Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • June 2023
    M T W T F S S
     1234
    567891011
    12131415161718
    19202122232425
    2627282930  
  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

Posts Tagged ‘እህተ ማርያም’

የኢትዮጵያ አየር መንገድን ለባዕዳኑ አሳልፈው ለመስጠት የተዘጋጁት እነ ዶ/ር አህመድ ማን ፈቀደላቸውና ነው?

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on June 12, 2019

ባለፈው ዓመት ላይ ሕዝብ ያለመረጠውና ለማ መገርሳ የተባለው ፖለቲከኛ የኢትዮጵያ አየር መንገድን፣ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክን እና የኢትዮጵያ ቴሌኮምን ለመሸጥ በድብቅ ወደ ጀርመን ሄዶ እንደነበር እኅተ ማርያም ጠቁማን ነበር። የጉዞው ዋና ዓላማ ኢትዮጵያን ቀስበቀስ ማጥፋት ይቻላቸው ዘንድ የኤኮኖሚ ጥቅም ያስገኝልናል በሚል የማታለያ ስልት በቅድሚያ “ኢትዮጵያ” የሚለውን ቃል የያዙትን ሦስቱን ተቋማት ለኢትዮጵያ ጠላቶች ማስረከብ ነው።

እንደዚሁ ከወራት በፊት በኢትዮጵያ ሕዝብ ያለተመረጠው አብይ አህመድ የተባለ ፖለቲከኛ ይህን ጉዳይ አስመልክቶ ከፈረንሳዩ ባላጋሩ ኤማኑኤል ማክሮን ጋር የሚከተለውን መግለጫ አውጥቶ ነበር፦

Joint Declaration Between PM Abiy and President Macronበጥቂቱ:

Both States welcome the intensification of the French Development Agency’s activities in Ethiopia. For this purpose, France and Ethiopia have signed two declarations of intent regarding:

  • the support to Ethiopian Airlines investment program;
  • Macron and Abiy also pledged to increase cultural cooperation, especially on World Heritage sites such as the rock-hewn churches of Lalibela. France will contribute to the maintenance and renovation of the site, Abiy said.
  • Macron announced he will visit Ethiopia in March. (M & M = Mason)

የእነዚህ ከሃዲዎች ዕቅድ “ኢትዮጵያ” የሚለውን ስም ለማጥፋት ነው። ሰሞኑን እንደምንሰማው፤ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክን እያዘረፉ የውጭ ምንዛሬ እጥረት ገጠመን ይላሉ፣ በኢትዮጵያ ቴሌኮም ደግሞ አስፈላጊውን ግልጋሎት የመስጠት አቅም የለውም ለማለት የስልክ መስመሮችን ሆን ብለው ይቆራርጣሉ፣ የኢንተርኔት ግኑኝነት እንዳይኖር አገልጋዮችን ይዘጋሉ። በኢትዮጵያ አየር መንግድም እንደዚሁ አደጋዎች እንዲዘወትሩ እየተደረገ ነው። “አልቻልንም፤ ባካችሁ እርዱን!” ለማለት፤ የአውሬውን Problem – Reaction – Solution ፎርሙላ በመጠቀም።

ለመሆኑ እነዚህ ሕብ ያልመረጣቸው የቀበሌ ፖለቲከኞች ምን መብት አላቸው የኢትዮጵያ አየር መንገድን የመሰለ የሰባዓመትእድሜያለውያገራችንኩራትን ለባዕዳኑ አሳልፈው ለመስጠት የተዘጋጁት? ማን ፈቀደላቸውና?

አዳዲስ መረጃዎች፦

  • + በኢትዮጵያ የኢንተርኔት ግንኙነት ጠቅላላ ቆመ

    Total Internet shutdown in Ethiopia

  • + የኢትዮጵያ ቴሌኮምን እነዚህ ባዕዳውያን ተቋማት ሊወርሱት ነው ይለናል አሁን የወጣው ዜና፤

ወራሾቹ፦

  • + ደቡብ አፍሪቃ

  • + ፈረንሳይ

  • + የተባበሩት አረብ ኤሚራቶች

Ethiopia Plans To Issue Telco Licences by Year-End

Vodafone, South African operator MTN, France’s Orange and Etisalat of the United Arab Emirates are likely to be among the leading contenders vying for entry into the Ethiopian market.

__________________

Posted in Conspiracies, Ethiopia, Infos | Tagged: , , , , , , , , , | Leave a Comment »

ትንቢተ እኅተ ማርያም በሥራ ላይ | ዶ/ር አብይ ወደ አውሮፓ የሄዱት “ኢትዮጵያን” ለመሸጥ ነውን?

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on October 31, 2018

ጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ ፈረንሳይን እና ጀርመንን በመጎብኘት ላይ ናቸው። ፈረንሳይና ጀርመን የአውሮፓው አውሬ ዋንኛ ቀንዶች ናቸው። የ ዶ/ር አብይ ጉብኝት የአቶ ለማ መገርሳን ፊርማ ለማጽደቅ ነውን?

እኅተ ማርያም የምትለንን በጥሞና እናዳምጥ፦

ከጥቂት ወራት በፊት ለማ መገርሳ የኢትዮጵያ አየር መንገድን፣ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክን እና የኢትዮጵያ ቴሌኮምን ለመሸጥ በድብቅ ወደ ጀርመን ሄዶ ነበር፤ የተፈለገውም ሦስቱ ድርጅቶች መጠሪያ ላይ “ኢትዮጵያ” የሚለው ቃል ስላለ፡ ኢትዮጵያን ለመሸጥ ነው። ለሦስት ጀርመናውያን ኢትዮጵያን ወክሎ ፊርማውን ፈርሞላቸዋል። ከእነዚህ ሦስት ጀርመናውያን መካከል ሁለቱ የሰው ልጆች ሲሆኑ ሦስተኛው ግን የሰው ዘር አይደለም።”

Joint Declaration Between PM Abiy and President Macron በጥቂቱ:

Both States welcome the intensification of the French Development Agency’s activities in Ethiopia. For this purpose, France and Ethiopia have signed two declarations of intent regarding:

  • the support to Ethiopian Airlines investment program;
  • Macron and Abiy also pledged to increase cultural cooperation, especially on World Heritage sites such as the rock-hewn churches of Lalibela. France will contribute to the maintenance and renovation of the site, Abiy said.
  • Macron announced he will visit Ethiopia in March. (M & M = Mason)

ልጅአልባዎቹና ሰዶማውያኑ መሪዎቻቸው፤ ሜርከልና ማክሮን (M & M) እንኳን ለእኛ ሊቆረቆሩ ቀርቶ ለራሳቸው ዜጎች የማያስቡ፤ የሉሲፈራውያንን ቡድኖች ፍላጎት ከማሟላት በቀር ለመጭው ትውልዳቸው የማይጨነቁ እርኩስ መሪዎቹ እንደሆኑ በመደቆስ ላይ ያሉት ሕዝቦቻቸው ይመሰክራሉ። ፕሪዚደንት ማክሮን በፈረንሳይ፣ አንጌላ ሜርከል በጀርመን የተጠሉ ፖለቲከኞች ናቸው።

አንጌል ኤሊዛቤል ሜርከል ያው በትናንትናው ዕለት ከፖለቲካው ዓለም ለመሰናበት ቃል ገብተዋል (አንድ ቀን፡ ከወስላታው ማክሮን ጋር የአውሮፓው ህብረት መሪ ለመሆን ስለሚፈልጉ ምናልባት ከሃላፊነትና ተጠያቂነት ለመሸሽ በማሰብ ሊሆን ይችላል፤ ሆኖም፡ የኢትዮጵያ አምላክ መልአክቱንና መልዕክቱን ልኳል፤ ዶ/ር አብይ ጀርመንን በሚጎበኙበት ዋዜማ)

ሰዶማውያን የተደሰቱበት፣ እነ ሜርከል፣ ማክሮን፣ ሜይ እና መሀመዳውያን (4 x M) የሚያሞካክሹትና የሚደግፉት የእኛ መሪ ለሕዝባችን በጎ ነገር ሊሠራ በፍጹም አይችልም፤ በጭራሽ አይሆንም!!!

እህታችን በእውነት ትልቅ መልዕክት ነበር ባለፈው ነሐሴ ወር ላይ ያስተላለፈችልን። እንመናት፤ አውሮፓና አሜሪካ ውስጥ ሰውመሰል ፍጥረታት በየቦታው አሉ፤ በእብራይስጡ ኔፌሊም፣ በግዕዙ ደግሞ ረዓያት ከሚባሉት የወደቁ መላዕክት የተገኙ ዘሮች በመካከላችን አሉ ማለት ነው።

በመጽሐፈ ሄኖክ ላይ ግዕዙ “መላእክት ውሉደ ሰማያት” የሚል መጠሪያን ይጠቀማል። ይህም ሲተረጎም የሰማያት ልጆች መላእክት ማለት ይሆናል። አንደ ማስረጃ ከሚጠቀሱት ጥቅሶች መካከል እንመልከት፡

የሰው ልጆች ከበዙ በኋላ እንዲህ ሆነ። በእነዚያ ወራት መልከ መልካሞችና ደመ ግቡዎች ሴቶች ልጆች ተወለዱላቸው። የሰማይ ልጆች መላእክትም እነርሱን አይተው ወደዷቸው። እርስ በርሳቸውም – “ኑ ለእኛ ከሰው ልጆች ሴቶችን እንምረጥ፤ ለእኛም ልጆችን እንውለድ” አሉ። አለቃቸው ስማዝያ – “እኔስ ይህ ሥራ ይሠራ ዘንድ ምናልባት አትወድዱ እንደ ሆነ እፈራለሁ። የዚህችም ታላቅ ኀጢያት ፍዳ ተቀባይ እኔ ብቻ እሆናለሁ” አላቸው። “ይችን ምክር እንዳንለውጣት÷ ይችንም ምክር ቁም ነገር እንድናደርጋት ሁላችን መሐላ እንማማል፤ እርስ በእርሳችንም እንወጋገዝ” ብለው ሁሉም መለሱለት። ያንጊዜም ሁሉም አንድ ሆነው ማሉ፤ እርስ በርሳቸውም በነገሩ ተወጋገዙ፤ ሁሉም ሁለት መቶ ሆኑ። አርዲስ ወደሚባል ቦታም ወረዱ፤ ይኸውም የኤርሞን ተራራ ራስ ነው።” [ሄኖክ21-7]

ይህ መጽሐፈ ሄኖክ በእነዚህ “መላእክት” ተብለው በተገለጹት እና በሰው ልጆች መካከል የነበረው ጾታዊ ተራክቦ ውጤት የነበሩትን “ኔፊሊም” ወይም “ረዓይት” ስለተባሉት ፍጥረቶች ሲገልጽ እንዲህ ይላል፡

እነርሱም ፀንሰው ረጃጅሞች ረዓይትን ወለዱ። ቁመታቸው ሦስት ሦስት ሺህ ክንድ ነበር። እነዚህም ሰዎች እነርሱን መመገብ እስኪሳናቸው ድረስ ሰው የደከመበትን ሁሉ በሉ። ረዓይትም ሰዎችን ይበሏቸው ዘንድ ተመለሱባቸው። በወፎችና በአራዊት÷ በሚንቀሳቀሱና በዓሳዎቸም ይበድሉ ዘንድ ጀመሩ። እርስ በርሳቸውም ሥጋቸውን ተባሉ፤ ከእርሷም ደምን ጠጡ። ያንጊዜም ምድር ዐመፀኞችን ከሰሰቻቸው።” ሄኖክ [212-16]

የ ረዓይቶች ዝርያው ስኮትላናዳዊው ነፃግምበኛ ጄምስ ብሩስ መጽሐፈ ሄኖክንና ሌሎችንም የኢትዮጵያ ንብረቶችን ሠርቆ መውሰዱን አንረሳም።

አሁን መጠየቅ ያለብን፡ የተመረጡትን ጨምሮ፡ ብዙ ኢትዮጵያውያንን በአስገራሚ መልክና ፍጥነት ያሳቱት የእኛስ መሪዎች ከእነዚህ የረዓይት ዘሮች የተገኙ ይሆኑን? ወይስ ሊቁ አባታችን መሪራስ አማን በላይ “መጽሐፍ ብሩክ፤ ዣንሸዋ ቀዳማዊ” በሚለው ድንቅ መጽሐፋቸው ላይ እንደገለጹት “በኢዩር ሰማይ ክልል ውስጥ ከአሉት አሥራ ሁለት ዓለሞች ስም መካከል፡ “ሰውድ” የሚባለው ዓለም ይገኝበታል።” ብለው እንደገለጹት መሪዎቻችን ከሰውድ ዓለም ነውን የተገኙት?

______

Posted in Ethiopia, Faith, Infos | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

እኅተ ማርያም | የእግዚአብሔርን ቃል ደግፉ ፤ መንግስት ብቻ አይደለም ለአገራችን ውድቀት ተጠያቂው፡ ሕዝብም እንጂ

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on June 24, 2018

የእመቤታችን አሥራት አገር ኢትዮጵያ፡ መሠረቷ ክርስቶስ ነው!

ወገኖች መንግስቱን ዘረኛ ነው እያሉ፡ “ነፃነት ባለበት” ውጭ አገር እንኳን ሳይቀር በጎሣ ተከፋፍለዋል። አይገርምም! ከተዋሕዶ ትግሬ መሪ ሙስሊም ኦሮሞ መሪ የተመረጠበት ግዜ ላይ ደርሰናል፤ ሆይሆይ የሚለውን ሰው ብዛት ስናይ፡ ለስላሳው ፀረክርስቶስ ጨረቃዋን መጎተት ሲጀምር ምን ያህል ተከታይ እንደሚኖረው መገመት አያዳግተንም። የሚፈለገው ይህ ነው፤ አላማውም ያ ነው።

ሰው በኢትዮጵያ መሠረት ላይ (ትግራይ ነው የሚገኘው) ጥላቻ እንዲኖረው በማድረግ መሬት መንቀጥቀጥ መፍጠር መቻል፡ ነው አላማው። በዚህም መልክ በተዋሕዶ ሃይማኖት አማኙ ህዝብ መካከል ልዩነትን ለመፍጠር ሙከራ ተደርጓል። ላለፉት ሺህ ዓመታት ጦርነቱ፣ ረሃቡና በሽታው ሁሉ ይከሰት የነበረው በወሎ ላሊበላ አካባቢ እና በትግራይ ነው። በዱሮ ጊዜ ጣዖት አምላኪዎችን (ራያ) ወደ ሰሜኑ የኢትዮጵያ ክፍል አምጥተው አስፈሩ፤ በኋላ ላይ ደግሞ የደርግ መንግስት ትግርኛ ተናጋሪ ክርስቲያኖችን ከትግራይ በማፈናቀል በደቡቡ ኢትዮጵያ ለማስፈርና ትግራይን ከተዋሕዶ ለማጽዳት ሞክሯል። Problem – Reaction – Solution” ብሎታል፡ ተንኮለኛው ፈላስፋ ሄገል።

ልክ በአይሁዶች በኩል የእስራኤልን መሠረት ለመነቅነቅ እንደሚሞክሩት፡ አሁን በአገራችንም በትግሬዎች በኩል የኢትዮጵያን መሠረት ነቅንቀው ለማፍረስ እየታገሉ ነው። ይህ ቁልጭ ብሎ እየታየ ነው።

______

Posted in Curiosity, Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

እኅተ ማርያም | እስልምና ለኢትዮጵያ ምን አበርክቷል? የእስራኤል አምላክ በኢትዮጵያ ላይ የእስልምና ስግደት በቃ ብሏል

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on May 19, 2018

ተወዳዳሪ የሌለው፣ ክርስቲያን ነን የምንል ሁሉ ደጋግመን ልናስተላልፈው የሚገባን እጅግ በጣም ድንቅ፣ ድንቅ መልዕክት ነው!!!

ቃለ ሕይወት ያሰማልን፤ እህታችን!

ይድረስ፡ በመሀመድ ለተሠረቁትና ለጠፉት የኢትዮጵያ በጎች፤

እስልምና ኢትዮጵያዊነት አይደለም፤ ኢትዮጵያዊነት እስልምናነት አይደለም! ካለባበስ ጀምሮ ምናችሁ ነው ኢትዮጵያዊነታችሁን የሚያሳየው?

በቀን ሰባት ጊዜ መስገዳችሁ በቤታችሁ ምን አመጣላችሁ? እስኪ እራሳችሁን ጠይቁ!

ብትታመሙ እኮ ቅድስት ቤተክርስቲያን ጸበል መጥታችሁ እኮ ነው የምትጠመቁት። መምህር ግርማ ጋር መጥታችሁ ስንቶቻችሁ ተፈውሳችኋል?! ምክኒያቱ በመስጊዳችሁ መፍትሄ ስለሌለ አይደለምን? ምክኒያቱም አምላክ ብላችሁ የምትሰግዱለት እግዚአብሔር አምላክ አይደለምና ነው፣ ሆኖም አያውቅም፣ ሊሆንም አይችልም! የእናንተ አምላክ ከሞት አያነሳም! በቀን ሰባቴ እየሰገዳችሁለት ምንም ምልክት አያሳያችሁም! እስኪ ተንበርከኩና ህሊናችሁን ጠይቁ፤ የእናንተ አምላክ ሦስት ምልክት መስጠት አይችልም። ሦስት ምልክት በትክክል መስጠት የሚችል የእግዚአብሔር መንፈሥ ቅዱስ ብቻ ነው። በየጸበል ቦታ የምትታዩት እናንተ ናችሁ።

በቀን ሰባት ጊዜ የምትሰግዱለት አምላክ ምን ሰጣችሁ? ይህን ሁሉ ጊዜ ስታመልኩት በህይወታችሁ ምን ለውጥ አመጣላችሁ? እስኪ አዕምሯችሁን ልቦናችሁን ጠይቁት፤ ውስጣችሁ ምን ሰላም አገኛችሁ?

እግዚአብሔር የመጣው ሕዝብን ባጠቃላይ ለማዳን ነው። የእምነት መሪዎቻችሁ፡ ሕዝብን በቀን ሰባት ጊዜ ለጣዖትና ለመሀመድ የምታሰግዱ፤ ወዮላችሁ! ተብላችኋል። የእስራኤል አምላክ በኢትዮጵያ ላይ የእስልምና ስግደት በቃ ተብለናል።

መስጊድ ማብዛታችሁ የኢትዮጵያን ኦርቶዶስ ተዋሕዶ ሃይማኖት ለማጥፋት ነው። አይሳካላችሁምና አትድከሙ!

በኢትዮጵያ ላይ መስጊድ አይኖርም፤ መስጊድ ይነሳል፤ ምልክቱን ታያላችሁ፤ መስጊዶቹንም እራሳችሁ ታፈርሳላችሁ፤ እግዚአብሔር በመስጊዶች ላይ ቁጣውን ያሳያል!

በቀን ሰባቴ እየሰገዳችሁ ለኢትዮጵያ ምን አደረጋችሁላት? የምታጤሱት እጣን እንኳን ሽታው መዓዛው የማይረባ ነው። እስኪ እዩት እራሳችሁ! ኢትዮጵያውያኖች ሆናችሁ ሌላ እምነት መያዝ ምን ይሉታል?! እነ ሳዑዲ አረቢያ የራሳቸው ጉዳይ፤ ግን በኢትዮጵያ ላይ ይህ ዓይነት አምልኮ ምን ይሉታል? አዎ! ተሸፋፍኖ መሄድ ደስ ይላል፤ ግን ስንቶቻችሁ ናችሁ የውስጥ እርካታ ያገኛችሁበት?! እስኪ ወደ ሰማይ እዩና እውነተኛውን አምላክ ተገለጽልን ብላችሁ ለምኑት፤ አናግረን መሃይሞች ነን በሉት!

በእስልምና እምነት ያላችሁ ስግደጃችሁ በቃ፤ የምትሰግዱለት አምላክ መልዕክት የለውም፣ ኃይል የለውም፣ አቅም የለውም!!! አቅም ያለው የቀራንዮ አምላክ፣ ሞትን ድል አድርጎ የተነሳው አብ፣ ወልድ፣ መንፈስ ቅዱስ ብቻ ነው!”

______

Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , | Leave a Comment »

RT ክርክር | ኢትዮጵያ ከ 150 ዓመታት በፊት የተሠረቁትን ንብረቷን እንድትመልስ እንግሊዝን ጠየቀች

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on April 29, 2018

የማርያም መቀነቱን ምልክት ላለማየት፣ የነጎድጓዱን ድምጽ መልዕክት ላለመስማት አሻፈረኝ እያሉ ነው፤ የእንግሊዙ ጋዜጠኛ ትዕቢትና ግትርነት “የ ሌባ ዓይን ደረቅ መልሶ ብ ያደርቅ!” ያሰብላል

ኤግዚቢሽ የተዘጋጀው በለንደን ከሚገኘው የኢትዮጵያ ማኅበረሰብ ጋር በመመካከር ነው….መብታችን ነው፡ ኢትዮጵያ እንደ ኢራቅና ሶርያ ህግ አልባ ልትሆን ስለምትችል እዚህ መቆየት አለበት….ቅብርጥሴ.”

ምን እያዘጋጁልን እንደሆነ ልብ በሉ!

የቀማኞቹ የዔሳውና እስማኤል ዘሮች እኛን ከማታለል፣ እርስበርስ ከማዳቆስና ከማባላት አያርፉም

ትንቢተ ሚክያስ ምዕራፍ ፪:

በመኝታቸው ላይ በደልን ለሚያስቡ ክፋትንም ለሚያደርጉ ወዮላቸው! ኃይል በእጃቸው ነውና ሲነጋ ይፈጽሙታል።

በእርሻው ላይ ይመኛሉ፥ በግዴታም ይይዙታል፤ በቤቶችም ላይ ይመኛሉ፥ ይወስዱአቸውማል፤ ሰውንና ቤቱን፥ ሰውንና ርስቱንም ይነጥቃሉ።

ስለዚህ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል። እነሆ፥ በዚህ ወገን ላይ በክፉ አስባለሁ፥ ከዚያም አንገታችሁን አታነሡም፤ ዘመኑም ክፉ ነውና ቀጥ ብላችሁ አትሄዱም።

በዚያ ቀን በምሳሌ ይመስሉባችኋል፥ በጽኑ ልቅሶም ያለቅሱላችኋል፤ እነርሱም። ፈጽመን ጠፍተናል፤ የሕዝቤን እድል ፈንታ ይሰፍራል፥ እርሱንም የሚከለክል የለም፤ እርሻችንን ለዓመፀኞች ይከፍላል ይላሉ።

ስለዚህ በእግዚአብሔር ጉባኤ መካከል በዕጣ ገመድ የሚጥል አይኖርህም።

ትንቢት አትናገሩ ብለው ይናገራሉ፤ በእነዚህ ላይ ትንቢት አይናገሩም፥ ስድብም አይርቅም።

የያዕቆብ ቤት የተባልህ ሆይ፥ በውኑ የእግዚአብሔር መንፈስ የማይታገሥ ነውን? ወይስ ሥራው እንደዚች ናትን? ቃሌስ በቅን ለሚሄድ በጎነት አያደርግምን?

ነገር ግን ከቅርብ ጊዜ ጀምሮ ሕዝቤ እንደ ጠላት ሆኖ ተነሥቶአል፤ ቀሚስንና መጐናጸፊያን ገፈፋችሁ፤ ሳይፈሩም፤ የሚያልፉትን ከሰልፍ እንደሚመለሱ አደረጋችኋቸው።

የሕዝቤንም ሴቶች ከተሸለሙ ቤቶቻቸው አሳደዳችኋቸው፤ ከሕፃናቶቻቸውም ክብሬን ለዘላለም ወሰዳችሁ።

በዚህ ዕረፍት የላችሁምና ተነሥታችሁ ሂዱ፤ በርኵሰት ምክንያት ክፉ ጥፋት ታጠፋችኋለች።


Ethiopia Demands UK Return Pillaged Treasure Taken 150 Years Ago (DEBATE)


Ethiopia is calling for the return of valuable artefacts plundered by British forces 150 years ago. The East African treasures are currently on display at the Victoria and Albert Museum in London.

The country has demanded that all of the looted antiquities be sent back to Ethiopia on a permanent basis, refusing an offer of a long-term loan by the V&A Museum.

Among the treasures are a gold crown and chalice seized by British forces during the Battle of Maqdala in 1868 after troops ransacked the fortress of Emperor Tewodros II. The items were sold to raise money for the British military and were first exhibited in 1872.

Crown, probably made in Gondar, Ethiopia, around 1740 © Victoria and Albert Museum, London

The V&A announced in February it was staging an exhibition with the looted treasure, reigniting the diplomatic row. Addis Ababa first requested the artefacts back in 2007, according to Ethiopian Minister of Culture and Tourism Hirut Woldemariam.

Tristram Hunt, director of the Victoria and Albert Museum (V&A), says the exhibition was organized in consultation with the Ethiopian community in London and remains “committed to continuing the important and wide-ranging dialogue with colleagues at the Ethiopian Embassy in London.”

The issue remains a bone of contention between the two nations, as commentators from both sides outlined to RT.

British broadcaster Jon Gaunt pointed to Iraq and Syria where antiquities have been looted by ISIS, suggesting unstable nations like Ethiopia can not be tasked with looking after their own treasures.

This argument was refuted by Ethiopian political commentator Awol Allo, blasting it as “condescending” and a “colonial narrative.” Allo said people should be able to visit Ethiopia and see the national treasures there.

Selected Comments:

I would punch that brit right between its beard and his eyes. These are thief eyes, on what ground is UK entitled to keep stolen goods. Oh, it was 200 years ago, but as everybody know stolen goods are still stolen, even after 2000 years, so they should be returned with apologies.

The British looted & stolen many things from Poor countries around the world & now they must return to the real owners.

The British museums would be empty if they decide to gave back artefacts. What about all the Great British Countryside Mansions paid for by African Slaves blood.

So, would Britain feel the same way if Ethiopia had important looted British historical artifacts on display in an Ethiopian museum? I think not. Looted history should be returned to the owners when at all possible. Theft is theft..time does not turn a theft into a legal transfer by virtue of the thief managing to hold onto it for a few generations.

Shame on the British Empire! An ancient Christian Empire looted of its Royal regalia by a professed Christian State. They even stripped the crowns from the bodies of the Emperors in their burial vault. How would the British have felt if a group of marauding Ethiopians exhumed the body of Queen Victoria and stripped the rings from her fingers? Send the loot back now!

Unless the British create ISIS in Ethiopia in the near future, there is no terrorist in Ethiopia. Ethiopian is a peaceful country. Just give the item back without any excuse …

I have a theory the U.K. wants to put Zera Yacob, Crown Prince and heir to Haile Selassie on the Ethiopian throne. He was educated at Eton. Presumably they will then return the regalia. All part of the U.K. elite’s plan to reassert control over the Horn of Africa. Al Shabaab will fulfill a similar role in Somalia. British Empire Mk ll.

Source

______

Posted in Conspiracies, Ethiopia | Tagged: , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

የእህተ ማርያም ቃል ተከሰተ | በመብረቅ የታጀበቸው የማርያም መቀነት ያልታወቀ ነገር በእንግሊዝ ሰማይ ላይ ወረወረች

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on April 28, 2018

ከአራት ቀናት በፊት የእንግሊዝ ሰማይ ላይ አንድ የብዙዎችን ቀልብ የገፈፈ ይህ ተዓምር ታይቶ ነበር።

መለኮታዊ ምልክት? መለኮታዊ ጣልቃ ገብነት?

ከጥቂት ዓመታት በፊት፡ በሮም ከተማ ተተክሎ የነበረው የአክሱም ኃውልትም በመብረቅ ሲመታ ነበር ጣሊያን ሳትወድ ለኢትዮጵያ እንድትመልስ የተገደደችው።

አሁንም፡ ይህ ለእንግሊዝና አባሪዎቿ የተሰጠ ማስጠንቀቂያ ነው፤ “ የሠረቅሺውን ንብረቷን ሁሉ መልሺ፣ ኢትዮጵያን መተናኮሉን አቁሚ፣ በቃሽ!” እየተባለች ነው።

______

Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

እህተ ማርያም | በጣና ሐይቅ ቅዱሳን ገዳማት፡ ነጮች ማደር አይፈቀድላቸውም፡ ቅርሶቻችንን ይሠርቃሉና

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on April 21, 2018

ከጥቂት አመታት በፊት አክሱም ላይ ትንሽ ሃውልት ሰርቆ በጉያው አስገብቶ ለመውጣት ሲል አንድ አባት የያዙት የአንድ አውሮፓ ቤተ መዘክር አስተዳዳሪ ታሪክ ትዝ ይለኛል። ታሥሮ እንደነበር አስታውሳለሁ።

ትክክል ነው፤ ወደ አገራችን የሚጓዙትና እኛን የሚቀርቡን ነጮች ለእኛ በፍጹም በጎ ነገር አያስቡልንም፣ አያደርጉልንም። በእርግጥ እንደ መልአክ የሆኑ ነጮች አሉ፤ ነገር ግን ወደ እኛ የመቅረብ እድሉ የላቸውም፤ 90% የሚሆነው ነጭ ግን ለፀረ-ክርስቶሱ መንግሥት የተዘጋጀ ኤዶማዊ ነው፤ በመሪዎቹ በቀላሉ የሚነዳ ነው፡ የእኛ ጠላት እንዲሆን ተደርጎ የተኮተኮተ ነው፣ “የአፍሪቃውያን ድኽነት የእኛ ኃብት ነው፣ እነርሱ ኃብታም ከሆኑ እኛ እንደኽያለን” የሚለውን መርኾ ተቀብሎ የሚኖር ነው ።

ነጮቹም ቢሆኑ “ብሔራዊ” በሚሏቸው ቁልፍ ቁልፍ ቦታዎች ላይ አፍሪቃውያንን ማሳደር ቀርቶ፡ ለጉብኝት እንኳን አያስገቧቸውም። በየላብራቶሪው እንኳን፡ እራሳቸውን ሙሉ በሙሉ ከሸጡት ወገኖቻችን በቀር፡ ጥቁሩን አስገብተው ለማሠራት ፈቃደኞች አይደሉም። ምስጢራት ናቸው የሚሏቸውን ነገሮች ለጥቁር ሕዝቦች አያካፍሉም።

ለምሳሌ፡ በጥቁር ሰው አካል ላይ በተፈጥሮ በብዛት እንድተቀበረ የሚነገርለትን “አምላካዊ የሜላኒን ቅመም” በተመለከተ በአውሮፓ፣ አሜሪካና አውስትራሊያ በየዓመቱ ምስጢራዊ ስብሰባዎች ይካሄዳሉ፤ ነገር ግን አንድም ጥቁር በስብሰባዎቹ ተካፍሎ አያውቅም። የኢሉሚናቲዎቹ የቢልደርበርግ ስብሰባም ጥቁሮችን ያገለለ ነው። በሌላ በኩል፤ በረጅሙ የጠፈር ምርመራ ታሪክ፡ ይህን ሁሉ ዘመን፡ አንድም “አፍሪቃዊ” ወደ ጠፈር ተልኮ አያውቅም፤ አንድም! ሁሌ ተፎካካሪዎች መስለው እርስበርስ የሚጠዛጠዙትና ለጦርነት የሚዘጋጁት አውሮፓውያን፣ አሜሪካውያንና ሩሳውያን ጠፈር ላይ ቤት ሠርተው እስያዊውንና አረቡን እየጋበዙ በሕብረት “ምርምሮችን” ያካሂዳሉ። አፍሪቃውያን ግን አይጋበዙም፤ ለጠፈር ብቁ የሆነ አፍሪቃዊ ጠፍቶ ነውን? አይደለም!

የጣና ሀይቅ ገዳማት አባቶች ለሌላውም “ፈረንጅ አምላኪ” ወገናችን ትልቅ አርአያ ሊሆኑ ይገባቸዋል።

______

Posted in Conspiracies, Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , | Leave a Comment »

እህተ ማርያም | ቡና፣ ጫት፣ ሺሻ፣ ሰንደል፣ ጥንቁልና፣ ቀይ መጋረጃ፣ የኢሬቻ በዓል፤ ሁሉም ከሰይጣን ናቸው

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on March 18, 2018

ሁሉም የክርስቶስን ልጆች ለማጥፋት በዲያብሎስ የተተከሉ አረሞች ናቸው። ክርስቶስን ወይም አረሙን ምረጡ”

ይህ እንከን የማይወጣለት ኃይለኛ መልዕክት ነው። በጣም የሚደንቅ ነው፤ እህታችን ጥቃቅን መስለው የሚታዩትን ነገሮች ሁሉ ነው እንድትታዘብ እድሉ የተሰጣት፤ ጆሮ ያለው ያዳምጥ!

ባለፈው መስከረም ላይ የ ቅ/እስጢፋኖስ ዕለት በቤተክርስቲያኗ ግቢ ውስጥ ቁጭ ብዬ እንዳለሁ፤ አንዲት ሴት መኪና እየነዳች መጥታ አጠገቤ አቆመች፤ ከዚያም ወርዳ እኔ አጠገብ ቁጭ አለችና ቦታው የማይፈቅድልንን ጥያቄዎች ትጠይቀኝ ጀመር፡ በዝምታ ሳልፋት ስልኳን ከፍታ ስታወራው የነበረው ብልግና ለጆሮ የሚቀፍ ነበር። በዚህ ወቅት በቃ “ጠንቋይ” መሆን አለባት ብዬ ተንስቼ ሄድኩ።

አዎ! አይጦቹ በየጎረቤቱ፣ የተለከፉት ሴትና ወንድ በየቤተክርስቲያኑ እየተላኩ ነው።

በተዋሕዶ ልጆች ላይ ያነጣጠረው ቀስት ከሁሉም አቅጣጫ ነው ተወጥሮ የሚታየው። ይህ ጦርነት ዓለማቀፋዊ መልክ የያዘና በሁሉም አቅጣጫ የሚካሄድ ነው።

እኛ ክርስቲያኖች የብሔራዊ ስሜት ሳይገድበን የክርስቶስ ከሆኑ ወንደሞቻችንና እህቶቻችን ጋር እንድናብር እንታዘዛለን።

መድኃኔ ዓለም ክርስቶስ፡ “ይሁዳዊ ወይም የግሪክ ሰው የለም፥ ባሪያ ወይም ጨዋ ሰው የለም፥ ወንድም ሴትም የለም፤ ሁላችሁ በክርስቶስ ኢየሱስ አንድ ሰው ናችሁና” ይለናል።

ኮራጁ ዲያብሎስ ፀረክርስቶሱም የራሱ የሆኑትን ሁሉ ለዓላማው በመላው ዓለም በጋራ ሰብስቧቸዋል፦

ለምሳሌ ኮሙኒዝም “የዓለም ወዛደሮች ሁሉ ተባበሩ” በሚል መርሆ አመጸኞቹን ግራኞች ያስተባብራል፣ እስልምና ለ “ኡማችን / እናታችን” በሚል መርሆ በመላው ዓለም ያሉትን ግራኝ ሙስሊሞች ሁሉ ያስተባብራል፣ ዓለማዊነት/ ሴኩላሪዝም ደግሞ ዓማናይየሆኑትን ግራኝ ልጆቹን በመለው ዓለም ያስተባብራል። ዓለማውያኑ ምዕራባውያን ሙስሊሞችን አምልኳቸውን ወደ አገሮቻቸው ሲያስገቡ፣ ሙስሊሞቹ ደግሞ ወደ አገሮቻቸው የምዕራባውያኑን አምልኮና የገባያ ማዕከላት ያስገባሉ፤ ዓብያተ ክርስትያናትን ግን ይከለክላሉ።

እነዚህ ሦስት ቡድኖች የተለያየ የሚመስል መንገድ ቢከተሉም ግን የሁሉም መንፈስ አንድ ዓይነት ነው፤ ሁሉም የፀረክርስቶሱን ልብስ ለብሰዋልና። ምንም እንኳን ተልዕኳቸው ዓለም አቀፋዊ ባሕርይ የያዘ መስሎ ቢታይም፤ እግረ መንገዳቸውን ግን “ብሔራዊ” ማንነታቸውን በመላው ዓለም ለማሰራጨት ነው የተነሱት፦ ኮሙኒዝም እና ሴኩላሪዝም የምዕራባውያኑን ባሕል፣ ቋንቋና አምልኮት፤ እስልምና ደግሞ የአረቡን ባሕል፣ ቋንቋና አምልኮት ለማስፋፋት ይታገላሉ።

በአገራችን የሚታዩት ፀረኢትዮጵያዊነትና ፀረተዋሕዶ ዘመቻዎች የእነዚህ ሦስት ቡድኖች ወኪሎች መሆናቸው በግልጽ የሚታይ ነው። አኩሪውን ክርስቲያናዊው ኢትዮጵያዊ ማንነታችንን ለማጥፋት በክህደት ወሃ የተጠመቁት ወገኖቻችን ለዓለም አቀፋዊው የሉሲፈራዊ ሥርዓት እራሳቸውን አሳልፈው መስጠታቸው በጣም የሚያሳዝን ነው። ያውም ለጊዚያዊ ጥቅም ሲሉ!

የአረቡ፣ የህንዱ፣ የሱዳኑ፣ የሶማሌውና የቻይናው መጉረፍ፣ ጎረቤት አገሮች እየፈራረሱ ስደተኞች ወደ ኢትዮጵያ እንዲገቡ መደረጉ፣ እንዲሁም የጠንቋዩ፣ የቃልቻው፣ የዕጹ፣ የሺሻው፣ የቡናው ወዘተ ባህል መስፋፋት በኢትዮጲያዊነት ላይ የተጠነሰሰ ሤራ መኖሩን ይጠቁመናልኢትዮጵያዊነት = ክርስትና!

እህቶቻችንን ወደ አረብ አገር በመላክ በጋኔን እንዲሞሉና ወደ ኢትዮጵያም ተመልሰው ቡናውን ለሰዎች በየቦታው እንዲያጠጡ ይደረጋሉ፣ ሰይጣናዊውን የኢሬቻ በዓል ብሔራዊ በዓል ለማድረግ ይሞከራል፣ (መስቀልን ለምተካት … በመስቀል ክብረ በዓል ማግስት) ፣ የተዋሕዶ ወጣቶችን በእናት ቤተክርስቲያናቸው መንፈሳዊ መዝሙሮችን እንዳይዘምሩ ሲተናኮሏቸው፤ የራያ ጨፋሪዎች ግን በየቤተክርስቲያኑ ሰተት ብለው እንዲገቡና ባሕላቸውን እንዲያስተዋውቁ ይታዘዛሉ።

ይህን ከባድ የፈተና ጊዜ የመወጣቱ ኃላፊነት ያለብን እኛ እያንዳንዳችን ነን፤ በግላችን፡ ከታች ወደላይ ማድረግ የሚገባንን ሁሉ ማድረግ ከቻልን የጠላቶቻችንና ተባባሪዎቻቸው ሤራ ብዙም ሊያሳስበን አይገባም።

እስኪ ለጊዜው ከቡናው፣ በተለይ ደግሞ በጣም አደገኛ ከሆኑት ሺሻና ጫት እንቆጠብ፣ (እንደ አዲስ አበባ ከፍተኛማ በሆኑ ቦታዎች ጫትና ሺሻ የጤና ጠንቅ ናቸው)። እስኪ በእምነት ከማይመስሉን ጋር መደበላለቁን እናቁም። እነዚህን በእጃችን ያሉትን ቀላል ነገሮች እያንዳንዳችን ማድረግ ካልቻልን ሌላውን መውቀስና መኮነን መብት ሊኖረን አይገባም።

______

Posted in Ethiopia, Faith, Infos | Tagged: , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

የማርያም እህቶች በጣና ሐይቅ ላይ የኖኅን መርከብ አዩ

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on March 11, 2018

[የማቴዎስ ወንጌል ምዕራፍ ፳፬፥፴፯]

የኖኅ ዘመን እንደ ነበረ የሰው ልጅ መምጣት እንዲሁ ይሆናልና።”

ድንቅ ነው፤ እግዚአብሔር በደመናዎች ላይ ብዙ ምልክቶችን እያሳየን ነውና ወደ ታች ሳይሆን ወደላይ መመልከቱን ማዘውተር ሊኖርብን ነው።

በእኛ በኢትዮጵያውያን ዘንድ “ሰባቱ ኪዳናት” ተብለው የሚታወቁትና የቅዱሱ ኪዳን አካላት የኾኑት፡ የኢትዮጵያዊነት ተዋህዶ ሃያማነኖታችን መሠረቶች፡ መደበኛ ስማቸውና መለያ ምልክታቸው ተለይቶና ተዘርዝሮ ይገኛል። እነዚህም፦

  1. ኪዳነ አዳምና ሔዋን፥

  2. ኪዳነ ኖኅ፥

  3. ኪዳነ መልከ ጼዴቅ፥

  4. ኪዳነ አብርሃም፥

  5. ኪዳነ ሙሴና

  6. ኪዳነ ዳዊት፥ በመጨረሻም

  7. በድንግል ማርያምና በኢየሱስ ክርስቶስ የተገኘው “ኪዳነ ምሕረት

የሚባሉት ናቸው።

______

Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , , | 1 Comment »

የ እህተ ማርያም ኃይለኛ መልዕክት | ወሊድ መከላከያ የምትጠቀሙ ከሆነ 666 ዘንዶውን/ አውሬውን ለመከተል በፈቃዳችሁ መርጣችኋል ማለት ነው

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on February 24, 2018

ወደ ቤ/ክርስቲያን መግባት አትችሉም፣ ሥጋውንና ደሙን መቀበል አትችሉም፣ መጠመቅ አትችሉም፤ የእየሱስ ክርስቶስና የእናቱ የቅ/ ማርያም ልጆች ነን ማለት አትችሉም።

ይህ የእህታችን ሌላ ታላቅ ትምህርት ነው። የተቀበለችው መረጃ ለአገራችን እጅግ በጣም ጠቃሚ ከሆኑት መረጃዎች መካከል አንዱ ነው። ይህን መረጃ ዓብያተክርስትያናቱ በየዕለቱ ሳራችን ብለው በሰበካዎቻቸው ወቅት ደግመው ደጋግመው ሊናገሩልት ይገባል።

እህቶች እባካችሁ የወሊድ መከላከያውን በጭራሽ አትጠቀሙ፤ ለማስወረድማ የምታስቡት ጉዳይ አይደልም” ብለው በየቀኑ መናገር ይኖርባቸዋል። ግማሽ ደቂቃ እንኳን የማትወስድ አንዲት ዓረፍተ ነገር ናት።

666ቱ አውሬ ጋር የተመሳጠሩት ሜዲያዎች ባዕዳውያኑ የወሊድ መከላከያና ህጻናት ገዳይ ድርጅቶች ማስታወቂያ ይሠራሉ እንጂ ለእህቶቻችን ማስጠንቀቂያ ሊሰጡ ፈቃደኞች አይደሉም። አቤት ጉዳቸው!

7000 አመታት በላይ ትክክለኛው አምልኮተ እግዚአብሔር የምትፈጽመው ሃገረ እግዚአብሔር ኢትዮጵያ ከእግዚአብሔር በመመረጥዋና የእግዚአብሔር ጥበቦች መገኛና ማስፈጸምያ በመሆንዋ በተለያዩ ጊዜያት ይህንን የሚያውቁ ባዕዳውያን ሃይሎች ወደ ሃገራችን በመምጣትና በርቀትም ጥበብዋን ለመዝረፍና ጥንታዊው ኦርቶዶክሳዊ ተዋህዶ ሃይማኖትዋን ለመበረዝ የተለያዩ የሰይጣን አምላኪዎች የሆኑ የምስጥር ማህበራት ጥረት አድርገዋል። በእግዚአብሔር ጥበቃ እስከ አሁን ብት ዘልቅም አውሬው(666) ግን ተቃውሞውና ሴራው ለማስፈጸም እስከ መጨረሻ እንደሚጥር የታወቀ ነው።

ልብ ብለን እንከታተል፦ ዶር ቴዎድሮስ አድሃኖምን ለዓለም ጤና ድርጅት ዳይሬክተርነት አሁን መምረጣቸው ያለ ምክንያት አይመስለኝም፤ ያቀዱት ትልቅ ሴራ በመኖሩ ነው። ጊዜ ያሳየናል።

የህዝባችንን ቁጥር በጦርነት፣ በርሃብ፣ በበሽታ፣ በ HIV ኤድስ ሊቀንሱት አልቻሉም፤ ስለዚህ አሁን የመጨረሻው ጦርነት ላይ ገብተዋል፤ በዚህም ሁለት ወፍ በአንድ ድንጋይ ለመምታት ቆርተው ተነስተዋል፤ ይህም፦ ቁጥሩን መቀነስ እንዲሁም የሚወለዱትን በአውሬው መንፈስ ቁጥጥር ማስገባት።

ባካችሁ፣ ባካችሁ የወሊድ መከላከያ አትጠቀሙ፣ ህጻናቱንም መርፌ አታስወጉ። እስኪ ወሊድ መከላከያ ለምን እንደምትጠቀሙ እራሳችሁን ጠይቁ! ለማመንዘር አይደለምን? እስኪ የተረገዘውን ለምን እንደምታስወርዱ እራሳችሁን ጠይቁ! ግድያ አይደለምን? በእነዚህ ድርጊቶች ብቻ ሙሉውን የእግዚአብሔርን አሠርቱ ትዕዛዛት እያወቃችሁ ሽራችኋቸዋል፤ ከእየሱስና እናቱ ጋር በጽኑ ተጣልታችኋል ማለት ነው። ከዚህ የበለጠ አስከፊ ነገር ይኖራልን?

  1. እግዚአብሔር አምላክህ እኔ ነኝ ከእኔ በቀር ሌሎች አማልክት አይሁኑልህ፡፡ ዘጸ 202-3፡፡
  2. የእግዚአብሔር የአምላክህን ስም በከንቱ አትጥራ፡፡ ዘጸ 207፡፡
  3. የሰንበትን ቀን ትቀድሰው ዘንድ አስብ አክብረውም፡፡ ዘጸ 2010፡፡
  4. አባትህንና እናትህን አክብር፡፡ ዘጸ 2012፡፡
  5. አትግደል፡፡ ዘጸ 2013፡፡
  6. አታመንዝር፡፡ ዘጸ 2014፡፡
  7. አትስረቅ፡፡ ዘጸ 2015፡፡
  8. በሐሰት አትመስክር፡፡ ዘጸ 2016፡፡
  9. አትመኝ፡፡ ዘጸ 2017፡፡
  10. ባልንጀራህን እንደራስህ ውደድ፡፡ ዘሌ 1918፡፡

ይህ ኢትዮጵያና ተዋሕዶ ሃይማኖቷን ለመለወጥና ለማጥፋት የሚደረግ ሴራ ተግባራዊ ለማድረግ እንቅል እንደማይወስዳቸው ያውም ኢትዮጵያዊነታቸውን በካዱት ግለሰቦች ድጋፍ ተጨምሮበት እውን ለማድረግ መጣራቸው ግልጽ ነው።

ሰብዓዊነተቻችንና ማንነታችንን ለማጥፋትና ደካማውን የምዕራባውያንን ባዕዳዊ እምነትን በሕዝባችን ላይ ለመጫን የአውሬው ሠራዊት የሚያደርገውን ጥረት ሁሉ መቃወምና እግዚአብሔር የሰጠነንን ልዩ ማንነት መጠበቅ ይገባናል።

______

Posted in Ethiopia, Faith, Infos, Life | Tagged: , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

 
%d bloggers like this: