Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World

Posts Tagged ‘ኢየሱስ ክርስቶስ’

የእኅተማርያም እህቶችና ወንድሞች | “ዶ/ር አብይ ጥምቀትን አስመልክቶ የተናገረው ቃል ፀረ-ተዋሕዶ ነው”

Posted by addisethiopia on January 27, 2019

እኅቶቻችን እና ወንድሞቻችን ከተናገሯቸው ነገሮች መካከል፦

 • + /ር አብይ የተናገሩት እንኳን አንድ አገር እመራለሁ ከሚል ሰው፤ ከአንድ ምዕመን እንኳን የማይጠበቅ ነው፤ ጠቅላይ ሚንስትሩ ለሕዝቡ ይቅርታ መጠየቅ አለባቸው

 • + ጠቅላይ ሚንስትሩ ይህን ማለታቸው፤ ሃይማኖታችን ጠፍቶ ሁሉ ነገር እንደ ፌስቲቫል እንዲሆን ነው

 • + እራሱን የመቻል ብቃት ያለው ቅዱስ ታቦት ለምንድን ነው በታጠቁ ወታደሮች ታጅቦ እንዲሄድ የሚደረገው? ምን ዓይነት ቅሌት ነው?!

 • + አብይ አህመድ ኦርቶዶክስን ወዴት እየወሰደው ነው? የሚለውን ጥያቄ ሁሉም ሰው ሊጠይቀው የሚገባው ነገር ነው። ወዴት ወዴት ፎቀቅ እያልን ነው? ሃይማኖቱን ሁሉ ጨምቀው አንድ ሃይማኖት ለመፍጠር እየታገሉ ነው፤ አባቶች ስለዚህ ጉዳይ መናገር ይጠበቅባቸዋል።

 • + ትናንትና ስልጣን ላይ የወጣ ሰው እንዴት ይህን ያህል ተዋሕዶን ደፍሮ ሊናገር ቻለ?!

ቃለ ሕይወት ያሰማለን፤ እኅቶች እና ወንድሞች፤ ጀግኖች! ምን አለ እያናዳንዱ የተዋሕዶ ልጅ እንደ እናንተ መሆን ቢችል! ቸኩለው “አብይ አብይ” ሲሉ የነበሩት የአንዳንድ አባቶች ዝምታ ያደነቁራል። እየተካሄደ ስላለው ነገር እንዴት ዝም ማለት ይቻላል?

ዔዶማውያኑ ምዕራባውያን እና እስማኤላውያኑ ሕዝባችንን ከውስጥ እስከ ውጭ አብጠርጥረው አጥንተውታል፤ ቀስ በቀስ በማለማመድ ሕዝባችንን ፀረክርስቶሱን እንዲቀበል ለማድረግ ማዘጋጀት ከጀመሩ ቆይተዋል። ምን እንደሚፈልግ፣ ምን መስማት እንዳለበት፣ ማንን መቀበል እንደሚችል በደንብ አውቀውታል። ስለዚህ ሕዝባችንን ሙሉ በሙሉ ለመቆጣጠር ይችሉ ዘንድ ሰዎች እራሳቸው ፈቃደኛ ሆነው መርዛቸውን እንዲቀበሉላቸውና የፈጠሩት አጋጣሚም እንዳያመልጣቸው አሁን በጣም በመጣደፍ ላይ ናቸው።

ልክ ከዚህ በፊት ሻለቃ መንግስቱ ኃይለማርያም እና አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ እንዳደረጉት እነ ዶ/ር አብይ አህመድ አሊም (ስሙ ላይ በደንብ እናተኩር፤ ቍልፍ ሚና ይጫወታልና) በሲ.አይ.ኤ እና ኤፍ..አይ እንዲሁም በእንግሊዝ የስለላ ድርጅቶች አማካኝነት ስልጠናን አድረገዋል። እነዚህ ድርጅቶች የ666ቱ ዋና ተዋንያን ናቸው። መሪዎቻችን የእነርሱን ትዕዛዝ መቀበል አለባቸው፤ የማይቀበሉ ከሆነ፡ ልክ እንደ አቶ መለስ ዜናዊ ይገደለሉ።

እነ ዶ/ር አብይ አኅመድንና አቶ ለማ ለገሰን ሰልጣን ላይ ለማውጣት የወሰኑት ገና ከ፳፯ ዓመታት በፊት ነበር፤ ኦነግ የኢሕአዴግ መንግስትን ለቅቆ እንዲወጣ የተደረገው በሉሲፈራውያኑ ፕላን ነው፤ ምክኒያቱም፡ ፩ኛ. በቋንቋ የተከፋፉሉ ክልሎች ተመሥርተዋል፤ “እስከ መገንጠል” የሚለው ሕገ መንግስት በመጽደቁም ግቡን መትቷል፣ ፪ኛ. የመስተዳደሩን ኃላፊነት በተለይ ለትግርኛ ተናጋሪዎች በማስረከብ የተዋሕዶ የጀርባ አጥንት በሆኑት ትግሬዎች ላይ መጥፎ ስም በመስጠትና በመኮነን ሕዝቡ ጥላቻ እንዲኖረው ለማድረግ ይችላሉና ነው። በ፳፭ ዓመት ውስጥ የኢትዮጵያን ታሪክ እና ሁኔታ መረዳት የማይችል አንድ ትውልድ ተፈጥሯልና። ይህን አሁን በተከታታይ በግልጽ የምናየው ነው።

ኢትዮጵያውያን መስማት የሚፈልጉትንና ማየት የሚመኙትን ድራማ እንዲነግሯቸውና እንዲያሳዩአቸው እነ ዶር አብይ አህመድን መረጡ፤ ግን እነርሱን በደንብ ከማስተዋወቃቸው በፊት፡ ሉሲፈራውያኑ ያዘጋጇቸው ምሁራኑ እና ሜዲያዎቹ “ኢትዮጵያ፣ ኢትዮጵያ፣ ኢትዮጵያ” አሉ (መንግስቱ ኃይለማርያምም “ያለምንም ደም፤ ኢትዮጵያ ትቅደም! እያለ ነበር ሥልጣን ላይ የወጣው) ፣ “ባንዲራችን ላይ ኮከቡ መስፈሩ ተገቢ ነው አይደለም ” እያሉ የመረጧቸውን ሰዎች በማወያየት ኢትዮጵያውያንን አጠኑ፤ ሕዝቡ የት ድረስ አብሯቸው ሊጓዝ እንደሚችል ተገነዘቡ።

በኢትዮጵያዊነት ፍቅር የተጠሙ አገር ወዳዶቹ ኢትዮጵያውያን በየዋህነት “ኢትዮጵያ፣ ኢትዮጵያ” የሚለውን መፈክር አብረው ማሰማት፣ ኮከቡ ያላረፈበትንም ባንዲራ በየአደባባዩ ይዘው በመውጣት መፈንደቅ ጀመሩ። አሁን ይህ አገር ወዳድ የሆነው ኢትዮጵያዊ፡ ልክ፡ ቀደም ሲል “ነፍጠኛ” በማለት አማርኛ ተናጋሪውን ሲኮንኑት እንደነበረው፤ አሁን ደግሞ “ወያኔ” በማለት ትግርኛ ተናጋሪውን መኮነን እንዲበቃ ተደረገ፤ አንጎሉ ታጠበ። “ነፍጠኛ” እና “ወያኔ” የሚሉት የመወንጀያ ቃላት መግቢያ ሆኖ ለ “ተዋሕዶ ክርስቲያኖች” የተሰጠ ኮድ ናቸው።

የእኅተማርያም ማሕበር አባላት ግሩም በሆነ መልክ በትክክል ጠቁመውታል፤ ኮከቡ ያላረፈበትን ባንዲራችንን በየቤተክርስቲያኑ መሰቀል ጀምረው ነበር፤ አሁን ግን ሁሉም ኮከቡን እንደገና እንዲለጥፉ ታዘዋል።

/ር አብይ ሥልጣኑን በተረከበ ማግስት፤ “እውነት ሕዝባችንን ለማገልገል የመጣ ሰው ከሆነ እነዚህን ሦስት ነገሮች በፍጥነት መፈጸም ይኖርበታል” ብዬ ነበር፦

 • ፩ኛ. በቋንቋ የተከፋፈልውን የክልል ሥርዓት እንዲያፈርስ

 • ፪ኛ. ኮከቡን ከባንዲራችን ላይ በአዋጅ እንዲየነሳ

 • ፫ኛ. ከአረብ አገሮች ጋር ያለንን ጥብቅ ግኑኝነት እንዲያላላ

አመት ሆነው፤ ግን ሦስቱንም ጉዳዮች እስካሁን ለማስተካከል ሙከራ አላደረገም፤ እንዲያውም ሁኔታዎችን ወደ ባሰ መንግድ እየመራቸው ነው፤ በዚህም ሉሲፈራውያኑ ምዕራባውያን፣ አረቦችና የተባበሩት መንግስታት ፈላጭ ቆራጮች ታይቶ በማይታወቅ መልክ እያጨበጨቡለት ነው። ይህም በጣም ስላደፋፈረው፡ መጀመሪያ በትግርኛ ተናጋሪዎች ላይ ሤራ መጠንሰስ ጀመረ፤ አሁን ደግሞ ወደ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ዞረ። አቤት ድፍረት!

የእኅተ ማርያም እኅቶችና ወንድሞች ያሉት ትክክል ነው፤ ሁኔታዎችን በደንብ የሚቃኝ እያንዳንዱ የተዋሕዶ ልጅ ሊወስደው የሚገባው ግንዛቤ ነው። አዎ! /ር አብይ እና አጋሮቹ የ666ቱን ማህተብ ካልተቀበሉ በቀር ሥልጣን ላይ አይወጡም፤ አይቆዩምም። ሥልጣን ላይ ከወጡ ደግሞ የሉሲፈራውያኑን ትዕዛዝ መቀበል ግድ ነው፤ አሻፈረን ካሉ የመለስ ዜናዊ ዓይነት ዕጣ ስለሚደርሳቸው ይፈራሉ፤ ስለዚህ ፀረኢትዮጵያ፣ ፀረተዋሕዶ የሆነውን አጀንዳ የማራመድ ግዴታ አለባቸው ማለት ነው። እንደነርሱ ከሆነ የኢትዮጵያ ምሰሶ የሆነችው ተዋሕዶ መጥፋት አለባት፤ እርሷ ከጠፋች የአንድ ዓለም ሃይማኖት እና መንግስት መመስረት ይቀላቸዋል።

ግን አይሳካላቸውም፤ ወዮላቸው! ሁሉን የሚያይ እግዚአብሔር አምላክ የቀዳውን ቪዲዮ አንድ ባንድ ተንትኖ በኋላ ያሳያቸዋል። እነርሱን አያድርገን!

አዎ የሚያምን ከማያምን ጋር ምንም ሕብረት ሊኖረው አይገባም፦

[፪ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች ምዕራፍ ፮፥ ፲፬፡ ፲፭]

ከማያምኑ ጋር በማይመች አካሄድ አትጠመዱ፤ ጽድቅ ከዓመፅ ጋር ምን ተካፋይነት አለውና? ብርሃንም ከጨለማ ጋር ምን ኅብረት አለው? ክርስቶስስ ከቤልሆር ጋር ምን መስማማት አለው? ወይስ የሚያምን ከማያምን ጋር ምን ክፍል አለው?

[የማቴዎስ ወንጌል ምዕራፍ ፲፥ ፴፬፡፴፮]

በምድር ላይ ሰላምን ለማምጣት የመጣሁ አይምሰላችሁ፤ ሰይፍን እንጂ ሰላምን ለማምጣት አልመጣሁም። ሰውን ከአባቱ፥ ሴት ልጅንም ከእናትዋ፥ ምራትንም ከአማትዋ እለያይ ዘንድ መጥቻለሁና፤ ለሰውም ቤተ ሰዎቹ ጠላቶች ይሆኑበታል።

__________

Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

የሩሲያው መሪ ጥምቀትን በኦርቶዶክሷ ሰርቢያ ሲያከብሩ፡ የኛዎቹ ደግሞ ‘፫ኛውን ሂጂራ’ ወደ ኢትዮጵያን በማመቻቸት ላይ ናቸው

Posted by addisethiopia on January 19, 2019

መዝሙረ ዳዊት ምዕራፍ ፻፴፫]

ወንድሞች በኅብረት ቢቀመጡ፥ እነሆ፥ መልካም ነው፥ እነሆም፥ ያማረ ነው።

ከራስ እስከ ጢም እንደሚፈስስ፥ እስከ አሮን ጢም፥ በልብሱ መደረቢያ እንደሚወርድ ሽቱ ነው።

ኦርቶዶክሱ ፕሬዚደንት ፑቲን ለጉብኝት እህት አገር ወደ ሆነችው ወደ ሰርቢያ አምርተዋል። በሚሊየን የሚቆጠሩ ኦርቶዶክስ ክርስቲያኖች በዝነኛው የቅዱስ ሳቫ (የሰርቢያ ቅዱስ) ቤተክርስቲያን የሞቀ አቀባበል አድርገውላቸዋል።

በሉሲፈራዊያኑ የቱርክ፣ የናዚዎች እና በቅርቡም የኔቶ ሠራዊት በታሪኳ ብዙ ጥቃት የደረሰባት ኦርቶዶክስ ሰርቢያ መጀመሪያ በእርሷ እርዳታ ኃያል ለመሆን የበቃችውን ዩጎዛላቪያን በታትነው አደከሟት፤ ከዚያም፡ በቅርቡ፡ የክርስትና ስልጣኔዋ ታሪካዊ ቦታ የሆነችውን ኮሶቮን ገንጥለው ወሰዱባት።

..አ በ1999 .ም እሑድ በትንሳኤ በዓል ወቅት የአሜሪካው ፕሬዚደንት ቢል ክሊንተን ዋና ከተማዋን ቤዖግራድን በከፋ መልክ በቦምብ ማስደብደቡን አንረሳም፤ በኦርቶዶክስ ትንሳኤ ዕለት! እዚህ ያንብቡ

ያው እንግዲህ፤ ሉሲፈራውያኑ ከዚያ ጊዜ ጀምሮ ጦርነቱን ኦርቶዶክስ ክርስቲያን በሆኑት ሰርቢያ፣ ማኬዶኒያ፣ አርሜኒያ፣ ጆርጂያ፣ ሩሲያ፣ ዩክሬይን ቆጵሮስ፣ ሶሪያ፣ ግብጽ እና ኢትዮጵያ ላይ በማጧጧፍ ላይ ናቸው።

____________

Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

አንድ ጌታ፣ አንድ ሐይማኖት፣ አንዲት ጥምቀት | ኢትዮጵያ ላይ የሚኖረው የተጠመቀ ብቻ ነው

Posted by addisethiopia on January 18, 2019

በጥምቀትያልተጠመቀ የእግዚአብሔርን መንግሥት አይወርስምና[ኤፌ. ፬ ፥ ፭]

በሕፃናት እና ሴቶች ላይ ያተኮሩት የሦስቱ ሉሲፈራውያን (ሰዶማውያን፤ ኢ–ዓማንያን፤ ጂሃዲስቶች) ተልዕኮ ብዙ ነው። አሁን ትኩረታቸው “ጥምቀት” ላይ ይሆናል፤ አዎ! በተለይ የክርስቲያን ህፃናት ጥምቀት ላይ። “ሕፃናት ያለ ፈቃዳቸው መጠመቅ የለባቸውም” የሚል መፈክር አሁን ይዘው መጥተዋል። ግን ይህ ፔዶፊላዊ የዲያብሎስ ተልዕኳቸው አይሳካላቸውም።

አምኖ ያልተጠመቀ አይድንም፤ መንገሥተ ሰማያት ቀርባለችና ንስሐ ግቡ!

እንኳን ለብርሃነ ጥምቀቱ በሰላም በጤና አደረሰን!

________________

Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

ገነተ ኢየሱስ | ሰላም ያለው ሰላምን ያወራል፣ ክፉውንም ዘመን በእሱ ይሻገራል

Posted by addisethiopia on January 14, 2019

ይህ ጽሑፍ ከሰባት ዓመት በፊት በዚሁ ጦማሬ ላይ የቀረበ ነበር፦

በአይሁድና ክርስትና እምነቶች ላይ የሚካሄደው ጦርነት – የ፬ ሺህ ዓመት መለኮታዊ ሥርዓት ላይ የተመዘዘው ሳንጃ

በዓለ ግዝረት” መሢሑ ሕፃን ከቅድስት ድንግል ማርያም በቤተልሔም በበረት ከተወልደ በኋላ “ስምንት ቀንም በተፈጸመ ጊዜ ሕፃኑን ሊገዝሩት ወሰዱት ስሙኑም ገና በማሕፀን ሳይፀነስ አስቀድሞ መልአኩ እንደሰየመው ‘ኢየሱስ አሉት።‘” በሚለው የወንጌላዊው ቃል መሠረት፤ በ፰ኛው (8ኛው) ቀን ፡ “ኢየሱስ” ተብሎ የኪዳነ አብርሃምን ሥርዓት የፈጸሙበትን ዕለት በማስታወስ የምናከብረው በዓል ነው፤ እርሱም “በዓለ ግርዘተ ኢየሱስ” ተብሎ በጥር ፮ ቀን ይክበራል። [ሉቃ.፪፥፳፩]። ንቡረ እድ ኤርምያስ ወልደ ኢየሱስ መስከረም ፰ ነው የሚከበረው ይላሉ። የክርስቶስ ልደት መስከረም ፩ ነው የሚል ፅንሰ–ሃሳብ ስላላቸው።

እኛ ኢትዮጵያውያን ይህን በዓል የምናከብረው የኢየሱስ ክርስቶስን ግዝረት ለማስታወስ ብቻ ሳይሆን ሥርዓቱን ቀድሞም በኪዳነ ልቦና ማለትም ከአብርሃም በፊት በኖርንበት አምልኮተ እግዚአብሔር ስንፈጽመው የቆየን ኋላም በኪዳነ ኦሪቱ በአብርሃም በመጨረሻም በኪዳነ መንፈስ ቅዱስ ምክንያት ያንኑ ጥንታዊ ሥርዓታችንን አጽንተን የቀጠልን መሆናችንን ለማረጋገጥ ጭምር ነው። በዚህም እየራሳችን በቅዱሱ ኪዳን ጸጋ በነፍስ የሃይማኖትን ግዝረት፡ በሥጋም የምግባርን ግዝረትን ተቀብለን በመንፈስ ቅዱስ አማናዊውን የእግዚአብሔር ልጅነትን ክብር የተቀዳጀን መሆናችንን እናዘክርበታለን።

እኛ ኢትዮጵያውያን፡ ልክ እንደ አይሁዳውያን፡ ላለፉት 4ሺህ ዓመታት ያለማቋረጥ ወንዶች ሕፃናትን ከተወለዱ ከ8 ቀናት በኋላ እንዲገረዙ እናደርጋለን። ይህን ቅዱስ አይሁደ–ክርስቲያናዊ ሥርዓት የተቀረው የክርስቲያን ዓለም አልተከተለውም። ሙስሊሞችም ይህን ስነሥርዓት ከኛ ወስደው ሕፃናቶቻቸውን ከ 4 – 14 ባለው እድሜአቸው ይገርዛሉ። ግን ይህን አስመልክቶ በትውፊት ከአይሁዶችና ክርስቲያኖች ያገኙት እንጂ በቁራናቸው የተገለጸ ነገር የለም፤ ነብያቸውንም ተገርዞ ነው የተወለደው ነው የሚሉት።

የአውሮፓ ክርስቲያኖችም መጽሐፍ ቅዱሳዊ የሆነ የግዝረትን ሥርዓት አይከተሉም፡ ነገር ግን በተውፊት ስላገኙት ከ10 – 15% ብቻ የሚሆኑት አውሮፓውያን ወንዶች ተገርዘዋል፡ ይህም በጎልማሳ እድሜቸው። 75% የሚሆኑት አሜሪካውያን ተገርዘዋል። በብዛት ግን አይሁዳውያንና አፍሪካውያን ናቸው የሚገረዙት።

ግዝረት ሥጋዊና መንፈሳዊ ተልዕኮ ያለው ሥርዓት ስለሆነ፡ በሥጋ የተወለዱትና ለሥጋ ብቻ የሚኖሩት፡ ለኃጢአትና ለሞት የተዳረጉት ሉሲፈራውያኑ የሰው ልጆች፡ በአሁኑ ጊዜ ጦራቸውን በመምዘዝ ግዝረትን በመዋጋት ላይ ናቸው።

ጀርመን አገር በኮሎኝ ከተማ የሚገኝ አንድ ፍርድ ቤት ከጥቂት ቀናት በፊት ግዝረት ወንጀል ነው፡ በሕፃናት ላይ የሚሰነዘር ጥቃት ነው፡ ሕፃናት “ያለፈቃዳቸው” ሲገረዙ ለሥጋዊና ሥነ ልቦናዊ ቀውስ ይጋለጣሉ፡ ስለዚህ ሕፃናትን የሚገርዙ ወላጆች በፌደራል ሕግ መሠረት ይቀጣሉ የሚል ሕግ አስተላለፈ። እዚህች ይመልከቱ ። በታሪክ ተመሳሳይ የሆነ ፍርድ ለመጀመሪያ ጊዜ ተሰጥቶ የነበረው በአምባገነናዊው የናዚ ዘመን ነበር። አንዳንድ የስካንዲኔቪያ አገሮችም እስካሁን ድረስ እንደከለከሉ ናቸው።

ይህን መሠረተ–ቢስና አሳፋሪ የሆነ ድርጊት በሥራ ላይ ለማዋል፡ እንደሁልጊዜው የሚጠቀሙት ሙስሊሞችን ነው። ወደ አገሮቻቸው ሙስሊሞችን በብዛት ያጎረፉበት አንዱ ምክኒያትም የአይሁድ–ክርስቲያናዊውን ሥልጣኔ ከሥር መሠረቱ ነቃቅሎ ለማጥፋት የሺህ ዘመን ዕቅድ ስላላቸው ነው።

በአውሮፓ ግዝረትን እንደ ዋና የኃይማኖታቸው ምሰሶ አድርገው የሚወስዱት አይሁዶች ብቻ ናቸው። ያልተገረዘ አይሁድ አይሁድ ሊባል አይችልም! ታች ያለው እንግሊዛዊ ጽሑፍ ላይ እንደተቀመጠው፤ ከጥቂት ቀናት በፊት በኮሎኝ ከተማ አንድ 4 ዓመት እድሜ የሞላው ሙስሊም በሚገዘርበት ወቅት ብዙ ደም ፈስሶት ጤንነቱ ተቃውሷል የሚል ምክኒያት በመስጠት የከተማዋ ፍርድ ቤት ይህን ጸረ–ግዝረት ሕግ አጸደቀ። ይህን አስመልክቶ በዜና ማሰራጫዎች ከፍተኛ ውይይት በመካሄድ ላይ ይገኛል፤ 2/3 የሚሆኑት ጀርመናውያንም ግዝረትን ያወግዛሉ፤ የተላለፈውንም ሕግ ይደግፋሉ።

ምንም እንኳን ኮሎኝ የካቶሊኮች ከተማ ብትሆንም፤ ላለፉት 20/30 ዓመታት የአውሮፓ ሰዶማውያን ዋና ከሆኑት ከተሞች መካከል አንዷ ለመሆን በቅታለች። የፕሮቴስታንታዊው እንቅስቃሴ፤ ቅዱሳንን በማግለል፣ ቅዱሳዊ ሥርዓቶችን በመተው እንዲሁም ቅዱሳን ምስሎችና ምልክቶች በተከታዮቹ ዘንድ ተቀባይነት እንዳያገኙ ካደረገ በኋላ አውሮፓዊውን ለነፍሳዊና መንፈሳዊ ድክመት አጋለጠው። አሁን ደግሞ ለስጋዊው ድክመት በመጋለጥ ላይ ይገኛል። ግዝረትም ቁልፍ የሆነ ሚና እንደሚጫወት ተደርሶበታል።

ሰዶማዊነትን ወደ አፍሪካ ለማሰራጨት የሚካሄደው ዓይን ያወጣ እንቅስቃሴ ምን እንደሚመስል ለማወቅ እዚህች ላይ ይመልከቱ

ከዚህ ፀረ–ግዝረት እንቅስቃሴ ጀርባ፤ ሰዶማውያን፤ ኢ–ዓማንያን እና ጂሃዲስቶች ቆመዋል። እንዴት ጂሃዲስቶች? ብለን እንጠይቅ ይሆናል። አዎ! ምክኒያቱም፤ በእስልምና አንድ ልጅ 14 ዓመት እድሜ ሲሞላው ሊገዘር ስለሚችል፤ ቁራንም ስለ ግዝረት ስለማይናገር፤ ግዝረት በተለይ ለአይሁዳውያን ትልቅ ትርጉም ስላለው ነው። ኢ–ዓማንያኑንና ሰዶማውያንን የሚወክሉት የፍርድ ‘ሊቆች‘፡ ጠበቃዎችና ፖለቲከኞች የሚሉትም፡ ሕፃኑ 14 ዓመት ዕድሜ ሲሞለው ነው መገረዝ አለበት ነው። አሁን አይሁዳውያንና እስላሞች አንድ ላይ ሆነው የፍርድ ቤቱን ውሳኔ በመቃወማቸው ሁለቱም ተበዳዮች/ተጠቂዎች እንደሆኑ አድርገን ልንወስድ እንችል ይሆናል፤ ነገር ግን ይህ ትልቅ ስህተት ነው። ለአይሁዳውያኑ፡ ግዝረት፡ በምንም ዓይነት ለድርድር የሚቀርብ ጉዳይ ስላልሆን ለወንጀል የሚያበቃቸው ከሆነ አውሮፓን ለቅቀው ይወጣሉ፤ ከስካንዲኔቪያ ቀስበቀስ በመውጣት ላይ ናቸው(እስላሞች በሚያደርጉባቸው ጥቃቶች ሳቢያ)። በተፈጥሮዊው አካባቢአችን ንቦች እየጠፉ የሚሄዱ ከሆነ በዙሪያችን የተበላሸ ነገር እንዳለ፤ አደጋ እየመጣብን እንደሆነ እንረዳለን፤ በማሕበረሰብም ደረጃ በአውሮፓ አይሁዳውያን ለዘመናት ከሚኖሩቧቸው ቦታዎች የሚፈናቀሉ ከሆነ አስከፊ ጊዜ፡ ተመሳሳይ አደጋ እየመጣ እንደሆነ መገንዘብ ይኖርብናል።

ነፃ የወጡ የሳይንስ ሰዎች ግዝረት ከብዙ በሽታዎች (ኤይድስን ጨምሮ)እንደሚከላከል በግልጽ ይናገራሉ። እዚህች ይጫኑ ።

የሦስቱ ሉሲፈራውያን (ሰዶማውያን፤ ኢ–ዓማንያን፤ ጂሃዲስቶች) ተልዕኮ በዚህ ብቻ አይገታም። ተከታዩ ትኩረታቸው “ጥምቀት” ላይ ይሆናል፤ አዎ! የክርስቲያን ህፃናት ጥምቀት ላይ። “ሕፃናት ያለፈቃዳቸው መጠመቅ የለባቸውም” የሚል መፈክር በቅርቡ ይዘው እንደሚመጡ አንጠራጠር። የዓብያተ ክርስቲያናትን ደወሎች ለማስከልከልም በመንቀሳቀስ ላይ ናቸው።

______

Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , | Leave a Comment »

የሩሲያ መሪዎች በቤተክርስቲያን | አንድ የአገራችን መሪ ግን ለመጨረሻ ጊዜ ቤተክርስቲያን የሄደው ከ፵፭/ 45 ዓመታት በፊት ነበር

Posted by addisethiopia on January 13, 2019

እስኪ አስቡበትአብረን እናስብበትአንድ የኢትዮጵያ መሪ የክርስቶስ የሆነችውን እናት ቤተክርስቲያን የጎበኘው ከአርባ አምስት ዓመታት በፊት ነበር። ዋው!

የኮሙኒዝምን ሥርዓት ሲያገለግሉ የነበሩት የሩሲያው ፕሬዚደንት ቭላዲሚር ፑቲን የሉሲፈራውያኑን ርዕዮተ ዓለም እርግፍ አድርገው በመተው ወደ ክርስቶስ መጥተዋል። በሶቪየት ኮሙኒዝም ጊዜ የቭላዲሚር ፑቲን እናት በቅዱስ ፒተርስቡርግ ከተማ ወደሚገኘው ቤተክርስቲያን በድብቅ ቭላዲሚር ፑቲንን አምጥተዋቸው አስጠምቀዋቸው ነበር። (ቤተክርስቲያን የሚሄዱ ሩሲያውያን ክትትልና አድሎ ይደረግባቸው ነበርና)

በአንድ ወቅት፤ “አንገቴ ላይ ያደርግኳት ይህች መስቀል ሕይወቴን አድናታለች” በማለት መስክረው የነበሩት ፕሬዚደንት ፑቲን በዚሁ በተጠመቁበት ቤተክርስቲያን ነበር ባለፈው እሑድ የገና በዓልን ተመስጠው ሲያከብሩ የሚታዩት። ጠቅላይ ሚንስትር ሚድቪዴም ለፀሎት ሦስት ጊዜ ሲያማትቡ ይታያሉ።

ወደ አገራችን ስንመጣ፤ ቪዲዮው ላይ እንደሚታየው፡ አንድ የአገራችን መሪ ለመጨረሻ ጊዜ ኢትዮጵያዊቷን ቤተክርስቲያን የጎበኘው ከአርባ አምስት ዓመታት በፊት ነበር። እንዴት ነውይህ ክስተት እርርይ! ! ! አያሰኘንምን። ምን ዓይነት ኃጢዓት ብንሠራ ነው ኢትዮጵያን እና አምላኳን የሚጠሉ መሪዎች የተሰጡን?! እንደ መስቀል፣ ገና እና ጥምቀት በመሳሰሉት አንጋፋ የኢትዮጵያውያን ክብረ በዓላት (ሰባ ሚሊዬን ኢትዮጵያውያን የሚያከብሯቸው) ላይ ለመሳተፍ ፈቃደኛ የሆኑ መሪዎች እንኳን የሉንም። በመስከረሙ የመስቀል ደመራ በዓል ወቅት ዶ/ር አብይ በመስቀል አደባባይ ይገኙ ይሆናል የሚል ጭምጭምታ ነበር፤ ነገር ግን እርሳቸውም ያው ከ666ቱ ስለሆኑ ሳይሳተፉ ቀሩ።

ባለፈው ጊዜ፡ በዚምባብዌ፡ ለገዳዩ መንግስቱ ኃይለማርያም የሰገዱት የቀድሞው ጠ/ሚንስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ከስልጣን ከመውረዳቸው በፊት በኢየሩሳሌም የምትገኘውን የኢትዮጵያ ቤትከርስቲያን በእስራኤል መንግስት ግፊት ለመጎብኘት ሲገደዱ ጫማቸውን እንኳን ሳያወልቁ ነበር የገቡት፤ አቤት ድፍረት! አቤት ትዕቢት አቤት ቅሌት!

! ለሉሲፈራውያኑ ወኪሎች፤ ሕዝባችንን ኋለኞች ለማድረግ ተግተው ለሚሠሩት፤ ዋ!

እኛ የተዋሕዶ ልጆች ግን በገዢዎች ተስፋ ከማድረግ ይልቅ በእግዚአብሔር ተስፋ ማድረጉን እንመርጣለን፦

[ ፪ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች ምዕራፍ ፮፥፩፡፲]

አብረንም እየሠራን የእግዚአብሔርን ጸጋ በከንቱ እንዳትቀበሉ ደግሞ እንለምናለን፤ በተወደደ ሰዓት ሰማሁህ በመዳንም ቀን ረዳሁህ ይላልና፤ እነሆ፥ የተወደደው ሰዓት አሁን ነው፤ እነሆ፥ የመዳን ቀን አሁን ነው። አገልግሎታችንም እንዳይነቀፍ በአንዳች ነገር ማሰናከያ ከቶ አንሰጥም። ነገር ግን በሁሉ እንደ እግዚአብሔር አገልጋዮች ራሳችንን እናማጥናለን፤ በብዙ መጽናት፥ በመከራ፥ በችግር፥ በጭንቀት፥ በመገረፍ፥ በወኅኒ፥ በሁከት፥ በድካም፥ እንቅልፍ በማጣት፥ በመጦም፥ በንጽህና፥ በእውቀት፥ በትዕግሥት፥ በቸርነት፥ በመንፈስ ቅዱስ፥ ግብዝነት በሌለው ፍቅር፥ በእውነት ቃል፥ በእግዚአብሔር ኃይል፥ ለቀኝና ለግራ በሚሆን በጽድቅ የጦር ዕቃ፥ በክብርና በውርደት፥ በክፉ ወሬና በመልካም ወሬ ራሳችንን እናማጥናለን፤ አሳቾች ስንባል እውነተኞች ነን፤ ያልታወቁ ስንባል የታወቅን ነን፤ የምንሞት ስንመስል እነሆ ሕያዋን ነን፤ የተቀጣን ስንሆን አንገደልም፤ ኀዘንተኞች ስንሆን ዘወትር ደስ ይለናል፤ ድሆች ስንሆን ብዙዎችን ባለ ጠጎች እናደርጋለን፤ አንዳች የሌለን ስንሆን ሁሉ የእኛ ነው።”

__________________

Posted in Curiosity, Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

የሰማዕታት ደም የቤተ ክርስቲያን ምርጥ ዘር ነው | በአረቡ አለም አንጋፋው ቤተክርስቲያን በግብጽ ተመረቀ

Posted by addisethiopia on January 7, 2019

ከ ካይሮ በስተ ምሥራቅ በሚገኝ ቦታ ላይ በመካከለኛው ምስራቅ አንጋፋ የሆነውን ቤተክርስቲያን ሕንፃ ፓትሪያርክ ታዎድሮስ እና የግብጹ ፕሬዚደንት አብዱልፋታህ አሌሲሲ መርቀው ከፈተዋል። ሕንፃው “የልደት ካቴድራል” የሚል ስም ተሰጥቶታል።

ቀደም ሲል፡ በቅዳሜው ዕለት፡ ሙስሊሞች ቤተከርስቲያኑን በቦምብ ለማፈንዳት ባቅራቢው በሚገኝ ትልቅ መስጊድ ጣራ ላይ ቦምብ አጥምደው ተገኝተው ነበር። ቦምቡን ያከሸፍ ዘንድ ወደ መስጊዱ ተልኮ የነበረው አንድ ፖሊስ በፍንዳታ ሳቢያ ሕይወቱን አጥቷል።

የግብጽ ፕሬዚዳንት በመክፈቻው ሥነ ሥርዓት ላይ ይህ ታሪካዊና አስፈላጊ ጊዜ ነው

ነገር ግን፤ እኛ እዚህ በአንድ ላይ የተከልነውን የፍቅር ዛፍ መጠበቅ አለብንበማለት ተናግረዋል።

የመሀመድ አርበኞች የክርስቶስ ተከታዮችን ክፉኛ በመምታት ላይ በሚገኙበት በዚህ ዘመን፡ በእስያ እና አፍሪቃ ክርስትና እንደ ምስማር በመጥበቅ ላይ ነው።

ይህ ድንቅ የገና ተዓምር ነው! በእውነት ለክርስቲያን ወገኖቻችን ትልቅ ድል ነው፤ እንግዲህ ዲያብሎስና አርበኞቹ አሁን እርር፡ ፍርክስክስ ይበሉ፤ ጊዚያቸው አጭር ነው።

እውነት ነው፤ የሰማዕታት ደም የቤተ ክርስቲያን [ምርጥ] ዘር ነው። እኛ ክርስቲያኖች እንገፋለን እንጂ አንወድቅም፤ አዎ! ክርስቲያን እንደ ምስማር ሲመቱት የሚጠብቅ ነው።

+++የባሪያይቱን መዋረድ አይቶ+++

+++ንጉሥ ወደደሽ ከሴት ለይቶ+++

+++ዝቅ ማለትሽ ከፍ አድርጐሻል+++

+++ድንግል ትሕትናሽ ፍቅር አስጊጦሻል+++

__________________

Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

ኮፕት አባታችን በላሊበላ የገና በዓል | “ግሩም ታሪክና ሃይማኖታዊ ሥርዓት ስላላችሁ ልትኮሩበት ይገባል”

Posted by addisethiopia on January 6, 2019

ይህን ያሉት በጀርመን የኮፕት ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ጳጳስ የሆኑት አንባ ዳሚያን ናቸው። (ቪዲዮው ላይ “ዳንኤል” ያለው በስህተት ነው)። ግልጽና ቀጥተኛ የሆነ ቃል የሚናገሩና የማደንቃቸው አባት ናቸው። ቃለ ሕይወት ያሰማልን! ለኮፕት ወገኖቻችንም ይህን የልደት በዓል በሰላም እንዲያከብሩት እንመኝላቸዋለን!

ብሩክ ገና!!!

______________

Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , | 1 Comment »

ድንግል ፈጣሪዋን ወለደችው | ብሩክ የልደት በዓል

Posted by addisethiopia on January 5, 2019

ይህ የልደት በዓል ታኅሣሥ ፳፰ / ጃንዋሪ 7 በ፤

 • + ኢትዮጵያ (ኤርትራን ጨምሮ)

 • + እስራኤል

 • + ግብጽ

 • + አርመኒያ

 • + ጆርጂያ

 • + ሩሲያ

 • + ዩክሬን

 • + ቤላሩስ

 • + ሞልዶቫ

 • + ካዛክስታን

 • + ሰርቢያ

 • + ማኬዶኒያ

 • + ሞንቴኔግሮ

በቆንጆ መልክ ይከበራልእንኳን አደረሰን!

________________

Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , | Leave a Comment »

የእኅተ ማርያም ማኅበር | እምቦጩ የኢትዮጵያን ቅዱሳት ቦታዎች ለማጥፋት የተፈጠረ አረም ነው

Posted by addisethiopia on December 31, 2018

ያውም ገዳማቱ መግቢያ መግቢያ ቦታ ላይ ነው እንዲበቅል የተደረገው

ወንድማችን ትክክል ነው፤ ከእምቦጩ አረም መብቀል ጋር በተያያዝ ሤራው የተጠነሰሰው በየኢትዮጵያ ጠላቶች ነው። ይህ አያጠራጥረን! እንዲያውም ይህ በአይናችን ለማየት የበቃነው አንዱ ክስተት ብቻ ነው። መታየትና መታወቅ ያለባቸው ገና ብዙ ብዙ ነገሮች አሉ። ጎብኚዎች ብቻ ሳይሆኑ የአረሙ ተካዮች፡ በዚያ በኩል የሚይልፉ አውሮፕላኖች በእነ ዋልድባ፣ አክሱም፣ ላሊበላ፣ ጊሸን፣ ዝቋላ፣ ቍልቢ በኩል እያለፉ መርዛቸውን በውሃና ደኑ ላይ ይረጫሉ። በአባቶቻችን ጊዜ ተደጋግሞ ይከሰት የነበረው የወሎና ትግራይ ድርቅ መንስዔ በዚህ መልክ ነበር የተካሄደው።

ወንድማችን እንዳወሳው፡ ከመቶ አመት በፊት አንስቶ ወደ ውጭ አገር እየተላክንና ስለ ጠላቶቻችንን ተንኮል ለመማርና ለማወቅ እድሉ ያለን “ኢትዮጵያውያን” ይህን ሤራ ለማጋለጥ ፈቃደኞች አለመሆናችን ሁልጊዜ የሚከነክነኝና የሚያሳዝነኝ ጉዳይ ነው። በኢትዮጵያውያን የዘር ውርስ ወይም ጀነቲክስ ላይ ምርምር የሚያካሂድ አንድ የስታንፎርድ ወይም ኬምብሪጅ ዩኒቨርሲቲ ምሩቅ “ኢትዮጵያዊ” ለምሳሌ ሴቶቻችንን መኸን ለማድረግ ሕጻናቶቻችን ለማኮላሸት የተጠነሰሰ ሤራ እንዳለ በደንብ ነው የሚያውቀው። ታዲያ እንዴት ነው፡ በድብቅ እንኳን ለሕዝባችን ሹክ ከማለት የተቆጠቡት? በጣም ያሳዝናል፡ ለንስሃ እንኳን ሳንበቃ የዶክተርና የማስተርስ ማዕረጉን ይዘን ወደ አፈር ውስጥ መግባታችን እኮ ነው።

ድንቅ ሥራ እየሠራችሁ ነው እኅቶቻችን እና ወንድሞቻችን፤ እግዚአብሔር ይስጥልን!!!

 ______

Posted in Conspiracies, Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

የካናዳ ኢማም | “ክርስቲያኖችን እንኳን አደረሳችሁ የሚል፡ ወይም ሰላምታ የሚሰጥ ሙስሊም ከ ገዳይ የበለጠ ኅጢአተኛ ነው”

Posted by addisethiopia on December 28, 2018

ይህ በካናዳዋ ብሪቲሽ ኮሎቢያ ዋና ከተማ በቪክቶሪያ ተቀማጭነት ያለው የእስላሞች ኢማም የሚከተሉትን ፀረክርስቲያን ቃላት ወጣት ሙስሊሞች በተሰበሰቡት እንዲህ በማለት ይጀምራል፦

በአካባቢያችን ያሉ ሰዎች የገናን በዓል ለማክበር በመዘጋጀት ላይ ናቸው።

ሙስሊሞች ክርስቲያኖችን ለገና በዓል እንኳን አደረሳችሁ ሲሏቸው በመስማቴ

በጣም አዝኛለሁ፤ አንዳንዶቹማ ክርስቲያኖችን ለሐሰተኛ በዓላቻው እንኳን አደረሳችሁ ሲሉ እና ሰላምታ ሲሰጡ ብቻ ሳይሆን የሚታዩት፡ እንዲያውም ከእነርሱ ጋር በዓሉን አብረው ያከብራሉ። ይህ ቀላል ነገር አይምሰላችሁ።

ሰዎች ኢየሱስን ሲያመልኩ ወይም ኢየሱስ የአምላክ ልጅ ነው ሲሉ ስናይ

እናንተን እና እኔን በጣም ሊያስቆጣን ይገባል።

ለክርስቲያኖች “ብሩክ ገና!”የሚሉ ሙስሊሞች አሉ፤ ለመሆኑ ለምኑ ነው እንኳን ደስ አላችሁ የምትሏቸው? ለጌታችሁ ልደት እንኳን ደሳላችሁ ነው?!

ይህን መመኝት ለአንድ ሙስሊም ይፈቀድለታልን?! የእነርሱን እምነት እያረጋገጣችሁላቸው አይደለምን?!

አንድ ሙስሊም ክርስቲያኖችን ለሐሰተኛ በዓላቻው እንኳን አደረሳችሁ ቢል እና ሰላምታ ቢሰጥ፡ እንደ ዝሙት፣ ወለድ፣ ውሸት እና ነፍስ ግድያ ከመሳሰሉት ከባድ ኃጢአቶች የበለጠ ኃጢአት ሠርቷል ማለት ነው።

ሙስሊም ያልሆኑትን ሂዱና ግደሏቸው ማለቴ ግን አይደለም፤ ለፍትህ መቆም ይገባናል ማለቴ እንጂአብራካዳብራ!

ዋውውው! ያውም የኩፋር አገር ወደሚላት ካናዳ መጥቶ!?

እንግዲህ ይህ ነው ትክክለኛው እስልምና! የእያንዳንዱ ትክክለኛ ሙስሊም አመለካከትም ይህ ነው። በሳዑዲ ባርባሪያ ጥቁር ድንኳን ለብሳ በበረሃ ሙቀት የምትቀቀለው ወገናችንም ይህን ነው ቪዲዮው ላይ የምታረጋግጠው።

ግን ድፍረታቸው ይገርማል፤ የዱር አህዮቹ እስማኤላውያኑ ሁሉ ነገራቸው ሰይጣናዊ ነው። ሁልጊዜ ነገሮችን ፕሮጀክት እንዳደረጉ ወይም እንዳንጸባረቁ ነው፦

ክርስቲያኖችን “እንኳን አደረሳችሁ!” አንልም በማለት ከእነርሱ በተሻለ መልክ ትሁት ለመሆን የሚጥሩትን ክርስቲያኖችን ጣዖታዊ ለሆኑት የእስልምና በዓላቶቻቸው፡ “እንኳን አደረሳችሁ!” ይሏቸው ዘንድ ለመቆስቆስ የታቀደ ተንኮል ነው።

እኛ ክርስቲያኖች እንኳን ለገዳዩና ህፃናት ደፋሪው መሀመድ የልደት ቀን እነርሱን “እንኳን አደረሳችሁ!” (እንኳን ለሲዖል አበቃችሁ! እንደማለት ነው) ማለት የለብንም፤ እነርሱም ይህን ያውቁታል፤ ግን አምልኳቸውን እንድናረጋግጥላቸው ለበዓላቸው እንኳን አደረሳችሁ እንድንላቸው ይመኛሉ። ለዚህ ነው እኛን ሁሌ ቀድመው የሚኮንኑት፤ ልክ እነርሱ ገዳዮች ሆነው ተገዳዩን ቀድመው እንደሚኮንኑት ማለት ነው። “ጥቃት ከሁሉ የተሻለው መከላከያ ነው!” ብለው ስለሚያምኑ።

ደግሞ የሚገርመው እስልምና ከጌታችን ልደት ከስድስት መቶ አመት በኋላ መጥቶ፡ “ሰዎች ኢየሱስን ሲያመልኩ ወይም ኢየሱስ የአምላክ ልጅ ነው ሲሉ ካየን እናንተን እና እኔን ሊያስቆጣን ይገባል” ይሉናል።

እንግዲህ፡ አምላካችንን ለምን ዝቅ አደረጋችሁት፤ ለምን ነብይ ብቻ ነው አላችሁት? ለምን አልተወልደም፣ አልተሰቀልም ብላችሁ ታስቀይሙናላቸው? በማለት እንዳንኮንናቸው ቀድምው ሲያጠቁን ነው።

ባጭሩ፡ እነዚህ ሙስሊም ውሸታሞች … “ኢየሱስን እንደ አምላክ ነብይ እናደንቀዋለን፣ እንወደዋለን” በማለት ይዋሹናል ነገር ግን የእርሱን ልደት አታክብሩ እያሉ ጥሪ ያስተላልፋሉ፤ ተከታዮቹንም ያርዳሉ ሁሉንም ነብያት እናከብራልን ይላሉ፤ ነገር ግን ስለ ሁሉም ነብያት ብዙ የሚናገረውን መጽሐፍ ቅዱስን መስጊዶቻቸው ውስጥ ለስብከት አይጠቀሙበትም።

የዚህ ኢማም መልዕክት ባጭሩ፦ “አንድ ሙስሊም “ብሩክ ገና!” ካለ ይገደል!” በሌላ አነጋገር አንድ ሙስሊም “እንኳን አደረሳችሁ!” ከሚላችሁ ቢግድላችሁ ይቅለዋል ማለት ነው። ወደ ሺርያ ህግ እንኳን ደህና መጣችሁ!

እስላም ሰይጣንን ያመልካልና “እንኳን አደረሳችሁ!” ባይሉን ይመረጣል፤ በአላሃቸው ስም ከመረቁን ወይም “እንኳን አደረሳችሁ!” ካሉን ለእኛ እንደ እርግማን ነው የሚሆነው። በአላህ ስም ከመረቋችሁ፡ ሦስት ጊዜ ማማተብ እንጅ፡ አሜን! አትበሏቸው!

______

Posted in Ethiopia, Faith, Infos | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

 
%d bloggers like this: