Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • June 2023
    M T W T F S S
     1234
    567891011
    12131415161718
    19202122232425
    2627282930  
  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

Posts Tagged ‘እንባ’

ተዓምር ነው! የደም እምባ በአሜሪካ ሰማይ

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on May 2, 2022

👉 ገብርኤል 👉 ማርያም 👉 ኡራኤል 👉 ጊዮርጊስ 😇 ተክለ ሐይማኖት 👉 ዮሴፍ 👉 መድኃኔ ዓለም

❖❖❖[የሉቃስ ወንጌል ምዕራፍ ፳፩፥፳፭፡፳፰]❖❖❖

በፀሐይና በጨረቃም በከዋክብትም ምልክት ይሆናል፤ በምድር ላይም አሕዛብ ከባሕሩና ከሞገዱም ድምፅ የተነሣ እያመነቱ ይጨነቃሉ፤ ሰዎችም ከፍርሃትና በዓለም የሚመጣበትን ከመጠበቅ የተነሣ ይደክማሉ፤ የሰማያት ኃይላት ይናወጣሉና። በዚያን ጊዜም የሰው ልጅ በኃይልና በብዙ ክብር በደመና ሲመጣ ያዩታል። ይህም ሊሆን ሲጀምር ቤዛችሁ ቀርቦአልና አሻቅባችሁ ራሳችሁን አንሡ።”

🛑 ከሳምንታት በፊት በኢትዮጵያ ሰማይ የታየችውን በማርያም መቀነት አክሊል የተከበብችውን ፀሐይ እናስታውሳለን?

  • ክሊቭላንድ ሚሲሲፒ፤ ፳፪/22ሚያዝያ ፪ሺ፲፬ ዓ.ም ፥ የቅዱስ ኡራኤል ዕለት
  • አሪዞና፤ ፳፫/23 ሚያዝያ ፪ሺ፲፬ ዓ.ም ፥ የቅዱስ ጊዮርጊስ ዕለት

🛑 አሜሪካ፤ በቃ! አረመኔውን ወኪልሽን ግራኝን ከሥልጣን አስወግጂው!

👉 ከአክሱማዊቷ ኢትዮጵያ ላይ እጃችሁን አንሱ! ብለናል። 👈

______________

Posted in Curiosity, Ethiopia, Faith, War & Crisis | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

ሰሙነ ሕማማት – ረቡዕ ፤ የይሁዳ ክህደት፥ ምክረ አይሁድ፥ የዕንባ ቀን፥ የመልካም መዓዛ ቀን

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on April 28, 2021

ለምን የምክር ቀን ተባለ?

ምክንያቱም የአይሁድ ሊቃነ ካህናትና ጸሐፍት ጌታን እንዴት መያዝ እንደሚገባቸው ምክር ያጠናቀቁበት ቀን ነውና፡፡ በዚህ ምክራቸው ላይ በጣም ትልቅ ጭንቀት ነበር፡፡ ምክንያቱም ወቅቱ የፋሲካ በዓላቸውን የሚያከብሩበት ቀን የተቃረበ በመሆኑ፣ ብዙው ሕዝብም በጌታችን ትምህርት የተማረኩ፣ ተአምራቱንም የሚያደንቁ ስለ ነበር ሁከት እንዳይፈጠር ነው፡፡ በዚህ ጭንቀት ሳሉ ከደቀ መዛሙርቱ አንዱ የአስቆሮቱ ይሁዳ፣ በመካከላቸው በመገኘት የምክራቸው ተባባሪ ሆኖ ጭንቀታቸውን አስወግዶላቸዋል፡፡ [ማቴ. ፳፮፥፩፡፲፬ ፣ ማር. ፲፬፥፩፡፪ ቁ ፲.፲፩፣ ሉቃ. ፳፪፥ ፩፡፮]

የመልካም መዓዛ ቀንም ይባላል

ምክንያቱም ጌታችን በዚህ ዕለት በቤተ ስምዖን ዘለምጽ ተቀምጦ ሳለ፣ መላ ሕይወቷን ለዝሙት አስገዝታ ትኖር የነበረችው ማርያም እንተ እፍረት፣ /ባለሽቱዋ ማርያም/፤ “ከእንግዲህ ወዲህ በኃጢአት ተበላሽቶ ይኖር የነበረውን ሕይወቴን እንደዚህ መልካም ሽቱ የሚያጣፍጥ፣ ኃጢአትን ይቅር የሚል አምላክ መጣ” ስትል ዋጋው እጅግ በጣም ውድ የሆነ፣ ከሦስት መቶ ዲናር በላይ የሚያወጣ፣ በአልባስጥሮስ ብልቃጥ የተሞላ ሽቱ ይዛ በመሔድ በጠጉሩ /በራሱ/ ላይ በማርከፍከፍ ስለቀባችው ነው ረቡዕ የመዓዛ ቀን የተባለው፡፡

የእንባ ቀንም ይባላል

ይህም ይህቸው ሴት በጌታችን እግር ላይ ተደፍታ፣ መላ ኃጢአቷን ይቅር እንዲላት በዕንባዋ እግሩን አጥባዋለችና፣ በጠጉሯም በእንባዋ ያጠበችውን እግሩን አብሳዋለችና፡፡ [ማቴ.፳፮፥፮፡፲፫ ፣ ማር.፲፬፥፫፡፱፣ ዮሐ.፲፪፥፩፡፰] ከዚህ ልንማር የሚገባው ነገር አለ፤ ይኸውም የራስን ኃጢአት በማሰብ ማልቀስና የተወደደ መሥዋዕት አድርጐ ለእግዚአብሔር ማቅረብን ነው፡፡ የማርያም እንተ ዕፍረትን ኃጢአት ይቅር ብሎ መብዓዋን የተቀበለ አምላክ ዛሬም በመካከላችን አለና፡፡

የአስቆሮቱ ይሁዳ ጌታችንን አሳልፎ ሰጠው። ምህሩንና ጌታውን ክዶ፣ ስሞ ለግርፋት እና ለመስቀል ሞት ተስማማ። ይህንን የጌታን ሕማማት፣ ስቅላት፣ ሞትና ትንሣኤ በምናስብበት በአሁኑ ወቅት የትግራይ ሕዝብ ለሕማም፣ ለስቅላት እና ለሞት አሳልፎ ተስጥቷል። ይሁዳ ለ፴/30 ዲናር ጌታችንን አሳልፎ ሰጠው፤ ከዚያም ዲናሩን መልሶ እራሱን አጠፋ። የዘመናችን ሰቃልያን የሆኑት ኦሮማራዎቹ የዋቄዮ-አላህ ጭፍሮች ደግሞ “አክሱም ጽዮን ለብዙ ሺህ ዓመታት ያፈራችውን እውቀት፣ ስልጣኔና ሀብት በሙሉ ለመዝረፍ፣ አሳልፎ ለመስጠትና ለማውደም ጊዜው አሁን ነው” ብለው የዓለማችን ፈላጭ ቆራጮች ከሆኑት አህዛብ፣ መናፍቃንና ግብረ-ሰዶማውያን ጋር ተባበሩ። በዚህም በዚያም ትልቅ ክህደት እና ስቅለት። በተለይ ተዋሕዶ ክርስትናን የተቀብሉትና ማሕተብ ያጠለቁት አማራ ወገኖች ክህደት ታሪክ የማይረሳው ነው፤ ብዙ ዋጋም የሚያስከፍላቸውና ከሌሎቹ ሁሉ የከፋው ክህደት ነው። ከይሁዳ ይልቅ የጴጥሮስ ዓይነት ክህደት ያድርግላቸው።

የአስቆሮቱ ይሁዳ ክህደት + የቃኤል ቅናት = ☠️

አወቁትም አላወቁትም፤ ዛሬ በአማራዎችና ኦሮሞዎች ህብረት በትግራይ ሕዝብ ላይ እየተካሄደ ያለው ጂሃዳዊ የጭፍጨፋ ዘመቻ የመጨረሻው ግብ፤ ተዋሕዶ ክርስቲያኖች ትግራዋያንን ከአኩም ጽዮን አጽድቶ የሕይወት ዛፍ እና ጽላተ ሙሴ የሚገኙበትን ቅድስት ምድር ለተለከፉት ባዕዳውያኑ ውሾች ማስረከብ ነው። አዎ! ኢትዮጵያን/አክሱም ጽዮንን ለባዕዳውያኑ ሉሲፈራውያን ለማስረከብ በትግራይ ሕዝብ ላይ ጦርነት ከፈቱ። እስኪ እናስበው! ዋው!

በሰባዎቹ ዓመታት ሉሲፈራውያኑ ድርቅና ረሃብ ፈጥረው በዚህ አካባቢ የምዕራባውያኑ ኔቶ ሃገራት፤ በተለይ ብሪታኒያ፣ ጀርመን እና ፈረንሳይ ሰራዊቶቻቸውን በእርዳታ ስም አስፍረው እንደነበር እናስታውስ። ከዚያ በሰማኒያዎቹ እና በባድሜው ጦርነት የተባበሩት መንግስታት “ሰላም አስከባሪዎች” እንዲገቡ ተደርጎ ነበር። ዛሬም ዓለም የተራቡ የትግራይን ሕፃናት ምስሎች በበቂ እንድታይ ከተደረገች በኋላና የተረፉትንም ትግራይ ወገኖቼንም በስደት የተቀደሰችውን ምድር እየለቀቁ እንዲወጡ (የአውሮፓን እና አሜሪካን ድንበሮች ይከፍቱላቸዋል፤ ከጥቂት ከፍተኛ ቦታ ላይ ከሚገኙት የዓለማችን ቦታዎች በቀር አውሮፓና አሜሪካ ሌሎችም አኅጉራት ይጠፋሉ የሚል ድምዳሜ ላይ ደርሰዋል) ከተደረጉ በኋላ የምዕራባውያኑ ኔቶ ሠራዊቶች በትግራይ ይሰፍራሉ።

ገና ከአሥራ አምስት ዓመታት በፊት “ኔቶ በአፍጋኒስታን የሚገኘው ለኢትዮጵያ ለመለማመድ ነው፤ ተመሳሳይ የመልከዓ ምድር አቀማመጥ ስላላቸው…” በማለጥ ጽፌ ነበር። ምዕራባውያኑ እዚያ መስፈር ከጀመሩ በኋላ ቀስ በቀስ ዜጎቻቸውን ማስገባት ይጀምሩና በመጨረሻም “ኢትዮጵያውያኑም ተዋሕዶ ክርስቲያኖቹም እኛ ነን” በማለት እያታለሉና ደማቸውን እያፈሰሱ ለብዙ ሺህ ዓመታት ጠብቀውት የነበረውን ብኩርናቸውን በምስር ወጥ እንዲሸጡ ብሎም የመንፈስ ማንነታቸውንና ምንነታቸውን እየተነጠቁ “ኢትዮጵያዊነትንና ተዋሕዶ ክርስትናን” ቀስበቀስ እንዲከዱ ይደረጓቸውን “የቀድሞ ኢትዮጵያውያን” “አናስገባም!” ብለው ከኢትዮጵያ ድንብር ይመልሷቸዋል። ይህ ትንቢት ሳይሆን የሉሲፈራውያኑ ግልጽ የሆነ ተልዕኮ ነው። እግዚአብሔር ይህን ተልዕኳቸውን እንደሚያጨናግፈው አልጠራጠረም፤ ነገር ግን በኢትዮጵያውያኑ ደንቆሮነት፣ ስንፍና እና እንደ ግራኝ ያሉትን የውስጥ ጠላታቸውን በሰዓቱ ለማስወገድ ባለመድፈራቸው ብሎም አክሱም ጽዮንን ለመከላከል ባለመሻታቸው ብዙ መስዋዕት ይከፍሉ ዘንድ ግድ ይሆናል። በተለይ ከሃዲዎቹ ኦሮማራዎች!

የተከዱትንና የተገፉትን የአክሱም ጽዮን ልጆችን፤ በፈተና፣ በመከራ፣ በድካምና በስቃይ ላይ ያሉትን ወገኖቻችንን ሁሉ ያለ ደዌና ያለ ከፋ ሕማም ለክርስቶስ ትንሣኤ ያድርሰልን ፤ ቀናተኞችና አረመኔዎች የሆኑትን እርጉም ጠላቶቻቸውን/ጠላቶቻችንን ሁሉ በቶሎ ያንበርክክልን!!! አሜን።

____________________________________

Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

አቡነ ማትያስ ያኔ ለኦሮሚያ ሲዖል ሰማዕታት እንባቸውን አነቡ ፥ ምነው ዛሬ ስለ አክሱም ጽዮን ዝም አሉ?

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on March 22, 2021

ልጆቼ፥ እንባዬን እያፈሰስኩ ስለ እናንተ ስቃይ አምላካችንን በጸሎት እየጠየቅኩ ነውአቡነ ማቲያስ ከዓመት ተኩል በፊት

በኦሮሚያ ሲዖል ከዓመት ተኩል በፊት በተዋሕዶ ልጆች ላይ ከተደረገው አሰቃቂ ጭፍጨፋ በኋላ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት የሚከተለውን መልዕክት ከሃዘንና እንባ ጋር አስተላልፈው ነበር።

ልጆቼ እኔ የሃይማኖት አባት ነኝ። እኔ የእናንተ ጠባቂ ነኝ።ይሁንና ከመታረድ ልታደጋችሁ አልቻልኩም።ከሞት ላድናችሁ አልቻልኩም። እኔ የጦር መሪ አይደለሁም።ገዳዮቻችሁን ለፍርድ ለማቅረብ አቅሙ ዬለኝም። በእጄ ሽጉጥ ሳይሆን መስቀል ነው የምይዘው። ልጆቼ እንባዬን እያፈሰስኩ ስለ እናንተ ስቃይ አምላካችንን በጽሎቴ እየጠየኩ ነው። መንግስትንም ዘውትር እየተማጸንኩኝ ነው። ዛሬ ሆድ ብሶኛል።አልቅስ አልቅስ ልክ እንደ ህፃን ይለኛል። ልቤ በሐዘን ተኮማትሯል። እንቅልፍ በአይኔ ጠፍቶ እንባ ብቻ ሆኗል።ከዛሬ ነገ ይሻላል እያልን መንግስትንም እንዲያስቆም ብንጠይቅ ምንም ያየነው ለውጥ የለም። ይልቅስ ልጆቼን አስጨረስኩ።ሰላም ሰላም እያልኩ እናንተን ሳስተምር ሰላምን ማያውቁ ሰላም ነሷችሁ።ልጆቼ አትቀየሙኝ።ዝም ያልኳችሁ እንዳይመስላችሁ።ሁሌም ስለ እናንተ እንዳለቀስኩ ነው።ጌታ ሆይ ፍረድ ወይም ውረድ።በቁሜ የልጆቼን ሰቆቃ ከምታሳዬኝ ሞቴን አቅርብልኝ።ልጆቼ ላይ የሚፈጸመውን ልከላከልላቸው አልቻልኩም። አንተው ተመልክተህ ፍርድ ስጥ!”

ታዲያ ይህን መልዕክት ከሦስት ሣምንታት በፊት የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ የ፰ተኛ ዓመት በዓለ ሲመት አከባበር ላይ ካስተላለፉት መልዕክት ጋርና በምን ዓይነት መልክ እንዳስተላለፉት እናነጻጽረው። “ለቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ” ሆነው ሳለ የአክሱም ጽዮንን ጭፍጨፋ ሊያነሱ እንኳን ያልቻሉበት/ያልፈለጉበት ሁኔታ በጣም አሳዝኖኛል። ተሳስቼ ከሆነ ይቅርታ እጠይቃለሁ፤ ግን የግራኝ አብዮት አህመድ አማካሪ ጋንኤል ውርደት ጽፎ የሰጣቸውን ጽሁፍ ያነበቡ ሆኖ ነው የተሰማኝ፤ “ጸሎትና ምሕላ ከማድረግና ገንዘብ ከመስጠት በቀር በኢትዮጵያ እየተካሄደ ስላለው የእርስበርስ ግጭት ምንም ማድረግ አንችልም” ሲሉ፤ ልክ ወንጀለኛው ግራኝ አህመድ አሊ“ከመደመር መጽሐፌ ሽያጭ የወር ደሞዜን አክየበት ለትግራይ ሕዝብ እሰጣለሁ” ያለውን እንዳስታውስ ነው ያረገኝ። ያውም እርሱ በጠላትነትም ቢሆን የሚጨፈጭፋትን የትግራይን ስም ጠርቷል፤ አቡነ ማትያስ ግን ላለፉት አራት ወራት፤ በሁሉም አጋጣሚዎች የትግራይን ስም ሊያነሱ እንኳን አልፈለጉም፤ ምክኒያታቸው ምን ይሆን?

ምናልባት ልክ እንደተቀረው የትግራይ ሕዝብ ለራሱ የአክሱም ጽዮን ሕዝብ በይበልጥ ከመቆርቆር ይልቅ በይሉኝታ ለተቀረው በጠላትነት ለቆመበት ሕዝብ በይበልጥ ተቆርቁረው ይሆን? ህወሃቶች ለምሳሌ ባለፉት ፳፯/27 ዓመታት እና ከዚያም በላይ ለትግራይ ሕዝብ ከዋሉት ውለታ ይቅር፤ በኅልማቸው እንኳን ያላለሟትን ግማሽ ኢትዮጵያን እስከማስረከብ ድረስ ለኦሮሞዎች የዋሉት ውለታ እጅግ በጣም ትልቅ ነው። ዛሬም እንኳን የደቡብ ሕዝቦችን፣ ሶማሌዎችን፣ ቤን አሚሮችን፣ ራሻይዳዎችን፣ አማራዎችንና አረቦችን አስተባብረው በመምራት በትግራይ ሕዝብ ላይ፣ በአክሱም ጽዮን ላይ፣ በምዕመናኑ እና ካህናቱ ላይ በጣም ከፍተኛ የሆነ ግፍ እየሠሩ ያሉት ኦሮሞዎች ሆነው እያሉ፤ ህወሃቶች ክደዋቸው ከአዲስ አበባ ካባረሯቸው ኦሮሞዎች ጎን ተሰልፈው ይታያሉ። ግራኝ አብዮት አህመድ እንኳን “ለሕዝባችሁ” ብሎ ሰሞኑን ሲሳለቅ የነበረው “እኔ ለኦሮሞ ሕዝብ ስልና እንዳይጎዳ ስላሰብኩለት ነው ጦረንቱን ወደ ሰሜን ያዞርኩት፤ ለሕዝቤ ስል እስከ ሰማዕትነት ለመድረስ ዝግጁ ነኝ።” ለማለት ነው። ይህ የዲያብሎስ ጭፍራ ክልጅነቱ ጀምሮ ወደ ትግራይ በመግባት ሲሰልልና ሲያጠና ቆይቷል። ይህ እጅግ በጣም የሚያሳዝንና የሚያሳፍር ጉዳይ ነው፤ ዓይናቸው እያየ አልማር ባዮች፣ ተምልሶ ተመላልሶ ወደ ጭቃ! ምናልባት የማናውቀው የእነ ጌታቸው ረዳ “የራያ” ምስጢር አለ?!

ምንም እንኳን አፄ ዮሐንስም ብሔር ሳይለዩ ዛሬ ሱዳኖች በሚያሸቷት በመተማ ለአማራዎች አንገታቸውን ቢሰጡም፤ ዛሬ ግን ቢኖሩ ኖሮ ለትግራይ ሕዝብ ሲሉ አስመራን፣ ጂቡቲን፣ ካርቱምን፣ ሞቃዲሾን፣ ጁባንና ኤደንን ከሃያ ዓመታት በፊት ተቆጣጠረው ታላቂቷንና ኃያሏን ኢትዮጵያ መመሥረት በቻሉ ነበር። አፄ ዮሐንስ ናፈቁኝ፤ ለትግራይ ሕዝብ ዳግማዊ አፄ ዮሐንስን ቶሎ ያስነሳለት። አሜን!

እንደ እኔ ከሆነ አቡነ ማትያስ የፓትርያርክነታቸውን ዘውድ እንደ ሮማው ጳጳስ ቤነዲክት፲፮ኛ/Benedict XVI (በእሳቸውም ዙሪያ ጫና የሚያደርጉባቸው የካቶሊክ ጳጳሳት ነበሩ) አስረክበው ገዳም ይገቡ ዘንድ እመኝላቸዋለሁ። አረመኔው ግራኝ አብዮት አህመድ አሊ ባፋጣኝ እስካልተደፋ ድረስ አቡነ ማትያስን አስወግዶ ወይ ኤሬቻ በላይን ወይ አቡነ ናትናኤልን ፓትርያርክ አድርጎ ለመሾም አመቺ የሆነውን ወቅት እየጠበቀ ነው። በዲያብሎስ እንጂ በእግዚአብሔር ላልተቀባው ለአረመኔው ግራኝ አብዮት አህመድ አሊ፤ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ለሌላው ነገር ሁሉ አስቀድመው፤ “አንተ የዲያብሎስ ጭፍራ፤ ጦርነቱንና ጭፍጨፋውን ባፋጣኝ አቁም፣ ስልጣኑንም አስረክበህ ለምድራዊ ፍርድ ቅረብ፤ በሰማይ ቤት ተፈርዶብሃል!” ሊሉት ይገባል።

________________________________

Posted in Ethiopia, Faith, Life | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

ይገርማል! | የተዋሕዶ ልጆች በሊብያ እና በናዝሬት በአንድ ዕለት ነው የተሰዉት | በትንሣኤ

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on April 26, 2020

+አንድ ማሳሰቢያ!+

የአውሬውን የ”Copyright” ጨዋታ መብት በመጠቀም ይህን ቻነል ለማዘጋት እየሠሩ ያሉ “ተዋሕዶ ነን” የሚሉ ዩቱበሮች፦

👉 ቻነል ፦ “Lule Quanquayenesh (ሉሌ ቋንቋዬ ነሽ)”

👉 Content removed by Lule Quanquayenesh (ሉሌ ቋንቋዬ ነሽ)

👉 ቪዲዮዎች፦

+ “ኢትዮጵያ ማለት ቤተክርስቲያን ናት ፤ እየታረዱላት ያሉትም የተዋሕዶ ልጆች ናቸው”

+ “የሰይጣን ምልክት 666 ነው ፥ የክርስቶስ የሆኑት ደግሞ ባንገታቸው ላይ ያለው ማሕተብ ነው”

👉 ቻነል Semayat/ ሰማያት

👉 ቪዲዮ፦ + “በዶክተሮች ሊፈታ የማይችለው ወረርሽኝ በጻድቁ ማእጠንት ይታጠናል | የማእጠንት ፀሎት በአሜሪካ”

Content removed by Semayat የደብረ ከርቤ ቅድስት ማርያም ወአቡነ ሀብተማርያም የማእጠንት ፀሎት በተወሰኑ የቨርጂንያ መንደሮችና

እንግዲህ እነዚህ ዩቱበሮች አውሬው ተነካባቸው መሰለን በምናቀርበው ነገር የተደሰቱ ሆነው አላገኘናቸውም። መልስ እንዲሰጡን ጊዜ ሰጥተናቸው ነበር።

ማንም የሜዲያ ሰው ነኝ ማለት በሚችልበትና መላው የሰው ልጅ በወረርሽኝ ጉዳይ በተጠመደበትና በተገኘው አጋጣሚ ሁሉ ወገን መቀራረብና መፈቃቀር በሚኖርበት በዚህ የጭንቀት ዘመን ነጋዴ እንጅ አንድ “ክርስቲያን ነኝ” የሚል አካል በጭራሽ “Copyright“ የተባለውን ዝባዝንኬ እንደ መሀመዳውያኑ መጠቀም የለበትም። በተለይ በፋሲካ ሰሞን፤ ያውም “ሰለጠነች” በምትባለዋ አሜሪካ እየኖሩ። የኛን ቪዲዮዎች ማንም መጠቀም ይችላል፤ እንዳውም ደስ ይለናል!

ልብ ብላችሁ ከሆነ እንደ ውቂያኖስ ሰፊ በሆነ የዩቱብ ቪዲዮዎች ዓለም “Copyright“ን በብዛት የሚጠቀሙት ኢትዮጵያዊ ነን” የሚሉ ዩቱበሮች ናቸው። ታዲያ ይህ የስግብግብነት፣ የምቀኝነት፣ የክፋትና የጠላትነት መገለጫ አይደለምን? 21ኛው ክፍለ ዘመን ፤ ምናልባትም ኢንተርኔት የሚባል ነገር በቅርቡ እልም ብሎ ሊጠፋ በተዘጋጀበት ወቅት በራስህ ወገን ላይ ይህን መሰል እቃ እቃ ጨዋታ መጫወቱ አያሳዝንምን? ሰው እንዲማርበት ነው፤ ““ኮፒራይት” ከ666ቱ ምልክቶች አንዱ ነው፤ የአውሬው ባሪያ ከመሆን ለመዳን ከዩቱብና ጓደኞቹ ገንዘብ አትቀበሉ” ለማለት ነው።

ይህ ቀላል ነገር ነው፤ ዋናው እና ትልቁ ተል ዕኳችን አውሬውን መታገል ነው፤ ሕዝባችንን የሚያሰቃይብንን፣ ሕፃናቱን የሚገድልብንን፣ ካህናትን የሚያስርና የሚገድልብንን፣ እናቶችን የሚያፈናቅልብንን የአውሬ ሥርዓት ማጋለጥ ነው፤ የተሰውትን ሰማዕታት ወገኖቻችንን ማስታወስ ነው።

ለማንኛውም ሌላው ቻነላችን እዚህ ይገኛል፦

+++ዘመነ ኢትዮጵያ+++

ከምስጋና ጋር

___________________________________

Posted in Curiosity, Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

የክፉ ትንቢት መፈጸሚያዎቹ ግራኝ አብዮት እና ኢሳያስ አፈቆርኪ ይህን ሲያዩ ምን ይሰማቸው ይሆን?

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on September 1, 2019

በጣም አሳዛኝ ነው፤ መከራቸው በዛ፡ ወገኖቼ ፥ ነፍሳቸውን ይማርላቸው!

[፪ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች ምዕራፍ ፬፥፲፯፡፲፰]

የማይታየውን እንጂ የሚታየውን ባንመለከት፥ ቀላል የሆነ የጊዜው መከራችን የክብርን የዘላለም ብዛት ከሁሉ መጠን ይልቅ ያደርግልናልና፤ የሚታየው የጊዜው ነውና፥ የማይታየው ግን የዘላለም ነው።

___________________

Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

ሰማዕታት ተዋህዶ በ ሊብያ | ፬ኛ አመት ሙት መታሰቢያ ሳምንት

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on April 22, 2019

ሚያዝያ ፲፩/ ፪ሺ፯ ዓ.ም – ከ፬ ዓመታት በፊት፡ ልክ በዚህ ዕለት ወንድሞቻችን ሰማዕትነትን የተቀበሉበት ቀን ነው።

የሰማዕታት ደም የቤተ ክርስቲያን ችግኝ ነው! በረከታቸው ይድረሰ!

ምነው ወንድሞቻችንን እረሳናቸው? ሌሎቹስ ይተውት፡ የራሳቸው ጉዳይ! ግን፡ ማህበራዊ ሜዲያዎች ምነው ፀጥ አልን? አራተኛ አመትን አስመልክቶ አንድም የቀረበ የመታሰቢያ ጽሑፍ ወይም ቪዲዮ እስካሁን አላየሁም፤ ለምን? ምን መጣብን? ግድየለሽነት ይሆን?

ከአራት ወራት በፊት “የሰላሳ አራቱ ተዋሕዶ ሰማዕታት መቃብር በሊቢያ ተገኘ” የሚለውን ቪዲዮ አቅርቤ ነበር፤ ነገር ግን ጉዳዩ የት ደረጃ ላይ እንደደረስ፣ ወይም የ፴፬ቱን ሰማዕታት አካላትን ወደ አገራቸው ለመመለስ ምን እየተሠራ እንደሆነ ለማወቅ በጣም ተቸግረናል። ከመንግስት ብዙ መጠበቅ የለብንም፤ እንዲያውም የግራኝ አህመድ መንግስት በዚህ ጉዳይ ላይ ቆሻሻ እጁን በጭራሽ ማስገባት የለበትም፤ አይመለከተውምና! ግን ቤተ ክህነት ምን እየሠራች ነው? በተለይ፡ በመካከለኛው ምስራቅ ይኖሩ የነበሩትና በዚህ ረገድ ልምዱም ያላቸው አቡነ ማቲያስ ይህን የቤት ሥራ የመሥራት ግዴታ አለባቸው እኮ! ምን እየሠሩ ነው እሳቸው? ኧረ ዝምታው አደነቆረን!

[ትንቢተ ሆሴዕ ምዕራፍ ፬፥፮]

ሕዝቤ እውቀት ከማጣቱ የተነሣ ጠፍቶአል፤ አንተም እውቀትን ጠልተሃልና እኔ ካህን እንዳትሆነኝ እጠላሃለሁ፤ የአምላክህንም ሕግ ረስተሃልና እኔ ደግሞ ልጆችህን እረሳለሁ።

[የዮሐንስ ራእይ ምዕራፍ ፮፡]

አምስተኛውንም ማኅተም በፈታ ጊዜ፥ ስለ እግዚአብሔር ቃልና ስለ ጠበቁት ምስክር የታረዱትን የሰዎች ነፍሳት ከመሠዊያ በታች አየሁ

በታላቅ ድምፅም እየጮኹ። ቅዱስና እውነተኛ ጌታ ሆይ፥ እስከ መቼ ድረስ አትፈርድም ደማችንንስ በምድር በሚኖሩት ላይ እስከ መቼ አትበቀልም? አሉ

፲፩ ለእያንዳንዳቸውም ነጭ ልብስ ተሰጣቸው፥ እንደ እነርሱም ደግሞ ይገደሉ ዘንድ ያላቸው የባሪያዎች ባልንጀራዎቻቸውና የወንድሞቻቸው ቍጥር እስኪፈጸም ድረስ፥ ገና ጥቂት ዘመን እንዲያርፉ ተባለላቸው

_____________________

Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

 
%d bloggers like this: