Posts Tagged ‘ኢንዶኔዥያ’
Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on October 16, 2019
በሙስሊሞች ቁጥር በዓለም የመጀመሪያውን ቦታ የያዘችው ኤንዶኒዥያ፡ በዋና ከተማዋ በጃካርታ፡ አሆክ የተባለው የቻይና ዝርያ ያለው ክርስቲያን ኢንዶኔዢያዊ ለከንቲባነት / አስተዳዳሪነት ሲመረጥ ሙስሊሞቹ የከተማዋ ነዋሪዎች፡ አለመታደል ሆኖ፡ “ክርስቲያን ከንቲባ አንፈልግም!” የሚል መፈክር በመያዝ ወደ መንግዶች ግልብጥ ብለው ሲወጡና ቁጣቸውን ለሳምንታት ሲያሳዩ ቆይተው ነበር። በአጭር ጊዜ ውስጥም ከንቲባው ከስልጣን እንዲወገድ ብሎም እንዲታሰር አድርገውታል። በጃካርታ አብዛኛዎቹ ነዋሪዎች የጃቫ እና ሱንዳን ብሔረሰቦች አባላትና ሙስሊሞችም ሲሆኑ ከንቲባው ግን ክርስቲያን እና የቻይና ብሔረሰብም አባል ነው። በኢንዶኔዥያ እስከ 300 ብሔረሰቦች ተመዝግበዋል።
85% የሚሆኑት የጃካርታ ነዋሪዎች ሙስሊሞች ናቸው።
ከ10 ሚሊየን በላይ ነዋሪዎች ያሏት ጃካርታ በፍጥነት ወደ ምድር እየሰጠመች መሆኑ የኢንዶኔዢያ ባለስልጣናትን አሳስቧቸዋል። የጃካርታን ሥነ ምድራዊ አቀማመጥ የሚያጠኑ ተመራማሪዎች እንደገለጹት ከተማዋ በአውሮፓውያኑ 2050 ሙሉ በሙሉ የምትሰጥም ሲሆን ባለፉት 10 ዓመታት ብቻ 2.5 ሜትር ወደታች ሰጥማለች። ይህ ማለት ደግሞ ከተማዋ በየዓመቱ ከ1 እስከ 15 ሴንቲሜትር ወደታች ትገባለች ማለት ነው።
ሕገ–ወጡና ውርንጭላው የአዲስ አበባ ከንቲባ ታኮ ጎማ የዶክትሬት ዲግሪውን በጃካርታ ኢንዶኔዥያ ቢሠራ ጥሩ ነው፤ “አንዲት ከተማ እንዴት ወደታች ትሰጥማለች?” በሚል ርዕስ። LOL!
85% የሚሆኑት የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ተዋሕዶ ክርስቲያኖች ናቸው።
አብዛኞቹ የጃካርታ ነዋሪዎች ክርስቲያን የሆነ ከንቲባ አንፈልግም ካሉ፤ አዲስ አበቤዎችም ተዋሕዶ ያልሆነ ከንቲባ አንፈልግም የማለት ሙሉ መብት አላቸውና ተዋሕዶ ያልሆኑ ወረበሎች ደም ሳያስለቅሷቸው ይህን መብታቸውን ለማስከበር እንደ ሙስሊሞቹ መጮህን መታገል ይኖርባቸዋል።
የሙስሊሞቹ ጪኸት፡ በጃካርታ እንደምናየው፡ ወደ ጥልቁ ለመግባትና ወደ ጥፋትም ለመሄድ ሲሆን፣ የክርስቲያኖች ጪኸት ግን ርግቦች ወደ ቤታቸው እንደሚበርሩ፥ እንደ ደመና በመብረርና ወደ ሰማይ ቤት ለመውጣት ነው።
_________________________
Like this:
Like Loading...
Posted in Curiosity, Ethiopia, Infos | Tagged: ሙስሊሞች, ንፅፅር, አዲስ አበባ, ኢንዶኔዥያ, ከንቲባ ምርጫ, ክርስቲያኖች, ጃካርታ, ፍትህ | Leave a Comment »
Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on January 17, 2019
ከአዲስ አበባ ወደ ሆንግ ኮንግ ይበር የነበረውን የኢትዮጵያ አየር መንገድ የጭነት አውሮፕላን “ኢት 3728” በኢንዶኔዥያ አየር ክልል አልፏል በሚል ሁለት ኤፍ 16 የጦር አውሮፕላኖች አጅበው በኢንዶኒዥያ እንዲያርፍ አስገድደውታል።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግን በተከሰተው ነገር አልተስማማም፡ ምክኒያቱም አንድ አውሮፕላን ወዳጅ በሆኑ አገራት አየር ላይ የማለፍ መብት እንዳለው የዓለም አቀፍ በረራ ስምምነቶች ያጸድቃሉና።
ከዚህ ቅሌት ጀርባ ተንኮል ይኖርበታል፦
በሙስሊሞች ሕዝብ ቁጥር በዓለም የመጀመሪያውን ቦታ የምትይዘዋ ኢንዶኔዥያ የኢትዮጵያ ወዳጅ ልትሆን አትችልም። ስልጣን ላይ የተቀመጡት መሪዎቻችን ከሙስሊም አገራት ጋር የጠበቀ ግኑኝነት ለመፍጠር ሲፈጨረጨሩ ይታያሉ (ያው ዛሬ ደግሞ ካታርን ወደ ኢትዮጵያ ለማስገባት ጥሪ አቅርበዋል) ነገር ግን፡ ሃቁ፡ ሙስሊም የሆኑ አገሮች የኢትዮጵያ ወዳጆች ሊሆኑ አይችሉም፤ እሳት እና ውሃን ለመቀላቀል፤ እንዴት ይሆናል?! በጭራሽ አይሆንም! ኢትዮጵያ ልክ እንደ እስራኤል፡ ከእግዚአብሔር በቀር ወዳጅ የሆነ ሌላ አገር ወይም ሕዝብ የላትም። ሃቁ ይህ ነው!
__________________
Like this:
Like Loading...
Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: ሆንግ ኮንግ, ተዋጊ አውሮፕላኖች, አዲስ አበባ, ኢንዶኔዥያ, የኢትዮጵያ አየር መንገድ, የጭነት አውሮፕላን | Leave a Comment »
Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on December 23, 2018
በሙስሊሞች ቁጥር ብዛት በዓለም የመጀሪያውን ቦታ የያዘቸው ኢንዶኔዥያ በክርስቶስ ተከታዮች ላይ ከፍተኛ በደል በመፈጸም ላይ ትገኛለች። ባለፈው ዓመት በዋና ከተማዋ ጃካርታ አንድ ክርስቲያን ጠቅላይ ገዢ ወይም ከንቲባ ሊሆን አይችልም በማለት ሙስሊሞቹ አምጸው ክርስቲያኑን ፖለቲከኛ እንደወነጀሉትና ከስልጣኑ እንዳስወረዱት የሚታወስ ነው። በዛሬዋ ኢንዶኔዥያ፤ ዓብያተክርስቲያናት ማሠራት ልክ እንደ ሳውዲ አረቢያ እና ግብጽ ከባድ እየሆነ መጥቷል። ቪዲዮው ላይ እንደሚታየው ያሉትም ዓብያተክርስቲያናት በመሀመድ አርበኞች በመፈራረስ ላይ ናቸው። ለከርስቲያኖች ያላቸውን ጥላቻ እንመልከት!
ከሦስት ቀናት በፊት ክርስቲያኑ ቄስ የተቀበሩበት መቃብር ላይ የተተከለውን የእንጨት መስቀል ሙስሊሞች “ይህች የእስላም አገር ናት” በማለት ሰባብረውታል። ለሙታን እንኳን ተገቢውን ክብር አለመስጠታቸው በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ ምን ያህል ጥላቻ እንዳላቸው ነው የሚያሳየው።
እግዚአብሔር አምላክ ግን “በቃ!” የሚልበት ዘመን ላይ ደርሰናል፤ የሚፈጸሙብንን ግፎች ዝም ብሎ አያልፍም።
በገና በዓል አካባቢ ኢንዶኔዥያ በተፈጥሮ አደጋ ብዙ ጊዜ ትናወጣለች፤ ዛሬም እሳተ ገሞራው ፈነዳ፤ ባሕሩም ኃይለኛ ሞገድ ሠራ በመስቀሉ ጠላቶች ላይ ከፍተኛ ቁጣ መጣ!
[የማቴዎስ ወንጌል ምዕራፍ ፳፯፥፶፡፶፩]
“ኢየሱስም ሁለተኛ በታላቅ ድምፅ ጮኾ ነፍሱን ተወ።
እነሆም፥ የቤተ መቅደስ መጋረጃ ከላይ እስከ ታች ከሁለት ተቀደደ፥
ምድርም ተናወጠች፥ ዓለቶችም ተሰነጠቁ፤“
____________
Like this:
Like Loading...
Posted in Curiosity, Ethiopia, Faith | Tagged: መሬት መንቀጥቀጥ, መስቀል, ሱናሚ, አድሎ, ኢንዶኔዥያ, እሳተ ገሞራ, ጥላቻ, ፀረ-ክርስቲያን ዘመቻ, Christian Persecution, Divine Warning, Indonesia, Karakatoa, Tsunami, Volcano | Leave a Comment »
Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on October 30, 2018
– በዛሬው ዕለት፡ እ.አ.አ ጥቅምት 29 / 2018፦
189 መንገደኞችን የያዘው የኢንዶኔዢያ አውሮፕላን ከመከስከሱና ሁሉም ተሳፋሪዎች ከመሞታቸው በፊት እንዴት እንደሚጮሁና አላሃቸውንም እንደሚማጸኑ ቪዲዮው ያሳየናል።
+ ማክሰኞ ዕለት፡ እ.አ.አ. ነሐሴ 31 / 2018 ዓ.ም፦
103 ተሳፋሪዎችን ይዞ የነበረው የሜክሲኮ አውሮፕላን ተመሳሳይ አደገኛ ሁኔታ ላይ ነበር፤ ቀጣዩ ቪዲዮ ላይም መንገደኞቹ አንዱን አምላካችንን ኢየሱስ ክርስቶስን ሲማጸኑ ይሰማሉ። ሁሉም ተሳፋሪዎች በተዓምሩ ተርፈዋል።
ተዓምሩን በከፊልም ቢሆን በቪዲዮ የቀረጸው አብሮ ይጓዝ የነበረውና፡ እስልምናን በመተው ወደ ክርስትና የመጣው ኢራናዊ ነው።
ሁለት ደቂቃ በሚወስደው ቪዲዮው ላይ፡ አውሮፕላኑ ከመነሳቱ በፊት እና ከአደጋውም በኋላ ከበስተጀርባ ሴቶች፣ ወንዶች እና ሕፃናት ሲጯጯሁ ይሰማል፤ የ እግዚአብሔርን ስም ጮክ ብለው ሲጠሩ እና “ኢየሱስ ክርስቶስ ባክህ በሩን ክፈተው” በማለት ሲማፀኑ ይሰማሉ።
የቪዲዮው አንሺ ኢራናዊ በትዊተር ገጹ ላይ የሚከተለውን ተናግሮ ነበር፦
“በእግዚአብሔር ጸጋ ደህና ነኝ፡ እርሱ ይመስገን በህይወት አለን፣ ይህ ሌላ ነገር አይደለም ትልቅ የእግዚአብሔር ተዓምር ነው፣ ሕይወት ስላለሁ ለኢየሱስ ክርስቶስ ብድር አለበኝ፣ ዲያቢሎስ ሕይወቴን ሊወስድ እችላለሁ ብሎ አስቦ ነበር፡ ነገር ግን አሁን እንዲያውም ለ ኢየሱስ ክርስቶስ እራሴን በይበልጥ እንደሰጥ ረድቶኛል”
______
Like this:
Like Loading...
Posted in Curiosity, Ethiopia, Faith | Tagged: ሙስሊሞች, ሜክሲኮ, ተዓምር, አላህ, ኢንዶኔዥያ, ኢየሱስ ክርስቶስ, ኤሮ ሜክሲኮ, ክርስቲያኖች, ክርስትና የአውሮፕላን አደጋ | Leave a Comment »