ይህ ግሩም ትንቢት–አዘል ትምህርት የቀረበው ከሦስት ዓመታት በፊት ነበር። በወቅቱ በሌላኛው ቻነሌ አቅርቤው ነበር። ከግማሽ ሚሊየን በላይ ክሊክ አግኝቶ ነበር። እግዚአብሔር ይይላቸውና በተዋሕዷውያን ዘንድ ተወዳጅ የነበረውን ቻኔሌን የግራኝ አብይ አህመድ ደጋፊዎች የሆኑት “ተዋሕዶ ነን” የሚሉ ግን እንደሚመስለኝ “የተሀድሶ” የሆኑት ቻነሎች አዘግተውብኛል (“Semayat/ ሰማያት” + “ሉሌ ቋንቋየ ነሽ” የተባሉት)። የተዋሕዶ ልጆች፤ ተጠንቀቁ! የበግ ለመድ ከለበሱት ይሰውራችሁ!
በሃገራችን እየሆነ ያለው ሁሉ ይህ ነው!
👉 ከሦስት ዓመታት በፊት የሚከተለውን በጦማሬ ጽፌ ነበር፦
“የኢትዮጵያችን ውድቀት የተጀመረው ከ 1500 ዓመታት በፊት፤ ሮማውያኑ ወኪሎቻቸው የሆኑትን እነ መሀመድ እና ተከታዮቹን ወደ ኢትዮጵያ ልከው ነገሥታቶቻችን ካታለሉበት ጊዜ ጀምሮ ነበር። ባለፉት 100 ዓመታትም ቢሆን፣ በነገሥታቶቻችን ላይ የምዕራባውያኑ እና የአረቦቹ ተጽእኖ በደንብ ይታይባቸው ነበር። የነግሥታቶቻችን አማካሪ ማጣትና መታለል ባለፉት 40 ዓመታት ኢ–አማኒያዊ እና እስላማዊ ለሆነው የመከፋፈያ መንገድ በሩን ከፍቷል። ላለፉት 40 ዓመታት ዓለማዊ ኢ–አማንያንና ሙስሊሞች ኢትዮጵያን ያስተዳድሯታል ብል የተሳሳትኩ አይመስለኝም።
በቅርቡ እንኳን፣ በስጋውያኑ ኤዶማውያ ምዕራባውያን እና እስማኤላውያን ልጆች ርኩስ ርዕዮተ ዓለማት የተታለሉት የአፄ ኃይለ ሥላሴ እና የክሎኔል መንግስቱ መስተዳደሮች(ልብ እንበል፡ መስተዳደር)ወሎን፣ ትግራይን እና ኤርትራን ለምዕራባውያኑ የዓየር–ጠባይ ቅየራ ቴክኖሎጁ በሩን በመክፈት ለአስቃቂ ድርቅና ረሃብ እንዲጋለጡ አደርገዋቸው ነበር። ልክ ይህን ድርጊት ከፈጸሙ በኋላ የኔቶ ሠራዊት በ”እርዳታ ሰጭነት” መልክ ወደ ሰሜን ኢትዮጵያ እንዲገባና ያዘጋጇቸውን የጊዜ ቦንቦችን በድብቅ እንዲቀብሩ አደረጉ። መንፈሳዊ ኢትዮጵያውያን የሆኑት የተዋሕዶ ልጆች በረሀብና በድርቅ ብዙ ተሰውተዋል። አፄ ሚኒልክ የምወዳቸው ድንቅ ንጉሥ ቢሆኑም፤ ነገር ግን በአባታቸው በኩል ያገኙትን መንፈሳዊ ማንነት በመርሳት ስጋዊ የሆነውን የእናታቸውን ማንነት በመውሰዳቸው ከባዕዳውያኑ ስጋውያን(ከጣልያንና ጀርመን)ጋር በመቀራረባቸው በሃገረ ኢትዮጵያ ከፍተኛ ድርቅና ረሃብ ተከስቶ ነበር። ምናልባት የመጀመሪያው፤ በጣልያኖች በኩል መርዛማ አጽዋትን ከውጭ አስመጥተው እንዲተከሉ በመፍቀዳቸው። በዚህም ድርቅና ረሃብ የተቀጠፉት መንፍሳውያኑ ኢትዮጵያውያን ነበሩ (የሰሚን ሸዋ፣ የቤተ አምሃራ እና የትግራይ ነዋሪዎች)። ይህም ለስጋውያኑ የጋላ ነገዶች ተከታታይ መስፋፋት አመቺ ሁኔታ ፈጥሯል።
ከታሪክ ለመማር ፈቃደኞች አይደለንምና ሰሜን ኢትዮጵያ ወይም ኤርትራ ከእናቷ እንደተቆረሰችም፣ የ ጠ/ምኒስትር መለስ ዜናዊ (ነፍሳቸውን ይማርላቸው!)እና ፕሬዚደንት ኢሳያስ አፈወርቂ ለምዕራባውያኑ እና ለአረቦቹ በገቡላቸው ቃል መሠረት፤ “ባድሜ የኛ ነው” በሚል ሰበብ በሚሊየን የሚቆጠሩ መንፈሳውያኑ ክርስቲያን ኢትዮጵያውያንን በድጋሚ ለመሰዋት በቅተዋል።
በሚቀጥለው የእብዶች ዙር ደግሞ እስካሁን በጦርነቱም ሆነ በረሃቡ ጉዳት ያልደረሰባቸውና ከሰሜኑ ጋር ሲወዳደር እምብዛም ደማቸው ያልፈሰሰውና “ተበድላችኋል!“ እየተባሉ፡ ልክ እንደ አረብ ፍልስጤሞች የተበዳይነት ካርድ እንዲጫወቱ የተደረጉትን ኦሮምኛ ተናጋሪ ኢትዮጵያውያን ወንድሞቻችንን ነው በመጠቀም ላይ ያሉት። ይህ ታዲያ በጣም አያሳዝንም? መቼ ነው የምንማረው? ያሰኛል። በመጽሐፍ ቅዱሳችን፡ እግዚአብሔር “ሕዝቤ እውቀት ከማጣት የተነሳ ጠፍቷል።” ያለዉ ይህን ለማናስተውል ህዝቦች መሆኑ ነው።
ባጭሩ፡ የጨካኞቹ ኤዶማውያን እና እስማኤላውያን መንፈስ አገራችን ከገባበት ጊዜ አንስቶ ባልሆነ ነገር እርስበርስ ለመከፋፈል ስለበቃን ሳንወድ በግድ ከጠላቶቻችን ጋር እንደንመሳጠር፣ ለእነርሱ የረጅም ጊዜ የጥፋት ሤራ እንድንጋለጥ ተደርገናል። እግዚአብሔር ከሌላ ደም መፋሰስ ይጠብቀን፡ ነገር ግን ከመጣም፤ ኢትዮጵያውነታቸውንና ክርስቶስን የካዱት እንዲሁም በኢትዮጵያ ላይ ሰይፋቸውን የመዘዙት ሁሉ ፍርክስክሳቸው ለመጨርሻ ጊዜ መሬት ውስጥ ተቀብሮ ይቀራል። በዚህ አንጠራጠር!”
👉[ወደ ገላትያ ሰዎች ምዕራፍ ፬፥]
- ፳፰ እኛም፥ ወንድሞች ሆይ፥ እንደ ይስሐቅ የተስፋ ቃል ልጆች ነን።
- ፳፱ ነገር ግን እንደ ሥጋ የተወለደው እንደ መንፈስ የተወለደውን በዚያን ጊዜ እንዳሳደደው ዛሬም እንዲሁ ነው።
- ፴ ነገር ግን መጽሐፍ ምን ይላል? የባሪያይቱ ልጅ ከጨዋይቱ ልጅ ጋር አይወርስምና ባሪያይቱን ከልጅዋ ጋር አውጣት።
- ፴፩ ስለዚህ፥ ወንድሞች ሆይ፥ የጨዋይቱ ልጆች ነን እንጂ የባሪያይቱ አይደለንም።