Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • June 2023
    M T W T F S S
     1234
    567891011
    12131415161718
    19202122232425
    2627282930  
  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

Posts Tagged ‘እርግብ’

የጰራቅሊጦስ ድንቅ ተዓምር፤ ሰክሬአለሁ፤ ቃላት የለኝም!

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on June 11, 2022

😇 አዎ! ጰራቅሊጦስ ሐዋርያትን የወይን ጠጅ ሳይጠጡ እንዳሰከራቸውና በሀገሩ ሁሉ እንዳናገራቸው እኔም በእነዚህ ቀናት የሰከርኩ መስሎ ነው የተሰማኝ፤ ክርስቶስንና ቤተሰቦቹን በተመለከት ከብዙዎች ጋር በመነጋገር ላይ ነኝ፤ ሰው ሁሉ በበጎ እየቀረበኝ ነው። በእውነት ድንቅ ነው! በእውነት ጰራቅሊጦስ የሃይማኖትን አልጫነት የሚያጣፍጥ የልቡና ጨው ነው። ጰራቅሊጦስ በጭለማ ላሉ የሚያበራ የይቅርታ ብርሃን ነው።

  • ወደ ጸሎት ቤት ስገባ
  • ጸሎት ቤት ውስጥ

😇 ቅድስት እናታችንና ልጇ እግዚአብሔር ወልድ + የማርያም መቀነት + ክቡር መስቀል

ከጸሎት ቤት ስወጣ፤ ማረፊያ ወንበሩ ላይ፤ ይህን አየሁት። የሕፃን ልጅ መጫወቻ ነው፤

እንጠንቀቅ! ቀስተ ደመና የሰዶማውያን አይደለም! “ኬኛ!” ብለው ሊነጥቁን ግን ይሻሉ!

  • ከጸሎት ቤት ልክ ስወጣ ሜዳው ላይ ሰባት እርግቦችን አገኘሁ
  • ማታ ላይ ቤቴ እንደገባሁ መብራቱ ይህን ሠርቶ ነበር።
  • ጠዋት ላይ ደግሞ የእመቤታችን ሥዕል የማርያም መቀነትን ቤቴ ግርግዳ ላይ አንጸባርቆ ይታይ ነበር፤ ድንቅ ነው!

❖❖❖ እምዕርገት እስከ ጰራቅሊጦስ መዝሙር “በሰንበት ዐርገ ሐመረ” ❖❖❖

(በ፫/) በሰንበት ዐርገ ሐመረ ገሠፀ ባሕረ፤ ወገሠፆሙ ለነፋሳት፤ ወይቤሎሙ ኢትናፍቁ ወኢይምጻእ ኑፋቄ ውስተ ልብክሙ፤ በከመ ፈነወኒ አቡየ አነኒ እፌንወክሙ ውስተ ቤተ አቡየ ብዙኅ ማኅደር ቦቱ፤ ካዕበ እመጽእ ወእነሥአክሙ፤ ከመ ተሀልዉ ምስሌየ በመንግሥተ አቡየ ዘበሰማያት።

አመላለሰ

ከመ ተሀልዉ ምስሌየ በመንግሥተ አቡየ፤

በመንግሥተ አቡየ ዘበሰማያት።

ዓራራት

ትንሣኤሁ ገብረ በሰንበት ወሰበረ ኆኃተ ብርት እግዚአ ለሰንበት አመ ሣልስት ዕለት ምዖ ለሞት ወዓርገ ውስተ ሰማያት።

ሰላም

ወልድ እኁየ ውእቱ ፍቁርየ ውእቱ ተንሥአ እሙታን ገብረ ሰላመ ለኵሉ ዓለም ዓርገ በስብሐት ውስተ ሰማያት ሎቱ ስብሐት ለዘቀደሳ ለሰንበት።

ዘቅዳሴ ምንባባት

  • ሮሜ ፲፥፩ ፡ ፍ፤
  • ፩ጴጥ ፫፥፲፭ ፡ ፍ፤
  • ግብ ፩፥፩ ፡ ፍ፤

ዘቅዳሴ ምስባክ፦

  • ዐርገ እግዚአብሔር በይባቤ፤
  • ወእግዚእነ በቃለ ቀርን፤
  • ዘምሩ ለአምላክነ ዘምሩ። መዝ ፵፮፥፭

ወንጌል፦ ሉቃ ፳፬፥፵፭ ፡ፍ

ቅዳሴ ዘዲዮስቆሮስ (እምቅድመ ዓለም)

❖❖❖ /7 እርግቦች ❖❖❖

  • ሐዋሪያት ተባበሩ
  • በአዲስ ቋንቋ እየተናገሩ
  • ቃሉን አስተማሩ

❖ ፯ / ሰባት ፍጹም ቁጥር ነው

በቅዱስ መጽሐፍ አቆጣጠር ሰባት (፯) ፍጹምና ሙሉ ቁጥር በመሆኑ ከአንድ እስከ ሰባት ( ፩–፯ ) የተዘረዘሩት ምስጢራተ ቤተክርስቲያንም እንከንና ጉድለት የሌለባቸው ፍጹማን ናቸው።
ሰባት ቁጥር በመጽሐፍ ቅዱስ ሥርዓት ፍጹም ለመሆን ለማወቅ ከዚህ የሚከተሉትን ማስረጃዎች እንመልከት፦

❖ ሰባት ቁጥር ምስጢራት በቤተክርስቲያን፤

በመጽሐፍ ቅዱስና በስርዓተ ቤተ-ክርስቲያን አስተምህሮ ስባት ቁጥር ብዙ ምሳሌ እንዳለው ይታወቃል፡፡ በዕብራዊያን ዘንድም ሰባት ፍጹም ቁጥር ነው፡፡ ምሳሌ ፳፬፡፲፮ እግዚአብሔር ከሰኞ
እስከ እሑድ ያሉትን ቀናት በሰባት ቁጥሮች ወስኗል ሕዝበ እስራኤል ከግብጽ ባርነት ወጥተው በሲና በርሀ ሲጓዙ ይመሩት የነበሩት በ፯/7 ደመና እንደነበረ ይታወቃል፡፡ ዘዳ ፲፫፡፳፩

ከዚህ ቀጥለንም ለቤተ-ክርስቲያን አስተምህሮ የ፯ ቁጥር ምስጢራትን ምሉዕነትን የሚያስረዱ ልዩ ልዩ ማስረጃዎችን በዝርዝር እንመለከታለን፦

❖ ሀ/ ሰባቱ አባቶች

፩. ሰማያዊ አባታችን እግዚአብሔር
፪. የነፍስ አባት
፫. ወላጅ አባት
፬. የክርስትና አባት
፭. የጡት አባት
፮. የቆብ አባት
፯. የቀለም አባት

❖ ለ/ ሰባቱ ዲያቆናት

፩. ቅዱስ እስጢፋኖስ
፪. ቅዱስ ፊልጶስ
፫. ቅዱስ ጵሮክሮስ
፬. ቅዱስ ጢሞና
፭. ቅዱስ ኒቃሮና
፮. ቅዱስ ጳርሜና
፯. ቅዱስ ኒቆላዎስ

❖ ሐ/ ሰባት የጌታ ቃላት /እኔ ነኝ

፩. የሕይወት እንጅራ እኔ ነኝ
፪. የዓለም ብርሃን እኔ ነኝ
፫. እኔ የበጎች በር ነኝ
፬. መልካም እረኛ እኔ ነኝ
፭. ትነሣዔና ሕይወት እኔ ነኝ
፮. እኔ መንገድና ሕይወት ነኝ
፯. እውነተኛ የወይን ግንድ እኔ ነኝ

❖ መ/ ሰባቱ ሰማያት

፩. ጽርሐ አርያም
፪. መንበረ መንግሥት
፫. ሰማይ ውዱድ
፬. ኢየሩሳሌም ሰማያዊት
፭. ኢዮር
፮. ራማ
፯. ኤረር

❖ ሠ/ ሰባቱ ሊቃነ መላእክት

፩. ቅዱስ ሚካኤል
፪. ቅዱስ ገብርኤል
፫. ቅዱስ ሩፋኤል
፬. ቅዱስ ራጉኤል
፭. ቅዱስ ዑራኤል
፮. ቅዱስ ፋኑኤል
፯. ቅዱስ ሳቁኤል

❖ ረ/ ሰባቱ አብያተ ክርስቲያናት

፩. የኤፌሶን ቤተ ክርስቲያን
፪. የሰርምኔስ ቤተ ክርስቲያን
፫. የጴርጋሞን ቤተ ክርስቲያን
፬. የትያጥሮስ ቤተ ክርስቲያን
፭. የሰርዴስ ቤተ ክርስቲያን
፮. የፊልድልፍያ ቤተ ክርስቲያን
፯. የሎዶቅያ ቤተ ክርስቲያን

❖ ሰ/ ሰባቱ ተዐምራት

ጌታ እኛን ለማዳን በመስቀል ላይ በተሰቀለ ጊዜ የተፈጸሙ ተዐምራት

፩. ፀሐይ ጨልሟል
፪. ጨረቃ ደም ሆነ
፫. ከዋክብት ረገፉ
፬. ዐለቶች ተሠነጠቁ
፭. መቃብራት ተከፈቱ
፮. ሙታን ተነሡ
፯. የቤተ መቅደስም መጋረጃ

❖ ሸ/ ሰባቱ የመስቀሉ ቃላት

፩. አምላኬ አምላኬ ለምን ተውከኝ
፪. አባት ሆይ የሚያደርጉትን አያውቁምና ይቅር በላቸው
፫. ዛሬ ከእኔ ጋራ በገነት ትሆናለህ
፬. እነሆ ልጅሸ እናትህ እነሆት
፭. ተጠማሁ
፮. ተፈጸመ
፯. አባት ሆይ ነፍሴን በእጅህ አደራ እስጥሃለሁ

❖ ቀ/ ሰባቱ ምሥጢራተ ቤተ ክርስቲያን

፩. ምሥጢረ ጥምቀት
፪. ምሥጢረ ሜሮን
፫. ምሥጢረ ቁርባን
፬. ምሥጢረ ክህነት
፭. ምሥጢረ ተክሊል
፮. ምሥጢረ ንስሐ
፯. ምሥጢረ ቀንዲል

❖ በ/ ሰባቱ ዐበይት አጽዋማት

፩. ዐቢይ ጾም
፪. የሐዋርያት ጾም
፫. የፍልሰታ ጾም
፬. ጾመ ነቢያት
፭. ጾመ ገሀድ
፮. ጾመ ነነዌ
፯. ጾመ ድኅነት

ተ/ ሰባቱ በእግዚአብሔር ዘንድ የተጠሉ ነገሮች

፩. ትዕቢተኛ ዓይን ምሳ ፲፮፥፮፡፲፱
፪. ሃሰተኛ ምላስ
፫. ንፁህን ደም የምታፈስ እጅ
፬. ክፉ ሃሳብን የምታፈልቅ ልብ
፭. ለክፋት የምትፈጥን እጅ
፮. የሐሰት ምስክርነት
፯. በወንድሞች መካከል ጠብን የምታፈራ ምላስ

❖ ቸ/ ሰባቱ ፀሎት ጊዜያት

፩. ነግህ የጠዋት ጸሎት
፪. ሠለስት (የ፫ ሰዓት ጸሎት)
፫. ቀትር (የ፮ ሰዓት ጸሎት)
፬. ተሰአቱ (የ፱ ሰዓት ጸሎት)
፭. ሰርክ (የ፲፩ ሰዓት ጸሎት)
፮. ነዋም (የመኝታ ጸሎት)
፯. መንፈቀ ሌሊት (የሌሊት ጸሎት)

______________

Posted in Ethiopia, Faith, War & Crisis | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

ብዙ ተዓምራትን የምናይባቸው ቀናት እየመጡ ነው | ተዘጋጁ! እንዘጋጅ!

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on November 23, 2021

💭 ይህን አስደናቂ ክስተት ዓምና ልክ በዚህ ወቅት ነበር ያቀረብኩት፤

❖❖❖ ዛሬ ያጋጠመኝን ነገር ሁሉ ለመግለጽ ቃላት የሉኝም!❖❖❖

👉 ፀሐይ 👉 ብርሃን 👉 የኢትዮጵያ ቀለማት 👉 መስቀል 👉 የኢትዮጵያ ካርታ 👉 እርግብ 👉 ግራር 👉 ገብስ 👉 እጣን

ቀለማቱን አስመልክቶ ከሳምንታት በፊት ካቀረብኩት ቪዲዮ ጋር የተያያዘ ነው።

👉 ❖❖❖የጸሎት ቤቴ መስኮት ብርሃን❖❖❖

ጽዮናውያኑ የሰንደቃችን ቀለማት

👉 ዛሬ ደግሞ መንገዱ ላይ ቀለማታችን

❖❖❖ክቡር መስቀሉን ሠርተውልናል❖❖❖

👉 ወደ ቤቴ ስመለስ መንገድ ላይ እርግቧ ሞታ አገኘኋት

❖❖❖ እየተጨፈጨፉ ያሉትን ወገኖቼን አስታወስኩ ❖❖❖

ግራር? አይደለም! ጽድ ነው።

👉 ቃሪያ (ቀለማታችን) እና ፍራፍሬ ገዝቼ ቤት ገባሁ፤

እጣን ማጨሻ አሉ ወረቀቱን እንዲሁ ስቦጭቀው

❖❖❖ የሰራልኝ ተዓምር ይህን ይመስላል❖❖❖

👉 ከዚያም የገብሱ ቡናየ ላይ ❖❖❖ሌላ ተዓምር❖❖❖

ኢትዮጵያ ሃገሬን አይተዋትም! ይብላኝ ጦርነት ለከፈቱባት ጠላቶቿ! ወዮላቸው!

+++ ባለፈው የጌታችን ስቅለት ዕለት (ይገርማል፤ በማግስቱ ነበር ምቀኛው አውሬ ያኛውን ቻነሌን ያዘጋብኝ) በሃገራችን ታይታ የነበረችውን የማርያም መቀነት እናስታውሳለን? በጊዜው የሚከተለውን ጽፌ ነበር፦

👉 “አውሬው ቤተክርስቲያንን ለጌታ ቍርባን ዘግቶ በ666የተከተቡትን ዶሮዎች እንድትገዙ ገበያዎችን ፈቀደ”

👉 እርግብ እና በግ ታሥረዋል

የቤተ ክርስቲያናችንን እንቅስቃሴ በደንብ ነው የሚከታተሉት፤ በዕለተ ስቅለት የተነሳው ቪዲዮ ላይ የሚታየውን ዓይነት ብርቱ የሆነ የእምነት ፍቅርና ጽናት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አማኞች ዘንድ ብቻ እንደሚታይ የአውሬው ዓለም እያየው ነው። እናት፣ አባት፣ ህፃናት ከጥዋት እስከ ማታ ለጌታቸው ሲሰግዱ፣ ካህናትና ቀሳውስትም ሌሊቱን ሙሉ ቆመው የሚቀጥለውንም ቀን ያለማቋረጥ በሥርዓተ ጸሎትና ቅዳሴ ሲያሳልፉ የሚታዩባት ብቸኛ ቤተ ክርስቲያን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ብቻ ናት። ለመሆኑ በፕሮቴስታንቶች በተለይም በእስላሞች ዘንድ ሕፃናት ወደ አምልኮ ቦታዎች ሲሄዱ አይታችሁ ታውቃላችሁን? እኔ አልገጠመኝም።

አውሬው በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን በጣም ይቀናል! ለዚህም ነው ልክ ፪ሺ፲፪/ 2012 ዓመተ ምሕረትን ጠብቆ፣ ልክ የሑዳዴ ጾም ሲገባ የኮሮና ቫይረስን ዓየር ላይ የለቀቀው። የአውሬው አምላኪዎች የሆኑት መሀመድውያንም ልክ ፋሲካ ሲገባደድ ረመዳናቸውን መጀመራችውም አውሬው ይህችን ዓመተ ምሕረት በጉጉት ሲጠብቅት እንደነበር ይጠቁመናል።

የአውሬው ተቀዳሚ ዓላማው ሕዝበ ክርስቲያኑን ከክርስቶስ ደም እና ስጋ እንዲሁም ከጥምቀት ማራቅ ነው። ይህንም በግልጽ እያየነው ነው። የተዋሕዶ ልጆች ስጋና ደሙን “በነጻ” እንዳይቀበሉ ቤተ ክርስቲያንን በሠራዊቱ አሳጠረ ፤ ፋሲካ ሲቃረብ ገበያዎቹን ከፍቶና የ”አበሻ” ዶሮዎችንና እንቁላሎችን አጥፍቶ በአውሬው መንፈስ የተበከሉትን የአላሙዲን ኤልፎራ ዶሮዎች ክርስቲያኑ ሺህ ብር እየከፈለ እንዲገዛና ለአውሬው የደም መስዋዕት እንዲያደርግለት ፣ እግረ መንገዱንም የዶሮውን ስጋና እንቁላል ተመግቦ በአጋንንት እንዲታሠር ያደርጋል። ይህ ግልጽ የሆነ የዲያብሎስ አካሄድ አይደለምን? በደንብ እንጅ!

_____________________

Posted in Curiosity, Ethiopia, Faith, War & Crisis | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

ጰ ፦ ብሂል ጰራቅሊጦስ መንፈሰ ጽድቅ ፥ ጰራቅሊጦስ እውነተኛ መንፈስ ቅዱስ ነው

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on June 20, 2021

❖❖❖ እንኳን ለበዓለ ጰራቅሊጦስ አደረሰን!❖❖❖

ጰራቅሊጦስ የሚለው ቃል ከሦስቱ አካላት አንዱ የኾነው የእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ መጠሪያ ስም ሲኾን፣ ትርጕሙም በጽርዕ (ግሪክ) ቋንቋ፦

❖ ናዛዚ (የሚናዝዝ)

❖ መጽንዒ (የሚያጸና)

❖ መስተፍሥሒ (የሚያስደስት) ማለት ነው።

መንፈስ ቅዱስ ለሐዋርያት በወረደበት ዕለት በቤተ ክርስቲያን የሚከበረው ይህ በዓል ‹በዓለ ጰራቅሊጦስ› ወይም ‹በዓለ ጰንጠቆስጤ› በመባል ይታወቃል። ‹ጰንጠቆስጤ› በግሪክ ቋንቋ በዓለ ኀምሳ፣ የፋሲካ ኀምሳኛ ዕለት፣ በዓለ ሠዊት (የእሸት፣ የመከር በዓል) ማለት ነው (ኪዳነ ወልድ ክፍሌ፣ ገጽ ፱፻፮-፱፻፯)።

ጌታችን አምላካችንና መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ካረገ በኋላ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም፣ ዐሥራ ሁለቱ ደቀ መዛሙርት፣ ሰባ ሁለቱ አርድእት፣ አምስት መቶው ባልንጀሮች እና ሠላሳ ስድስቱ ቅዱሳት አንስት በኢየሩሳሌም ከተማ በአንድነት ኾነው በጸሎት ይተጉ ነበር።

ጌታችን በሚያርግበት ጊዜ “እነሆ አባቴ የሰጠውን ተስፋ እኔ እልክላችኋለሁ፤ እናንተ ግን ከላይ ኃይል እስክትለብሱ ድረስ በኢየሩሳሌም ከተማ ቆዩ፤” ሲል ለሐዋርያቱ በሰጣቸው የተስፋ ቃል መሠረት በዐረገ በዐሥረኛው ቀን መንፈስ ቅዱስን ልኮላቸዋል (ሉቃ. ፳፬፥፵፱)። ዅሉም በአንድ ቦታ ተሰባስበው ሳሉ በበዓለ ጰራቅሊጦስ ማለዳ እንደ ዐውሎ ነፋስ ያለ ድምፅ ድንገት ከሰማይ ወርዶ የነበሩበትን ቤት ሞላው። ከዚያም የተከፋፈሉ የእሳት ላንቃዎች በዅሉም ላይ አረፉባቸው። በዚህ ጊዜ ዅላቸውም መንፈስ ቅዱስ ባደላቸው መጠን በየአገሩ ቋንቋዎች ዅሉ ተናገሩ (ሐዋ.፪፥፩-፬)።

ጌታችን መንፈስ ቅዱስን ለሐዋርያት የላከበት ይህ ዐቢይ በዓል ዐሥራቱን፣ በኵራቱን፣ ቀዳምያቱን ካህናተ ኦሪት ስለሚቀበሉበት በብሉይ ኪዳን በዓለ ሠዊት ተብሎ ይከበር ነበር። በሐዲስ ኪዳን ደግሞ ቅዱሳን ሐዋርያት መንፈስ ቅዱስን ስለ ተቀበሉበት በበዓለ ሠዊት ምትክ በዓለ ጰራቅሊጦስ ገብቶበታል። የበዓለ ትንሣኤ መነሻው የአይሁድ የፋሲካ በዓል ማለትም በግብጽ፣ እስራኤል ከሞት የዳኑበት የመታሰቢያ በዓል እንደ ኾነው ዅሉ፣ ለበዓለ ጰራቅሊጦስም መነሻው ይኸው የአይሁድ የፋሲካ በዓል ነው። የአይሁድ ፋሲካ ከተከበረ ከሰባት ሳምንታት በኋላ በኀምሳኛው ቀን የሩቆቹ ከከተሙበት ወጥተው፣ የቅርቦቹ ከተሰባሰቡበት ተገናኝተው ለበዓሉ ፍጻሜ የሚኾነውን በዓለ ሠዊት (የእሸት በዓል) ያከብሩ ነበር።

ሐዋርያት በጽርሐ ጽዮን ተሰባስበው ሳሉ መንፈስ ቅዱስ በእሳት አምሳል ወርዶ ሰማያዊ ሀብትን፣ ዕውቀትና ጸጋን አድሏቸዋል። መንፈስ ቅዱስ ከወረደላቸው በኋላም በአእምሮ ጐልምሰዋል፤ ጥቡዓን (ቈራጦች)፣ ጽኑዓን ኾነዋል፤ ለስብከተ ወንጌል የሚፋጠኑበትንና ለሰማዕትነት የሚዘጋጁበትን ልቡና ታድለዋል።

ቅድስት በኾነች በጽርሐ ጽዮን በሐዋርያት ላይ የወረደው የእግዚአብሔር አብ ጸጋ፣ የእግዚአብሔር ወልድ ፍቅር፣ የእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ አንድነት በዅላችን ላይ ይደር፤ እጽፍ ድርብም ይኹን

______________________________

Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

በእባቦች ፖለቲካ የሚያዋጣው እርግብነት (ፍቅር) ሳይሆን ንስርነት (ጥፍር) ነው

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on June 30, 2020

የቅ/ጊዮርጊስ ተዓምር፤ ይህን ቪዲዮ ሳዘጋጅ እርግቧ በመስኮቴ በኩል ብቅ አለችና መልዕክቷን አስተላልፋ በረረች።

________________________________________

Posted in Curiosity, Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , | Leave a Comment »

የፍጻሜው ዘመን ምልክቶች | አሁን ደግሞ ቍራዎቹ የቴክሳስን ግዛት ወረሯት

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on April 21, 2020

[የማቴዎስ ወንጌል ምዕራፍ ፳፬፥፴፯፡፴፱]

የኖኅ ዘመን እንደ ነበረ የሰው ልጅ መምጣት እንዲሁ ይሆናልና። በዚያች ወራት ከጥፋት ውኃ በፊት፥ ኖኅ ወደ መርከብ እስከገባበት ቀን ድረስ፥ ሲበሉና ሲጠጡ ሲያገቡና ሲጋቡም እንደ ነበሩ፥ የጥፋት ውኃም መጥቶ ሁሉን እስከ ወሰደ ድረስ እንዳላወቁ፥ የሰው ልጅ መምጣት ደግሞ እንዲሁ ይሆናል።

ወረራ እያካሄዱ ያሉት እነማን እንደሆኑ እያየናቸው ነው፤ አዎ! ይህም የቍራ ወረራ ቀላል ነገር አይመስለኝም፤ ቍራዎች በየሃገሩ በዝተዋል፣ ሌሊት ሁሉ ሳይቀር ሲጮሁ ይሰማሉ።

በመጽሐፍ ቅዱስ መጀመሪያ የተጠቀሰችው ወፍ ቍራ ስትሆን ቀጥሎም ርግብ ናት። ከተዓምረኛው የማርያም መቀነት ክስተት ጋር በተያያዘ ሰሞኑን አባታችን ኖህን እያስታወስነው ነው።

[ኦሪት ዘፍጥረት ምዕራፍ ፰፥]

ቁራንም ሰደደው፤ እርሱም ወጣ፤ ውኃው ከምድር ላይ እስኪደርቅ ድረስ ወዲያና ወዲህ ይበር ነበር።

ርግብንም ውኃው ከምድር ፊት ቀልሎ እንደ ሆነ እንድታይ ከእርሱ ዘንድ ሰደዳት።

ግጥም በብሩክ ሰለሞን – ሁለተኛ እድል፦

  • ኖህ ቁራን ሲልከው
  • በዚያው ሄዶ ቀረ
  • ክፉ ነገር ሁሉ
  • በዚያው ጠቁሮ ቀረ
  • ኖህ በመቀጠል
  • ላከ እርግብን
  • አመጣች መልካም ዜናን
  • እርግብ በዚያው ቀርታ
  • ቁራ ቢመለስ
  • ነገር ቢቀያየር
  • ታሪክ ሌላ ነበር
  • ፈጣሪ ከሰጠህ
  • ሁለተኛ እድል
  • እንደምንም ብለህ
  • ታሪክህን ቀይር
  • እንደ ቁራ ጠቁረህ አትቅር
  • እንደ እርግብ
  • የዋህ ሁን ገራገር

____________________________________

Posted in Curiosity, Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

የጣዖቱ ዋቄዮ ዛፍ ሲመለክበት በነበረበት ቦታ ላይ ተዓምረኛ የ ቅድስት አርሴማ ጸበል ፈለቀ

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on October 10, 2018

በጎጃም ይኖሩ የነበሩ ሁለት ወጣቶች በራዕይ ተመርተው ወደ አዲስ አበባ ንፋስ ስልክ ክፍለ ከተማ በመምጣት ይህችን ተዓምረኛ ጸበል ለማግኘት በቅተዋል። ጸበሏ በፈለቀችበት ቦታ ላይ፡ ከ20 ዓመታት በፊት፡ ጣዖታዊውን አምላክ ዋቄዮን የሚያመልኩት ወገኖች የዋንዛ ዛፉን ቅቤ ይቀቡበት ነበር።

አንድ ሌላ የገረመኝ ነገር፡ ቪዲዮው ላይ እንደሚሰማው፡ አንድ አባት እኔን በቅድስት አርሴማ ጸበል በሚያጠምቁበት ወቅት አንዲት እርግብ በርራ በመምጣት እራሳቸው ላይ ልታርፍባቸው መብቃቷ ነው። በዕለቱ እንዴት ከሩቅ ሠፈር ወደዚህ ቦታ ተመርቼ ለመሄድ እንደበቃሁ አላውቅም፤ ታክሲው ዝምብሎ አወረደኝ፤ ያውም እዚያ የደረስኩት የመጠመቂያው ሰዓት ካለፈ በኋላ ነበር። ተዓምር ነው!

በአዲስ አበባ ለቡ አካባቢ በምትገኘው በዚህች ጸበል ብዙ ሱባኤ የሚገቡ እህቶችና ወንድሞችን ለማየት በቅቼ ነበር።

እንኳን አደረሰን!

______

Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , | Leave a Comment »

ልደታ ለማርያም፡ “ኢያቄም እና ሐና ሰማይን ወለዱ!”

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on May 9, 2017

__

Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , | Leave a Comment »

 
%d bloggers like this: