Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • June 2023
    M T W T F S S
     1234
    567891011
    12131415161718
    19202122232425
    2627282930  
  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

Posts Tagged ‘እምነት’

Ethiopia Silenced! The Truth About Early Church History in Africa

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on May 21, 2023

❖ ኢትዮጵያ ታፍናለች! በአፍሪካ የቀደመችዋ ቤተክርስቲያን ታሪክ እውነት ❖

✞ ከአንጾኪያ፣ እስክንድርያ፣ እየሩሳሌም፣ ሮም እና ባይዛንቲየም፣ ጋር መካተት ያለበት ሌላ ከተማ ወይም አገር ቢኖሩ ኖሮ ከጎናቸው መሆን ያለባት ኢትዮጵያ ናት። ዛሬ የኒቆሚዲያው ዩሴቢየስ የቤተክርስቲያን ታሪክ ፪ ኛን መጽሐፍ ከዘኍልቍ ምዕራፍ ፲፪፣ የሐዋርያት ሥራ ምዕራፍ ፰ እና ከኢትዮጵያ ታሪክ ጋር ሲወሰዱ፣ ኢትዮጵያ በክርስትና እምነት ውስጥ እጅግ በጣም አስፈላጊ የሆነች አገር እንደነበረች የሚገልጹትን አንዳንድ ጠቃሚ እውነታዎችን ይዞ ይጀምራል።

አዎ! መምህር ኒክ ጃሬት ትክክል ናቸው፤ ግን ይህችኛው ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ ዘ-መንፈስ ናት። በአክሱማዊቷ ኢትዮጵያ ላይ ከጠላት አህዛብ ጋር አብራ የዘመተውን፡ የልፍስፍሱን፣ እራሱን የሚጠላውንና የዳግማዊ ምንሊክ ተረት ተረት ‘ብሔረ ብሔረሰብ’ የመጨረሻ ትውልድ የሆነውን’ኢትዮጵያ ዘ-ስጋን አይመለከትም። ለዚህም ነው ርዕሱ እንደሚጠቁመን ይህች በሰይጣን የምትመራዋ ዓለም ተገቢውን ትኩረት ልትሰጠው ያልፈለገችው። ላለፉት ሁለት ዓመታት እንኳን ከሚሊየን በላይ የተጨፈጨፈው ኢትዮጵያዊ ኦርቶዶክስ ክርስቲያኑ ሆኖ ሳለ፤ ይህ ጭፍጨፋ ሃይማኖታዊ ግብ እንዳለውና በሕዝበ ክርስቲያኑ ላይ ያነጣጠረ እንደሆነ ለመናገር የደፈረ አንድም ‘ኢትዮጵያዊ’ የለም።

ለዚህም እኮ ነው፡ እንኳን የተቀረው ዓለም፡ የኦርቶዶክስ ክርስቲያኑ ዓለም ሳይቀር ድጋፉን እንዲነፍገን የተደረገው። ከዚህ ጨፍጫፊ የጋላ-ኦሮሞ አገዛዝ ጋር ጎን እንደ ግብጽና ሩሲያ ያሉ የኦርቶዶክስ ክርስቲያን ሃገራት ሳይቀሩ የተሰለፉት። በኢትዮጵያ እየተፈጸመ ያለው ግፍና ጥቃት በኦርቶዶክስ ተውሕዶ ክርስቲያን ኢትዮጵያውያን ላይ መሆኑን እያንዳንዳችን እስካላሳወቅን ድረስና፣ “የዘር ማጥፋት ወንጀል በትግሬ ላይ፣ በአማራ ላይ፣ በጉራጌ ወዘተ ላይ ነው የተፈጸመው” ማለቱን፣ ብሎም ክቡር መስቀሉን እና ታቦተ ጽዮንን በመሸከም ፈንታ የሉሲፈርን/ቻይናን ባንዲራ ማውለብለቡን ከቀጠልን እግዚአብሔር አምላክም ፈጽሞ አይሰማንም፣ ከገባንበት መቀመቅም አያወጣንም። ምክኒያቱም ይህ ሃቁ አይደለምና ነው፤ ምክኒያቱም ፈጣሪያችን ‘ትግሬ’፣ ‘አማራ’፣ ጉራጌ ወዘተ የተሰኙትን የስጋ ማንነትና ምንነት ያላቸውን ብሔሮችን ወይንም ነገዶችን አያውቃቸውምና ነው።

ለምሳሌ ያ ዘምድኩን በቀለ የተባለው ግብዝ ሰው፤ “የአማራ አምላክ” “አማራ እንደ ኢየሱስ ክርስቶስ የሚሰቃየው ኢትዮጵያን ለማዳን ነው” እያለ ሲቀባጥር ስሰማው፤ እያቅለሸለሸኝ፤ “እንዴ ይህ ፍዬል ምን ያህል ጸያፍና እጅግ የሚያስኮንን ነገር እያስታወከ መሆኑን አይገነዘበውምን? የቀበሩለት ቺፕስ ነው ወይንስ ዋቄዮ-አላህ እንዲህ የሚያስቀባጥረው?!” ለማለት ነበር የተገደድኩት። እግዚዖ! አቤት ድፍረት! አቤት ውድቀት፤ እንደው ይህን ግለሰብ የሚመክረው ወገን የለምን?

✞ If there were another city or country that should be included with Antioch, Alexandria, Jerusalem, Rome, and Byzantium, Ethiopia, should be right along side them. Today Eusebius of Nicomedia kicks off book 2 of his Church history with some important facts that when taken with Numbers chapter 12, Acts chapter 8, and the history of Ethiopia, reveal it was a much more important Country in the Christian faith.

______________

Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

A Word on The End of The World | ስለ አለም መጨረሻ አንድ ቃል

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on May 21, 2023

😇 የቭላድሚር ቅዱስ ሴራፒዮን († 1275)

የቭላድሚር ቅዱስ ሴራፒዮን እ.አ.አ ከ 1247 እስከ 1274 ባለው ጊዜ ውስጥ የኪየቭ ዋሻዎች ገዳም ሊቀ ጳጳስ ነበሩ ። ከዚያ በኋላ የቭላድሚር ፣ ሱዝዳል እና የኒዝኒ ኖቭጎሮድ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ሆነው ተሾሙ ፣ እስከ ቀጣዩ የእረፍታቸው ዓመት ድረስ አስተዳደሩ። በወቅቱ የሀገረ ስብከቱ ግዛት የቭላድሚር ግራንድ ዱቺ እና የጎሮዴት ፣ ኮስትሮማ ፣ ሞስኮ ፣ ፔሬስላቭል ፣ ስታሮዱብ ፣ ሱዝዳል ፣ ኒዝኒ ኖቭጎሮድ እና ዩሪየቭ ርእሰ መስተዳድሮችን ያካተተ ነበር። የቅዱስ ሱራፒዮን አምስት ስብከቶች ተጠብቀው ቆይተዋል፣ አብዛኞቹ እንደ ተዋረዳዊው ዘመን እንደሆነ ይታመናል።

ወንድሞች ሆይ፣ የሚያስፈራው ቀን በድንገት ይመጣል፤ የኃጢአታችን ፅዋ ሞልቶ እጅግ አስፈሪ የሆነ የቅዱሱ የእግዚአብሔር ፍርድ ይጠብቀናልና የእግዚአብሔርን ፍርድ ፍሩ። በበጎ ምግባር ራሳችንን ካላዘጋጀን ራቁታችንን ቀርተንና እና ተቸግን በማይጠፋ እሳት እንቀጣለን።

ወንድሞች ሆይ ፣ እግዚአብሔርን በመፍራት ኑሩ ፣ የዚህ ሕይወት ጊዜ አጭር ነው እና እንደ ጭስ ይጠፋል። ከኃጢአታችን የተነሣ ብዙ መከራ ደረሰብን፥ ትንሽም ሐዘን አይደለም፥ የአሕዛብ ወረራ፥ በሰዎች መካከል መነሣሣት፥ የአብያተ ክርስቲያናት ረብሻ፥ በመኳንንት መካከል አለመረጋጋት፥ ሥጋን ብቻ የሚያስደስቱት አመፀኞቹ ካህናት ለነፍስ ደንታ የሌላቸው ናቸው። የመነኮሳት አለቆችም እንዲሁ። እናም መነኮሳቱ ስለ በዓላት መጨነቅ ይጀምራሉ፣ ግልፍተኛ እና ለፉክክር የተጋለጡ ይሆናሉ፣ እናም ለቅዱሳን አባቶች የማይመች ህይወት ይመራሉ። ሹማምንቱ በባለሥልጣናትና ኃያላን ፊት ይፈራሉ፣ በግል ጥቅማቸው ላይ ተመስርተው ይፈርዳሉ፣ ወላጅ አልባ ልጆችን ያሰናክላሉ፣ ለመበለቶችና ለድሆች አይማልዱም። በምእመናንም ውስጥ፣ አለማመን እና ዝሙት አለ፤ እና እውነትን ትተው ውሸት መፍጠር ይጀምራሉ።

በዚህ ዘመን ግን ማንም የሚፈልግ ቢኖር ይድናል፣ በመንግሥተ ሰማያትም ታላቅ ይባላል። በኖኅ ዘመንም እንዲሁ ነበርና፡ ይበሉም ይጠጡም፣ ያገቡም ያመነዝሩም ነበር ስለዚህ የጥፋት ውኃም መጣ ሁሉንም ስለ በደሉ አጠፋቸው። እንደዚህ ያለ አስፈሪ ክስተት ማየት እንዴት አሳዛኝ ነው! ኖህ ጌታ እንዳዘዘው መርከብን ሲሰራ ከህንድ የመጡ ዝሆኖች እና የፋርስ አንበሶች በጎች እና ፍየሎች ሳይጎዱ አብረው ተጓዙ; የሚሳቡ እንስሳትና አእዋፍ ኖኅ መርከቡን ወደሚሠራበት ቦታ አመሩ። ኖኅም አለቀሰ ሕዝቡንም “ንስሐ ግቡ! ጎርፉ እየመጣባህ ነው” አለው። እናም ይህን ሁሉ ሲያዩ፣ ቃሉን አልሰሙም እናም ትምህርቱን አልሰሙም የጥፋት ውሃ እስኪሸፍናቸው እና አስከፊ ሞት እስኪደርስባቸው ድረስ።

ወንድሞች ሆይ፣ እንፍራ፣ እነሆ፣ የተጻፈው ሁሉ ወደ ፍጻሜው እየመጣ ነው፣ እናም የተተነበዩት ምልክቶች እየፈተጸሙ ነውና። እና ከህይወታችን እና ከእድሜያችን ትንሽ የቀረ ነገር አለ።

ስለዚህ፣ መዳን የሚፈልግ፣ በትህትና፣ በመታቀብ እና በምጽዋት አሁን ይሥራ። ወዳጆች ሆይ፥ ማንም በወንበዴዎች እጅ ቢወድቅ ነፍሱ እንዲተርፍ ንብረቱንም በእነርሱ ፋንታ እንዲወስዱ እንዴት አዝኖ እንደሚለምን ተመልከቱ። ወንድሞች፣ ለመጥፎ ሕይወት ስንል ሁሉንም ነገር መጠቀማችን መጥፎ አይደለም፣ ነገር ግን ለመንፈሳዊ ጥቅማችን ግድ አንሰጥም? ለድሆች ስንሰጥ ለምን እንቆጫለን? ለምን ክፉውን ስራን አንተወውም እና ልባችንን ወደ ንስሃ ሕይወት ለምን አንመልስም?

😇 St. Serapion of Vladimir

St. Serapion of Vladimir (†1275) was archimandrite of the Kiev Caves Monastery from 1247 to 1274. He was then consecrated bishop of the Diocese of Vladimir, Suzdal, and Nizhny Novgorod, which he ruled until his repose the following year. At the time, the territory of the diocese consisted of the Grand Duchy of Vladimir and the principalities of Gorodets, Kostroma, Moscow, Pereslavl, Starodub, Suzdal, Nizhny Novgorod, and Yuriev. Five sermons from St. Serapion have been preserved, most believed to date from his time as a hierarch.

Brethren, fear the terrible and dread judgment of God, for that fearful day will come suddenly. If we don’t prepare ourselves with virtues, then naked and destitute we shall be condemned to unquenchable fire.

O brethren, live in the fear of God, for the time of this life is short and vanishes like smoke; and many calamities befall us for our sins, and no small sorrow: invasions of the heathen, agitation between people, the disorder of churches, unrest between princes, the lawlessness of priests who please only the flesh, taking no care for the soul. And abbots too. And the monks start to care about feasts, they become irascible and prone to rivalry, and they lead a life unbecoming of the Holy Fathers. The hierarchs cower before the powerful, they judge based on personal gain, they offend orphans and don’t intercede for widows and the poor. In the laity, there is unbelief and fornication; and abandoning the truth, they begin to create untruth.

But in such days, if anyone so desires, he will be saved and will be called great in the Kingdom of Heaven. For so it was in the days of Noah: They ate, they drank, they married, they fornicated, and the flood came and destroyed everyone for their iniquity. How awful to see such a fearful phenomenon! When Noah was building the ark as the Lord commanded him, then the elephants from India and lions from Persia traveled together with sheep and goats without harming each other; the reptiles and birds headed to where Noah was building the ark. And Noah wept and told the people: “Repent! The flood is coming for you.” And even seeing all this, they didn’t heed his words and didn’t listen to his teachings until the flood waters covered them and they suffered a wretched death. O brethren, let us be afraid, for behold, all that is written is coming to an end and the signs foretold are coming true. And there is already little left of our life and age.

Thus, whoever wants to be saved, let him labor now in humility, abstinence, and alms. For if anyone falls into the hands of robbers, beloved, then see how tenderly he entreats that his life be spared and that they take his property instead. How, brethren, is it not bad that for the sake of a bad life we are divested of everything, but we take no care for our spiritual benefit? Why do we regret giving to the poor? Why don’t we abandon evil deeds and why don’t we incline our hearts towards repentance?

👉 Courtesy: Orthochristian.com

______________

Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

An Iraqi Muslim Became a Christian After He Saw Jesus, Who Looks Like an Ethiopian, in a Dream

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on May 15, 2023

💭 ኢትዮጵያዊ የሚመስለውን ኢየሱስን በህልም ካየ በኋላ ኢራቃዊ ሙስሊም ክርስቲያን ሆነ

  • ✞ ኢራቃዊው የቀድሞ ሙስሊም በክርስቲያኑ ልዑል (ሲፒ)ፊት ሲመሰክር
  • ✞ The Iraqi Ex-Muslim testifying before Christian Prince (CP)

______________

Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

150-Year-Old Stained-Glass Window Reveals Jesus Christ With Dark Skin, Stirring Questions About Race

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on May 15, 2023

ኢትዮጵያ በ’ሰሜን ምስራቅ’ አፍሪቃ እንደምተገኘው፣ በ’ሰሜን ምስራቅ’ አሜሪካ በምትገኘዋ የሮድ አይላንድ ግዛት የ፻፶/150 አመት እድሜ ያለው ባለቀለም የመስታወት መስኮት ኢትዮጵያዊውን ኢየሱስ ክርስቶስን ያሳያል። ይህን እስካሁን ተሰውሮና ብዙ አትኩሮት ሳያገኝ ቀርቶ የነበረውን ክስተት ተከትሎ ስለ ዘር በጣም አነቃቂ ጥያቄዎች በመነሳት ላይ ናቸው።

በሃርቫርድ ዩኒቨርሲቲ የሥነ ጥበብ ታሪክ ምሁር ሃድሊ አርኖልድ በሮድ አይላንድ ቤተክርስቲያን ውስጥ የተገኘውና የ፻፶/150 አመት እድሜ ያለው ባለ መስታወት መስኮት ኢየሱስን እንደ ኢትዮጵያዊ ጠቆር ያለ ቆዳ ያለው ሰው እንደሆነ አድርጎ እንደሚያሳይ ተናግረዋል ።

..አ በ 1877 የተተገበረው መስኮት በዓይነቱ የመጀመሪያ ሊሆን ይችላል ብለው ምሑራኑ ያስባሉ። የሥነ ጥበብ ታሪክ ምሁር ቨርጂኒያ ራጊን ይህ በአሜሪካ ባሕል ውስጥ እንደ ዋና ምልክት ሆኖ ሊቆም ይገባዋልብለዋል።

ጠቆር ያለዉ ኢየሱስ ክርስቶስ በአዲስ ኪዳን ትዕይንቶች ከሴቶች ጋር ሲነጋገር የሚያሳየው ይህ በጽዮን ቀለማት የደመቀው መስታወት ስለ ዘረኝነት፣ ሮድ አይላንድ በባሪያ ንግድ ውስጥ ያላትን ሚና እንዲሁም የሴቶችን ቦታ በተመለከተ በ፲፱/19ኛው ክፍለ ዘመን የኒው ኢንግላንድ/አዲሷ የእንግሊዝ ማህበረሰብ የነበራትን አስትዋጽዖ ይጠቁማል።

ይህ ድንቅ የመስተዋት መስክቶ ስዕል የተሰቀለው በዋረን ከተማ ለረጅም ጊዜ በተዘጋው የቅዱስ ማርቆስ ኤጲስ ቆጶስ ቤተክርስቲያን እ... 1878 .ም ላይ ነበር።

በዎርሴስተር፣ ማሳቹሴትስ በሚገኘው የቅዱስ መስቀል ኮሌጅ የሰብአዊነት ፕሮፌሰር የሆኑት ቨርጂኒያ ራጊን እና የባለቀለም መስታወት ጥበብ ታሪክ ባለሙያዋ፤ “ይህ መስኮት ልዩ እና ያልተለመደ ነው፣ ይህን ምስል ለዛ ዘመን አይቼው አላውቅም።ብለዋል።

ባለ ፲፪/12 ጫማ ርዝመት እና ባለ ፭/5 ጫማ ስፋት ያለው ይህ መስኮት ሁለት የመጽሐፍ ቅዱስ ምንባቦችን ያሳያል። ሴቶቹም ጥቁር ቆዳ ያላቸውና ከክርስቶስ ጋር እኩል ሆነው ይታያሉ። አንዱ፡ ከሉቃስ ወንጌል፡ ክርስቶስ ከአልዓዛር እህቶች ከማርታ እና ከማርያም ጋር ሲነጋገር ያሳያል። ሌላው ደግሞ፡ ከዮሐንስ ወንጌል፡ ክርስቶስ ጉድጓድ አጠገብ ለሳምራዊቷ ሴት ሲናገር ያሳያል።

በእውነት ድንቅ ነው፤ እንግዲህ ከመቶ ሃምሳ ዓመታት በፊት ለወቅቱ በጭራሽ በማይታሰብ መልክ በአሜሪካ ኢትዮጵያዊኢየሱስ ክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ተስሎ ይታይ ነበር። አባቶቻችን ሲስሏቸው የነበሩትን ዓይነት ስዕሎችን ተከትሎ ነው የተሳለው። የጽዮን ቀለማቱም እንዲሁ።

አዎ! በዛሬዋ ዓለም ሕዝቦች ከመቼውም ጊዜ በከፋ የዘር ጉዳይ ላይ በጣም ስሜታዊና ጠበኞች እየሆኑ ነው። ባገራችንም በተቀሩት አገራትም የምናየው ነው። ሰሞኑን እንኳን መኖርና አለመኖሯ አጠራጣሪ የሆነችው የጥንታዊቷ ግብጽ ንግሥት ክሊዮፓትራ በኔትፍሊክስ ፊልም ላይ እንደ ጥቁር መሳሏ በግብጽና በመላው የምዕራቡ ዓለም ከፍተኛ ውዝግብ በማስነሳት ላይ ነው። እንዴት አንዲት ጥቁር ሴት የእኛ ንግሥት ሆና ፊልም ላይ ትታያላች?! ይህ በጭራሽ መሆን የለበትም፤ ክሊዮፓትራ ብሎንድ የጸጉር ቀለም የነበራት ግሪካዊት ነበረች…” እንግዲህ አሜሪካዊቷ ተዋናይ ክልስ ናት፤ እንደሚወራው ክሊዮፓትራም ክልስ ነበረች። ግን ምን ልዩነት አለው? ክሊዮፓትራን ጨምሮ የያኔዎቹ ግብጻውያን እኮ ወንጀለኞች ነበር፤ ታዲያ ማንም ድራማ ወይንም ቴአትር ቢሠራስ ምን ክፋት አለው? ታሪክ ተቀማን፤ ነው? የማን ታሪክ? የዛሬዎቹ ግብጻውያን ከኮፕቶች በቀር ሁሉም ወራሪ መሀመዳውያን አረቦች ናቸው። ለመሆኑ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ብሎንድና ሰማያዊ ዓይኖች ያሏቸው ተዋናውያን አልነበሩም እንዴ ሲወክሉት የነበሩት?! ንግሥታችንን ሳባን/መከዳን ለረጅም ጊዜ ሲወክሏት የነበሩት ነጭ ተዋናውያን አልነበሩምን? እንዴት ነው ከዚህ ሁሉ ዘመን በኋላ እንኳን ዛሬም በቆዳ ቀለም ላይ ያተኮረ ልዩነትን ፣ ጥላቻን እና ትንኮሳን የምታስተናግደው? በእውነት ይህ ስንፍና፣ ኋላ ቀርነትና ውድቀት እጅግ በጣም አሳፋሪ ነው!

ለማንኛውም፤ ይህን ድንቅ የጌታችንን ስዕል አመልክቶ ሌላው የሚገርመው ነገር ደግሞ ይህ የመስተዋት መስኮት ቅዱስ ማርቆስ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ የተገጠመ መሆኑ ነው። ባለፈው ሳምንት ልክ በዚህ በሰኞ ዕለት የሐዋርያው/ወንጌላዊው ቅዱስ ማርቆስን ዓመታዊ በዓል በዚህ መልክ አክብረነው ነበር፤

😇 ሐዋርያው ማርቆስን ያስገኘች ጽዮናዊቷ ኢትዮጵያ ናት | ፴ ሚያዝያ ቅዱስ ማርቆስ | ፻ኛ ዓመት

😇 የሐዋርያው/ወንጌላዊው ቅዱስ ማርቆስ ዓመታዊ በዓል 😇

👉 Related:

  • 2000 Year Old Ethiopian Christianity With The Dark-Skinned Jesus
  • Ethiopia’s oldest icon (1370-98) made in Byzantium, or Siena

👉 Courtesy: Associated Press

Harvard art historian claims 150-year-old stained glass window in Rhode Island church depicts Jesus as a person of color

  • A 150-year-old stained glass window that appears to show Jesus as a person of color has been uncovered in a Rhode Island church
  • The image is made using brown glass and was first spotted by Harvard art historian Hadley Arnold
  • Arnold has invited art historians and experts to view the window which is thought to be the first to ever depict Jesus as a person of color
  • Scholars think the window, commissioned in 1877, could be the first of its kind. ‘It should stand as a landmark in American culture,’ says art historian Virginia Raguin

A nearly 150-year-old stained-glass church window that depicts a dark-skinned Jesus Christ interacting with women in New Testament scenes has stirred up questions about race, Rhode Island’s role in the slave trade and the place of women in 19th century New England society.

The window installed at the long-closed St. Mark’s Episcopal Church in Warren in 1878 is the oldest known public example of stained glass on which Christ is depicted as a person of color that one expert has seen.

“This window is unique and highly unusual,” said Virginia Raguin, a professor of humanities emerita at the College of the Holy Cross in Worcester, Massachusetts, and an expert on the history of stained-glass art. “I have never seen this iconography for that time.”

The 12-foot tall, 5-foot wide window depicts two biblical passages in which women, also painted with dark skin, appear as equals to Christ. One shows Christ in conversation with Martha and Mary, the sisters of Lazarus, from the Gospel of Luke. The other shows Christ speaking to the Samaritan woman at the well from the Gospel of John.

The window made by the Henry E. Sharp studio in New York had largely been forgotten until a few years ago when Hadley Arnold and her family bought the 4,000-square-foot (371-square-meter) Greek Revival church building, which opened in 1830 and closed in 2010, to convert into their home.

When four stained-glass windows were removed in 2020 to be replaced with clear glass, Arnold took a closer look. It was a cold winter’s day with the sunlight shining at just the right angle and she was stunned by what she saw in one of them: The human figures had dark skin.

“The skin tones were nothing like the white Christ you usually see,” said Arnold, who teaches architectural design in California after growing up in Rhode Island and earning an art history degree from Harvard University.

The window has now been scrutinized by scholars, historians and experts trying to determine the motivations of the artist, the church and the woman who commissioned the window in memory of her two aunts, both of whom married into families that had been involved in the slave trade.

“Is this repudiation? Is this congratulations? Is this a secret sign?” said Arnold.

Raguin and other experts confirmed that the skin tones — in black and brown paint on milky white glass that was fired in an oven to set the image — were original and deliberate. The piece shows some signs of aging but remains in very good condition, she said.

But does it depict a Black Jesus? Arnold doesn’t feel comfortable using that term, preferring to say it depicts Christ as a person of color, probably Middle Eastern, which she says would make sense, given where the Galilean Jewish preacher was from.

Others think it’s open to interpretation.

The 12-foot tall, 5-foot wide window depicts two biblical passages in which women, also painted with dark skin, appear as equals to Christ.

“To me, being of African American and Native American heritage, I think that it could represent both people,” said Linda A’Vant-Deishinni, the former executive director of the Rhode Island Black Heritage Society. She now runs the Roman Catholic Diocese of Providence’s St. Martin de Porres Center, which provides services to older residents.

“The first time I saw it, it just kind of just blew me away,” A’Vant-Deishinni said.

Victoria Johnson, a retired educator who was the first Black woman named principal of a Rhode Island high school, thinks the figures in the glass are most certainly Black.

“When I see it, I see Black,” she said. “It was created in an era when at a white church in the North, the only people of color they knew were Black.”

Warren’s economy had been based on the building and outfitting of ships, some used in the slave trade, according to the town history. And although there are records of enslaved people in town before the Civil War, the racial makeup of St. Mark’s was likely mostly if not all white.

The window was commissioned by a Mary P. Carr in honor of two women, apparently her late aunts, whose names appear on the glass, Arnold said. Mrs. H. Gibbs and Mrs. R. B. DeWolf were sisters, and both married into families involved in the slave trade. The DeWolf family made a fortune as one of the nation’s leading slave-trading families; Gibbs married a sea captain who worked for the DeWolfs.

Both women had been listed as donors to the American Colonization Society, founded to support the migration of freed slaves to Liberia in Africa. The controversial effort was overwhelmingly rejected by Black people in America, leading many former supporters to become abolitionists instead. DeWolf also left money in her will to found another church in accord with egalitarian principles, according to the research.

Another clue is the timing, Arnold said. The window was commissioned at a critical juncture of U.S. history when supporters of Republican Rutherford B. Hayes and their Southern Democrat opponents agreed to settle the 1876 presidential election with what is known as the Compromise of 1877, which essentially ended Reconstruction-era efforts to grant and protect the legal rights of formerly enslaved Black people.

What was Carr trying to say about Gibbs’ and DeWolf’s links to slavery?

“We don’t know, but it would appear that she is honoring people of conscience however imperfect their actions or their effectiveness may have been,” Arnold said. “I don’t think it would be there otherwise.”

The window also is remarkable because it shows Christ interacting with woman as equals, Raguin said: “Both stories were selected to profile equality.”

For now, the window remains propped upright in a wooden frame where pews once stood. College classes have come to see it, and on one recent spring afternoon there was a visit from a diverse group of eighth graders from The Nativity School in Worcester, a Jesuit boys’ school.

The boys learned about the window’s history and significance from Raguin.

“When I first brought this up to them in religion class, it was the first time the kids had ever heard of something like this and they were genuinely curious as to what that was all about, why it mattered, why it existed,” religion teacher Bryan Montenegro said. “I thought that it would be very valuable to come and see it, and be so close to it, and really feel the diversity and inclusion that was so different for that time.”

💭 Selected Comments from NYPost:

  • – NBD. There is a famous mountain top cathedral near Avellino, Italy, with a portrait of a black Virgin Mary. The large painting has been there for centuries. It didn’t stop the Italians from doing their annual pilgrimage for the first communion of girls to womanhood. People need to get over themselves as if the world never existed before they got here.
  • – Who cares what color Jesus was when he was on earth? What matters is that we believe his message. He said the he is the way, the truth, and the life and no one comes to God but by him.
  • – Well he went to the cross for our sins… the ultimate sacrifice. So, His color is irrelevant. Plus it wouldn’t surprise me considering many Mediterranean Jews were/are of dark complexion.
  • – Of course Jesus was dark skinned. Everyone around that region was dark skinned 2000 years ago. Is this a real question?
  • – Every event that took place in the Bible took place in Ethiopia and Egypt (Africa). Which reflects the complexion of the Jesus displayed on the stain glass window. The first image depicting Jesus as non-African was by Leonardo da Vinci, which used a friend by the name of Cesare Borgia.(commision by King Louis XII of France). Do your own research I would start first by visiting the Vatican online and see for yourself all the biblical figures portrayed as white in America are in fact of dark skin complexion. At the end history is only factual when you do the research. If you don’t then, it’s whatever you believe it’s being told to you will be your historical fact but it will be wrong. Enjoy the rest of the year. Truth Serum.
  • P.S. Egypt is in Africa.
  • Eden/Africa is Ethiopia
  • Isreal and Palestine before “divided” are part of Africa.
  • The land of Canaan is in North Eastern Africa.

Facts are facts. There’s no rewriting history. It’s logical common sense period.

[Isaiah 53:2]

„For he grew up before him like a young plant, and like a root out of dry ground; he had no form or majesty that we should look at him, and no beauty that we should desire him.”

Looks is NOT the point when it comes to Jesus

______________

Posted in Curiosity, Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

ሐዋርያው ማርቆስን ያስገኘች ጽዮናዊቷ ኢትዮጵያ ናት | ፴ ሚያዝያ ቅዱስ ማርቆስ | ፻ኛ ዓመት

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on May 8, 2023

ከመቶ ዓመታት በፊት ይህን ውብ የቤተ ክርስቲያን ሕንፃ የሠራችለትም ( ፲፱፻፲፮ ዓ.ም/ 1916) ኢትዮጵያ ናት። ❖

😇 ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዓለም ላይ ካሰማራቸው ሐዋርያት መካከል ሐዋርያው ማርቆስ አንዱ ነው።

ሐዋርያው ማርቆስን በሚመለከት መሪራስ አማን በላይ “ሐዋርያው ማርቆስ ዜግነቱ ሮማያዊ ሲሆን፡ ትውልዱ ኢትዮጵያዊ ነው። በዚያን ጊዜ ግብጾች ቦታ አልነበራቸውም ሲሉ ተናግረዋል። ሐዋርያው ማርቆስ ቤተሰቦቹ ኢትዮጵያዊ ሲሆኑ ነዋሪነታቸው ግብጽና ኢየሩሳሌም እንደነበረ በታሪክ ተጠቅሷል።

አባ ተስፋ ሞገስ፡ ቅዱስ ማርቆስ ኢትዮጵያዊ ነው መድኃኔ ዓለም ኢየሱስ ክርስቶስ የይሑዳ አንበሳ ነው ሲሉ መጽሐፍ ጽፈዋል። ቅዱስ ማርቆስ ኢትዮጵያዊ ነው መድኃኒዓለም ኢየሱስ ክርስቶስ የይሑዳ አንበሳ ነው የተባለው መጽሐፍ ገጽ 100 ላይ “ማርቆስ ሙሉ በሙሉ ኢትዮጵያዊ ነው” ሲሉ ጽፈዋል። እኒህ አባት ሐዋርያው ማርቆስን ብቻ ሳይሆን ሌሎች ሐዋርያት ኢትዮጵያዊ ደም ያላቸው መሆናቸውን በማመለከት ከፍ ተብሎ በተጠቀሰው መጽሐፍ ገጽ 42 ላይ፡ “ከኢትዮጵያውያን ዘር የሚወለደው ፊልጶስም ነው” ሲሉ ሁለቱ ሐዋርያት ከጌታችን ጋር ያደረጉትን የቃላት ልውውጥ በሚመለከት ጽፈዋል።

ከዚህ ላይ ማየት ያለብን እነዚህ የኢትዮጵያ ሕዝቦች ቀድሞ ጀምረው ራሳቸውን ዝቅ የሚያደርጉና ለክብር የማይሮጡ በመሆናቸው ማንነታቸው ሊታወቅ አልቻለም። እንኳን ቀድሞ በቅርቡ የዳ/ዊ አጤ ቴዎድሮስን ታሪክ የፃፉት አንዱ ደራሲ መጽሐፉን የዘመኑ የታሪክ ሊቃውንቶችን ጥቅስ ለመውሰድ ሲሉ “የማይታወቀው ደራሲ” እንደጻፈው እየተባለ ነው የሚጠቀሰው። የጥንት ኢትዮጵያውያን “እወቁልን” የማይሉ በመሆናቸው ብዙ የታሪክ አባቶቻችን ስምና ታሪክ ተደብቆ ቀርቷል። በዚህ ባለንበት አገር አሉ ከሚባሉት ሊቆች መካከል ለአንዱ የሊቀ–ጠበብት ማዕረግ ዩኒቨርስቲው ሲሰጣቸው አስተዳዳሪው ለተሰብሳቢው እንግዳ እንዲህ ብለው ነበር፦

ኢትዮጵያውያን ይህን ሰርተናል የማይሉ በስራቸው እንጂ ለወረቀት የማይጓጉ በመሆናቸው ይህ ዶ/ር እገሌ እንደሌሎች ዶክተሮች ማመልከቻ ይዞ ወደ ጽሕፈት ቤቱ መጥቶ አስቸግሮኝ አያውቅም። የስራውን ጥራትና ብቃት ዩኒቨርስቲው በማየቱ የሌቀ–ጠበብት ማዕረግ ሰጥቶታል” ብለዋል።

ትቤ አክሱም ገጽ 67 “ቅዱስ ማርቆስም ያባቱን ሀገር አስቀድሞም ያውቀው ስለነበረ መጥቶ እንዳስተማረ” ሲሉ ጽፈዋል። ከዚህ ላይ የኢትዮጵያውያን ከቀድሞ ጀምሮ የመጣው ታሪክ የሚያመለክተው ለክርስትና ሐይማኖት ከፍተኛ ተጋድሎ ማድረጋቸውን ነው። ሐዋርያው ማርቆስን የመሰለ መምሕር ያስገኘች ኢትዮጵያ ናት። ላይ እንደተጠቀሰው ዛሬ ድረስ በህይወት ያሉ ደራሲያን ኮሎኔልነታቸውን፣ ጠበብትነታቸውን ወይም ሊቅነታቸውን ሳይጠቅሱ መጽሐፍ የጻፉ ደራሲያን ነበሩ። ምክኒያቱም ኢትዮጵያውያን አብዛኛው እወቁኝ የማይሉ ናቸው። በዚህ ምክንያት ከቀድሞ ጀምሮ ተያይዞ በመምጣቱ ሐዋርያው ማርቆስ ኢትዮጵያዊ መሆኑ ሳይታወቅ ኖሮ ነበር።

መሪራስ አማን በላይ፡ “ጉግሣ” መጽሔት ቅጽ 2 ቁጥር 3 መጋቢት 1993 .. ገጽ 17 ላይ “የማርቆስን አክስት ማለት የበርናባስንና የአርስጦሎስን እህት ጴጥሮስን አግብቶ ነበር። እንዲሁሙ ዜግነቱ ኢትዮጵያዊ የቤተ እስራኤል የሌዊና የይሑዳ ነገድ የሆነ ወደ ቀሬና ቀራኒዮ ወደ ቤተ መቅደስ ሊሰግድ መጥቶ ስሙም ስምዖን ይባል ነበር። በበነጋታው ከአባቱና ከናቱ ዘመድ ከስምዖን ጋር ማርቆስ የጌታችንን የክርስቶስን ግርፋትና ሕማማቱን እየተከተለ ተምልክቷል። አጎቱንም የአባቱን ዘመድ ኢትዮጵያዊ ስምዖን የተባለ የቀሬና ሰው የጌታን መስቀል እንዲሸከም አይሑዳ ሊያስገድዱት አይቷል ተመልክቷል” ሲሉ ጽፈዋል። ስምዖን ኢትዮጵያዊ መሆኑን የሚያረጋግጥበት ምክንያት ስምዖን ኢትዮጵያዊ መሆኑን የሚያረጋግጥበት ምክንያት ስምዖን ጥቁር መሆኑን በሌሎችም ታሪክ ታውቋል።

ሐዋርያው ማርቆስ ኢትዮጵያዊ ስለሆነና ታሪኩን ስላወቁ ቀዳማዊ አጤ ኃይለ አጽሙ አጽሙ ቬነስ ግዛት / ከተማ ከሚቀር ግብጽ መግባት ይኖርበታል ብለው ከቬነስ መንግሥትና ቤተ ክርስቲያን ጋር ያደረጉት ጥረት ቀላል አይደለም። ቀደም ሲል ግብጾች ሊያስመልሱ ያልቻሉትን አጤ ኃይለ በጥረታቸው የቅዱስ ሐዋርያው ማርቆስ አጽም ወደ አፍሪቃዋ ግብጽ እንዲገባ ሆነ። ይህ ታሪክ በመሆኑ ሊገለጽ የሚገባው ሲሆን፡ ጃንሆይ መሠረት ያደረጉት ዋናው ነጥብ ሐዋርያው ቅዱስ ማርቆስ በዘሩ ኢትዮጵያዊ በመሆኑ ነው።

የአጤ ኃይለ ታሪክ” ከሚለው መጽሐፋቸው ገጽ 1132 ላይ “ሐዋርያው ቅዱስ ማርቆስ ወደ ግብጽ ገብቶ ክርስትናን በማስተማር ላይ እያለ የክርስቲያኖችን ዕምነት የሚጠሉና በጣዖት የሚያመልኩ ከብዙ ጊዜ ጀምሮ ለምደውት ለቆየው አምላካቸው በጣም ቀናኢ የሆኑ በአሌክሳንድርያ መንገድ ላይ እየጎተቱ አሰቃይተው ገደሉት። እንደሞተም አሌክሰንድርያ በሚገኘው ቤተ ክርስቲያን ቀበሩት። በዚህ ቦታ ተቀብሮ ለብዙ ዘመን ከቆየ በኋላ በ820 .ም ሁለት የቬኑስ ነጋድያን አጽሙን በድብቅ ከተቀበረበት አስወጥተው ወደ ቬነስ ነጋድያን አጽሙን በድብቃ ከተቀበረበት አስወጥተው ወደ ቬነስ ወሰዱት በዚህ ከተማ በሚገኘው በቅዱስ ማርቆስ ቤተ ክርስቲያን አኑረውት ቦታው የበላይ ቅዱስ ሆኖ በክብር ይኖር ነበር። ስለሆነም የግብጽ ቤተ ክርስቲያን እንዲሰጣት በየጊዜው ከመጠየቅ አልቦዘነችም ነበር። ግርማዊ ንጉሠ ነገሥታት ቀዳማዊ ኃይለ ም ለግብጽ እንዲመለስ ብዙ ጊዜ ጠይቀዋል።

ነገር ግን ሁሉም የሚፈጸመው እግዚአብሔር በፈቀደው ጊዜ ስለሆነ ጊዜው ሲደርስ የሮማው ርዕሠ ሌቀ ጳጳስ ጳውሎስ 6ኛ ስለፈቀዱ በሞተ በ1900 በተወሰደ 1140 ዓመት ወደ ጥንተ ቦታው ለመመለስ በቃ።” ካለ በኋላ አጽሙ የገባበትን ቀን ሲገልጹና ጃንሆይም በስፍራው መኖራቸውን ሲያብራሩ ገጽ 1133 ላይ፡ “የቅዱስ ማርቆስ አጽም ከቬነስ ወደ ግብጽ የገባው ግርማዊ ንጉሠ ነገሥት በአለበት ሰኔ 17 ቀን 1960 .ም ነው።” ብለዋል።

የሐዋርያው ማርቆስ አጽም ግብጻውያን ራሳቸው ካልሸጡት አልያም ጠቋሚ ካልሆኑ ቁጥራቸው ትንሽ በሆነ ነጋዴዎች ተሰርቆ ሊወሰድ አይችልም። መሠረቱን ካወቁ ጀምሮ አጽሙን ለማስመለስ ብዙ ሙከራ ቢያደርጉም አልተሳካላቸውም ነበር። በዚህ ምክንያት የሐዋርያው ማርቆስን አጽም ለማስመለስ የቻሉት ኢትዮጵያዊው ቀዳማዊ አጤ ኃይለ ናቸው። ያም በመጀመሪያ ጌታ ሲወለድ የእጅ መንሻ የሰጡ ሰብዓ ሰገል ኢትዮጵያውያን ሲሆኑ ኋላም ጌታችን በስደት መጥቶ የኖረባት ስትሆን ተመልሶም መጥቶ ወንጌልን ያስተማረባት አገር ናት። ከዚያም በጅሮንድ ጃንደረባ ባኮስ በ34 .ም ተጠምቆ ተመልሶ ወንግጌልን ያስተማረባት ኢትዮጵያ አገራችን ናት።

______________

Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

ስምህን በማይጠሩ መንግሥታት ላይ በማያውቁህም አሕዛብ ላይ መዓትህን አፍስስ፤ ያዕቆብን በልተውታልና፥ ስፍራውንም ባድማ አድርገዋልና

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on May 7, 2023

አንተም የዘንዶውን ራሶች ቀጠቀጥህ፤ ለኢትዮጵያ ሰዎችም ምግባቸውን ሰጠሃቸው

❖❖❖[መዝሙረ ዳዊት ምዕራፍ ፸፫]❖❖❖

  • ፩ አቤቱ፥ ስለ ምን ለዘወትር ጣልኸኝ? በማሰማርያህ በጎች ላይስ ቍጣህን ስለ ምን ተቈጣህ?
  • ፪ አስቀድመህ የፈጠርሃትን ማኅበርህን፥ የተቤዤሃትንም የርስትህን በትር፥ በእርስዋ ያደርህባትን የጽዮንን ተራራ አስብ።
  • ፫ ጠላት በቅዱሳንህ ላይ እንደ ከፋ መጠን፥ ሁልጊዜም በትዕቢታቸው ላይ እጅህን አንሣ።
  • ፬ ጠላቶችህ በበዓል መካከል ተመኩ፤ የማያውቁትንም ምልክት ምልክታቸው አደረጉ።
  • ፭ እንደ ላይኛው መግቢያ ውስጥ በዱር እንዳሉም እንጨቶች፥ በመጥረቢያ በሮችዋን ሰበሩ።
  • ፮ እንዲሁ በመጥረቢያና በመዶሻ ሰበሩአት።
  • ፯ መቅደስህን በእሳት አቃጠሉ፤ የስምህንም ማደሪያ በምድር ውስጥ አረከሱ።
  • ፰ አንድ ሆነው በልባቸው በየሕዝባቸው። ኑ፥ የእግዚአብሔርን በዓሎች ከምድር እንሻር አሉ።
  • ፱ ምልክታችንን አናይም ከእንግዲህ ወዲህም ነቢይ የለም፤ እስከ መቼ እንዲኖር የሚያውቅ በኛ ዘንድ የለም።
  • ፲ አቤቱ፥ ጠላት እስከ መቼ ይሳደባል? ስምህን ጠላት ሁልጊዜ ያቃልላልን?
  • ፲፩ ቀኝህንም በብብትህ መካከል፥ እጅህንም ፈጽመህ ለምን ትመልሳለህ?
  • ፲፪ እግዚአብሔር ግን ከዓለም አስቀድሞ ንጉሥ ነው፥ በምድርም መካከል መድኃኒትን አደረገ።
  • ፲፫ አንተ ባሕርን በኃይልህ አጸናሃት፤ አንተ የእባቦችን ራስ በውኃ ውስጥ ሰበርህ።
  • ፲፬ አንተም የዘንዶውን ራሶች ቀጠቀጥህ፤ ለኢትዮጵያ ሰዎችም ምግባቸውን ሰጠሃቸው።
  • ፲፭ አንተ ምንጮቹንና ፈሳሾቹን ሰነጠቅህ፤ አንተ ሁልጊዜ የሚፈስሱትን ወንዞች አደረቅህ።
  • ፲፮ ቀኑ የአንተ ነው ሌሊቱም የአንተ ነው፤ አንተ ፀሓዩንና ጨረቃውን አዘጋጀህ።
  • ፲፯ አንተ የምድርን ዳርቻ ሁሉ ሠራህ፤ በጋንም ክረምትንም አንተ አደረግህ።
  • ፲፰ ይህን ፍጥረትህን አስብ። ጠላት እግዚአብሔርን ተላገደ፥ ሰነፍ ሕዝብም ስሙን አስቈጣ።
  • ፲፱ የምትገዛልህን ነፍስ ለአራዊት አትስጣት፤ የችግረኞችህን ነፍስ ለዘወትር አትርሳ።
  • ፳ ወደ ኪዳንህ ተመልከት፥ የምድር የጨለማ ስፍራዎች በኅጥኣን ቤቶች ተሞልተዋልና።
  • ፳፩ ችግረኛ አፍሮ አይመለስ፤ ችግረኛና ምስኪን ስምህን ያመሰግናሉ።
  • ፳፪ አቤቱ፥ ተነሥ በቀልህንም ተበቀል፤ ሰነፎች ሁልጊዜም የተላገዱህን አስብ።
  • ፳፫ የባሪያዎችህን ቃል አትርሳ፤ የጠላቶችህ ኵራት ሁልጊዜ ወደ አንተ ይወጣል።

❖❖❖[መዝሙረ ዳዊት ምዕራፍ ፸፰]❖❖❖

  • ፩ አቤቱ፥ አሕዛብ ወደ ርስትህ ገቡ፤ የቅድስናህንም መቅደስ አረከሱ፥ ኢየሩሳሌምንም እንደ መደብ አደረጉአት።
  • ፪ የባሪያዎችህንም በድኖች ለሰማይ ወፎች መብል አደረጉ፥ የጻድቃንህንም ሥራ ለምድር አራዊት፤
  • ፫ ደማቸውንም በኢየሩሳሌም ዙሪያ እንደ ውኃ አፈሰሱ፥ የሚቀብራቸውም አጡ።
  • ፬ ለጎረቤቶቻችንም ስድብ ሆንን፥ በዙሪያችንም ላሉ ሣቅና ዘበት።
  • ፭ አቤቱ፥ እስከ መቼ ለዘላለም ትቈጣለህ? ቅንዓትህም እንደ እሳት ይነድዳል?
  • ፮ ስምህን በማይጠሩ መንግሥታት ላይ በማያውቁህም አሕዛብ ላይ መዓትህን አፍስስ፤
  • ፯ ያዕቆብን በልተውታልና፥ ስፍራውንም ባድማ አድርገዋልና።
  • ፰ የቀደመውን በደላችንን አታስብብን፥ ምሕረትህ በቶሎ ታግኘን፥ እጅግ ተቸግረናልና።
  • ፱ አምላካችንና መድኃኒታችን ሆይ፥ እርዳን፤ ስለ ስምህ ክብር፥ አቤቱ፥ ታደገን፥ ስለ ስምህም ኃጢአታችንን አስተሰርይልን።
  • ፲ አሕዛብ፥ አምላካቸው ወዴት ነው? እንዳይሉ፥ የፈሰሰውን የባሪያዎችህን ደም በቀል በዓይኖቻችን ፊት አሕዛብ ያወቁ፤
  • ፲፩ የእስረኞች ጩኸት ወደ ፊትህ ይግባ፤ እንደ ክንድህም ታላቅነት ሊገደሉ የተፈረደባቸውን አድን።
  • ፲፪ አቤቱ፥ የተዘባበቱብህን መዘባበታቸውን ለጎረቤቶቻችን ሰባት እጥፍ በብብታቸው ክፈላቸው።
  • ፲፫ እኛ ሕዝብህ ግን፥ የማሰማርያህም በጎች፥ ለዘላለም እናመሰግንሃለን፤ ለልጅ ልጅም ምስጋናህን እንናገራለን።

______________

Posted in Ethiopia, Faith, War & Crisis | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

ዓርብ ስቅለት በደብረ ቤቴል አበ ብዙሃን-አብርሃም ገዳም | የማይረሳ መንፈሳዊ ዕለት

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on April 14, 2023

✞✞✞ ዓርብ ስቅለት (የድኅነት ቀን) –የዕዳ ደብዳቤያችን በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ለመጨረሻ ጊዜ የተደመሰሰበት፤ ከአጋንንት አገዛዝ ነጻ የወጣንበት ዕለት✞✞✞

ዓርብ ስቅለት የዕዳ ደብዳቤያችን በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ለመጨረሻ ጊዜ የተደመሰሰበት፤ ከአጋንንት አገዛዝ ነጻ የወጣንበት ዕለት ስለኾነ ‹የድኅነት ቀን› ይባላል፡፡

ጌታችን ከተያዘባት ሰዓት አንሥቶ አይሁድ ከቀያፋ ወደ ሐና፣ ከሐና ወደ ቀያፋ ሲያመላልሱት አደሩ፡፡ ሲነጋ ከቀያፋ ወደ ጲላጦስ አደባባይ አስረው ወሰዱት (ማቴ. ፳፯፥፩-፶፯)፡፡ አይሁድ ይህን አጥፍቶአል የሚሉት ነጥብ ሳይኖራቸው ነውና ጌታችንን ለፍርድ ያቀረቡት ጲላጦሰ እነርሱ ወደ ተሰባሰቡበት ቦታ ወጥቶ “ይህን ሰው ወደ እኔ ያመጣችሁበት በደል ምንድን ነው?” ሲል በጠየቃቸው ጊዜ በቂ ምላሽ አላቀረቡም፡፡

“ክፉ የሠራ ባይኾንስ ወደ አንተ ባላመጣነውም ነበር” በሚል የሸፍጥ ቃል ሲያጕረመርሙ ጲላጦስ መልሶ “እኔ ምንም ጥፋት አላገኘሁበትም፤ እናንተ ወስዳችሁ እንደ ሕጋችሁ ፍረዱበት፤” አላቸው፡፡ አይሁድም ኦሪት “ኢትቅትል ብእሴ ጻድቀ ወኀጥአ ኢታኅዩ፤ጻድቅን ሰ ውአትግደል፤ኀጥኡንም ከፍርድ አታድን፤” ትላለችና “እኛስ ማንንም ልንገድል አልተፈቀደልንም፤” ብለዋል (ዮሐ. ፲፰፥፳፰-፴፩)፡፡ ይኸውም መንፈስ ቅዱስ “በሕጋችን ጻድቀ ባሕርይ ክርስቶስን መግደልአ ይገባንም ሙሉ በሙሉ ጥፋተኞች ነን፤” ሲያሰኛቸው ነው፡፡ በኋላም እርሱ ሞቶ ዓለም ይድን ዘንድዳ ምድር መጥቷልና ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ያለ ጥፋቱ ሞት ተፈረደበት፡፡ ስለዚህም ገርፈው ሰቀሉት፡፡

ዓርብ ስቅለት | ተፈጸመ! | ከአጋንንት አገዛዝ ነጻ ወጣን

ልክ አሁን የሕማማተ መስቀልን ፀሎት አንብቤ እንደጨረስኩ፤ ከጎረቤቴ ሕንጻ ጣራ ላይ ፲፫ ርግቦች ተነስተው በዙሪያዬ አንድ ጊዜና በአንድ ላይ ጅው ብለው በመብረር የተነሱበት ጣራ ላይ ተመልሰው አረፉ። ተገርሜ በመመሰጥ፤ “ምን የሚሉኝ ነገር ሊኖር ይችላል?” የሚለውን ጥያቄ ጠየቅኩ። ፲፫/13ቱ ሕማማተ መስቀል?

ዓርብ ስቅለት የዕዳ ደብዳቤያችን በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ለመጨረሻ ጊዜ የተደመሰሰበት፤ ከአጋንንት አገዛዝ ነጻ የወጣንበት ዕለት ስለኾነ “የድኅነት ቀን” ይባላል፡

✞ ፲፫ቱ ሕማማተ መስቀል

  • ፩ኛ. ተአስሮ ድኅሪት (ወደኋላ መታሰር)
  • ፪ኛ. ተስሕቦ በሐብል (በገመድ መሳብ)
  • ፫ኛ. ወዲቅ ውስተ ምድር (በምድር ላይ መውደቅ)
  • ፬ኛ. ተከይዶ በእግረ አይሁድ (በእግረ አይሁድ መረገጥ)
  • ፭ኛ. ተገፍዖ ማዕከለ ዓምድ (ከምሶሶ ጋር መላተም)
  • ፮ኛ. ተጽፍዖ መልታሕት (በጥፊ መመታት)
  • ፯ኛ. ተቀስፎ ዘባን (ጀርባን በጅራፍ መገረፍ)
  • ፰ኛ. ተኰርዖተ ርእስ (ራስን በዱላ መመታት)
  • ፱ኛ. አክሊለ ሦክ (የሾህ አክሊል መድፋት)
  • ፲ኛ. ፀዊረ መስቀል (መስቀል መሸከም)
  • ፲፩ኛ. ተቀንዎ በቅንዎት (በችንካር መቸንከር)
  • ፲፪ኛ. ተሰቅሎ በዕፅ (በመስቀል ላይመሰቀል)
  • ፲፫ኛ. ሰሪበ ሐሞት (መራራ ሐሞትን መጠጣት)

✞ ጌታችን ሲሰቅል የሚከተሉት ሰባት ተአምራት ተፈጽመዋል፤

  • ፩. ፀሐይ ጨለመ፤
  • ፪. ጨረቃ ደም ኾነ፤
  • ፫. ከዋክብት ረገፉ፤
  • ፬. የቤተ መቅደስ መጋረጃ ተቀደደ፤
  • ፭. አለቶች ተፈረካከሱ፤
  • ፮. መቃብራት ተከፈቱ፤
  • ፯. ሙታን ተነሡ (ማቴ. ፳፯፥፶፩-፶፬)፡፡

✞ ጌታችን በመስቀል ላይ ሳለ የሚከተሉትን ሰባት ዐበይት ቃላት አሰምቶ ተናግሯል፤

  • ፩. “ኤሎሄ ኤሎሄ ላማ ሰበቅታኒ (አምላኪየ አምላኪየ ለምን ተውኸኝ?)”፤
  • ፪. “እውነት እውነት እልሃለሁ፤ ዛሬ ከእኔ ጋር በገነት ትኖራለህ”፤
  • ፫. “አባት ሆይ የሚያደርጉትን አያውቁትምና ይቅር በላቸው”፤
  • ፬. እመቤታችንን “ሴትዮሆይ፣እነሆ ልጅሽ” ደቀ መዝሙሩንም “እናትህ እነኋት” በማለት የቃል ኪዳን እናትነትና ልጅነት ማከናወኑ፤
  • ፭. “አባት ሆይ በአንተ እጅ ነፍሴን አደራ እሰጣለሁ”
  • ፮. “ተጠማሁ”፤
  • ፯. “ዅሉ ተፈጸመ” (ማቴ. ፳፯፥፵፭-፵፮፤ ሉቃ. ፳፫፥፵፫-፵፮፤ ዮሐ. ፲፱፥፲-፴)፡፡

ከሰድስት ሰዓት እስከ ዘጠኝ ሰዓት ጨለማ ኾኖ ከቈየ በኋላ ከዘጠኝ እስከ ማታ እንደ ተለመደው ብርሃን ሁኖአል፡፡ ወፍናሠር ክይበርህ ብርሃነ ፀሐይእንዲል (ዘካ. ፲፬፥፯)፡፡ በዚህ ዕለት ሰባት መስተፃርራን (ጠበኞች) ታረቁ፤ ተስማሙ፡፡ እነዚህም፡- ሰውና እግዚአብሔር፣ ሰውና መላእክት፣ ሕዝብና አሕዛብ፣ ነፍስና ሥጋ ናቸው (ኤፌ. ፪፥፲፤ ቈላ. ፩፥፳)፡፡ ጌታችን ጠዋት በሦስት ሰዓት ተገረፈ፤ በስድስት ሰዓት ተሰቀለ (ማቴ. ፳፯፥፩-፴፯፤ ሉቃ. ፳፫፥፩-፵፬፤ ዮሐ. ፲፱፥፩)፡፡

ጌታችን በውኃው ተጠምቀን፣ ደሙን ተቀብለን የእግዚአብሔር ልጆች እንኾን ዘንድ ከቀኝ ጎድኑ ጥሩ ውኃ፣ ትኩስ ደም አፈሰሰልን (ዮሐ. ፲፱፥፴፬)፡፡ በዐሥራ አንድ ሰዓት ዮሴፍና ኒቆዲሞስ ከመስቀል አውርደው ሽቶ እየረበረቡ በድርብ በፍታ ገንዘው ቀበሩት (ሉቃ. ፳፫፥፶-፶፬፤ ዮሐ. ፲፱፥፴፰-፵፪)፡፡ ነፍሱ ወደ ሲኦል ወርዳ ነፍሳትን ነጻ አወጣች (፩ኛ ጴጥ. ፫፥፲፱)፡፡ በዚህ ጊዜ በርሃነ መለኮቱ በሲኦል ተገለጠ፡፡ ስለዚህም “ንሴብሖ ለእግዚአብሔርእየተባለ ይዘመራል፡፡ ከሆሣዕና አንሥቶ ተከልክሎ የነበረው ኑዛዜ ይናዘዛል፤ ጸሎተ ፍትሐት ይደረጋል፡፡

ወስብሐት ለእግዚአብሔር፡፡

ምንጭ

______________

Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

Holy Thursday Ceremony of The Ethiopian Church in Golgotha, Jerusalem Where Jesus Was Crucified

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on April 14, 2023

❖ CHURCH OF THE HOLY SEPULCHRE in Jerusalem, Israel ❖

______________

Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

Double Moon During Hossana ( Palm Sunday ) Celebrations

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on April 9, 2023

🌿𝐇𝐚𝐩𝐩𝐲 𝐇𝐨𝐬𝐚𝐧𝐧𝐚 (𝐏𝐚𝐥𝐦 𝐒𝐮𝐧𝐝𝐚𝐲)!🌿

Hossana ( Palm Sunday ) is celebration of entry of Jesus to Jerusalem riding a donkey. Children in Jerusalem sang Hossana praising Jesus Christ. Source: cnewa.org. The day is celebrated in a peculiar way. It’s very common to see laity wearing cube shaped palm ring and wearing palm stripe on the head.

The Feast of Hosanna -Palm Sunday has been celebrated in Ethiopia since the earliest days of Christianity. Celebrated a week before Easter, the day marks the beginning of the Holy Week and commemorates the triumphal entry of Jesus Christ with his disciples into Jerusalem. On this day Ethiopian Orthodox laities wear headbands of palm leaves, a reminder of the palm leaves that were laid by a huge crowd of people when Jesus arrived at Jerusalem. The best place to observe this ceremony in Ethiopia is at Entoto St. Mary Church in Addis Ababa and St. Mary Zion Church in Axum, where on the 28th November 2020 Muslim soldiers from Ethiopia, Eritrea and Somalia armed by Iran, UAE and Turkey went on the rampage and massacred over 1000 Orthodox Christians.

Axum, a Holy City in Ethiopia’s northern Tigray region, whose main Church of Our Lady Mary of Zion is believed by Ethiopian Orthodox Christians to hold The Biblical Ark of Covenant.

______________

Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

የሆሣዕና ፳፻፲፫ ዓ.ም + የ፳፻፲፪ ዓ.ም ተዓምር በጨረቃ ላይ

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on April 9, 2023

🌴 ሆሣዕና በአርያም | ሰማያዊ ልዑል አምላክ ትሑት ሆኖ ተገለጠ 🌴

ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በአህያ ጀርባ ተቀምጦ ወደ ኢየሩሳሌም ገባ።

______________

Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

 
%d bloggers like this: