በየአብያተክርስቲያናቱ አባቶች፦“ሴቶቻችን ውስጥ የገባው ጋኔን ይውጣልን!”
እያሉ ጸሎት ማድረስ ጀምረዋል።
ዛሬ፤ እንደገና፡ ቀኑን ሙሉ ሲያሳስበኝ የዋለ ጉዳይ ነው…
ጌታዬ አምላኬ፣ ፈጣሪዬ ሆይ፡ ጠላቶችህ፡ በጥቁር አሜሪካውያን ላይ የተጠቀሙትን ዓይነት ዲያብሎሳዊ ትሪክ በየዋሆቹ እህቶቼ ላይ እየተጠቀሙ ነው፤ አባቴ ሆይ፡ አንተ ታያቸዋለህና ዝም አትበል…
በጣም ብዙ የሆንት እህቶቻችን የወሊድ መከላከያውን እንደ ክረሜላ ነው የሚወስዱት፤ የሚያስጠነቅቃቸው፣ የሚመክራቸውና የሚያስተምራቸው አካል የለም፤ በጣም ነው የሚያሳዝነው።
ምግብንም በሚመለክት፤ እንደ ምሳሌ አድርጌ ቪዲዮ ውስጥ “በርገር” ቤቱን አቅርቤዋለሁ፦
ቦሌ መድኃኔ ዓለም ፊት ለፊት፤ መድኃኔ ዓለም እየተባለ የሚጠራው ህንፃ ሥር፡ በእንግሊዝኛው ይጠራል፡ “InN Out Burger“ የሚባል ትልቅና “ዘመናዊ/ፈረንጃዊ” የፈጣን ምግብ ቤት አለ። ዶሮና ድንች ጥብስ፣ በርገሮችና የመሳሰሉትን የፈረንጅ ምግቦች ነው የሚያቀርቡት። ባጠቃላይ፡ ቦሌና ሃያሁለት በመሳሰሉት አካባቢዎች ጣፋጩንና ጤነኛውን ኢትዮጵያኛ የእንጀራ ምግብ ማግኘት በጣም ከባድ ነው። የሚገኝ ከሆነ እንኳን ምግቡ ሁሉ በአደገኛው ዘንባባ ዘይት የተሠራ ነው።
አንን ቀን አመሻሽ ላይ፡ እስኪ ልቅመሰው ብዬ በረንዳው ላይ ቁጭ አልኩ፤ የተቆራረጡ ዶሮዎችና (ሁሉ ነገር በእንግሊዝኛ ነው„Chicken Nuggets“ ብለውታል)የድንች ጥብሶች አቀረቡልኝ። ለመግለጽ ያዳግተኛል፤ አንዷን ቁራጭ ዶሮና ድንቹን እንደቀመስኩ በጣም አጥወለወልኝ፣ አፈር አፈር ይላል ብል አፈርን መስደብ ይሆንብኝል፤ አፈር የተሻለ ይጣፍጣል፡ የበለጠም ጥቅም ይኖረዋል፤ ይህ ግን ዶሮውም ድንቹም፡ ከፈርንጅ አገሩ እንኳን ሲነጻጸር በጣም የተለየ ነው።
አሳላፊውን ጠርቼ ይቅርታ ስለምቸኩል አልጨረስኩትም ብዬ ሂሳቤን ከከፈልኩ በኋላ ወርጄ ሄድኩ። ምነው ብለው ደነገጡ። ትንሽም ሄደት እንዳልኩ፤ አንዲት ወጣት እህታችን መንገድ ዳር ቁጭ ብላና ጨቅላዋን አቅፋ ትለምናለች…..ኩምሽሽ ብዬ አብሪያት ቁጭ አልኩ…እዚያ ሬስቶራንት ለዚያ ምግብ 95 ብር ነበር የከፈልኩት…ሬስቶራንቱ ውስጥ እስከ መቶ የሚጠጉ ወጣቶች እየተጯጯሁ ይመገባሉ፤ በብዙ ብር የሚገመት ምግብ ያዛሉ… በሽተኞች የሚያደርጋቸውን/ የሚያደርገንን ምግብ ይወስዳሉ/ እንወስዳለን…እዚህ ደግሞ እህታችን፡ ልክ እንደ ማርያም ልጇን አቅፋ፡ ትለምናለች….. ያው እስካሁን ልረሳው የማልችለው ገጠመኝ ነው፣ ልክ እንደ ኃይለኛ ነገር ሆኖ ነው የሚትየኝ።
እዚያ ምግብ ቤት እንዲሁ ለመታዘብ አልፎ አልፎ አለፍ እያልኩ ወደ ውስጥ አይ ነበር። ሁሌ ሙሉ ነበር። አንድ ሌላ የታዘብኩት ነገር ቢኖር፦ ባካባቢው የሚገኙት ብዙ ፈረንጆች ወደ እዚህ ቤት ገብተው ሲመገቡ አለማየቴ ነው። እ…ለምን ይሆን? የሚያውቁት ነገር ይኖር ይሆን? ለነገሩማ ለእነርሱ የት፣ ምን መብላት እንዳለባቸው ብዙ ጊዜ አስቀድሞ ባገራቸው/በኢንባሲዎቻቸው በኩል ይነገራቸው የለ!?
ዔዶማውያኑ እና እስማኤላውያኑ የሳጥናኤል ልጆች በተገኘው ቀዳዳ ሁሉ ነው እየገቡብን ያሉት፣ ዓይናችን እያየ ጆሮአችን እየሰማ ዲያብሎሳዊ ድርጊታቸውን በፈርኦናዊ ትዕቢትና ድፍረት በመፈጸም ላይ ናቸው። በተለይ አሁን ትኩረቱን ያደረጉት የሕብረተሰባችን ምሶሶዎች በሆኑት ሴቶቻችን እና ህፃናቶቻን ላይ ነው፤ በቅርቡ ደግሞ የወንዱን ዘር ለማድከም የተለያዮ ኬሚካሎችን፣ ጀርሞችንና ባክቴሪያዎችን እያዘጋጁልን ነው። ይህን እያንዳንዳችን ያልቸልተኝነት ልናውቅና ልናሳውቅ ግዴታ አለብን።
ለእህቶቻችን ውፍረት፦
መንስዔ ፩
ዲያብሎሳዊ ምግብና መጠጥ
ይህ ምግብ ፈረንጁ አገር “ጃንክ/ቆሻሻ” ምግብ ይባላል፤ የሚመገቡትም፤ ብዙ ያልተማሩና ድኾች የሚባሉት ናቸው።
በአዲስ አበባችን ደግሞ፣ ተምሯል፣ ያውቃል፣ ኃብታም ነው የሚባለው ነው በፈቃዱ ይህን ቆሻሻ የሚበላው።
+ የሚረጋ የዘንባባ(ፓልም)ዘይት(በውስጡ ፓልሚክ አሲድ የተባለ አደገኛ ኬሚካል የያዘ ነው)
+ ኦርጋኖፓስፌት በተባለ መርዝ የተቀቀለ የእርዳታ(አሜሪካ)ስንዴ
+ የፈረንጅ በርገር እና ጥብሳጥብስ
+ የ ”ፈረንጅ” ዶሮና እንቁላል
+ የ “ፈረንጅ” ወተትና እርጎ
+ ሚሪንዳና ኮካኮላ
+ የአረብ ዱቄቶች
+ የቱርክና ፓኪስታን ስኳር
+ ኤታኖል የተሽከራሪ ነዳጅ
መንስዔ ፪
ዲያብሎሳዊ የወሊድ መከላከያዎች
+ ውርጃ
+ እንክብሎች
+ ክትባቶች
+ ቅባቶች
መንስዔ ፫
ዲያብሎሳዊ የማሕበረሰብ ግኑኝነት መርዞች
+ በየጎረቤቱ ምግብና ውሃ ውስጥ የሚቀላቀሉ የአረብ ቅመሞች፣ ሽታዎች(መርዝ ጂሃድ)
+ በጎረቤት እንስሶች ላይ የሚካሄድ ጭካኔ፤ በተለይ በውሻ ላይ
+ በየትምህርት ቤቱ በህፃናት የምሳ እቃ ውስጥ በድብቅ የሚጨመሩ ጠብታዎች(መርዝ ጂሃድ)
+ የቱርክ የ”ፍቅር” ድራማዎች (የፍቅር ጂሃድ)
መዝሙረ ዳዊት ምዕራፍ ፹፫:
፩ አቤቱ፥ እንደ አንተ ማን ነው? አቤቱ፥ ዝም አትበል፥ ቸልም አትበል።
፪ እነሆ፥ ጠላቶችህ ጮኽዋልና፥ የሚጠሉህም ራሳቸውን አንሥተዋልና።
፫ ሕዝብህን በምክር ሸነገሉአቸው፥ በቅዱሳንህም ላይ ተማከሩ።
፬ ኑ ከሕዝብ እናጥፋቸው፥ ደግሞም የእስራኤል ስም አይታሰብ አሉ።
፭ አንድ ሆነው በአንተ ላይ ተማከሩ፤ በአንተ ላይ ቃል ኪዳን አደረጉ፤
፮ የኤዶማውያን ድንኳኖች እስማኤላውያንም፥ ሞዓብም አጋራውያንም፥
፯ ጌባል አሞንም አማሌቅም፥ ፍልስጥኤማውያንም ከጢሮስ ሰዎች ጋር፤
፰ አሦርም ከእነርሱ ጋር ተባበረ፥ ለሎጥ ልጆችም ረዳት ሆኑአቸው።