Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • June 2023
    M T W T F S S
     1234
    567891011
    12131415161718
    19202122232425
    2627282930  
  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

Posts Tagged ‘ኤጄቶ’

ተዋሕዶ አባቶችን የሚያርዱትን፣ ቤተክርስቲያንን የሚያቃጥሉትን ቅዱሱ ገብርኤል በሰይፉ ቀጥቅጦ ይጣላቸው

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on July 27, 2019

አሜን!

እንኳን አደረሰን! ስል፤ በ ኢትዮጵያ ሃገራችንና በቤተክርስቲያናችን ላይ ያነጣጠረ ጥቃት በመፈጸም ላይ ያሉትን ቀንደኛ ጠላቶቻችንን(አዎ! እናያቸዋለን! እናውቃቸዋለን!)

  • ዲያብሎስን

  • እስማኤላውያኑን

  • ኤሳውያኑን

  • ኢሉሚናቲዎቹን

  • አሕዛቡን

  • መናፍቃኑን

  • እነ አብዮት አህመድን

  • ቄሮን

  • ኢጄቶን

  • ቃልቾቹን

  • የሱዳን እና ሶማሌ መተተኞችን

  • አጋንንት ትርፍራፊዎችን ሁሉ

ኃያሉ መልአክ ቅዱስ ገብርኤል በያዘው ሰይፍ አንድ ባንድ አቃጥሎ እንዲያጠፋልን ከልብ እየተመኘን ነው። አሜን!

__________________

Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

ማመን ያዳግታል | አብዮት አህመድ በኢትዮጵያ እና በተዋሕዶ ቤተክርስቲያኗ እንዴት እንደሚያላግጥ ወገን ተመለከት

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on July 24, 2019

ይህ ሰው የቀን ጅብ አውሬ እንጂ ኃላፊነት ያለውና የኢትዮጵያን ህዝብ በቅን ለማስተዳደር የቆመ ሰው አይድለም፤ ውሻ እንኳን የበላበትን አይረሳም ፥ ይህ ከሃዲ ግን በኦርቶዶክስ ተዋህዶ በእግዚአብሔር ቤተመቅደስ ካባ ለብሶ ዛሬ የእግዚአብሔር ቤተመቅደስ ሲቃጠልና አባቶቻችን ሲታረዱ እየሸሸ ወደሌላ ሀገር ለሽርሽር ይሄዳል፣ የጂሃድ አጋሩን፡ ውርንጭላ ጃዋርን ወደ አሜሪካ ይልካል፡ በእርሱ ፈንታ ሌሎችን በእስር ቤት ያጉርና፤ ያው ወንጀለኞቹን አሁን ይዣቸዋለሁ!” በማለት ህዝቡ እንዳይነቃበት የእንቅልፍ ታብሌት ይሰጠዋል።

በጣም የሚያሳዝነው ደግሞ የተዋሕዶ ልጆች በታረዱበትና ፮ ዓብያተ ክርስቲያናት በተቃጠሉበት ማግስት፡ አብዮት አህመድ አዳማወደተባለችው ከተማ በማምራት ከዩኒቨርሲቲ ተመራቂዎች ጋር ጂሃዳዊ ድሉን አብሮ ለማክበር መወሰኑ ነው። ታዲያ ወገን፡ ይህ በግልጽና ሆን ተብሎ በንቀትና ማን አለብኝነት የሚፈጸም ተግባር አይደለምን?! እንኳን እንደርሱ ምንም ሳይሰራ የሕዝብን ፍቅር ቶሎ ያገኘ ቀርቶ፤ የትኛውም ሕዝብን አገለግላለሁ የሚል አንድ መሪ የተለየ አጀንዳ ቢኖረው እንኳን፡ ህዝቡ በአሰቃቂ ሁኔታ እየታደነ ሲገደልና ዓብያተ ክርስቲያናት በተከታታይ ሲቃጠሉ ሀገር ጥሎ ሊሸሽ አይችልም፡ በፍጹም!(ልብ በል ወገን፦ በዚህ ዓመት ብቻ ሃያ የተዋሕዶ ዓብያተ ክርስቲያናት ተቃጥለዋል።)

ይህን መሰሉ ጭካኔ በኢትዮጵያ ታሪክ የተከሰተው በግራኝ አህመድ እና በቤኒቶ ሙሶሊኒ ዘመናት ነበር። እነ ግራኝ አህመድና ጣሊያኑ ሙሶሊኒ መጨረሻቸው እነርሱን አያርገን እስኪያሰኝ ድረስ በጣም አስቃቂ እንደነበር የሚታወስ ነው። ታዲያ ሁንም በዚህ መልክ እንዲህ ከቀጠለ ኢትዮጵያውያን በቅርቡ አብዮት አህመድን በአንድ የአዲስ አበባ አደባባይ ላይ ልክ እንደ ሙሶሊኒ ሰቅለው ቢሸኑበት አይድነቀን።ሰይፍ የሚያነሡ ሁሉ በሰይፍ ይጠፋሉና። ቅዱስ እስጢፋኖስ በለተቀኑ ቶሎ ይንቀለው!

___________________

Posted in Ethiopia, Faith, Infos | Tagged: , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

በሲዳማ ለሚካሄደው ፀረ-ተዋሕዶ ጂሃድ ተጠያቂዎቹ ግራኝ አብዮት አህመድና ደጋፊዎቹ ናቸው

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on July 21, 2019

በዚህ አሳዛኝ፣ አስቆጪና በጣም አደገኛ ጉዳይ ላይ ሁሉም ጸጥ ብለዋልየውስጦቹም የውጮቹምመረጃዎች እንዳይወጡ አፍነዋቸዋልእንዲህ ዓይነት ቅሌት አይቼ አላውቅም!!!

ለሁሉም ጊዜ አለው!

ይህ 100% እስላማዊ ጂሃድ ነው፡ ወገኖቼ! ጠላቶች የሚጠቀሙት ግጭ እና ሩጥ!/ Hit & Runየሚባለውን ዲያብሎሳዊ ጥበብ ነው። አጋጣሚውን በመጠቀም የሚፈልጉትን ጽንፈኛ ተግባር ከፈጸሙ በኋል ፥ ሸሸት ይሉና እኛ እኮ እንደዚህ አይደለንም፣ እስልምና እኮር እነዚህ አይደለም፣ ጃዋር እኮ ሙስሊም አይደለም…” በማለት ያስተኙናልከዚያ ትንሽ ቆየት ብለው በሌላ አካባቢ የለመዱትን ጥቃት ይፈጽማሉ። ከእስልምና ጋር በተያያዘ ለ1400 ዓመታት ያህል የምናየው የቤተክርስቲያናችን ታሪክ ይህ ነው።

ስለዚህ ጉዳይ ስናስጠንቀቅ ብዙ ዓመታትን አስቆጥረናል፤ ያው አሁን ጌዜው ደረሷል። በሃገራችን እየተካሄደ ያለው ጦርነት በእግዚአብሔር አምላክና በዋቄዮአላህ መካከል ነው። ከእመነት በላይ ምንም ነገር የለምና፡ እያንዳንዱ የተዋሕዶ ልጅ በቅድሚያ በማወቅም ሆነ ባለማወቅ ጠላቶቹን አስመልክቶ የሚያሳየውን ለስላሳና ዝልግልጋማ የሆነ አካሄድ በመቀየር ለጠላቶቹ የሚሰጠውን ድጋፍ ዛሬውኑ ማቆም አለበት፤ ከዚያም ልክ እነደነ አፄ አምደጽዮንና አፄ ዮሐንስ በእነዚህ የዋቄዮአላህ አርበኞች ላይ ተገቢውን እርምጃ ለመውሰድ ዝግኙ ሊሆን ይገባዋል። አሊያ ይህ ጂሃዳዊ ጥቃት መቀጠሉ አይቀርም!

ተከታዩን የጽሑፍ መረጃ ላካፈለን ለወንድማችን፡ ለመምህር ዘመድኩን በቀለ የላቀ ምስጋና፦

በደቡብ ኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያንና ምእመናን እየነደዱና እየወደሙ ነው። በደቡብ ሲዳማ ዞን 5 አብያተ ክርስቲያናት ተቃጥለዋል ከ17 በላይ ሰዎች ታርደዋል።

ወዳጄ የሜንጫው አብዮት እንደሆነ በይፋ ተጀምሯል። አንተ ከዳር ሆነህ አንገትህ እስኪቆረጥ ቁርጥህን እየዞርክ ቁረጥ፣ እስክትለጋ አንቡላህን ለጋ። እነሱ ሥራ ላይ ናቸው።

ደም መጣጮች እንኳን ደስ ያላችሁ!!! የባለ ሜንጫው ደጋፊዎች እንኳን ደስ ያላችሁ። የጄነራል አሳምነው ጽጌ ስጋት ሳይውል ሳያድር ከተፍ እያለ ነው። ግራኝ አህመድ ከ 500 ዓመት በፊት።

ሃይ ባይ ከልካይ መንግሥት የለም። ሁሉም የእልሁ መወጫ ተዋሕዶና የተዋሕዶ ልጆች ናቸው። በሀገሪቱ ወሳኝ የአመራር ስፍራ ላይ ኦርቶዶክሳውያን ስለሌሉ ድርጊቱን ለማስቆም የሚከራከር ሰው እንኳ የለም።

በጅጅጋ፣ ቀጥሎ በከሚሴና በአጣዬ፣ አሁን ደግሞ በደቡብ ቤተ ክርስቲያን ኤጄቶና ቄሮ በተባሉ አልሸባቦች እየወደሙ ነው።

የአክሱም ጽዮን ልጆች ደግሞ ከሩቅ ቆመው ይስቃሉ።

ሲኖዶሱ ግን በህይወት አለን? እስቲ ጠይቃችሁ አጣርታችሁ ንገሩን።

እስከ በሲዳማ ሀገረ ስብከት በሀገረ ሰላም ወረዳ ቤተ ክህነት ውስጥ ከሚገኙት አብያተ ክርስቲያናት መካከል፦

  • ፩፦ ጭሮኒ አማኑኤል
  • ፪፦ ገተማ ገብረ ክርስቶስ
  • ፫፦ ዶያ ቅዱስ ሚካኤል
  • ፬፦ ሄጋ ቅዱስ ገብርኤል አብያተ ክርስቲያናትን ትናንት ሐምሌ ፲፪ ከሰዓት በኋላ አቃጥለዋቸዋል።
  • ፭፦ ቀጨኖ ልደታ እና
  • ፮፦ ቀራሮ ኢየሱስ

አብያተ ክርስቲያናት ተዘርፈዋል። በአብያተ ክርስቲያናቱ ዙሪያ የሚኖሩ ክርስቲያኖች በሙሉ ቤታቸው ወድማል። ግማሾቹ ተገድለዋል። የተረፋት በየጫካው ተደብቀው ይገኛሉ። ክርስቲያኖች እየተገደሉ ናቸው። የሚደርስላቸው የለም።

መንግሥት መረጃ እንዳይወጣ የስልክና የኢንተርኔት አገልግሎት ዘግቷል ተብሏል።

★★★ ባህርዳር ዐማራ ክልል አሳምነው ጽጌን ለመግደል የማንም ፈቃድ ሳያስፈልገው ከወር በፊት ሰተት ብሎ ወደ ክልሉ የገባው የፌደራሉ የመከላከያ ጦር፤ እነ አሰማኸኝና እነ ላቀ ሳይሰሙ በባህርዳር መፈንቅለ መንግሥት እየተካሄደ ነው ያለው ኢቲቪ እስከአሁን ስለ ጉዳዩ ምንም ትንፍሽ እያለ አይደለም።

በሌላም ዜናም ከዚያው ከደቡብ ክልል ሳንወጣ ሰሞኑን በጎፋ መሎ ለሃ ከተማ በሚገኘው የቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያንና በምእመናን ላይ በወረዳው የተደራጁ የመናፍቃን አመራሮች ከክልሉ ከታጠቁ ኃይሎች ጋር በመሆን በካህናት እና ምዕመናን ላይ ከፍተኛ ጥቃት በመፈፀም ላይ ያሉ መሆናቸውን ለሃገረ ስብከቱ ሊቀጳጳስ ለብፁዕ አቡነ ኤልያስም በደብዳቤ ገልጸዋል።

እስከ አሁን ድረስም ከ57 በላይ ምዕመናን በላሃ ፖሊስ ጣብያ ታስረዋል።

አንድ ካህን እና 3 ወጣቶች በጥይት ተመተው በሕክምና ላይ ናቸው።

አሁንም በርካታ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ምዕመናንን ለማሠር አደን ላይ ናቸው

በጥምቀት እና መስቀል በዓል ማክበርያ ቦታ ያለው መስቀል እና የመጠመቅያ ገንዳ አፍርሰው ወስደውታል።

በላሃ ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ግብ ውስጥ የተጠለሉ ምዕመናንን ለማሥወጣት ከ15 በላይ የጪስ ቦንብ በመወርወር ጥቃት ለመፈፀም ሙከራ ብያደርጉም ምዕመናኑ ባደረገው ተጋድሎ ተርፈዋል።

ስለለውጡና ስለ አቢቹ ለመደስኮር እንቅልፍ የሚያጡት ወንድሜ ዲያቆን ዳንኤል ክብረትና የኔታ እሸቱ አለማየሁስ ወዴት ጠፉ? ብሔራዊ ቲአቴር መድረክ ላይ ለመደስኮር እንደምትጣደፉት ምነው ይሄ ሲሆን ልሳናችሁ ተዘጋሳ?

ማኅበረ ቅዱሳን፣ የመንፈሳዊ ኮሌጅ የነገረ መለኮት ምሩቃን ሰባክያነ ወንጌል ወንድሞች ምን እያሰባችሁ ነው?

መምህር ዶር ዘበነ ለማ፣ መምህር ምህረተአብ አሰፋ፣ እነ መምህር ጳውሎስ መልክአ ሥላሴ፣ እነ ዶክተር ዘሪሁን ሙላት፣ ፀረ ተሃድሶ፣ ፀረ ተባዮች ምንጥስዬ ቅብጥርስዬዎች ምን እያሰባችሁ ነው?

ይሄ አሁን መግቢያ መውጫ አጥቶ በየጫካው እየታረደ ያለው ምዕመን ካሴታችሁን፣ መጻሕፍቶቻችሁን እየገዛ የቤት ኪራይ እየከፈለ ቀፈት ሆዳችሁን እየሞላ ክፉ ዘመን ያሳለፈላችሁ ደግ ህዝብ እኮ ነው። የሲዳሞን ህዝብ በዚህ ወቅት ምነው ዝም አላችሁት?

በአሜሪካና በአውሮጳ፣ በካናዳና በአውስትራሊያ፣ በዓረቡ ዓለም የምትገኙ የካህናት ኅብረት ለዐቢይ አህመድ ያሽቃበጣችሁትን ያህል ቤተ ክርስቲያን እንደ ጧፍ ስትነድ ምንድነው ዝምታው? ጉዳዩን ወደ ዓለምአቀፉ ማኅበረሰብ ለመውሰድ ማን አዚም አደረገባችሁ?

እኔ ግን እላለሁ !!! እምዬ ኦርቶዶክስ አንቺ እናትዓለም ፤ የእነ ቅዱስ ዲዮስቆሮስ ፣ የእነ ቅዱስ አትናቴዎስ እና ቅዱስ ቄርሎስ የእነ ቅዱስ ጊዮርጊስ ፣ የእነ ቅድስት አርሴማ ፣ የእነ አቡነ ተክለሃይማኖት ፣ የእነ አቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ ፣ የአባ ሳሙኤል ዘዋልድባና የአቡነ አረጋዊ ሃይማኖታቸው የሆንሽ ንጽህት ተዋሕዶ ሃይማኖቴ ሆይ ! ብረሳሽና ብከዳሽ ቀኜም ትርሳኝ፣ ትክዳኝም ። ባላስብሽና ባልሞትልሽ ምላሴ ከጉሮሮዬ ይጣበቅ ። ሳለጎበድድ ሳለከዳሽ እንድኖር አምላክሽ ይርዳኝ ። ይህን ባለደርግና ሳልጮህልሽ ዝም ብዬ ብሞት ስሜ ከህይወት መጽሐፍ ይደምሰስ።

ጌታ ሆይ! ከዚህ በፊት በሆነው ፤ አሁንም እየሆነ ባለው እና ወደፊትም በሚሆነው ነገር፤ ክብሩን ሁሉ አንተ ውሰድ ።አሜን!

ድንግል ሆይ እናቴ ! አዛኝቱ ዛሬም እንደትናንቱ ቅደሚ ከፊት ከኋላዬ

______________________

Posted in Ethiopia, Faith, Infos | Tagged: , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

 
%d bloggers like this: