Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • May 2023
    M T W T F S S
    1234567
    891011121314
    15161718192021
    22232425262728
    293031  
  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

Posts Tagged ‘ኢ-አማናይነት’

የፓሪሱ ካቴድራል ሲቃጠል የኦባማ ሚስት እዚያ ነበረች | የትራምፕ ልጅ ደግሞ በእስክስታ ሱስ ተጠመደች

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on April 18, 2019

አንዳንድ መረጃዎች እንደሚጠቁሙት፤ ይህ የእሳት ቃጠሎ ሆን ተብሎ እንደተቀሰቀሰ እና፤ ድርጊቱ በፕሬዚደንት ማክሮን፣ ካንዝለር አንጌላ ሜርከል እና ጠቅላይ ሚንስትር ተሪዛ ሜይ አቀነባባሪነት እንዲሁም በ ጳጳስ ፍራንሲስኮ ተባባሪነት ነው የተፈጸመው።

ባለፈው ሣምንት ላይ ተሪዛ ሜይ ወደ በርሊን ከተማ በመጓዝ ከ አንጌላ ሜርከል ጋር ከተገናኘች በኋላ – በፐርጋሞን ሙዚየም (የሰይጣን ዙፋን የሚገኝበት ቦታ ነው) አቅራቢያ ነበር የተሰባሰቡት – ወደ ፓሪስ አምርታ ከሦስተኛው “M” ማክሮን ጋር ተገናኘች። በርሊን የክርስቶስ ተቃዋሚው መቀመጫ ከሆኑት ከተሞች መካከል አንዷ ናት፤ ፖለቲካዊ ዋና ከተማ።

ማክሮን – ሜርከል – ሜይ – ኦባማ – ኢቫንካ

________________________

Posted in Conspiracies, Curiosity, Ethiopia | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

ተዓምር በፓሪስ | በተቃጠለው ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ኢየሱስ ታየ

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on April 17, 2019

ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንደሆነ ብዙ ሰዎች እየመሰከሩ ነው። ድንቅ ነው። የዛሬዎቹ ከሃዲ ፈረንሳይ አባቶች ይህን ድንቅ ቤተ ክርስቲያን ለጌታችን ክብር ሲሉ ከስምንት መቶ ዓመታት በፊት በስንት ድካምና መስዋዕት ሠሩት። የአሁኑ ተልካሻ ትውልድ ግን ከአውሬነት ነፃ አውጥቶ እየባረከ ፀጋውን የሰጣቸውን ጌታችንን በመተው እንደ ይሁዳ የክህደት ኑሮውን መረጡ። በዚህም ይህን ድንቅ ቤተክርስቲያን ለፀሎት፣ ለመንፈሳዊ ሕይወታቸው እና ለነፍስ ማደሻ በመገልገል ፈንታ ጎብኝዎችን በመጋበዝ የገንዘብ ማምረቻ መሣሪያ አደረጉት።

አዎ! ጌታችን በዚህ እጅግ በጣም አዝኗል፤ ስለዚህ፡ ቤቱ ለእርሱ ሲባል የተሠራ ነውና፤ እርሱ የማይመለክበት ከሆነ “እንግዲያውስ” በማለት እንዲቃጠልና እንዲፈርስ ፈቀደ። ፈረንሳዮች ሙሉ በሙሉ እንዳይፈራርሱ ከፈለጉ በጣም ማልቀስና ወደ ጌታችን መመለስ ይገባቸዋል።

አባቶቻቸው ቤተ ክርስቲያኑን ሠርተው ለመጨረስ ሁለት መቶ አመት ፈጅቶባቸው ነበር፤ ለስምንት መቶ ዓመታት ያህል ብዚ ጦርነቶችን እና የተፈጥሮ አደጋዎችን ምንም ሳይነካ አሳልፏል፤ ዛሬ ግን፡ እውቀት ጨምሯል፣ ቴክኖሎጂው ሁሉ በጣም ተራቅቋል በሚባልበት ዘመን፤ ሕንፃው በሰዓታት ውስጥ ወደመ። በሰሜን ተራሮች ቃጠሎ አገራችን “ውሃ፣ ውሃ!” እንደሚል ሕፃን “ሄሊኮፕተር፣ ሄሊኮፕተር!” በማለት ለመነች፤ “የመጠቅችው” ፈረንሳይ ግን በታላቅ ንብረቷ ላይ የደረስውን እሳት ከበሰተላይ ለማጥፋት አንድም ሄሊኮፕተር መጠቀም አልቻለችም። ዋው! አይገርምምን?!

_________________

Posted in Curiosity, Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

 
%d bloggers like this: