Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on June 2, 2022
✞ ዕርገት› በግእዝ ቋንቋ ማረግ፣ ከታች ወደ ላይ መውጣት ማለት ሲኾን የጌታችን ትንሣኤ በተከበረ በዐርባኛው ቀን የሚውለው ዐቢይ በዓልም ‹ዕርገት› ይባላል (ኪዳነ ወልድ ክፍሌ፣ ገጽ ፯፻፷)፡፡ በዓለ ዕርገት ጌታችን አምላካችንና መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከሙታን ከተነሣ በኋላ ለዐርባ ቀናት በግልጽም በስውርም ለቅዱሳን ሐዋርያትና ለቅዱሳት አንስት መጽሐፈ ኪዳንን፣ ትርጓሜ መጻሕፍትን፣ ምሥጢራትን፣ ሕግጋትንና ቀኖናተ ቤተ ክርስቲያንን ሲያስተምር ቆይቶ ወደ ቀደመ ዙፋኑ ወደ ሰማይ በክብር በምስጋና ማረጉን በደስታ የምንዘክርበት ዐቢይ በዓል ነው፡፡ በዓለ ዕርገት በቤተ ክርስቲያናችን በየዓመቱ በድምቀት ይከበራል፡፡ በዓሉ የሚውልበት ዕለት ሐሙስን ባይለቅም ቀኑ ግን የአጽዋማትና በዓላት ማውጫ ቀመርን ተከትሎ ከፍ እና ዝቅ ይላል፡፡
በዚህ መሠረት የዘንድሮው በዓለ ዕርገት ግንቦት ፱ ቀን ፳፻፲ ዓ.ም ይውላል ማለት ነው፡፡ ከጌታችን የዕርገት በዓል ጀምሮ (ከበዓለ ትንሣኤ ዐርባኛው ቀን) እስከ በዓለ ጰራቅሊጦስ ዋዜማ (ዐርባ ዘጠነኛው ቀን) ድረስ ያለው ወቅትም ‹ዘመነ ዕርገት› ተብሎ ይጠራል፡፡ በዘመነ ዕርገት ውስጥ በሚገኘው እሑድ (ሰንበት) ሌሊት ሊቃውንቱ የሚያደርሱት መዝሙርም ‹‹በሰንበት ዐርገ ሐመረ›› የሚል ሲኾን ይኸውም ጌታችን በሰንበት ወደ ታንኳ በመውጣት ባሕርንና ነፋሳትን እንደ ገሠፀ፤ ሐዋርያቱንም ‹‹ጥርጥር ወደ ልቡናችሁ አይግባ፤ አትጠራጠሩ›› እያለ በሃይማኖት ስለ መጽናት እንዳስተማራቸው፤ እንደዚሁም ወንጌልን ይሰብኩ፣ ያስተምሩ ዘንድ በመላው ዓለም እንደሚልካቸው፤ በሰማያዊ መንግሥቱ ይኖሩ ዘንድም ዳግመኛ መጥቶ እንደሚወስዳቸው የሚያስገነዝብ መልእክት አለው (ሉቃ.፰፥፳፪-፳፬፤ ዮሐ.፲፬፥፪፤ ፳፥፳፩)፡፡
በበዓለ ዕርገት ሊቃውንቱ ሌሊት በማኅሌት፣ በዝማሬ እግዚአብሔርን ሲያመሰግኑ ያድራሉ፡፡ ሥርዓተ ማኅሌቱ እንዳበቃ የሚሰበከው የነግህ ምስባክም፡- ‹‹ዘምሩ ለእግዚአብሔር ዘዐርገ ውስተ ሰማይ ሰማይ ዘመንገለ ጽባሕ ናሁ ይሁብ ቃሎ ቃለ ኃይል›› የሚለው የዳዊት መዝሙር ሲኾን፣ ቀጥተኛ ትርጕሙ፡- ‹‹በምሥራቅ በኩል ወደ ሰማየ ሰማያት ለወጣ (ላረገ) ለእግዚአብሔር ዘምሩ፤ የኀይል የኾነውን ቃሉን እነሆ ይሰጣል፤›› ማለት ነው (መዝ.፷፯፥፴፫)፡፡ ምሥጢራዊ ትርጕሙ ደግሞ ‹‹ነፍሳትን ይዞ ከሲኦል ወደ ገነት ለወጣ፤ አንድም በደብረ ዘይት በኩል ላረገ ለእግዚአብሔር ምስጋና አቅርቡ›› የሚል መልእክት አለው፡፡ እንደዚሁም ጌታችን በዐረገ በዐሥረኛው ቀን ‹የኀይል ቃል› የተባለ መንፈስ ቅዱስን ለሐዋርያት እንደ ላከላቸው፤ በተጨማሪም ጌታችን በሕያዋን እና በሙታን (በጻድቃን እና በኃጥአን) ላይ ለመፍረድ ዳግም እንደሚመጣ፤ እኛም ይህንን የጌታችንን የማዳን ሥራ እያደነቅን ለእርሱ ምስጋና፣ ዝማሬ ማቅረብ እንደሚገባን ያስረዳናል – ምስባኩ፡፡
በነግህ (ከቅዳሴ በፊት የሚነበበው) ወንጌል ደግሞ ሉቃስ ፳፬፥፵፭ እስከ መጨረሻው ድረስ ያለው ኃይለ ቃል ነው፡፡ ቃሉም ጌታችን አምላካችንና መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከሰማየ ሰማያት እንደሚወርድ፣ የሰውን ልጅ ለማዳን ሲል መከራ እንደሚቀበል፣ እንደሚሞት፣ ከሙታን ተለይቶ እንደሚነሣ፣ ወደ ሰማይ እንደሚያርግና ዳግም እንደሚመጣ በነቢያት የተነገረው ትንቢት መፈጸሙን፤ ለዚህም ቅዱሳን ሐዋርያት ምስክሮች መኾናቸውን ማለትም በመላው ዓለም እየዞሩ ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ የማዳን ሥራ እንዲሰብኩና በሰማዕትነት እንዲያልፉ፤ እንደዚሁም ሰማያዊ ሀብትንና ዕውቀትን እስኪያገኙ ድረስ በኢየሩሳሌም እንዲቆዩ መታዘዛቸውን ያስረዳል (ትርጓሜ ወንጌል)፡፡ ይህ ምሥጢር ለጊዜው የሐዋርያትን ተልእኮ የሚመለከት ይኹን እንጂ ለፍጻሜው ግን ዅላችንም ቅዱሳት መጻሕፍት የተናገሩትን ቃል አብነት አድርገን የእግዚአብሔርን ሰው መኾንና የማዳኑን ሥራ አምነን፣ ሌሎችንም በማሳመን በሃይማኖታችን ጸንተን መኖር እንደሚገባን፤ እግዚአብሔር አምላካችን ኃይሉን፣ ጸጋውን፣ ረድኤቱን እንዲያሳድርብንም ከቅድስት ቤተ ክርስቲያን መለየት እንደሌለብን የሚያስገነዝብ መልእክት አለው፡፡
በቅዳሴ ጊዜ የሚነበቡ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎችም ከቅዱስ ጳውሎስ መልእክት ዕብራውያን ፩፥፩ እስከ ፍጻሜው ድረስ፤ ከሌሎች መልእክታት ደግሞ ፩ኛ ጴጥሮስ ፫፥፲፰ እስከ ፍጻሜው፤ የሐዋርያት ሥራ ፩፥፩-፲፪ ሲኾኑ፣ ምስባኩም ‹‹ዐርገ እግዚአብሔር በይባቤ ወእግዚእነ በቃለ ቀርን ዘምሩ ለአምላክነ ዘምሩ›› የሚለው ነው፡፡ ትርጕሙም ‹‹በዕልልታና በመለከት ድምፅ ላረገ ለአምላካችን፣ ለጌታችንና ለመድኀኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ ምስጋና አቅርቡ›› ማለት ነው (መዝ.፵፮፥፭-፮)፡፡ ወንጌሉ ደግሞ፣ ማርቆስ ፲፮፥፲፬ እስከ ፍጻሜ ድረስ ሲኾን ቃሉም በነግህ ከተነበበው የወንጌል ክፍል ቃል ተመሳሳይነት አለው፡፡ ቅዳሴውም ቅዳሴ ዲዮስቆሮስ ሲኾን ይህ ቅዳሴ ከሦስቱ አካላት አንዱ የኾነውን የእግዚአብሔር ወልድን (የኢየሱስ ክርስቶስን) ዘለዓለማዊነት የሚያስረዳ፤ ሥጋዌዉን፣ ሕማሙን፣ ሞቱን፣ ትንሣኤዉን፣ ዕርገቱንና ዳግም ምጽአቱንም የሚናገር በመኾኑ በዘመነ ትንሣኤ፣ በዘመነ ዕርገትና በበዓለ ኀምሳ ሰሙን ይቀደሳል፡፡
ቅዱስ ዲዮስቆሮስ በቅዳሴዉ መጀመሪያ ላይ ሀልዎተ እግዚአብሔርንና ምሥጢረ ሥላሴን መሠረት በማድረግ ለእግዚአብሔር ምስጋና ካቀረበ በኋላ፣ ቍጥር ፴፩ ላይ ‹‹… ወበ፵ ዕለት አመ የዐርግ ሰማየ አዘዞሙ እንዘ ይብል ጽንሑ ተስፋሁ ለአብ፤ … ከሙታን ተለይቶ በተነሣ በዐርባኛው ቀን በብርሃን፣ በሥልጣን፣ በይባቤ ወደ ሰማይ በሚያርግበት ጊዜ አብ የሚሰድላችሁ መንፈስ ቅዱስን እስክትቀበሉ ድረስ ከዚህ ቆዩ ብሎ አዘዛቸው፤›› በማለት መጽሐፍ ቅዱሳዊ በኾነ ቋንቋ የጌታችንን ወደ ሰማይ ማረግና ለሐዋርያት የሰጠውን አምላካዊ ትእዛዝ ይናገራል (ሉቃ.፳፬፥፵፱)፡፡
_______
_______
Like this:
Like Loading...
Posted in Ethiopia, Faith, War & Crisis | Tagged: Addis Ababa, Aksum, Ascension, Axum, ረሃብ, ተዋሕዶ, ትግራይ, አረመኔነት, አዲስ አበባ, ኢትዮጵያ, ኢየሱስ ክርስቶስ, እርገት, ኦርቶዶክስ, ክርስትና, ዕርገት, ግድያ, ጥላቻ, ጦርነት, ጭካኔ, ጽዮናውያን, Famine, Genocide, Massacre, Tigray | Leave a Comment »
Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on May 28, 2020
ዕርገት› በግእዝ ቋንቋ ማረግ፣ ከታች ወደ ላይ መውጣት ማለት ሲኾን የጌታችን ትንሣኤ በተከበረ በዐርባኛው ቀን የሚውለው ዐቢይ በዓልም ‹ዕርገት› ይባላል (ኪዳነ ወልድ ክፍሌ፣ ገጽ ፯፻፷)፡፡ በዓለ ዕርገት ጌታችን አምላካችንና መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከሙታን ከተነሣ በኋላ ለዐርባ ቀናት በግልጽም በስውርም ለቅዱሳን ሐዋርያትና ለቅዱሳት አንስት መጽሐፈ ኪዳንን፣ ትርጓሜ መጻሕፍትን፣ ምሥጢራትን፣ ሕግጋትንና ቀኖናተ ቤተ ክርስቲያንን ሲያስተምር ቆይቶ ወደ ቀደመ ዙፋኑ ወደ ሰማይ በክብር በምስጋና ማረጉን በደስታ የምንዘክርበት ዐቢይ በዓል ነው፡፡ በዓለ ዕርገት በቤተ ክርስቲያናችን በየዓመቱ በድምቀት ይከበራል፡፡ በዓሉ የሚውልበት ዕለት ሐሙስን ባይለቅም ቀኑ ግን የአጽዋማትና በዓላት ማውጫ ቀመርን ተከትሎ ከፍ እና ዝቅ ይላል፡፡
በዚህ መሠረት የዘንድሮው በዓለ ዕርገት ግንቦት ፱ ቀን ፳፻፲ ዓ.ም ይውላል ማለት ነው፡፡ ከጌታችን የዕርገት በዓል ጀምሮ (ከበዓለ ትንሣኤ ዐርባኛው ቀን) እስከ በዓለ ጰራቅሊጦስ ዋዜማ (ዐርባ ዘጠነኛው ቀን) ድረስ ያለው ወቅትም ‹ዘመነ ዕርገት› ተብሎ ይጠራል፡፡ በዘመነ ዕርገት ውስጥ በሚገኘው እሑድ (ሰንበት) ሌሊት ሊቃውንቱ የሚያደርሱት መዝሙርም ‹‹በሰንበት ዐርገ ሐመረ›› የሚል ሲኾን ይኸውም ጌታችን በሰንበት ወደ ታንኳ በመውጣት ባሕርንና ነፋሳትን እንደ ገሠፀ፤ ሐዋርያቱንም ‹‹ጥርጥር ወደ ልቡናችሁ አይግባ፤ አትጠራጠሩ›› እያለ በሃይማኖት ስለ መጽናት እንዳስተማራቸው፤ እንደዚሁም ወንጌልን ይሰብኩ፣ ያስተምሩ ዘንድ በመላው ዓለም እንደሚልካቸው፤ በሰማያዊ መንግሥቱ ይኖሩ ዘንድም ዳግመኛ መጥቶ እንደሚወስዳቸው የሚያስገነዝብ መልእክት አለው (ሉቃ.፰፥፳፪–፳፬፤ ዮሐ.፲፬፥፪፤ ፳፥፳፩)፡፡
በበዓለ ዕርገት ሊቃውንቱ ሌሊት በማኅሌት፣ በዝማሬ እግዚአብሔርን ሲያመሰግኑ ያድራሉ፡፡ ሥርዓተ ማኅሌቱ እንዳበቃ የሚሰበከው የነግህ ምስባክም፡– ‹‹ዘምሩ ለእግዚአብሔር ዘዐርገ ውስተ ሰማይ ሰማይ ዘመንገለ ጽባሕ ናሁ ይሁብ ቃሎ ቃለ ኃይል›› የሚለው የዳዊት መዝሙር ሲኾን፣ ቀጥተኛ ትርጕሙ፡– ‹‹በምሥራቅ በኩል ወደ ሰማየ ሰማያት ለወጣ (ላረገ) ለእግዚአብሔር ዘምሩ፤ የኀይል የኾነውን ቃሉን እነሆ ይሰጣል፤›› ማለት ነው (መዝ.፷፯፥፴፫)፡፡ ምሥጢራዊ ትርጕሙ ደግሞ ‹‹ነፍሳትን ይዞ ከሲኦል ወደ ገነት ለወጣ፤ አንድም በደብረ ዘይት በኩል ላረገ ለእግዚአብሔር ምስጋና አቅርቡ›› የሚል መልእክት አለው፡፡ እንደዚሁም ጌታችን በዐረገ በዐሥረኛው ቀን ‹የኀይል ቃል› የተባለ መንፈስ ቅዱስን ለሐዋርያት እንደ ላከላቸው፤ በተጨማሪም ጌታችን በሕያዋን እና በሙታን (በጻድቃን እና በኃጥአን) ላይ ለመፍረድ ዳግም እንደሚመጣ፤ እኛም ይህንን የጌታችንን የማዳን ሥራ እያደነቅን ለእርሱ ምስጋና፣ ዝማሬ ማቅረብ እንደሚገባን ያስረዳናል – ምስባኩ፡፡
በነግህ (ከቅዳሴ በፊት የሚነበበው) ወንጌል ደግሞ ሉቃስ ፳፬፥፵፭ እስከ መጨረሻው ድረስ ያለው ኃይለ ቃል ነው፡፡ ቃሉም ጌታችን አምላካችንና መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከሰማየ ሰማያት እንደሚወርድ፣ የሰውን ልጅ ለማዳን ሲል መከራ እንደሚቀበል፣ እንደሚሞት፣ ከሙታን ተለይቶ እንደሚነሣ፣ ወደ ሰማይ እንደሚያርግና ዳግም እንደሚመጣ በነቢያት የተነገረው ትንቢት መፈጸሙን፤ ለዚህም ቅዱሳን ሐዋርያት ምስክሮች መኾናቸውን ማለትም በመላው ዓለም እየዞሩ ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ የማዳን ሥራ እንዲሰብኩና በሰማዕትነት እንዲያልፉ፤ እንደዚሁም ሰማያዊ ሀብትንና ዕውቀትን እስኪያገኙ ድረስ በኢየሩሳሌም እንዲቆዩ መታዘዛቸውን ያስረዳል (ትርጓሜ ወንጌል)፡፡ ይህ ምሥጢር ለጊዜው የሐዋርያትን ተልእኮ የሚመለከት ይኹን እንጂ ለፍጻሜው ግን ዅላችንም ቅዱሳት መጻሕፍት የተናገሩትን ቃል አብነት አድርገን የእግዚአብሔርን ሰው መኾንና የማዳኑን ሥራ አምነን፣ ሌሎችንም በማሳመን በሃይማኖታችን ጸንተን መኖር እንደሚገባን፤ እግዚአብሔር አምላካችን ኃይሉን፣ ጸጋውን፣ ረድኤቱን እንዲያሳድርብንም ከቅድስት ቤተ ክርስቲያን መለየት እንደሌለብን የሚያስገነዝብ መልእክት አለው፡፡
በቅዳሴ ጊዜ የሚነበቡ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎችም ከቅዱስ ጳውሎስ መልእክት ዕብራውያን ፩፥፩ እስከ ፍጻሜው ድረስ፤ ከሌሎች መልእክታት ደግሞ ፩ኛ ጴጥሮስ ፫፥፲፰ እስከ ፍጻሜው፤ የሐዋርያት ሥራ ፩፥፩–፲፪ ሲኾኑ፣ ምስባኩም ‹‹ዐርገ እግዚአብሔር በይባቤ ወእግዚእነ በቃለ ቀርን ዘምሩ ለአምላክነ ዘምሩ›› የሚለው ነው፡፡ ትርጕሙም ‹‹በዕልልታና በመለከት ድምፅ ላረገ ለአምላካችን፣ ለጌታችንና ለመድኀኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ ምስጋና አቅርቡ›› ማለት ነው (መዝ.፵፮፥፭–፮)፡፡ ወንጌሉ ደግሞ፣ ማርቆስ ፲፮፥፲፬ እስከ ፍጻሜ ድረስ ሲኾን ቃሉም በነግህ ከተነበበው የወንጌል ክፍል ቃል ተመሳሳይነት አለው፡፡ ቅዳሴውም ቅዳሴ ዲዮስቆሮስ ሲኾን ይህ ቅዳሴ ከሦስቱ አካላት አንዱ የኾነውን የእግዚአብሔር ወልድን (የኢየሱስ ክርስቶስን) ዘለዓለማዊነት የሚያስረዳ፤ ሥጋዌዉን፣ ሕማሙን፣ ሞቱን፣ ትንሣኤዉን፣ ዕርገቱንና ዳግም ምጽአቱንም የሚናገር በመኾኑ በዘመነ ትንሣኤ፣ በዘመነ ዕርገትና በበዓለ ኀምሳ ሰሙን ይቀደሳል፡፡
ቅዱስ ዲዮስቆሮስ በቅዳሴዉ መጀመሪያ ላይ ሀልዎተ እግዚአብሔርንና ምሥጢረ ሥላሴን መሠረት በማድረግ ለእግዚአብሔር ምስጋና ካቀረበ በኋላ፣ ቍጥር ፴፩ ላይ ‹‹… ወበ፵ ዕለት አመ የዐርግ ሰማየ አዘዞሙ እንዘ ይብል ጽንሑ ተስፋሁ ለአብ፤ … ከሙታን ተለይቶ በተነሣ በዐርባኛው ቀን በብርሃን፣ በሥልጣን፣ በይባቤ ወደ ሰማይ በሚያርግበት ጊዜ አብ የሚሰድላችሁ መንፈስ ቅዱስን እስክትቀበሉ ድረስ ከዚህ ቆዩ ብሎ አዘዛቸው፤›› በማለት መጽሐፍ ቅዱሳዊ በኾነ ቋንቋ የጌታችንን ወደ ሰማይ ማረግና ለሐዋርያት የሰጠውን አምላካዊ ትእዛዝ ይናገራል (ሉቃ.፳፬፥፵፱)፡፡
ምንጭ
___________________________
Like this:
Like Loading...
Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: ተዋሕዶ, ኢትዮጵያ, ኢየሱስ ክርስቶስ, እርገት, ኦርቶዶክስ, ክርስትና, ዕርገት, የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነት | Leave a Comment »
Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on August 21, 2019
ዲያብሎስ እንጅ ታዲያ ሌላ ማን እነዚህን መልአክ የሚመሳስሉትን ሕፃናትን ይተናኮላል?
በእነዚህ የበዓላት ቀናት ትዝ ሲሉኝ የሚውሉት በዚህ በክረምት የተፈናቀሉትና ከቦታ ቦታ እየተዘዋወሩ በብርድና ቸነፈር የሚጎሳቆሉት ሕፃናት ናቸው።
[የማቴዎስ ወንጌል ምዕራፍ ፲፰፥፲]
“ከነዚህ ከታናናሾቹ አንዱን እንዳትንቁ ተጠንቀቁ፤ መላእክቶቻቸው በሰማያት ዘወትር በሰማያት ያለውን የአባቴን ፊት ያያሉ እላችኋለሁና።”
ፍልሰታ ለማርያም – ነሐሴ ፲፮
የእመቤታችን ትንሣኤና እርገት መታሰቢያ – በጾመ ፍልሰታ ወቅት ብዙዎች ከቤታቸው ተለይተው በመቃብር ቤት ዘግተው፣ አልጋና ምንጣፍ ትተው፣ በመሬት ላይ ተኝተው ዝግን ጥሬ እፍኝ ውኃ እየቀመሱ በጾምና በጸሎት በመትጋት በታላቅ ተጋድሎ ይሰነብታሉ፡፡ በሰሙነ ፍልሰታ ምእመናን ለእመቤታችን ያላቸውን ጽኑና ጥልቅ ፍቅር የሚያሳዩበት ነው፡፡
ጌታችን ሦስት መዓልት ሦስት ሌሊት በከርሰ መቃብር ቆይቶ ሙስና መቃብር ሳያገኘው፣ መግነዝ ፍቱልኝ መቃብር ክፈቱልኝ ሳይል በሥልጣኑ እሑድ በመንፈቀ ሌሊት እንደተነሣ ሁሉ እርሷም በተቀበረች በሦስተኛው ቀን ማኅደረ መለኮት ናትና ሙስና መቃብር ሳያገኛት መግነዝ ፍቱልኝ፣ መቃብር ክፈቱልኝ ሳትል የልጅዋ ሥልጣን ኃይል ሆኗት መነሣቷን ትንሣኤዋ “ከመ ትንሣኤ ወልዳ፤ እንደ ልጅዋ ትንሣኤ”ነው ተብሎ ሲከበርላት ይኖራል፡፡
በዚሁ በነሐሴ ፲፮ ቀን የሰማእቱ የቅዱስ ጊዮርጊስ ፍልሰቱ ነው፡፡ ሥጋው ከፋርስ ሀገር ወደ ሀገሩ ወደ ልዳ በክብር የፈለሰበት ነው፡፡ ፍልሰቴን ከፍልሰትሽ አድርጊልኝ፣ ብሎ ለምኗት ስለነበር ፍልሰቱ ከእመቤታችን ፍልሰት ጋር እንዳሰበው ሆኖለታል፡፡ ስለዚህም እርሷን መውደዱ የሚያውቁ ሥእሉን ከሥእሏ አጠገብ ይስላሉ፡፡ በስሙ ለሚማጸኑ የድኅነት ወደብ ይሆን ዘንድ፡፡
የእመቤታችን አማላጅነቷ አይለየን አሜን፡፡
_____________________
Like this:
Like Loading...
Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: ሕፃናት, መንፈስ ቅዱስ, ቅድስት ማርያም, ኢትዮጵያ, ኢየሱስ ክርስቶስ, እመቤታችን, እርገት, እርግቦች, የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነት, ጾመ ፍልሰታ, ፍልሰታ, ፪ሺ፲፩, Ethiopian Orthodox Tewahedo Faith | Leave a Comment »
Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on April 8, 2019
ወንድማችን በየታክሲው ስለ ሚለጠፉት እምነት–ነክ ጥቅሶች በጥሩ መልክ ገልጾታል፤ አዎ! እኔም የታዘብኩት ይህን ነበር፤ ከኢየሱስ ክርስቶስ እና ድንግል እናታችን ስዕላት ጎን የግራኝ አህመድ እና ማንቸስተር ዩናትድ ፎቶዎች ተለጥፈው ይታያሉ። ሁሉም ዝም ብሎ አይደለም፤ ኃይለኛ መንፈሳዊ ጦርነት እየተካሄደ ነው፤ “በጣም የሚቃረኑ ጥቅሶች ግራና ቀኝ ታያላችሁ፤ በዚህ የሕይወት ጥቅስ፥ በዚህ የሞት ጥቅስ አለ።””እውነት ፓይለት መሆን ያሰኛል?…ለመሆኑ በአውሮፕላን እና በመኪና ከመጓዝ የትኛው ይቀላል? በመኪና!እውነት ለመናገር። ምክኒያቱም በአውሮፕላን ውስጥ ትንሽ ስህተት እንኳን ብትኖር አበቃ ነው፡ የመትረፍ ዕድል የለም!” ዋው!
ወዲያው ብልጭ ብሎ የታየኝ የተከሰከሰው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ነው፤ በፓለይቶቹ ለመፍረድ ሳይሆን፤ ሙስሊም የሆነ ሰው አውሮፕላን ማብረር የለበትም። በአስራሁለት ኪሎሜትር ከፍታ ላይ ልዩ የመንፈሳዊ ፈተና ስለመኖሩ በሌላ ጊዜ እመለስበታለሁ። የተከሰከሰውን አውሮፕላናችን ያበረሩት ብዙ ልምድ ያለው ክርስቲያኑ ወንድማችን ያሬድ እና ልምዱ የሌለው ወገናችን አህመድ ነበሩ። “የሕይወት ጥቅስ፣ የሞት ጥቅስ”።
በሌሎች ሃገራት የታዩትን ክስተቶች ሳንጨምር፡ በኮሞሮ የተከሰከሰው የኢትዮጵያ አየር መንገድን እና በሊባኖስ የፈነዳውን የኢትዮጵያ አየር መንገድን የኢትዮጵያ ከመሆናቸው ሌላ ምን የሚያገናኛቸው ነገር አለ? አዎ! ሁሉም አውሮፕላኖች በሙስሊሞች ነበር የተጠቁት። አንዳንዶቻችን ይህ አይዋጥልን ይሆናል፤ ነገር ግን የኢትዮጵያ አየር መንገድ፡ ለራሳቸው ለሙስሊሞች ሲባል፤ ሙስሊም አብራሪዎችን መቅጠር የለበትም። ከእኔ ጀምሮ፡ መላው ዓለም ሙስሊም አብራሪ የሚያበረው አውሮፕላን ውስጥ መሳፈር አይሻም። ይህ ሃቅ ነው!
ወንድማችን በጣም ትክክል ነው፤ በተለይ በዚህ ዘመን ዓላማ ያለውን ክርስትናን መያዝ ይኖርብናል፤ በተለይ አባቶቻችን ይከተሉት የነበረው ኮፍጠን ያለ፣‘ወንዳማ‘የሆነ ክርስትናን።
እግዚአብሔር ከኛ ጋር ከሆነ ምንም/ማንም አያስፈራንም!
__________________
Like this:
Like Loading...
Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: ሕይወት እና ሞት, ስብከት, ቤተክርስቲያን, ትምህርት, አውሮፕላን, እርገት, እግዚአብሔር, ክርስትና, የኢትዮጵያ አየር መንገድ, የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነት, ፍራቻ, ፓይለቶች, Ethiopian Orthodox Tewahedo Faith | Leave a Comment »