– በዛሬው ዕለት፡ እ.አ.አ ጥቅምት 29 / 2018፦
189 መንገደኞችን የያዘው የኢንዶኔዢያ አውሮፕላን ከመከስከሱና ሁሉም ተሳፋሪዎች ከመሞታቸው በፊት እንዴት እንደሚጮሁና አላሃቸውንም እንደሚማጸኑ ቪዲዮው ያሳየናል።
+ ማክሰኞ ዕለት፡ እ.አ.አ. ነሐሴ 31 / 2018 ዓ.ም፦
103 ተሳፋሪዎችን ይዞ የነበረው የሜክሲኮ አውሮፕላን ተመሳሳይ አደገኛ ሁኔታ ላይ ነበር፤ ቀጣዩ ቪዲዮ ላይም መንገደኞቹ አንዱን አምላካችንን ኢየሱስ ክርስቶስን ሲማጸኑ ይሰማሉ። ሁሉም ተሳፋሪዎች በተዓምሩ ተርፈዋል።
ተዓምሩን በከፊልም ቢሆን በቪዲዮ የቀረጸው አብሮ ይጓዝ የነበረውና፡ እስልምናን በመተው ወደ ክርስትና የመጣው ኢራናዊ ነው።
ሁለት ደቂቃ በሚወስደው ቪዲዮው ላይ፡ አውሮፕላኑ ከመነሳቱ በፊት እና ከአደጋውም በኋላ ከበስተጀርባ ሴቶች፣ ወንዶች እና ሕፃናት ሲጯጯሁ ይሰማል፤ የ እግዚአብሔርን ስም ጮክ ብለው ሲጠሩ እና “ኢየሱስ ክርስቶስ ባክህ በሩን ክፈተው” በማለት ሲማፀኑ ይሰማሉ።
የቪዲዮው አንሺ ኢራናዊ በትዊተር ገጹ ላይ የሚከተለውን ተናግሮ ነበር፦
“በእግዚአብሔር ጸጋ ደህና ነኝ፡ እርሱ ይመስገን በህይወት አለን፣ ይህ ሌላ ነገር አይደለም ትልቅ የእግዚአብሔር ተዓምር ነው፣ ሕይወት ስላለሁ ለኢየሱስ ክርስቶስ ብድር አለበኝ፣ ዲያቢሎስ ሕይወቴን ሊወስድ እችላለሁ ብሎ አስቦ ነበር፡ ነገር ግን አሁን እንዲያውም ለ ኢየሱስ ክርስቶስ እራሴን በይበልጥ እንደሰጥ ረድቶኛል”