Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • May 2023
    M T W T F S S
    1234567
    891011121314
    15161718192021
    22232425262728
    293031  
  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

Posts Tagged ‘እረኛዬ’

የዩክሬይን ሴቶች “ጠላታቸውን” ቤቱ ድረስ ሄደው ያፈነዱታል ፥ የሰሜን ኢትዮጵያ ወንዶች ግን ግራኝ በሠራላቸው የማታለያ ድራማ ያለቅሳሉ ፥ ለአሸንዳ ይጨፍራሉ

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on August 23, 2022

👉 የምዕራባውያኑ ኤዶማውያን ረጅም እጅ ቢኖርበትም፤ ከትናንትና ወዲያ የሩሲያ ፈላስፋውንና የፕሬዚደንት ፑቲን አማካሪን የአሌክሳንደር ዱጊን ሴት ልጅን በመኪና ቦምብ አፈንድታ የገደለቻት ዩክሬናዊት ሴት መሆኗን ስሰማ፤ እንዴት ነው ለአራት ዓመታት ያህል ከሚሊየን በላይ ሰሜን ኢትዮጵያውያን እናቶችን፣ አባቶችን፣ እንዲሁም ሕጻናቶቻቸውን በማሳደድ፣ በመጨፍጨፍ፣ በመመረዝና በማስራብ ላይ ያለው የአረመኔው ኦሮሞ አገዛዝ ቁንጮዎች አንዴም የግድያ ሙከራ እንኳን ያልተደረገባቸው? የሚለው ጥያቄ ነው። አንዱም! ታዲያ ሁሉም ተናብበው በመሥራት የሰሜኑን ሕዝበ ክርስቲያን ከምድረ-ገጽ እያጠፉት አይደለምን?

ከቀናት በፊት የዩቲውብ የቀጥታ ሥርጭት ቁልፎቹን ስጫን፤ “እረኛየ” ወደ ተሰኘው ድራማ ወደሚታይበት የ”አርት ቲቪ” ቻነል ወሰደኝ። “አርት ቲቪ” ከ”ኢቢ ኤስ” እና ብዙ ቻነሎች ጎን አውሬው 666 ለኢትዮጵያውያን ያዘጋጀው ቻነል መሆኑን ስለማውቅ ድራማውን ከፍቼ ለማየት ምንም ፍላጎቱ አልነበረኝም፤ እንኳን በዚህ በሃዘን ወቅት፣ እንኳን አውሬው ሥልጣን ላይ ያስቀመጠው ፋሺስቱ የኦሮሞ አገዛዝ ከሚቆጣጠራት ከአዲስ አበባ ከተማ የሚተላለፍ ድራማ። እጅግ የሚያሳዝን ነው፤ በመቶ ሽህ የሚቆጠሩ ሰዎች ይህን ድራማ በቀጥታ ይከታተሉት ነበር። እግዚኦ! ነበር ያልኩት! ድራማው ስለምን እንደሆነ ምርመራየን ሳካሂድ ግራኝ አብዮት አህመድና “ብልጽግና” የተሰኘው የፋሺስቱ ኦሮሞ አገዛዝ ቀስቃሾች ያዘጋጁት ድራማ መሆኑን ለማወቅ በቃሁ። ድራማውም በዚህ በሃገራችን ታሪክ አስከፊና አሳፋሪ በሆነ ወቅት እንዲዘጋጅ የተደረገበትም ምክኒያት በተንኮል መሆኑን ተረዳሁ። በተለይ የአዲስ አበባ ነዋሪውን ለአመጽ እንዳይነሳሳ ትንሽም ቢሆን ላለፉት ወራት የተቀሰቀሰበትን ቁጣና ወኔ በለቅሶና በእንባው እያበረደ በቀጣዩ ጦርነትና ጭፍጨፋ ተመልሶ እንዲያቀላፋ ብሎም ለፋሺስቱ ኦሮሞ ሰአራዊት ዝም ጭጭ ብሎ ድጋፉን እንዲሰጥ፤ ምናባዊ የሆነ ሁኔታ እንደፈጠሩለት በግልጽ ነው የተረዳሁት። በሕዝቡ ላይ ነው ድራማ እየሠሩበት ያሉት።

💭 በሌላ በኩል ደግሞ የሕወሓት ቡድኖችና ቱልቱላ ሜዲያዎቻቸው ለብዙ ቀናት ፤ “ከአሸንዳ” ሌላ ምንም የሚናገሩለት ጉዳይ የለም።

  • በቅዱሷ አክሱም ጽዮን ሰለተጨፈጨፉት ወገኖቼ
  • በደብረ ዳሞ አቡነ አረጋዊ ሰለተጨፈጨፉት ወገኖቼ
  • በደብረ አባይ ገዳም ሰለተጨፈጨፉት ወገኖቼ
  • በደንገላት ቅድስት ማርያም ሰለተጨፈጨፉት ወገኖቼ
  • በውቅሮ አማኑኤል ሰለተጨፈጨፉት ወገኖቼ
  • በዛላምበሳ ጨርቆስ ሰለተጨፈጨፉት ወገኖቼ
  • ከዋልድባ ገዳም በሑዳዴ ጾም ስለተጠረፉት ሺህ መነኮሳት አባቶቻችን
  • በገዳም ማርያም ውቅሮ እምባስነይቲ ሰለተጨፈጨፉት ወገኖቼ
  • በእንዳ ማርያም መድኃኒት አዲ ዳዕሮ ሰለተጨፈጨፉት ወገኖቼ
  • በማይካድራ፣ ዳንሻ እና ሁመራ በጅምላ ሰለተጨፈጨፉት ወገኖቼ
  • በቸሊ/ግጀት ጭፍጨፋ፤ ከሁለት መቶ በላይ ሰለተጨፈጨፉት ተዋሕዷውያን ሕፃናትና ወጣት ወገኖቼ
  • በደቡብ ትግራይ የቦራ የልደት ቀን ሰለተጨፈጨፉት ወገኖቼ
  • በአክሱም ማኅበረ ደጎ ተጨፍጭፈው ወደ ገደል ሰለተጣሉት ወገኖቼ
  • በእናቶቻችንና እኅቶቻችን ላይ እየደረሰ ስላለው ግፍና ስቃይ

ዝም፤ ጭጭ?! 😠😠😠 😢😢😢

የሕወሓት ሜዲያዎች ስለአሸንዳ ከሚያሳዩትና ከሚናገሩት አንድ መቶኛውን ያህል ስለ ሕዝበ ክርስቲያኑ ሰቆቃ ሊያሳዩና ሲናገሩ አላየናቸውም/አልሰማናቸውም። በሱዳን ስደት ላይ ስላሉት እንኳን ዘገባዎችን ሲያቀርቡ አይታዩም/አይሰሙም። በሚሊየን የሚቆጠሩ ክርስቲያን ወገኖቼን መታሰቢያ ዕለታት በነካ ነካ ዜና መልክ እንኳን ሲያቀርቡ አይታዩም። በጭራሽ! ግድ የላቸውም፤ ፈገግ ብለውና ከረባት አስረው በየሜዲያው ይቀርባሉ፤ ሰርግ ይደግሳሉ! ከባድና ጥልቅ ሃዘን ላይ በምንገኝበት በዚህ አስከፊ ወቅት፣ በእንባ ወደ ምሕላ በመግባት ፋንታ አሸንዳ አሸንዳ አሸንዳ እያሉ ይጨፍራሉ፣ ይህንንም በሁሉም ሜዲያዎቻቸው ለሳምንት ያህል ያለማቋረጥ ያሳያሉ። የአረመኔዎቹን የእነ ግራኝ አብዮት አህመድን ልጆችና ሚሶቶች አንድነው በመድፋት ፋንታ ጊዜ ለመግዛት፤ “ድረድር ድረድር!” እያሉ ሕዝባችንን አንድ በአንድ በዝምታ በመጨረስና በማስጨረስ ላይ ናቸው።

አዎ! ኢ-አማንያኑ ይህን ጦርነት የሚፈልጉትና ከአረመኔዎቹ አህዛብ የሻዕብያና ኦሮሞ ብልጽግና ቡድኖች ጋር በማበር የፀረ-አስኩም ጽዮን ዘመቻውን የጀመሩት ሕዝበ ክርስቲያኑን ለመፍጀት፣ የተረፉት ጽዮናውያን መንፈሳዊ ማንነታቸውንና ምንነታቸውን እንዲተውና “የአሸንዳ” ባሕልን ብቻ እንዲያዳብሩ፣ የቀሩትም ገዳማት፣ ዓብያተ ክርስቲያናትና ሃይማኖታዊ ቅርሶች የቱሪስት ማ ዕከላት ብቻ ሆነው የገንዘብ ምንጮች እንዲሆኑ ለማድረግ በማሰብ ነው። ይህንም በእኔ በኩል ከአስር ዓመታት በላይ በተለይ የዘርም ማጥፋት ጦርነቱ እንደተከፈተ በተደጋጋሚ ጠቁሜአለሁ።

አዎ! የሉሲፈራውያኑ ጭፍሮች ኦሮቶዶክስ ተዋሕዶ ክርስትና ሃይማኖትን/እመነትን በባህልና ድራማ ለመቀየር ተገተው እየሠሩ ነው።

R.I.P✞

ለወይዘሮ ዳርያ ዱጊና ነፍሷን ይማርላት

💭 ድርጊቱ ባይደገፍም፤ እስኪ ዩክሬናውያኑ እና ምዕራባውያኑ ደጋፊዎቻቸው ስለተገደለችው የሩሲያው ፈላስፋ ሴት ልጅ የሚሉትን እዚህ ገብተን እናንብብ።

👉 “ሩሲያውያኑ የዘሩትን ነው ያጨዱት፤ ልጆቻቸውን ያጡት የዩክሬይን እናቶች የደረሰባቸውን ሃዘን ሩሲያውያኑም ይቅመሱት ወዘተ” የሚሉትን አስተያየቶች ነው በብዛት በመስጠት ላይ ያሉት። ም ዕራቡ ለዩክሬይን የሚሰጠው ትኩረትና ሕዝባቸውም ለዩክሬናውያኑ የሚያሳየው አንድነት እጅግ በጣም የሚያስገርም ነው! ለኢትዮጵያ ጽዮናውያን ከእግዚአብሔር አምልክ፣ ጽዮን እናቱና ቅዱሳኑ በቀር ሌላ ማንም አይደርስለትም። ከራሱ አብራክ የወጡት ከሃዲዎች እንኳን ለአውሬው አሳልፈው ሰጥተውታል።

👉 ከ፪ሺህ በላይ አስተያየቶችን ወደያዘው ወደ “Sky News” አስተያየት መስጫ ሳጥን ይግቡ፤

______________

Posted in Ethiopia, News/ዜና, War & Crisis | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

 
%d bloggers like this: