!

አማላጅነቱ ኃይለ ረድኤቱ ለሁላችን ይደረግልንና የመልአክት አለቃ ቅዱስ ራጉኤል ያደረገው ተአምር ይህ ነው።

እስራኤል ከግብጽ ከወጡ በኋላ እግዚአብሔር ለአባቶቻቸው ተስፋ የሰጣት ወደ ከነዓን ምድር በገቡ ጊዜ የሃገሪቱን አውራጃውንና ወረዳውን ለይቶ በየነገዳቸውና በየወገናቸው ለእስራኤል ርስትን ያከፋፈለ የነዌ ልጅ ኢያሱ የሚባል አንድ መስፍን ነበረ።

ከእለታት በአንድ ቀን የአምሬውን ነገስታት ኢያሱን ይወጉት ዘንድ የእስራኤል ሕዝብ ወደሰፈረበት በገባዖን ምድር ወደ ገልገላ ተከማቹ። ኢያሱም ይህን በሰማ ጊዜ ከእርሱ ጋር የነበሩት የጦር ሰራዊትና የጦር አለቆችንም ሁሉ ይዞ ሌሊቱን ሁሉ ገስግሶ ድንገት ደረሰባቸው። ኢያሱም ከጠላቶቹ ጋር ገና በተፋፋመ ጦርነት እንዳለ ፀሐይ ልትጠልቅ ተቃረበች ምሽትም ሆነ ።

በዚያም ጊዜ ኢያሱ የነዌ ልጅ ወደ አምላኩ ወደ እግዚአብሔር እንዲህ ሲል ጸለየ ሕዝብህ እስራኤል ጠላቶቹን ፈጽሞ እስኪያጠፋ ድረስ ፀሐይ በገባዖን ትቅም ዘንድ በኤሎንም ሸለቆ ጨረቃ ይዘገይ ዘንድ አብርሃምን፣ ይስሐቅንና ያዕቆብን አስበህ ፀሎቴን ተቀበል በማለት ጸለየ። ሁሉን የሚገዛ እግዚአብሔርም የነዌ ልጅ የኢያሱን ጸሎት ሰማውና ፀሐይን ከምዕራብ ወደ ምስራቅ መልሶ ባለችበት ፀንታ ትቆም ዘንድ መልአከ ብርሃናት ራጉኤልን አዘዘለት።

የመልአክ አለቃ ቅዱስ ራጉኤልም እግዚአብሔር እንዳዘዘው ፀሐይን ከምዕራብ ወደ ምስራቅ መለሰውና ፀሐይ በሰማይ መካከል ቆመ አንድ ቀን ሙሉውን ወደ መግቢያው ለመሄድ አልተቻኮለም ሕዝቡም ጠላቶቻቸውን እስኪበቀሉ ድረስ ፀሐይም ጨረቃም ባሉበት ፀንተው ቆዩ እንጂ።

የመላእክት አለቃ ራጉኤል በፀሐይ በጨረቃና በከዋክብት በሌሎችም ብርሃናት ሁሉ ላይ የሰለጠነ ነውና። መስፍኑ ኢያሱም በጠላቶቹ በገባዖን ሰዎች ላይ ድልን ከተቀዳጀ በኋላ በቅዱስ ራጉኤል መሪነት ፀሐይ ቦታውን አውቆ ወደ መግቢያው ተቀላቀለ። በዚህም ጊዜ መስፍኑ ኢያሱ የነዌ ልጅ በመልአከ ብርሃናት ራጉኤል እጅ ፀሐይን አቁሞ እግዚአብሔር ስላደረገለት ታላቅ ኃይል ፈጽሞ ተደሰተ ፈጣሪውንም አመሰገነ።

የሊቀ መላእክት ቅዱስ ራጉኤል አማላጅነቱ ለሀገራችን ለኢትዮጵያና ለመላው ህዝቦቿ ለዘለዓለሙ በእውነት ይደረግልን አሜን!

______________________________

Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , | Leave a Comment »

የታገቱትንና የተገደሉትን በማስታወስ “አቤቱ የሆነብንን አስብ!” ብለን በመጮህ ወደ ኪዳነ ምሕረት እንቅረብ

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on February 24, 2020

እህቶቻችን ከጠፉ ልክ ዛሬ ፹ (ሰማንያ) ቀናት ሆነዋቸዋል።

ባለፈው ቅዳሜ በመስቀል አደባባይ ወደ ተካሄድው የቴዲ አፍሮ የሙዚቃ ኮንሰርት የአዲስ አበባ ወጣቶች ምን ፈልገው፣ ምን አቅደው እንደሄዱና ለሃገራቸውም ምን በጎ ነገር እንዳመጡም የማውቀው ነገር የለም። ነገር ግን እህቶቻችን ከደንቢደሎ ዩኒቨርሲቲ እልም ብለው በጠፉበት ማግስት፤ ተዋሕዶ የአዲስ አበባ ልጆች በቤተ ክርስቲያናቸው ውስጥ በግፍ በተረሸኑበት ማግስት፤ ጌታችን በተሰቀለበት መስቀል ስም በተሰየመበት ቦታ ላይ ለዳንኪራ እና ጭፈራ በመውጣት የመምህር ምሕረተአብን የማንቂያ ደወል ለማቆምና የገዳይ አብይን አጀንዳ ለማስፈጸም ወጥተው ከሆነ እጅግ በጣም ነው የማዝነው። ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የሰጠን የመስቀል ስር ስጦታ የሆነችው ውዷ እናታችን ቅድስት ድንግል ማርያምም እንደ እናትነቷ አብዝታ ታዝንባቸዋለች።

ይህ ዕለት እናታችን ቅድስት ኪዳነ ምሕረት ከልጇ ቃል ኪዳን የተቀበለችበት ቀን ነው። የእመቤታችን ቃል ኪዳን ለየት ያለ ነው። ለየት የሚለውም በሁለት ዐበይት ምክንያቶች ነው። የመጀመሪያው እርሷ ምልዕተ ፀጋ በመሆኗና ፍጽምት ርህርህተ ሕሊና ከመሆንዋ የተነሣ ስለ ሰው ልጆች አብዝታ የማለደች እናት እና ክርስቲያኖች ሁሉ ይድኑ ዘንድ ከሌሎቹ በተለየ የለመነች በመሆንዋ ነው።እንኳን እግዚአብሔር ጨካኙ ዳኛ እንኳን አብዝታ ለለመነችው መበለት ያደረገውን እናውቃለንና።(ሉቃ. ፲፰፡፩)

ሁለተኛው ምክንያት ደግሞ ወላዲተ አምላክ ለመባል የበቃች ከእርስዋ በቀር ሌላ የሌለ፤ በዚህም መልዕልተ ፍጡራን ትሆን ዘንድ አምላክ ያከበራት በመሆንዋ ልዩ ቃል ኪዳን ይገባላት ዘንድ የተገባት ናት። ለአምላክ እናትነት(ልዩ) ሆና መመረጧን ለሚያምን ሁሉ ልዩ ቃል ኪዳን መቀበሏ ጥያቄ አይሆንበትም። ስለዚህም ልዩ ቃል ኪዳን ተገብቶላታል። ነቢዪ ኢሳይያስ ወይወጽእ እምጽዮን መድኅን ወየዐትት ኃጢአተ እም ያዕቆብ ወዛቲ ይእቲ ኪዳኖሙ እንተ እምኀቤየ ይቤ እግዚአብሔር፦ መድኅን (ክርስቶስ) ከጽዮን ይወጣል (ከእመቤታችን ይወለዳል)፣ ኃጢአትንም ከያዕቆብ (ከእስራኤል ዘነፍስ) ያርቃል፤ ለእስራኤል የማልሁላቸው መሐላ የገባሁላቸው ቃልኪዳንም ይህቺ ናት፤ ሲል እንደተናገረ እግዚአብሔር ልዩ ውልና ስምምነት ከእስራኤል ዘነፍስ ጋር አለው።(ኢሳ.፶፱፡፳፳፩) ከዚህ ውስጥ አንዱና ዋናው ከእመቤታችን ጋር ያደረገው ነው።

ይህ ኪዳን ልዩ ከሆነበት ነገሩ አንዱ የራሱ መታሰቢያ ዕለት ያለው መሆኑ ነው። ዕለቱም ጌታችን በጌቴሰማኒ ተገልጾ ኪዳኑን የገባበት ዕለት ነው፤ ይኸውም የካቲት ፲፮ ቀን ነው። እመቤታችን ከላይ እንደተገለጸው ወደ ጎልጎታ ወደ ጌታ መቃብር እየሄደች አብዝታ ትለምን ነበር። በዚህም ምክንያት መላእክት ወደ ሰማያት አሳርገው ገነትንና ሲዖልን አስጎብኝተዋታል። እርስዋም በሲዖል ያሉ ነፍሳትን አይታ በእጅጉ አዝናላቸዋለች፤ ከዚህም በኋላ ስለ ኃጥአን አብዝታ ስትለምን ጌታችን አምላካችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዚች ዕለት ተገልጾ ልዩ የምሕረት ቃልኪዳን ስለገባላት ኪዳነ ምሕረት እየተባለች ትከበራለች።

እኛም ከዚህ እጅግ ሊያስተውሉት ከሚገባ ታላቅ መልእክት የምናገኘው ትልቅና ታላቅ ቁም ነገር እግዚአብሔር ከመረጣቸውና ካከበራቸው ጋር እንዴት ቃል ኪዳን እንደሚያደርግ ሲሆን አብዝተው ለጠየቁትና ለተማጸኑት የቅርብ አምላክ እንጂ የሩቅ አምላክ አለመሆኑን ማሳየቱና ጸሎታቸውንና ልመናቸውን ሰምቶ ምላሽ መስጠቱን ነው። ስለሆነም አምላካችን ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ቃል ኪዳን ከገባላት የመስቀል ስጦታ እናታችን በረከትን ለማግኘት ዘወትር በተሰበረ ልብና በተዋረደ መንፈስ መቅረብ ያስፈልጋል። ነቢዩ ኤርምያስ “አቤቱ የሆነብንን አስብ” ብሎ እንደጮኸው ጩኸት እያንዳንዳችን የምሕረት ቃል ኪዳንን ወደተቀበለች ወደ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም እንቅረብ። ልዑል እግዚአብሔር ንጉሥ ሰሎሞንን ስለ አባትህ ስለ ዳዊት ስል በትረ ንግሥናህን ከአንተ አልወስድም ብሎ ቃል እንደገባለት እኛም የዘላለም ቃል ኪዳን ስለገባላት ስለ ቅድስት ድንግል ማርያም ሲል እንዲምረን ፍጹም ትህትናን ገንዘብ አድርገን እግዚአብሔር ያከበራቸውን አክብረን መገኘት ይኖርብናል። በዚህ ታላቅ ፆምም በረከትን ለማግኘት ፆማችንን ከግብር ጋር አገናኝተነው ደካሞች የሚረዱበትን፣ ታማሚዎች የሚጠየቁበትን፣ እስረኞች የሚጎበኙበትን፣ የታረዙ የሚለብሱበትን፣ የተራቡ የሚጠግቡበትን፣ የተጠሙ የሚጠጡበትን መንገድ ለማመቻቸት የተዘጋጀን መሆን ይኖርብናል። ከሥራ የተለየ እምነት የሞተ ነው ብሎ ሐዋርያው ያዕቆብ እንደተናገረ እኛም ፆምንና ምፅዋትን አስማምተን ለበጎ ሥራ የተዘጋጀን እንድንሆን አምላካችን በቸርነቱ ይርዳን፤ እመቤታችን በተገባላት ቃል ኪዳን ትጠብቀን።

ወ ስ ብ ሐ ት ለ እ ግ ዚ አ ብ ሔ ር

___________________________

Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , | Leave a Comment »

ለመራዡ ኡማ የ፲ሚሊየን ብር ሽልማት | ፫መቶ ታዳጊ የቅኔ ተማሪዎች ግን እየተራቡ ነው

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on December 7, 2019

ይሄ እንዴት ሊሆን ቻለ? የቄሳርን ለቄሣር?

ይህ በጣም ከሚያሳዝኑኝና ከሚያንገበግቡኝ ጉዳዮች መካከል አንዱ ነው። የአዲስ አበባን ሕፃናት በመመረዝ ላይ ላለው ለታከለ ኡማ መመረዣ ዳቦውን እና ማርመላታውን ይገዛበት ዘንድ ቤተክህነት አስር ሚሊየን ብር መለገሷን ሰምተናል፤ በቤተክርስቲያን ሥር የሚገኙ ሕፃናት ግን በመራብ ላይ ናቸው። እንዴት?

በርካታ ቀዳሚ የኢትዮጵያ ምሁራን መነሻቸው ከአብነት ትምህርት ቤት ነው። የአብነት ትምህርት ከዘመናዊ ትምህርት መስፋፋት ጋር ተያይዞ የወትሮ ሚናውን ማጣቱ ቢስተዋልም፤ አሁንም ጥቂት ለማይባሉ ወጣቶች ምርጫ መሆኑ አልቀረም።

የዕውቀት በርን የሚከፍትላቸውን የቅኔ ትምህርትን በንባብ ቤት፣ ዜማ ቤት፣ አቋቋም ቤት፣ ቅኔ ቤት፣ ቅዳሴ ቤት እና መፃሕፍት ቤት ለመከታተል ሦስት መቶ የቅኔ ተማሪዎች በድንቁ የአቡነ ሀብተ ማርያም ገዳም ይገኛሉ። ይሁንና የትምህርት ቤቶቹ ህልውና ከሚያስተዳድሯቸው ገዳማትና አብያተ ክርስትያናት መድከምና መጠንከር ጋር የተሳሰረ በመሆኑ ለፈተና ሲዳረጉ ይስተዋላሉ። ተተኪ የቤተክርስቲያን አገልጋዮች በቂ የመተዳደሪያ የገቢ ምንጭ ስለሌላቸውና ከቤተክህነትም እንኳን ምፅዋት ስለማያገኙ አሁን በመቸገር እና በመራብ ላይ ናቸው። አዎ! በአዲስ አበባ፣ ያውም በጣም ሰላማዊና ገነታማ ከሆኑት የከተማዋ ክፍሎች መካከል በአንዱ።

_____________________________

Posted in Ethiopia, Faith, Infos | Tagged: , , , , , , , , , , , , , | 1 Comment »

አዲስ አበባን ከጠላቶቿ የሚጠብቃት አንጋፋ መስቀል በእንጦጦ ተራሮች ላይ ሊሠራ ነው

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on March 19, 2019

እንኳን ለበአለ መስቀል አደረሰን!

ክቡር መስቀሉ የሚሠራው በደብረ መድኃኒት አቡነ ሃብተማርያም፣ ቅድስት ልደታ እና ቅድስት አርሴማ ገዳም ጫፍ ላይ ነው። ከዚህ ተራራ ጫፍ ሆኖ በመላው አዲስ አበባን አካባቢዋ ሊታይ ይችላል፤ ማታ ላይም በደንብ እንዲታይ መብራት ይኖረዋል።

ይህ የተቀደሰ ሥራ ከሁሉም ሥራዎች ቀድሞ በፍጥነት መከናወን ይኖርበታል እላለሁ። ላለፉት አስራ አምስት ዓመታት “እንጦጦ ማርያም ጫፍ ላይ አንድ ትልቅ መስቀል መተከል አለበት” እያልኩ ብዙ አባቶችን በየጊዜው ስወተውት ነበር፤ አሁን ህልሜ ዕውን ሆነ።

ጻድቁ አባታችን አቡነ ሃብተማርያም ወደ ገዳማቸው መርተውኝ ይህን የመስቀል ሥራ ንድፍ ሳይ፡ ባጋጣሚው፡ ማመን እስኪያቅተኝ ድረስ ተገርሜም ተደስቼም ነበር። እስከ አሁንም ድረስ ብዙ ነገሮች ይታዩኛል፤ ለምሳሌ፡ በአንድ በኩል ቤተ ክህነት ኃላፊነቱን ወስዳ ቶሎ ማሠራት አለባት እላለሁ፤ በሌላ በኩል ደግሞ አዲስ አበባውያን፥ ውጭ ካለነው ኢትዮጵያውያን ጋር በመተባበር ባጭር ጊዜ ውስጥ – እንዲያውም ፻፹ ሜትር ከፍ በማድረግ – ማሠራት እንችላለን ብዬ አስባለሁ። እያንዳንዱ የአዲስ አበባ ተዋሕዶ ልጅ በፍጥነት ተረባርቦ በተግባር ሊያውለው የሚገባው ሥራ ነው።

የአቡነ ሃብተማርያምን የፀሎት መጽሐፍ በብሔረ ፅጌ ቅድስት ማርያም ቤተክርስቲያን ሲያከፋፍል የነበረውን የቤተክርስቲያን አገልጋይ ወንድማችንን፡ “መስቀል አቡነ ሃብተማርያም ገዳም ጫፍ ላይ ሊተከል ነው፤ ምን ይሰማሃል” ስለው፤ ቪዲዮው ላይ የቀረበውን ግሩም ትምህርት በደስታ አካፍሎኝ ነበር። እርሱም እንደ አብዛኛው/መላው አዲስ አበቤ መስቀል እዚያ የመትከል ዕቅድ አልሰማም። ቃለ ሕይወት ያሰማልን!

በመጭዎቹ ወራት አዲስ አበባውያን የተዋሕዶ ልጆች በሚከተሉት ሁለት ነገሮች ይፈተናሉ፦

፩ኛ፦ ለክቡር መስቀሉ ምን ያህል ፍቅር እንዳላቸው በማሳየት

፪ኛ፦ በሊቢያ በሙስሊሞች ለተሰውት ሰማዕታት አስከሬን እንዴት አቀባበል እንደሚያደርጉ

በመቅሰፍት የተመታችው አዲስ አበባ መዳን የምትችለው በፖለቲከኞች የተመሰቃቀለ ጭንቅላት ሳይሆን በክቡር መስቀሉ ነው። ቶሎ እናሠራው! መስቀል ኀይላችን፣ ጽንዓችን፣ ቤዛችን፣ የነፍሳችን መዳኛ ነው!!!

ልዑል እግዚአብሔር በመስቀሉ ኃይል ኹላችንንም ከልዩ ልዩ ዓይነት መከራ ይጠብቀን፡፡

__________________

Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

በኢትዮጵያ ጠላቶች የተገደሉት ወጣቶች የቀብር ሥርዓት በቁስቋም ማርያም

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on October 11, 2018

በመስከረም ወር ላይ የኦሮሞ ሙስሊሞችን እንቅስቃሴ ለመቃወም በሰላማዊ መልክ በአደባባይ ወጥተው ከነበሩት ብዙ ወገኖቻችን መካከል ሁለት ወጣቶች መገደላቸው የሚታወስ ነው። ከዚህ ጋር በተያያዘ በ መስከረም ፱፡ ፪ሺ፲፩ ዓ.ም በታሪካዊው ቁስቋም ማርያም ቤተክርስቲያን አውደ ምህረት ላይ የወጣቶቹን ጸሎተ ፍትሀት እና ጸሎት በማከናወን አስፈላጊ የሆነውን ክብርም ተሰጥቷቸው ነበር።

የኀዘን ሥርዓቱ ላይም ብዙዎች ነጭ ለብሰው ይታያሉ።

በቁስቋም ማርያም ውሎዬ ይህን መሰሉ ታሪካዊ ነገር ይገጥመኛል ብዬ አላስብኩም ነበር፤ ቀደም ሲል ስለ ቀብር ሥርዓቱ ምንም የማውቀው ነገር አልነበረምና። ይህን እታዘብ ዘንድ መንፈስ ቅዱስ ነው ወደዚህች ቅድስት ቦታ የመራኝ

በረከታቸው ይደርብን!

______

Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , | Leave a Comment »

 
%d bloggers like this: