Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • June 2023
    M T W T F S S
     1234
    567891011
    12131415161718
    19202122232425
    2627282930  
  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

Posts Tagged ‘እመ ብርሃን’

ሰይጣን ጥልቅ ጉድጓድን አስቆፍሮ ፀሐይን (መስቀሉን) ለመሰወር ሞክሮ ነበር

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on October 1, 2020

ነገር ግን ዲያብሎስ ድካሙ ከንቱ ሆኖ ቀረ ፥ ፀሐይን መስወር አይቻልም፤ ፀሐይን ማጥለቅም ማውጣትም የሚቻለው እግዚአብሔርን ብቻ ነው ፥ ስለዚህ ፀሐይን መሰወር እንደማይቻለው ሁሉ፤ ዓለምን ያበራው፣ ጨለማውን ዓለም ያስወገደ እውነተኛው ፀሐይ የተባለ መስቀል ተቆፍሮ ተቀብሮ አልቀረም፤ መስቀል ወጥቷል፣ የምንበላውን የምንጠጣውን አስገኘትቶልናል።

ግሩም ነው፤ ይህ ትምህርት የተሰጠው ዓምና ልክ በዛሬው ዕለት መስከረም ፳፩ / ፪ሺ፲፪ .ም በ እመቤታችን ክብረ በዓል ወቅት በመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም / ፭ኪሎ አዲስ አበባ ፥ ዓ.ም ነበር።

የሚገርም ነው! ልክ ከዓመት በኋላ በኦሮሚያ ሲዖል ውዳቂዎቹ የዋቄዮ-አላህ ልጆች መስቀሉን ጉድጓድ ቆፍረን እንቀብረዋለን ብለው ዛቱ።

__________________________

Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , | Leave a Comment »

የታገቱትንና የተገደሉትን በማስታወስ “አቤቱ የሆነብንን አስብ!” ብለን በመጮህ ወደ ኪዳነ ምሕረት እንቅረብ

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on February 24, 2020

እህቶቻችን ከጠፉ ልክ ዛሬ ፹ (ሰማንያ) ቀናት ሆነዋቸዋል።

ባለፈው ቅዳሜ በመስቀል አደባባይ ወደ ተካሄድው የቴዲ አፍሮ የሙዚቃ ኮንሰርት የአዲስ አበባ ወጣቶች ምን ፈልገው፣ ምን አቅደው እንደሄዱና ለሃገራቸውም ምን በጎ ነገር እንዳመጡም የማውቀው ነገር የለም። ነገር ግን እህቶቻችን ከደንቢደሎ ዩኒቨርሲቲ እልም ብለው በጠፉበት ማግስት፤ ተዋሕዶ የአዲስ አበባ ልጆች በቤተ ክርስቲያናቸው ውስጥ በግፍ በተረሸኑበት ማግስት፤ ጌታችን በተሰቀለበት መስቀል ስም በተሰየመበት ቦታ ላይ ለዳንኪራ እና ጭፈራ በመውጣት የመምህር ምሕረተአብን የማንቂያ ደወል ለማቆምና የገዳይ አብይን አጀንዳ ለማስፈጸም ወጥተው ከሆነ እጅግ በጣም ነው የማዝነው። ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የሰጠን የመስቀል ስር ስጦታ የሆነችው ውዷ እናታችን ቅድስት ድንግል ማርያምም እንደ እናትነቷ አብዝታ ታዝንባቸዋለች።

ይህ ዕለት እናታችን ቅድስት ኪዳነ ምሕረት ከልጇ ቃል ኪዳን የተቀበለችበት ቀን ነው። የእመቤታችን ቃል ኪዳን ለየት ያለ ነው። ለየት የሚለውም በሁለት ዐበይት ምክንያቶች ነው። የመጀመሪያው እርሷ ምልዕተ ፀጋ በመሆኗና ፍጽምት ርህርህተ ሕሊና ከመሆንዋ የተነሣ ስለ ሰው ልጆች አብዝታ የማለደች እናት እና ክርስቲያኖች ሁሉ ይድኑ ዘንድ ከሌሎቹ በተለየ የለመነች በመሆንዋ ነው።እንኳን እግዚአብሔር ጨካኙ ዳኛ እንኳን አብዝታ ለለመነችው መበለት ያደረገውን እናውቃለንና።(ሉቃ. ፲፰፡፩)

ሁለተኛው ምክንያት ደግሞ ወላዲተ አምላክ ለመባል የበቃች ከእርስዋ በቀር ሌላ የሌለ፤ በዚህም መልዕልተ ፍጡራን ትሆን ዘንድ አምላክ ያከበራት በመሆንዋ ልዩ ቃል ኪዳን ይገባላት ዘንድ የተገባት ናት። ለአምላክ እናትነት(ልዩ) ሆና መመረጧን ለሚያምን ሁሉ ልዩ ቃል ኪዳን መቀበሏ ጥያቄ አይሆንበትም። ስለዚህም ልዩ ቃል ኪዳን ተገብቶላታል። ነቢዪ ኢሳይያስ ወይወጽእ እምጽዮን መድኅን ወየዐትት ኃጢአተ እም ያዕቆብ ወዛቲ ይእቲ ኪዳኖሙ እንተ እምኀቤየ ይቤ እግዚአብሔር፦ መድኅን (ክርስቶስ) ከጽዮን ይወጣል (ከእመቤታችን ይወለዳል)፣ ኃጢአትንም ከያዕቆብ (ከእስራኤል ዘነፍስ) ያርቃል፤ ለእስራኤል የማልሁላቸው መሐላ የገባሁላቸው ቃልኪዳንም ይህቺ ናት፤ ሲል እንደተናገረ እግዚአብሔር ልዩ ውልና ስምምነት ከእስራኤል ዘነፍስ ጋር አለው።(ኢሳ.፶፱፡፳፳፩) ከዚህ ውስጥ አንዱና ዋናው ከእመቤታችን ጋር ያደረገው ነው።

ይህ ኪዳን ልዩ ከሆነበት ነገሩ አንዱ የራሱ መታሰቢያ ዕለት ያለው መሆኑ ነው። ዕለቱም ጌታችን በጌቴሰማኒ ተገልጾ ኪዳኑን የገባበት ዕለት ነው፤ ይኸውም የካቲት ፲፮ ቀን ነው። እመቤታችን ከላይ እንደተገለጸው ወደ ጎልጎታ ወደ ጌታ መቃብር እየሄደች አብዝታ ትለምን ነበር። በዚህም ምክንያት መላእክት ወደ ሰማያት አሳርገው ገነትንና ሲዖልን አስጎብኝተዋታል። እርስዋም በሲዖል ያሉ ነፍሳትን አይታ በእጅጉ አዝናላቸዋለች፤ ከዚህም በኋላ ስለ ኃጥአን አብዝታ ስትለምን ጌታችን አምላካችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዚች ዕለት ተገልጾ ልዩ የምሕረት ቃልኪዳን ስለገባላት ኪዳነ ምሕረት እየተባለች ትከበራለች።

እኛም ከዚህ እጅግ ሊያስተውሉት ከሚገባ ታላቅ መልእክት የምናገኘው ትልቅና ታላቅ ቁም ነገር እግዚአብሔር ከመረጣቸውና ካከበራቸው ጋር እንዴት ቃል ኪዳን እንደሚያደርግ ሲሆን አብዝተው ለጠየቁትና ለተማጸኑት የቅርብ አምላክ እንጂ የሩቅ አምላክ አለመሆኑን ማሳየቱና ጸሎታቸውንና ልመናቸውን ሰምቶ ምላሽ መስጠቱን ነው። ስለሆነም አምላካችን ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ቃል ኪዳን ከገባላት የመስቀል ስጦታ እናታችን በረከትን ለማግኘት ዘወትር በተሰበረ ልብና በተዋረደ መንፈስ መቅረብ ያስፈልጋል። ነቢዩ ኤርምያስ “አቤቱ የሆነብንን አስብ” ብሎ እንደጮኸው ጩኸት እያንዳንዳችን የምሕረት ቃል ኪዳንን ወደተቀበለች ወደ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም እንቅረብ። ልዑል እግዚአብሔር ንጉሥ ሰሎሞንን ስለ አባትህ ስለ ዳዊት ስል በትረ ንግሥናህን ከአንተ አልወስድም ብሎ ቃል እንደገባለት እኛም የዘላለም ቃል ኪዳን ስለገባላት ስለ ቅድስት ድንግል ማርያም ሲል እንዲምረን ፍጹም ትህትናን ገንዘብ አድርገን እግዚአብሔር ያከበራቸውን አክብረን መገኘት ይኖርብናል። በዚህ ታላቅ ፆምም በረከትን ለማግኘት ፆማችንን ከግብር ጋር አገናኝተነው ደካሞች የሚረዱበትን፣ ታማሚዎች የሚጠየቁበትን፣ እስረኞች የሚጎበኙበትን፣ የታረዙ የሚለብሱበትን፣ የተራቡ የሚጠግቡበትን፣ የተጠሙ የሚጠጡበትን መንገድ ለማመቻቸት የተዘጋጀን መሆን ይኖርብናል። ከሥራ የተለየ እምነት የሞተ ነው ብሎ ሐዋርያው ያዕቆብ እንደተናገረ እኛም ፆምንና ምፅዋትን አስማምተን ለበጎ ሥራ የተዘጋጀን እንድንሆን አምላካችን በቸርነቱ ይርዳን፤ እመቤታችን በተገባላት ቃል ኪዳን ትጠብቀን።

ወ ስ ብ ሐ ት ለ እ ግ ዚ አ ብ ሔ ር

___________________________

Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , | Leave a Comment »

ተዓምረ ማርያም | Statue Of Mary Miraculously Survives Hurricane Harvey

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on August 29, 2017

እግዚአብሔር አምላክ ብዙ ድንቅ የሆኑ ምልክቶችን እያሳየን ነው፤ ዓይን ያለው ይመልከት፤ ጆሮ ያለው ይስማ!

በፖርቱጋሏ ማዴራ ደሴት የፍልሰታ ማርያም በዓል በሚከበርበት ወቅት አንድ የ200 ዓመት እድሜ ያለው ዛፍ ወድቆ የ11 ሰዎች ህይወት ማለፉን በትናንትናው ዕለት ጽፌ ነበር፡ እዚህ ይመልከቱ(ነፍሳቸውን ይማርላቸው፤ ህፃናቱ በቀጥታ ወደ ገነት ይገባሉ፤ ለእኛ ግን ምልክት ይሆነን ዘንድ የተከሰተ ይመስለኛል)

A statue of the Virgin Mary was the only item to withstand a devastating fire that destroyed three Corpus Christi-area homes during Hurricane Harvey.

The homeowner noted the significance of a holy statue of the Blessed Mother remaining standing through the ongoing disaster.

Some may blame God and some may blame the hurricane, but the only thing standing were holy things,” Natali Rojas told local NBC affiliate KRIS. “As you can see, this statue is the only thing that survived. I dug in there for things and all I found is a Virgin Mary.”

The Rojas family prepared their homes and evacuated as Harvey approached. But an electrical fire broke out in one of the houses when the storm hit, and the category 4 hurricane’s high winds caused the fire to spread to all three on the property before firefighters could respond. All three homes were completely destroyed.

Search and rescue has continued around the clock, and officials have said it will be some time before the full extent of the storm’s destruction and resulting fatalities are known.

Natali’s father, Jesus Rojas, was thankful that no lives were lost in the fire and stressed the importance of faith and family.

“I believe that throughout my life I’ve suffered a lot. We were migrants,” Jesus Rojas said. “We worked all of our lives in fields and trying to show our families how to stay strong, how to believe in God and keep everybody together as a family.”

Natalie Rojas expressed gratitude as well.

“The first thing I thought is we would have died in here if we would have stayed,” she said. “We left, so we’re alive and I just wish this wouldn’t have happened.”

They thanked the Robstown Fire Department for doing all it could in an impossible situation and said it took courage for the firefighters to come out and try their best during the hurricane.

The appearance of the family’s Our Lady of Guadalupe statue as the sole item remaining among the rubble of their home in the middle of so much devastation provided a powerful image of hope.

“Appreciate what you have,” Natali Rojas said, “listen to the warnings, hug your children, and thank God for today and yesterday, and pray for a better tomorrow.”

Source

______

Posted in Ethiopia, Faith, Life | Tagged: , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

 
%d bloggers like this: