ያውም ገዳማቱ መግቢያ መግቢያ ቦታ ላይ ነው እንዲበቅል የተደረገው…
ወንድማችን ትክክል ነው፤ ከእምቦጩ አረም መብቀል ጋር በተያያዝ ሤራው የተጠነሰሰው በየኢትዮጵያ ጠላቶች ነው። ይህ አያጠራጥረን! እንዲያውም ይህ በአይናችን ለማየት የበቃነው አንዱ ክስተት ብቻ ነው። መታየትና መታወቅ ያለባቸው ገና ብዙ ብዙ ነገሮች አሉ። ጎብኚዎች ብቻ ሳይሆኑ የአረሙ ተካዮች፡ በዚያ በኩል የሚይልፉ አውሮፕላኖች በእነ ዋልድባ፣ አክሱም፣ ላሊበላ፣ ጊሸን፣ ዝቋላ፣ ቍልቢ በኩል እያለፉ መርዛቸውን በውሃና ደኑ ላይ ይረጫሉ። በአባቶቻችን ጊዜ ተደጋግሞ ይከሰት የነበረው የወሎና ትግራይ ድርቅ መንስዔ በዚህ መልክ ነበር የተካሄደው።
ወንድማችን እንዳወሳው፡ ከመቶ አመት በፊት አንስቶ ወደ ውጭ አገር እየተላክንና ስለ ጠላቶቻችንን ተንኮል ለመማርና ለማወቅ እድሉ ያለን “ኢትዮጵያውያን” ይህን ሤራ ለማጋለጥ ፈቃደኞች አለመሆናችን ሁልጊዜ የሚከነክነኝና የሚያሳዝነኝ ጉዳይ ነው። በኢትዮጵያውያን የዘር ውርስ ወይም ጀነቲክስ ላይ ምርምር የሚያካሂድ አንድ የስታንፎርድ ወይም ኬምብሪጅ ዩኒቨርሲቲ ምሩቅ “ኢትዮጵያዊ” ለምሳሌ ሴቶቻችንን መኸን ለማድረግ ሕጻናቶቻችን ለማኮላሸት የተጠነሰሰ ሤራ እንዳለ በደንብ ነው የሚያውቀው። ታዲያ እንዴት ነው፡ በድብቅ እንኳን ለሕዝባችን ሹክ ከማለት የተቆጠቡት? በጣም ያሳዝናል፡ ለንስሃ እንኳን ሳንበቃ የዶክተርና የማስተርስ ማዕረጉን ይዘን ወደ አፈር ውስጥ መግባታችን እኮ ነው።
ድንቅ ሥራ እየሠራችሁ ነው እኅቶቻችን እና ወንድሞቻችን፤ እግዚአብሔር ይስጥልን!!!