Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World

 • April 2017
  M T W T F S S
  « Mar    
   12
  3456789
  10111213141516
  17181920212223
  24252627282930
 • Archives

 • Categories

 • Recent Posts

Posts Tagged ‘ኢትዮጵያ’

ጸሎተ ሐሙስ | ይህ ዕለት ለኃጢአትና ለዲያብሎስ ባሪያ ኾኖ መኖር ማብቃቱ የተገለጠበት፤ የሰው ልጅ ያጣውን ክብር መልሶ ማግኘቱ የተረጋገጠበት ቀን ነው

Posted by addisethiopia on April 13, 2017

ሚያዝያ ፬ ቀን ፳፻፱ ዓ.

ጸሎተ ሐሙስ በብሉይ ኪዳን

ጸሎተ ሐሙስ በብሉይ ኪዳን ለፋሲካ ዝግጅት ተደርጎበታል (ማቴ. ፳፮፥፯፲፫)፡፡ ‹ፋሲካ› ማለት ማለፍ ማለት ነው፡፡ ይኸውም እስራኤላውያን በግብጽ ምድር ሳሉ መልአኩን ልኮ እያንዳንዱ እስራኤላዊ የበግ ጠቦት እንዲያርድና ደሙን በበሩ ወይም በመቃኑ እንዲቀባ ለሙሴ ነገረው፡፡ ሙሴም የታዘዘውን ለሕዝቡ ነገረ፤ ዅሉም እንደ ታዘዙት ፈጸሙ፡፡ በኋላ ከእግዚአብሔር ዘንድ መቅሠፍት ታዞ መልአኩ የደም ምልክት የሌለበትን የግብጻውያንን ቤት በሞተ በኵር ሲመታ፤ የበጉ ደም ምልክት ያለበትን የእስራኤላውያንን ቤት ምልክቱን እያየ አልፏል፡፡ ፋሲካ መባሉም ይህን ምሥጢር ለማስታወስ ነው (ዘፀ. ፲፪፥፩)፡፡

በዚህ መነሻነት በየዓመቱ እስራኤላውያን በመጀመሪያው ወር በዐሥራ አራተኛው ቀን በግ እያረዱ የፋሲካን በዓል ያከብራሉ፡፡ አገራችን ኢትዮጵያም አስቀድማ ብሉይ ኪዳንን የተቀበለች አገር እንደ መኾኗ ይህን ሥርዓት ትፈጽም ነበር፡፡ በሐዲስ ኪዳንም የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ትንሣኤ ‹ፋሲካ› ተብሎ የተጠራበት ምክንያት ጌታችን በዚህ በፋሲካ በዓል ራሱን የተወደደ ምሥዋዕት አድርጎ ደሙን ስላፈሰሰልን ነው፡፡ በደሙ መፍሰስም ሞተ በኵር የተባለ ሞተ ነፍስ ርቆልናል፡፡ ስለዚህም ክርስቶስን ‹ፋሲካችን› እንለዋን (፩ኛ ቆሮ. ፭፥፯፤ ፩ኛ ጴጥ. ፩፥፲፰፲፱)፡፡

የጸሎተ ሐሙስ ስያሜዎች

ጸሎተ ሐሙስ በቤተ ክርስቲያን በርካታ ስያሜዎች አሉት፡፡ የዓለም መድኃኒት ኢየሱስ ክርስቶስ ሥጋን የተዋሐደ አምላክ መኾኑን ለመግለጥና ለአርአያነት ጠላቶቹ መጥተው እስኪይዙት ድረስ ሲጸልይ ያደረበት ቀን ነውና ‹ጸሎተ ሐሙስ› ይባላል (ማቴ. ፳፮፥፴፮፶፮)፡፡ ጌታችን በዚህ ዕለት የደቀ መዛሙርቱን እግር በፍጹም ትሕትና ዝቅ ብሎ አጥቧል፡፡ ይህም ኢየሱስ ክርስቶስ የዓለምን ዅሉ ኃጢአት ለማጠብ የመጣ የንጽሕና፣ የቅድስና አምላክ መኾኑን ያጠይቃል፡፡ ስለዚህም ዕለቱ ‹ሕጽበተ ሐሙስ› ይባላል፡፡ ይህን ለማስታወስ ዛሬም ሊቃነ ጳጳሳትና ቀሳውስት ‹‹በመካከላችን ተገኝተህ የእኛንና የሕዝብህን ኃጢአት እጠብ፤ እኛም የአንተን አርአያነት ተከትለን የልጆቻችንን እግር እናጥባለን፤›› ሲሉ በቤተ ክርስቲያን የተገኙ ምእመናንን እግር በወይንና በወይራ ቅጠል ያጥባሉ፡፡

ከሰባቱ ምሥጢራተ ቤተ ክርስቲያን አንዱ ምሥጢረ ቍርባን በዚህ ቀን ተመሥርቷልና ዕለቱ ‹የምሥጢር ቀን› ይባላል፡፡ ይኸውም ጌታችን ኅብስቱንና ጽዋውን አንሥቶ ‹‹ይህ ስለ እናንተ በመስቀል ላይ የሚቈረሰው ሥጋዬ ነው፡፡ እንካችሁ፤ ብሉ፡፡ ይህ ስለ እናንተ ነገ በመስቀል ላይ የሚፈስ ደሜ ነው፤ ከእርሱም ጠጡ፤›› በማለት እርሱ ከእኛ፤ እኛም ከእርሱ ጋር አንድ የምንኾንበትን ምሥጢር ከጠላት ዲያብሎስ ሰውሮ፣ ለደቀ መዛሙርቱ የገለጠበት ቀን በመኾኑ የተሰጠ ስያሜ ነው፡፡ በዚህ ዕለት ክርስቲያን የኾነ ዅሉ በንስሐ ታጥቦ ቅዱስ ሥጋውንና ክቡር ደሙን ለመቀበል ይዘጋጃል፡፡

መድኃኒታችን ክርስቶስ መሥዋዕተ ኦሪት ማለትም በእንስሳት ደም የሚቀርበው መሥዋዕት ማብቃቱን ገልጦ፣ ለድኅነተ ዓለም ራሱን የተወደደ መሥዋዕት አድርጎ ያቀረበበት ዕለት በመኾኑ ይህ ዕለት ‹የሐዲስ ኪዳን ሐሙስ› ይባላል (ሉቃ. ፳፪፥፳)፡፡ ‹ኪዳን› ማለት በሁለት ወገን መካከል የሚደረግ ውል፣ ስምምነት፣ መሐላ ማለት ነው፡፡ በዚህ መሠረት ጌታችን ለአዳምና ለልጆቹ ዅሉ ዘለዓለማዊውን ቃል ኪዳን በራሱ ደም የፈጸመበት ዕለት ስለ ኾነ ሐሙስ ‹የሐዲስ ኪዳን ሐሙስ› ተባለ፡፡

ይህ ዕለት ለኃጢአትና ለዲያብሎስ ባሪያ ኾኖ መኖር ማብቃቱ የተገለጠበት፤ የሰው ልጅ ያጣውን ክብር መልሶ ማግኘቱ የተረጋገጠበት ቀን ስለ ኾነ ‹የነጻነት ሐሙስ› ይባላል፡፡ ጌታችን ስለ ሰው ልጅ ነጻነት ሲናገር ‹‹ከእንግዲህ ወዲህ ባሮች አልላችሁም፤ ባርያ ጌታው የሚያደርገውን አያውቅምና፡፡ ወዳጆች ግን ብያችኋለሁ፤›› በማለት ከባርነት የወጣንበትን፤ ልጆች የተባልንበትን ቀን የምናስብበት በመኾኑ ሊቃውንቱ ‹የነጻነት ሐሙስ› አሉት (ዮሐ. ፲፭፥፲፭)፡፡ እያንዳንዱ ክርስቲያንም ከኃጢአት ባርነት ርቆ፣ ከእግዚአብሔር ጋር የሚወዳጀውን መልካም ሥራ በመሥራት ሕይወቱን መምራት ይኖርባታል፡፡ ባሮች ሳይኾን ወዳጆች ተብለን በክርስቶስ ተጠርተናልና፡፡

በዚህ ዕለት እንደ ማክሰኞ ዅሉ ጌታችን በዮሐንስ ወንጌል ፲፬፥፲፮ የሚገኘውን ሰፊ ትምህርት ለደቀ መዛሙርቱ አስተምሯል፡፡ የትምህርቱም ዋና ዋና ክፍሎችም ምሥጢረ ሥላሴን፣ ምሥጢረ ሥጋዌንና ምሥጢረ ትንሣኤ ሙታንን ያካትታሉ፡፡ ጌታችን እነዚህን ትምህርቶች በስፋትና በጥልቀት መማር እንደሚገባ ሲያስረዳ፣ ለደቀ መዛርቱ ምሥጢሩን በተአምራት ሊገልጥላቸው ሲቻለው በሰፊ ማብራርያ እንዲረዱት አድርጓል፡፡ ደቀ መዛሙርቱም ያልገባቸውንም እየጠየቁ ተረድተዋል፡፡ ምእመናንም በቤተ ክርስቲያን ተገኝተን መማርና ያልገባንን ጠይቀን መረዳት እንደሚገባን ከዚህ እንማራለን፡፡ መድኃኒታችን ክርስቶስ ራሱን ለአይሁድ አሳልፎ የሰጠውም በዚሁ ዕለት ከምሽቱ በሦስት ሰዓት ነው (ማቴ. ፳፮፥፵፯፶፰)፡፡

በጸሎተ ሐሙስ በቤተ ክርስቲያን የሚፈጸም ሥርዓት

በዚህ ዕለት ስግደቱ፣ ጸሎቱ፣ ምንባባቱ እንደ ተለመደው ይከናወናሉ፡፡ መንበሩ (ታቦቱ) ጥቁር ልብስ ይለብሳል፡፡ ጸሎተ ዕጣን ይጸለያል፤ ቤተ ክርስቲያኑም በማዕጠንት ይታጠናል፡፡ ሕጽበተ እግር ይደረጋል፡፡ ቅዳሴ ይቀደሳል፡፡ በየቤቱ ደግሞ ጉልባን ይዘጋጃል፡፡

ሕጽበተ እግር

ከቀኑ በዘጠኝ ሰዓት ዲያቆኑ ሁለት ኵስኵስቶችን ውኃ ሞልቶ ያቀርባል፤ አንዱ ለእግር፣ አንዱ ለእጅ መታጠቢያ፡፡ ‹ጸሎተ አኰቴት› በመባል የሚታወቀው የጸሎት ዓይነት ይጸለያል፡፡ ወንጌል ተነቦ ውኃው በካህኑ (በሊቀ ጳጳሱ) ይባረክና የሕጽበተ እግር ሥርዓት ይከናወናል፡፡ ይኸውም ጌታችን የደቀ መዛሙርቱን እግር በማጠብ ያሳየውን የተግባር ትምህርት ለማሳየት ነው (ዮሐ. ፲፫፥፲፬)፡፡ ከውኃው በተጨማሪ የወይራና የወይን ቅጠልንም ለሥርዓተ ሕጽበቱ ማስፈጸሚያነት እንጠቀምባቸዋለን፡፡ ምሥጢሩም የሚከተለው ነው፤

ወይራ ጸኑዕ ነው፡፡ ወይራ ክርስቶስም ጽኑዕ መከራ መቀበሉን ከማስረዳቱ በተጨማሪ እኛም (እግራችንን የሚያጥቡን አባቶች እና የምንታጠበው ምእመናን) መከራ ለመቀበል ዝግጁ ነን ለማለት ሥርዓተ ሕጽበቱን በወይራ እንፈጽማለን፡፡ የወይኑ ቅጠልም መድኃኒታችን ክርስቶስ በወይን የተመሰለ ደሙን አፍስሶ ለምእመናን የሕይወት መጠጥ አድርጎ መስጠቱን ለማዘከር በወይን ሥርዓተ ሕጽበትን እናከናውናለን (ማቴ. ፳፮፥፳፮)፡፡ በቀኝና በግራ የቆሙ ሊቃውንትም ‹‹ሐዋርያቲሁ ከበበ እግረ አርዳኢሁ ሐጸበ›› እያሉ ይዘምራሉ፡፡ ይህ ሥርዓት ከተጠናቀቀ በኋላ ሥርዓተ ቅዳሴው ተከናውኖ ቅዱስ ሥጋውን ክቡር ደሙን ምእመናን ይቀበላሉ፡፡

ቅዳሴ

የጸሎተ ሐሙስ ቅዳሴ የሚከናወነው በተመጠነ ድምፅ ሲኾን፣ እንደ ደወል (ቃጭል) የምንጠቀመውም ጸናጽልን ነው፡፡ ልኡካኑ የድምፅ ማጉያ ሳይጠቀሙ በለኆሣሥ (በቀስታ) ይቀድሳሉ፡፡ ምክንያቱም ይሁዳ በምሥጢር ጌታችንን ማስያዙን ለመጠቆም ሲኾን፣ በሌላ በኩል ደግሞ የዘመነ ብሉይ ጸሎት ዋጋው ምድራዊ እንደ ነበር ለማስታወስ ነው፡፡ በመቀጠል ክብር ይእቲ፣ ዕጣነ ሞገር፣ ዝማሬ የተባሉ የድጓ ክፍሎች ተዘምረው አገልግሎቱ ይጠናቀቃል፡፡ ሕዝቡም ያለ ኑዛዜና ቡራኬ ይሰናበታሉ፡፡

ጉልባን

ጉልባን ከባቄላ ክክ፣ ከስንዴ ወይንም ከተፈተገ ገብስ ጋር አንድ ላይ ተቀቅሎ የሚዘጋጅና የጸሎተ ሐሙስ ዕለት የሚበላ ንፍሮ ነው፡፡ በጸሎተ ሐሙስ በቤት ውስጥ ከሚፈጸሙ ተግባራት አንዱ ጉልባን ማዘጋጀት ነው፡፡ ጉልባን እስራኤላውያን ከግብጽ ባርነት ሲወጡ በችኮላ መጓዛቸውን የምናስታውስበት ከእስራኤላውያን የመጣ ትውፊታዊ ሥርዓት ነው፡፡ በአገራችን ኢትዮጵያ አብዛኞቹ የትውፊት ክንዋኔዎች የብሉይ ኪዳን መነሻ ስላላቸው ይህ ሥርዓት ዛሬም በኢትዮጵያውያን ምእመናን ዘንድ ይከበራል፡፡

ጉልባን እስራኤላውያን ከባርነት በወጡ ጊዜ አቡክተው፣ ጋግረው መብላት አለመቻላቸውን ያስታውሰናል፡፡ በወቅቱ ያልቦካውን ሊጥ እየጋገሩ ቂጣ መመገብ፤ ንፍሮ ቀቅለው ስንቅ መያዝ የመንገድ ተግባራቸው ነበርና፡፡ ይህን ታሪክ ለማሰብም በሰሙነ ሕማማት በተለይም በጸሎተ ሐሙስ ቂጣና ጉልባን ይዘጋጃል፡፡ በጸሎተ ሐሙስ የሚዘጋጀው ጉልባንና ቂጣ ጨው በዛ ተደርጎ ይጨመርበታል፡፡ ይኸውም ጨው ውኃ እንደሚያስጠማ ዅሉ፣ ጌታችንም በመከራው ወቅት ውኃ መጠማቱን ለማስታወስ ነው፡፡

ወስብሐት ለእግዚአብሔር፡፡

ምንጭ

___

Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , | Leave a Comment »

እርኩስ አረብ ኢትዮጵያውያን ሕፃናትን በእናት አገራቸው ሲደፍራቸው ማዬት በጣም ያስቆጣል

Posted by addisethiopia on April 5, 2017

የብርሃነ ጥምቀት ዕለት፡ ጥር ፲፩ ፡ ፪ሺ፱ ዓ..

በአዲስ አበባ ቦሌ ቅድስት መድኃኔ ዓለም ቤተክርስቲያን ከአክስቴ ልጅ ጋር ደስ በሚል ሁኔታ ቅዱስ ታቦቱን በክብር ካስገባን በኋላ፡ ከቤተክርስቲያኗ ፊትለፊት ወደሚገኘው የካልዲስ ቡናቤት አምርተን በረንዳው ላይ ቁጭ አለን። ቡናቤቷ በቱርኮች እና አረቦች ተሞልታለች። ወቸውጉድ! እያልን ቡና እና አምቦ ውሃ ካዘዝን በኋላ፡ ህፃናት የኔቢጤዎች በረንዳው ላይ ጠልጠል እያሉ መለመን ጀመሩ። እኛም ትንሽ ገንዘብ አካፈልናቸው። ልጆቹም ቀጥለው ባጠገባችን ወደነበሩ አረቦች አመሩ፤ እነዚህ በጣም እየጮሁ ሲነጋገሩ የነበሩት አራት አረቦች ልጆቹን ሲያዩ ጩኽታቸውና ቁጣቸው ዓየለ፤ ከዚያም በጣም እያመናጨኩ አባረሯቸው። እኛም በእንግሊዝኛው ቆጣ ብለን፡ “ለምንድን ነው ይህን ያህል የምትጮኹባቸው፡ መስጠት ካልፈለጋቸሁ የለንም! አንስጠም! በሉ” አልናቸውና፡ ሂሳባችንን ከፍለን እያጉረመረምን ወደ ኤድና ሞል አካባቢ አመራን። እዚያም፡ ሌሎች የኔ ቢጤ ህፃናት ያው የኛን ከተቀበሉ በኋላ አልፈውን የሚሄዱትን ሁለት አረቦች እየተከተሉ፤ “አባብዬ! አባብዬ” እያሉ ሲለምኗቸው፤ አንድኛው “የላላ፤ ታዓዓል!„ እያለ በመጮህ፡ ልክ ቪዲዮው መግቢያ ላይ የምትታየውን ቆንጅዬ የመሰለች ልጃችንን ወርውሮ ጣላት (በነርሱ የተለመደ ነው፤ ልክ ቪድዮው መጨረሻ ላይ እንደሚታየው)። እኛም አላስቻለንም፡ “እንዴ!„ ብለን ወደ አረቦች መሮጥ ስንጀምር አፈትልከው አመለጡን። እኔ እምባ በእንባ ሆኑኩ፡ አይይይ! አልኩ፤ በጣም አዘንኩ። እስካሁን አረብ በገጠመኝ ቁጥር ያ ስዕል ነው ብልጭ የሚልብኝ። በኢትዮጵያ ቆይታዬ እጅግ በጣም ካሳዘኑኝ ሁኔታዎች አንዱ እና ፈጽሞ ልረሳው የማልችለው ክስተት ነው። ማነው ይህን ያህል ያጠገባቸው?! በአገራቸው ያው እንደ ውሻ ያሳድዱናል፤ በአገራችን ግን በጭራሽ ይህን ዓይነት ድርጊት በእነዚህ እርጉሞች ሊከስትብን አይገባም። ያውም በብርሃነ ጥምቀቱ?! ማነው ለዚህ አቻ ለሌለው ድፍረት እንዲበቁና እንዲደፍሩን የሚረዳቸው??!!

መድኃኔ ዓለም ኢየሱስ ክርስቶስ ፈጥኖ ይምጣና ይፍረድባቸው!!!

ተዓምረኛዋ ደብረ ቀራንዮ መድኃኒዓለም | አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ቀለም የያዘ ብርሃን መልአክ ዙሪያ ያፈነጥቃል

በጣም ድንቅ ነው! ቪዲዮው ወደ መጨረሻ ላይ ይታያል። በያሬዳዊ ወረብ ወቅት ክቡሩ ባለሶስት ቀለማችን በበሩ መሃከል ያፈነጥቃል፤ በመልአክ የተመሰለውን ኃይለኛ ነጭ ብርሃንም ክንፎች ሠርቶለታል (መስቀል)፤ በ “ቀራንዮ”። ልብ ካልን፡ ቀለማቱ ከበስተ ውስጥ ነው የሚታዩት፡ ቤተመቅደሱ ውስጥም ቀለማቱም በሩ ላይ ወይም ሌላ ቦታ ላይ አልተቀቡም፤ በወቅቱም በዓይኔ በፍጹም አይታየኝም ነበር፡ አሁን ነው ቪዲዮውን ሳዘጋጅ ልብ ያልኩት። እስከመጨረሻው መቅረጽ ሳልችል መቅረቴ ቢያሳዝነኝም፡ (ምክኒያቱም ዲያብሎስ መጥቶ አቋረጠኝ፡ ከለከለኝ)፡ ሆኖም ግን፡ ይህን አስገራሚ ክስተት ለመታዘብ በመብቃቴ መድኃኒዓለም ይመስገን!

___

Posted in Ethiopia, Faith, Infos | Tagged: , , , , , | Leave a Comment »

የኤች አይቪ ቫይረስ በደሙ ውስጥ ያለበት አንድ ኢትዮጵያዊ ስደተኛ ሁለት ስዊድናዊያን ልጃገረድ ሴቶችን በመድፈሩ ተከሰሰ

Posted by addisethiopia on March 29, 2017

ዝርዝሩን እዚህ ይመልከቱ

አቤት መደንዘዝ! አቤት አረመኔነት!! አቤት ጭካኔ!!!

ይህን አረመኔነት፣ ይህን ጭካኔ ከየት ተምሮት ይሆን? የአረቡን ዲያብሎሳዊ ስነምግባር የወሰደውን ባለጌ ናሆምን እናፍርበታለን፤ ስለ ጽዮን ዝም የማይለው ናሆም ወንድማችን ደግሞ፣ ምስጋና ይድረሰውና፤ ይህን ድንቅ ትምህርት አቅርቦልናል፦

__

Posted in Curiosity, Ethiopia, Health, Infos | Tagged: , , , , | Leave a Comment »

ከሲኦል ጋር ለመተዋወቅ ወደ አረብ አገር መሄድ አያስፈልግም

Posted by addisethiopia on March 11, 2017

ይገርማል፡ ወደ ራጉኤል ቤተክርስቲያን ለመጀመሪያ ጊዜ ነበር የሄድኩት፤

ይህች ቆንጆ ቤተክርስቲያን በሲኦል ተከብባለች። በአስቀያሚ የገባያ ቦታዎች፣ በመስጊዶች እና በቆሻሻዎች ነው የተከበበችው። የአካባቢው ሰው ቀዥቃዣነትና ስነምግባር አልባነት፣ የመስጊዱ ጩኽት፣ ጥቁር ድንኳን ለብሰው የሚሄዱት ሴቶች ብዛት፣ አቧራው፣ የቆሻሻው ሽታ፡ ከአካባቢው ቶሎ ውጡ ውጡ የሚያሰኝ ነው። ሁሉም ነገር ጭልምልም ያለ ነው!

እያጋነንኩ አይደልም፤ ልክ ራጉኤል ቤተክርስቲያን ቅጥር ግቢ ውስጥ ስገባ ያ ሁሉ መጥፎ ነገር እልም ብሎ ጠፋ፤ ብርሃኑ ፈካ ብሎ ይታያል፡ የሚገርም ነው! ተዓምር ነው! በአንድ ሰዓት ውስጥ የሲዖልን እና የመንግሥተ ሰማያትን የተለያዩ ተፈጥሮዎች ለመገንዘብ በቃሁ። ይህን ላሳዩኝ ቅዱሳን ምስጋና ይገባቸዋል።


በጅማ ዩኒቨርስቲ: በማዕተብ ጉዳይ ከመምህሩ ጋራ የተጋጨው ተማሪ ራሱን አጠፋ፤ መምህሩ ታሰረ፤ “ቤተ ክርስቲያን፥ የእምነት ነጻነታችንን ታስከብርልን”/ተማሪዎቹ/


 • መምህሩ፣ በተመሳሳይ ጥፋት በተወሰደበት የዲስፕሊን ርምጃ ተባርሮ የተመለሰ ነው፤
 • ኦርቶዶክሳውያን ተማሪዎች፣ የእምነት ነጻነታቸው እንዲከበር አቤቱታ አቅርበዋል፤
 • በነጻነት መማር አልቻልንም፤ የእምነት ነጻነታችን ይከበር፤ የሕግ ከለላ ይሰጠን!”

በጅማ ዩኒቨርስቲ መምህራን ኮሌጅ፣ የኹለተኛ ዓመት የእንግሊዝኛ ቋንቋ ተማሪ የነበረው ወጣት፣ በማዕተብ ጉዳይ ከመምህሩ ጋራ ተጋጭቶ የትምህርቱ ውጤት በመበላሸቱ ራሱን አጠፋ፡፡

ተስፋዬ ገመዳ የተባለው ተማሪው፣ የሥነ ልቡና ሳይንስ መምህሩ፣ በቡድን የሰጧቸውን የቤት ሥራ አዘጋጅተው በመድረክ ሊያቀርብ ሲል፣ መምህሩ፥በአንገትኽ ላይ ያደረግኽውን ማዕተብ አውልቅ ወይም ሸፍነው፤” ሲሉት ተማሪው፥ ይኼ የእምነቴ መግለጫ ነው፤ ያዘዙኝን ማድረግ አልችልም፤” የሚል ምላሽ እንደሰጣቸውና መምህሩም፥ ያዘዝኩኽን ማድረግ ካልቻልክ የሠራኸውንም ማቅረብ አትችልም፤” ስላሉት ከመድረኩ ወርዶ በእጁ የያዘውን የቡድን ሥራ ሪፖርት በብስጭት ቀድዶ መቀመጡን የዓይን እማኞች አስረድተዋል፡፡

በወቅቱ ተማሪው፣ ክፍለ ጊዜውን አቋርጦ መውጣቱንና ተመልሶ ሊገባ ሲል፣ መምህሩ፣ አትገባም ብለው እንደከለከሉት፤ ተማሪውም፣ ስሜታዊ ኾኖ ከመምህሩ ጋራ ለጠብ መጋበዙንና ሌሎች ተማሪዎች በመሀል ገብተው እንደገላገሏቸው፤ የኮሌጁ አካዳሚክ ዲን፣ በቦታው ተገኝተው ስለተጠፈረው ችግር ተማሪዎችን በመጠየቅ ጠቡን ማረጋጋታቸውን፣ እማኞቹ ለአዲስ አድማስ ተናግረዋል፡፡

በሌላ ቀን፣ ተማሪ ተስፋዬ እንደተለመደው፣ የሥነ ልቡና ትምህርቱን ለመከታተል ወደ ክፍል ሲገባ መምህሩ ከክፍል እንዳስወጡት፣ ለአካዳሚክ ዲኑ አቤቱታ ማቅረቡንና፣ የትምህርቱ የመጨረሻ ክፍለ ጊዜ ስለኾነ በቃ ተወው፤ በውጤትኽ ላይ ምንም ለውጥ አያመጣም፤” ብለው አረጋግተው እንደሸኙት የተማሪው የቅርብ ጓደኞች ገልጸዋል፡፡

በኋላም ለፈተናው የተቀመጠ ሲኾን፣ የተለጠፈው የፈተና ውጤት ግን No Grade’’/ምንም ውጤት የለም/ የሚል ስለነበረ፣ ወዲያው በንዴት ወደተከራየበት ቤት በማምራት በግቢው በሚገኝ የማንጎ ዛፍ ላይ ራሱን ሰቅሎ መግደሉን ጓደኞቹ አስረድተዋል፡፡

ፖሊስና የአካባቢው ኅብረተሰብ ከቦታው ደርሰው ከተሰቀለበት ሲያወርዱት፣ ነፍሱ ከሥጋው እንዳልተለየችና ወደ ሆስፒታል ይዘውት በማምራት ላይ ሳሉ ሕይወቱ ማለፉን ምንጮች አስታውቀዋል፡፡ አስከሬኑ፣ ማክሰኞ፣ የካቲት 28 ቀን 2009 .. መሸኘቱንና የቀብር ሥነ ሥርዓቱም፣ በትውልድ ስፍራው በሰሜን ምዕራብ ሸዋ ዞን፣ ደገሞ ወረዳ ከትላንት በስቲያ መፈጸሙን ለማወቅ ተችሏል፡፡

አስከሬኑን ለቤተ ሰዎቹ ያደረሱት መርማሪ ፖሊስ ዮሐንስ መገርሳ፣ ተማሪው ከመምህሩ ጋራ በመጣላቱ ራሱን እንዳጠፋ ጥርጣሬ መኖሩንና፣ የሆስፒታል የምርመራ ውጤት በመጠበቅ ላይ መኾኑን፤ ጉዳዩም ገና በመጣራት ላይ እንዳለ ለአዲስ አድማስ ገልጸዋል፡፡

[ተማሪው የደረሰበትን በደል ቀደም ብሎ ለጅማ ሀገረ ስብከትም በማስታወቅ እገዛ ጠይቆ እንደነበር ያወሱ ምንጮች፣ ጽ/ቤቱ ከትላንት በስቲያ ኃሙስ ጀምሮ ጉዳዩን እየተከታተለው መኾኑን ተናግረዋል፡፡

የዩኒቨርስቲው የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነት ተከታዮችም፣ የሃይማኖት ነጻነታቸው እንዲከበር የሚጠይቅ አቤቱታ ተፈራርመው፣ ለሀገረ ስብከቱ ጽ/ቤት አስገብተዋል፤ ለሚመለከታቸው የኮሌጁና የመንግሥት ሓላፊዎችም በየደረጃው እንደሚያደርሱ ተነግሯል፡፡

በአቤቱታቸው፥ ከዚኽም በፊት፣ በአጽዋማት ወቅት ሥርዓተ እምነታቸውን በአግባቡ እንዳይፈጽሙ በሴኩላሪዝምና በአካዳሚክ ነጻነት ስም የተደረገባቸውን አድልዎ በማካተትበነጻነት መማር አልቻልንም፤ ቤተ ክርስቲያን የእምነት ነጻነታችንን ታስከብርልን፤ የሕግ ከለላ ይሰጠን፤ ሲሉ ጠይቀዋል፡፡ ለሀገረ ስብከቱ የደረሰው አቤቱታ፣ በሊቀ ጳጳሱ ብፁዕ አቡነ እስጢፋኖስ አማካይነት፣ ከዞን እስከ ፌዴራል መንግሥት አካላት ድረስ እንደሚቀርብ ተገልጿል፤ የሟች ቤተሰብም በሕግ እንደሚጠይቅ ተጠቁሟል፡፡]

 • አካዳሚክ ዲኑ ግጭቱን ሲያጣሩ፣ መምህሩ፥ ሊደበድበኝ ነው፤ ብሎ ተማሪውን ከሦት ነበር፤ የክፍል ጓደኞቹን ሲጠይቁ ግን፥ ማዕተብኽን ካልበጠስክ፤ ብሎት በዚያ የተነሣ እንደኾነ ተረድተዋል፤ ጥፋቱም የመምህሩ እንደኾነ ነግረውና ይቅርታ ጠይቀው ልጁን አረጋግተውት ነበር፤ ከዚያ በኋላ በነበረ አንድ ክፍለ ጊዜ፣ ውጣ ብሎ እንዳይገባ ሲከለክለውም ለአካዳሚክ ዲኑ አስታውቋል፤ እርሳቸውም፣ ለኮርሱ፥ የመጨረሻ ክፍለ ጊዜ ነው፤ በሚል አባብለውታል፤ ፈተናውን ተፈትኖ ውጤቱን ሲያበላሽበትም ወደ አካዳሚክ ዲኑ ሊያመለክት ሔዶ ነበር፤ አላገኛቸውምና በየአንጻሩ፣ ለመምህሩ በሚታየው የአስተዳደሩ ከልክ ያለፈ
  መለሳለስ ምክንያት ነው የተበሳጨው፤
 • መምህሩ፣ ከዚኽም በፊት በተመሳሳይ የዲስፕሊን ችግር ከማስተማር ሥራው ተባርሮ የነበረ ሲኾን፣ በአንዳንድ ሓላፊዎች ልመና ከተመለሰ ገና አንድ ዓመቱ ነው፤ የአእምሮም እክል እንዳለበት ነው የሚነገረው፤ እብሪትም ይታይበታል፤ የዲኑ ቢሮ ገብቶ ወንበራቸው ላይ ተቀምጦ፣ ጸሐፊዋን፥ ከዚኽ በኋላ ማንም ሰው እንዳይገባ፤ ዲኑ እኔ ነኝ” የሚልበት ጊዜ አለ፤
 • ተማሪው ራሱን ባጠፋበት ቀን ምሽት፣ መምህሩ በቁጥጥር ሥር ውሎ በእስር ላይ ነው ያለው፤ አስከሬኑ በተሸኘበት ዕለትም፣ በዩኒቨርስቲው በር ላይ ተማሪዎች ቁጣቸውን ሲገልጹ የነበረ ሲኾን፣ ፖሊስ በአስለቃሽ ጢስ በትኗቸዋል፤ ማምሻውንም ከዐሥር የማያንሱቱ ከየዶርሚተራቸው እየተያዙ ተወስደዋል፤
 • ተማሪው ከመሞቱ በፊት ለጓደኞቹ አራት ጊዜ በተከታታይ ደውሎ ነበር፤ ወደሚግባባው ጎረቤት ባለሱቅም ሔዶ ነበር፤ አላገኛቸውም፤ ብሶቱን የሚተነፍስበትና የሚያናግረው ሰው እየፈለገ ነበር፤ በርግጥ፣ የንስሐ አባቱን በዚያኑ ቀን ጠዋት አግኝቷቸው፣ ከመምህሩ ጋራ መጋጨቱን ነግሯቸው፣ እንደ መንፈሳዊ አባት አጽናንተውት ነው ወደ ቅዳሴ የገቡት፤ ከጸሎተ ቅዳሴው ሲወጡ የተረዱት ግን አሳዛኝ ኅልፈቱን ነበር፡፡
 • በጅማ ዩኒቨርስቲ መምህራን ኮሌጅ፣ በእንግሊዝኛ ዲፓርትመንት፣ የኹለተኛ ዓመት ተማሪ የነበረው ተስፋዬ ገመዳ(ወስመ ጥምቀቱ ወልደ ገብርኤል)3.6 በላይ ድምር አጠቃላይ ውጤት ያለው ጎበዝ ኦርቶዶክሳዊ ወጣት ነበር፡፡

ምንጭ

__

Posted in Ethiopia, Faith, Life | Tagged: , , , , , , , , | Leave a Comment »

የክርስቶስን “ደብረዘይት” “ቢሸፍቱ” በሚል መጠሪያ የለወጡት ጣዖት-አምላኪዎች ለዲያብሎስ አምላካቸው መስዋዕት አበርክተዋል

Posted by addisethiopia on October 3, 2016

ደብረ ዘይት = ደብረ ዘይት በሚል ርዕስ ከሦስት ዓመት በፊት ያቀረብኩት ይህ ጽሑፍ፡ በቀድሞዋ ደብረዘይት በሰንበት እለት ለተከሰተው አሳዛኝ እልቂት ትንቢታዊነት ነበረው ማለት ነው

Re-posted from April 6, 2013

debrezeytከሦስት ዓመታት በፊት ከአራት ሰዎች ጋር ሆኜ ከ አዲስ አበባ ወደ ደብረ ዘይት ከተማ በመጓዝ ላይ ነበርኩ። ቃሊቲን አለፍ እንዳልን፡ መኪናዋን ቤንዚንና ዘይት ሞላናት። እግረ መንገዳችንንም ብርቱካን እንዲሁም አብረውን ለነበሩት አክስታችን ቅቤ ገዝተን ጉዟችንን ቀጠልን። በመኻልም እኔና አክስታችን ብርቱካን እየላጠን ለሾፌሩና ለወንድማችን ማካፈል ጀመርን። አክስታችን ለሾፌሩ፡ ይህችን ብርቱካን እንካ ላጉርስህ” ሲሉ፡ ሾፌራችንም ” ኧረኧረየርስዎ እጅ ቅቤ ነክቷል፡ ባይሆን የእርሱ ቤንዚንና ዘይት ቢነካውም ቅቤ ከነካው የቤንዚኑ ይሻለኛል፡ እርሱ ያጕርሰኝ!” ብሎ፡ አሳቀን፤ አስገረመን።

መጠሪያ ስሞቻችን፣ የክርስትና ስሞቻችን ወይም ክርስቲያናዊ የሆኑ የቦታ ስሞችን የሚሰጠው መንፈስ ቅዱስ ነው። የእግዚአብሔር አምላክን ገናናነት ለማሳወቅ፡ ለእርሱ ክብር ለመስጠት የምንሰይማቸው ቦታዎች ወይም ከተሞች በርሱ ዘንድ ከፍተኛ ትርጕም አላቸው፤ ለኛም ሰላምን፣ ጽድቅንና በረከትን ያመጡልናል። ሶማሊያዎች እስከ ናዝሬት ከተማ ድረስ ያለው ግዛት የኛ ነው በማለት በህልማቸው የነደፉትን ካርታ ጥገኝነቱን ለሰጣቸው እንግዳ ተቀባይ የአዲስ አበባ ነዋሪ በድፍረት/በንቀት ያሳያሉ። ይህን በቅርብ ሆኜ ለመታዘብ በቅቻለሁ። ለመሆኑ በፊት ጂጂጋ ደርሰው ናዝሬት” ዘው ለማለት ያቃታቸው ለምን ይመስለናል? “ናዝሬት” “እየሩሳሌም፡ የእነዚህ ቦታዎች መጠሪያ ሁልጊዜ የጦርነት ወኔያቸውን ይቀሰቅሰዋል፡ ለምንመልሱን ሁላችንም እናውቀዋለን።

ታዲያ ሁለት ሺህ ዓመታት በሞሉት የክርስትና ታሪካችን፡ ብዛት ያላቸው ምሳሌዎችን ለማየት እየበቃን፡ እንደ ደብረ ዘይት” የመሳሰሉትን የቦታ መጠሪያዎች በዘፈቃድ ለመለወጥ የሚሹ ግለሰቦች በምን ተዓምር አሁን ሊመጡብን ቻሉ? ከተራራው በረሃውን፥ ከቅቤው ቤንዚኑን፥ ከደብረ ዘይት የመኪና ዘይትን የሚመርጥ ትውልድ፡ የመቅሰፍት ምንጭ አይሆንብንምንመቼም ለክርስቶስ ጥላቻ ያላቸው፣ ጸረክርስቶስ የሉሲፈር ፈቃደኛ ወኪሎች ካልሆኑ በቀር እዚህ ድረስ ሊያደርሳቸው የሚችል ሌላ ነገር ሊኖር ይችላልንአይመስለኝምይህ እንደ ቀላል ነገር ተደርጎ መታየት ያለበት ጉዳይ አይደለም፡ ምክኒያቱም በግለሰቦቹ ላይ ሊመጣባቸው የሚችለው ፍርድ ልክ መንፈስ ቅዱስን የሚያስቀይሙት ግለሰቦች ከሚመጣባቸው ኃይለኛ ፍርድ የሚለይ አይሆንምና፤ የመንፈስ ቅዱስን ክብር ደፍረዋልና!

ደብረ ዘይት

ደብረ ዘይት በግእዝ ልሣን ደብረዘይት ማለት የወይራ ተራራ ማለት ነው። ቦታው ከኢየሩሳሌም በስተምስራቅ የሚገኝ የወይራ ዛፍ የበዛበት ተራራ ሲሆን ስሙም ከወይራ ዛፉ:-ደብረ ዘይት (የወይራ ዛፍ ተራራበመሰኘት ተገኝቷል። በቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ደብረ ዘይት በዓል ሆኖ የሚከበርበት ምክንያት ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በደብረዘይት ተራራ ላይ ሳለ ለቅዱሳን ደቀመዛሙርቱ ስለ ዓለም ፍጻሜ እና ስለ ዳግም ምጽአቱ ስላስተማራቸዉ በጌታችን ትምህርት መሰረት ነገረ ምጽአቱን (የመምጣቱን ነገርእንድናስታዉስ ወይም እያሰብን እንድንዘጋጅ ለማድረግ ነዉ።

በዚያ ልማድ መሠረት ጌታችን ዓለምን ለማሳለፍ ደግሞ የሚመጣበትን ምልክትና ጠቋሚ ነገር ምን ምን እንደሆነ፣ እርሱ ከመምጣቱ በፊት በዓለም ላይ ምን፥ ምን እንደሚደረግና ምን እንደሚታይ ለደቀመዛሙርቱ የነገራቸው በደብረ ዘይት ተራራ ላይ ተቀምጦ ነው። (ማቴ. 241-51) ስለ ዓለም ሁሉ ቤዛ ለመሆን በሚሰቀልበት ቀን ዋዜማ ማለት በትልቁ ሐሙስ (ጸሎተ ሐሙስበለበሰው ሥጋ የጸለየው ከደብረ ዘይት ጋር ተያይዞ በሚገኘው ቦታ በጌተሴማኒ ነበር። (ማቴ. 2636) በኃላ ከሙታን ተለይቶ ከተነሣ በኋላም ለደቀመዛሙርቱ እንዲነግሩ ሲልካቸው፥ “ሂዱና ወደ ገሊላ ይቀድማችኋል፥ በዚያም ታዩኛላችሁ ብላችሁ ንገሩአቸው፥” ብሎ የላካቸው በደብረ ዘይት ገሊላ ተብላ ትጠራ ወደ ነበረችው ቦታ ነው። (ማቴ. 289) ገሊላውያን ወደ ኤየሩሳሌም ሲመጡ በደብረ ዘይት ያርፍ ነበርና እነሱ ሲያርፉባት የነበረችው ቦታ ገሊላ እየተባለች ትጠራ ነበር። መድኃኔዓለም ክርስቶስ የድኅነት ሥራ ፈጽሞ ወደ ሰማይ ያረገው ከዚህ ተራራ ተነሥቶ ነው። (ሐዋ. 112) ቀደም ብሎም የሆሳእናው የመድኃኔዓለም አስደናቂ ጉዞ የተጀመረው ከደብረ ዘይት ሥር ነበር። (ማቴ. 211-16)

ወስብሓት ለእግዚአብሔር

__

Posted in Conspiracies, Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , | Leave a Comment »

እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ በሰላም አደረሰን

Posted by addisethiopia on September 26, 2016

meskeldemera2

ክብረ መስቀል በኢትዮጵያ

መስቀል ስንል ሦስት መሠረታዊ ቁም ነገሮችን መጥቀስ ይቻላል፤ የመጀመሪያው ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የሰውን ልጅ ከሞተ ነፍስ ለማዳን ሲል የተቀበለው መከራና የከፈለው መሥዋዕትነት መስቀል ይባላል፡፡ ሁለተኛው በክርስእንትና ውስጥ የሚያጋጥም ልዩ ልዩ ዓይነት መከራም መስቀል ነው፡፡ ጌታችን ‹‹እኔን መከተል የሚወድ ቢኖር ራሱን ይካድ፤ መስቀሉንም ተሸክሞ ይከተለኝ›› /ማቴ.፲፮፥፳፬/ በማለት መናገሩም በክርስትና ሕይወት ውስጥ የሚደርሰውን ይህንኑ መከራ መታገሥ ተገቢ መኾኑን ሲያመለክተን ነው፡፡ ሦስተኛው ደግሞ ጌታችን የተሰቀለበት ዕፀ መስቀል ነው፡፡ በሦስቱም ቁም ነገሮች ነገረ መስቀል (የመስቀሉ ነገር) ከክርስትና ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት አለው፡፡ ስለ ክርስትና ሕይወት ሲነሣ ነገረ መስቀልም አብሮ ይታወሳል፡፡ ስለ ክርስትና ሲነገር ክርስቶስ የተቀበለው መከራ፣ የተሰቃየበትና ነፍሱን በፈቃዱ አሳልፎ የሰጠበት ዕፀ መስቀል፣ በክርስትና ሕይወት ውስጥ የሚከሠት ፈተና አብረው የሚነሡ ጉዳዮች ናቸው፡፡

ስለ መስቀል ሲነገር ክርስቶስ ሰውን ለማዳን ሲል በሥጋው የተቀበለው ስቃይ፤ ሰማዕታት በሃይማኖታቸው ምክንያት የሚደርስባቸው ስደት፣ መከራና ሞት፤ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን በየዘመኑ በአረማውያንም በውስጥ ጠላቶችም የሚያጋጥማት የዘረፋና የቃጠሎ፣ እንደዚሁም የሰላም እጦትና የመልካም አስተዳደር እጥረት፤ በተጨማሪም በክርስትና ሕይወት ውስጥ የሚከሠቱ የኑሮ ውጣ ውረዶች መስቀልና ክርስትና የማይነጣጠሉ የአንድ ሳንቲም ሁለት ገጽታዎች ለመኾናቸው ማስረጃዎች ናቸው፡፡ ከዚሁ ኹሉ ጋርም መስቀል ሲባል ክርስቶስ መከራ የተቀበለበት፣ ቅድስት ነፍሱን ከቅዱስ ሥጋው የለየበት፣ ድንቅ ተአምራትን ያደረገበት፣ ከኹሉም በላይ ለአዳምና ለልጆቹ ነጻነትን ያወጀበት ዕፀ መስቀልም አንዱ የክርስትናችን አካል ነው፡፡

ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን በጉልላቷና በሌሎችም ንዋያተ ቅድሳቷ መስቀልን እንደ ምልክት ትጠቀመዋለች፡፡ መሠረቷ፣ የልጆቿ መድኀኒት ክርስቶስ በመስቀል ላይ የከፈለው ዋጋ ነውና ሰንደቅ ዓላማዋ መስቀል ነው፡፡ አባቶች ካህናት ጸሎት ሲያደርጉ ‹‹ከመስቀሉ ዓላማ፣ ከወንጌሉ ከተማ አያውጣን›› እያሉ የሚመርቁትም ስለዚህ ነው፡፡ በእጃቸው ይዘውት የሚንቀሳቀሱት፣ እኛንም የሚባርኩትም በመስቀል ነው፡፡ መስቀል የጠላት ሰይጣን ተንኮል የከሸፈበት፣ የክርስቶስ ቤዛነት የተረጋገጠበት የድኅነት ኃይል ነውና፡፡ በየገዳማቱና በየአብነት ት/ቤቱ፤ እንደዚሁም በክርስቲያኖች መኖሪያ ቤቶች ውስጥ በሚከናወኑ ተግባራት መስቀል ሰፊ ድርሻ አለው፡፡ በቅዳሴ ጊዜ፣ በጠበል ቦታ፣ በጸሎት ጊዜያት፣ ወዘተ ቡራኬ የሚፈጸመው በመስቀል በማማተብ ነው፡፡ የመስቀሉን ምልክት ባዩ ጊዜ አጋንንት ይንቀጠቀጣሉ፤ ካደሩበት ሰው ላይም በፍጥነት ይወጣሉ፡፡ ምእመናን በመስቀሉ ስንዳሰስ ከልዩ ልዩ ደዌ እንፈወሳለን፡፡

ወደ አገራችን ክርስቲያዊ ባህል ስንመለስ በኢትዮጵያ የመድኀኒታችን የክርስቶስ መስቀል በብዙ ተግባራት ላይ በምልክትነት ጥቅም ላይ ሲውል ይታያል፡፡ ለምሳሌ በቡልኮ፣ ጋቢ፣ ነጠላ፣ ቀሚስ ወዘተ የመሳሰሉ የሸማ ልብሶች፤ እንደዚሁም በጆሮ፣ በአንገት፣ በእጅና ሌሎችም ጌጣጌጦች ላይ የመስቀል ምልክት አለ፡፡ ክርስቲያን ልጃገረዶች (በተለይ በሰሜኑ የአገራችን ክፍል) በግንባራቸው፣ በጉንጫቸው፣ በአንገታቸው፣ በደረታቸውና በእጃቸው ላይ በመስቀል ቅርፅ እየተነቀሱ ያጌጡበታል፡፡ ክርስቲያኖች ከዚህ ዓለም በሞት ስንለይም በመቃብር ሣጥናችን ወይም በሐውልቶቻችን ላይ የመስቀል ምልክት ይቀመጣል፡፡ በቤት ውስጥም ስንተኛና ከእንቅልፋችን ስንነቃ ፊታችንንና መላ ሰውነታችንን በትእምርተ መስቀል እናማትባለን፤ አባቶችና እናቶችም ውሃ ሲቀዱ፣ ሊጥ ሲያቦኩ፣ እንጀራ ሲጋግሩ፣ ምግብ ሲቈርሱ፣ ወዘተ በመስቀል አማትበው ነው፡፡ በአጠቃላይ መስቀል ብዙ ነገር ነው፤ መስቀል በክርስትና ሕይወት ውስጥ በሚደረጉ ተግባራት ኹሉ ያለው ድርሻ ጕልህ ነው፡፡ /ለተጨማሪ መረጃ ግሸን ደብረ ከርቤ የቃል ኪዳን አምባ፣ መስከረም ፲፱፻፺፮ ዓ.ም፤ ገጽ ፺፮፻፪ ይመልከቱ/፡፡

በክርስቶስ ደም የተቀደሰው ይህ ክቡር መስቀል ለበርካታ ዓመታት በአይሁድ ምቀኝነት በጎልጎታ ተቀብሮ ከኖረ በኋላ በንግሥት ዕሌኒና በልጇ ቈስጠንጢኖስ ጥረት ከተቀበረበት ወጥቶ ከፀሐይ ብርሃን በላይ አብርቷል፤ ሙት በማስነሣት፣ ሕሙማንን በመፈወስ ብዙ ተአምራትን አሳይቷል፡፡ በመላው ዓለም በሚገኙ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አብያተ ክርስቲያናት ደመራ ተደምሮ በዓሉ የሚከበረውም ንግሥት ዕሌኒ መስቀሉ የተቀበረበትን ቦታ ለማግኘት ከእግዚአብሔር መልአክ በተሰጣት አቅጣጫ መሠረት ያነደደችውን ዕጣንና የመስቀሉን መገኛ የጠቆማትን ጢስ ለማስታዎስ ነው፡፡ እግዚአብሔር የተመሰገነ ይኹን! በንጉሥ ዳዊት በልጃቸው በዘርዐ ያዕቆብ አማካይነት ወደ አገራችን የመጣው የጌታችን መስቀል ቀኝ ክፍል በአገራችን ኢትዮጵያ በደቡብ ወሎ ሀገረ ስብከት በግሸን ደብረ ከርቤ ይገኛል፡፡ ከቅዱስ መስቀሉና ከገዳሙ በረከት ለመሳተፍ ብዙ ምእመናን በየዓመቱ ቦታው ድረስ በመሔድ በዓለ መስቀልን ያከብራሉ፡፡

በዓለ መስቀል በቤተ ክርስቲያን ብቻ ሳይኾን በየመንደሩና በየቤቱም ምእመናን ደመራ በመደመር፣ ጸበል ጸሪቅ በማዘጋጀት በድምቀት ያከብሩታል፡፡ በተለይ በደቡቡ የአገራችን ክፍል በዓለ መስቀል በደማቅ ሥርዓት ይከበራል፡፡ ይህም የቀደሙ አባቶቻችን ስለ በዓለ መስቀል ይሰጡት የነበረው ትምህርት ቁም ነገር ላይ መዋሉን የሚያስረዳ መንፈሳዊ ትውፊት ነው፡፡ የአከባበሩ ባህል ከቦታ ቦታ ይለያይ እንጂ በዓለ መስቀል በየዓመቱ በመስከረም አጋማሽ በመላው ኢትዮጵያ በልዩ ድምቀትና በመንፈሳዊ ሥርዓት ይከበራል፡፡ በአገራችን መስቀልና ክርስትና እንዲህ ሳይነጣጠሉ ተሳስረው ይኖራሉ፡፡ እኛም አባቶቻችን እንዳስተማሩን ይህንን በክርስቶስ ደም የተቀደሰውን መስቀል በዘወትር ጸሎታችን ‹‹… መስቀል ኃይልነ መስቀል ጽንዕነ መስቀል ቤዛነ መስቀል መድኃኒተ ነፍስነ አይሁድ ክህዱ ንሕነሰ አመነ ወእለ አመነ በኃይለ መስቀሉ ድኅነ፤ … መስቀል ኀይላችን፣ ጽንዓችን፣ ቤዛችን፣ የነፍሳችን መዳኛ ነው፡፡ አይሁድ ይክዱታል፤ እኛ ግን እናምንበታለን፡፡ ያመነውም እኛ በመስቀሉ ኀይል እንድናለን፤ ድነናልም›› እያልን ለመስቀሉ ያለንን ክብር እንገልጻለን፤ በክርስቶስ መስቀል ኀይል መዳናችንንም ስንመሰክር እንኖራለን፡፡ ልዑል እግዚአብሔር በመስቀሉ ኃይል ኹላችንንም ከልዩ ልዩ ዓይነት መከራ ይጠብቀን፡፡

ምንጭ

__

Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , | 2 Comments »

የG20 ሉሲፈራውያን በኢትዮጵያውያን ላይ ሲዝቱና ሲያፌዙ

Posted by addisethiopia on August 24, 2016

ለእነርሱ ቴአትር እና ድራማ ነው፤ የ ‘REALITY SHOW’ ነው። አሁን የመጨረሻው ደረጃ ላይ ስለደረሱ አይደብቁልንም፡ በቀልድ፣ በፌዝና ቧልታ መልክ መልዕክቶቻቸውን ያስተላልፋሉ፤ ማዬት የሚችል ይመልከት!

/ ሚንስትር መለስ ዜናዊን ያለ ዓላማና ያለ ምክኒያት አልነበረም ከአንድ የG20G8፡ የ UN, EU ስብሰባ ወደ ሌላው እየጋበዙ ሲያሳትፏቸው የነበረው። ምንም እንኳን ጠ/ሚንስትር መለስ አንዳንድ መከሰት ያልነበረባቸውን ስህተቶች እንዲሠሩ በሉሲፈራውያኑ ቢገደዱም፡ የኢትዮጵያዊ መልካቸውንና ማንነታቸውን በመመርመር ከስህተታቸው ለመመለስ ብሎም ኢትዮጵያዊነታቸውን እንደገና ለመቀበል ሲጀምሩ ነበር በሉሲፈራውያኑ የኢትዮጵያ ጠላቶች የተገደሉት። ከስህተቱ የሚማረውን ኢትዮጵያዊ በጣም ይፈሩታልና! ነፍሳቸውን ይማርላቸው!

የእግዚአብሔር እስትንፋስ፡ የአቡነ ተክለሃይማኖት ፈጣን ሮኬት ጠላቶቻችንን ያቃጥልልን! አሜን!!

__

Posted in Conspiracies, Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , | Leave a Comment »

ታሪካዊው የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር የመጀመሪያዎቹ ቀናት

Posted by addisethiopia on October 19, 2015

 

በባቡሩ መመረቂያ ዕለት ብዙ የሚያዝናኑ እና የሚያስገርሙ ነገሮችን ለመታዘብ በቅቼ ነበር፤ ቪዲዎቹን እንመልከት፤ ድምጾቹንም እናዳምጥ፤ በእውነት ታሪካዊ የሆነ ቆይታ ነበረኝ።

3:00 ደቂቃ ላይ፤ በለው! በለው! በለው! (..) በሳቅ ሞትኩ፤ ግን አያስቅም፤ ወንድማችን ላይ ቶሎ የፈረዱበት መሰለኝ።

ኧረግ! ኧረግ! ኧረግ!” አሉ አቶ ሀይሉ….ደጋግማ እንዲህ አለችኝ፡ “ዋዋዋ! እኔን……” እንዲህ ነው እንዴ የሴት ፖሊሶች የሚጠብሱት?’… እህታችን ፈገግታውን አመጣችብኝ።

በርግጥ ይህን መሰሉ የማመላለሻ ዘይቤ በአዲስ አበባችን መዘርጋቱ ከጥቂት ዓመታት በፊት የማናስበው ነበር፤ በእውነት በጣም የሚደነቅ ነው። በጥራታቸው ላይ አሁን ለመፍረድ ባይቻልም፡ የማይነቃነቁት ባቡሮች ከፍተኛ ምቾት አላቸው። ተጓዡም ቀስ በቀስ እየተለማመዳቸው፡ እንዲሁም ጥንቃቄና ስንሥርዓት በያዘ መልከ እየተንከባከባቸው መሆኑ የሚያበረታታ ነው። ነጭናጫ የመኪና ጩኽትና አደገኛ ጭስ የሚቀነስ ነገር ሁሉ የተባረከ ነው።

አንዳንድ አስፈላጊና መስተካከል ካለባቸው ነገሮች መካከል፤

1. የባቡሩ ነጂዎች ሁሉም ቻይናውያን ናቸው፤ ይህ ቶሎ መለወጥ አለበት። በሰማይ የሚሂዱትን ጠያራዎች ለዘመናት ማብረር የበቁ ኢትዮጵያውያን የምድሩን ባቡር በፍጥነት ለመረከብ ምንም አይሳናቸውምና

2. ቀጣዩን መውረጃ በኮምፒውተር ድምጽ አማካይነት የሚያስተዋውቁት ሴቶች፤ ቪዲዮው ላይ እንደሚሰማው፤ መጀመሪያ በእንግሊዝኛ ከዚያም በአማርኛ ቁንቋዎች ነው። ይህ ስህተት እንዴት ሊከሰት ቻለ? የትም ሌላ አገር የማይታይ የተሳሳተ ተግባር ነው። ኔው ዮርክ ወይም ለንደን አይደለንም ያለነው፤ ተሳፋሪው 99% ኢትዮጵያዊ ሆኖ ሳለ እንግሊዝኛው ለምን እንዲቀድም ተደረገ? ቅደም ተከተሉ ቶሎ መቀየር ይኖርበታል!

__

Posted in Ethiopia, Infos | Tagged: , , , , , | Leave a Comment »

በዓለም ካለው ይልቅ በእናንተ ያለው ትልቅ ነው

Posted by addisethiopia on July 15, 2015

Timket

የታሪክ ሠሪነትሱስ የያዛቸው የሚመስሉት የወቅቱ የአሜሪካ ፕሬዚደንት፡ ባራክ ኦባማ ሥልጣናቸውን ከማስረከባቸው በፊት በመጨረሻ ኢትዮጵያን በመጎብኘት የመጀመሪያው የአሜሪካ ፕሬዚደንት ሊሆኑ እንደሚችሉ ከዚህ በፊት ሳሰላስለው ነበር። ኦባማ ለጉብኝታቸው የሐምሌን ወር ብሎም የልደት ቀኔን መምረጣቸው ግን በጣም ገረመኝ፡ ኦ! ! አሰኘኝ። በዚህ የሐምሌ ወር ታሪካዊ ትርጉም የሚኖራቸው ብዙ ድርጊቶች በዓለማችን እየተከስቱ ነው። አብዛኛዎቹ እነዚህ ድርጊቶች ዓለማችንን ያመሰቃቅሏታል፤ ጥሩው እንደ መጥፎ፥ መጥፎው እንደ ጥሩ የሚቆጠሩበት ወቅት ላይ፤ መጥፎ ልጅ (ኢራን፥ ሳዑዲ) የሚሸለምበት፤ ጨዋ ልጅ (ኢትዮጵያ) የሚቀጣበት ዘምን ላይ ደርሰናል።

ብዙ ሰዎችን ሰሞኑን በማነጋገር ላይ ያለውና በአሜሪካኖቹም ዘንድ፡ Jade Helmየሚል ስያሜ የተሰጠው የአሜሪካ ጦር ሠራዊት ልምምድ በዚህ ወር ይካሄዳል። የህ ልዩ የጦር ሠራዊት እንቅስቃሴ ከ እስላማውያን ሽብር ጥቃት ጋር ሊያያዝ እንደሚችል ታዛቢዎች ይገምታሉ። የተመረጠው ጊዜ የሙስሊሞቹን ረመዳንተከትሎ ነው። በረመዳን ወቅት ብዙ ሽብሮች የሚከሰቱበት ወቅት ስለሆነ አስከፊ የሆነ ጥቃት ሊከሰት ይችላል የሚል ግምት አለ።

ላለፉት ወራት የዲያብሎስ ልጆች በሆኑት አይሲስጭካኔ የተሞላባቸውን ግድያዎች በቴሌቪዥኖቻችን መስኮት ስንመለከት ቆይተናል። እነዚህ ግድያዎች በአብዛኛው ክርስቲያን በሆኑ ወንድሞቻችን ላይ (ሴቶች የሉም!) እየተካሄዱ መሆናቸው በሕዝበ ክርስቲያኑ ላይ እየመጣ ያለው አስከፊ የበደል ዘመን ምን እንደሚመስል ይጠቁመናል።

ኢትዮጵያውያን ስንጠይቀው የነበረው አንድ ነገር ቢኖር፡ ከአሜሪካ ጋር የጠበቀ ግንኙነት በመክፈት በአፍሪካ የመጀመሪያዋ የሆነቸው ኢትዮጵያ ለምንድን ነው ስልጣን ላይ በተቀመጡ የአሜሪካ ፕሬዚደንቶች እስካሁን ድረስ ያልተጎበኘችው? ፕሬዚደንት ኦባማስ እንዴት / ለምን የመጀመሪያው ሊሆኑ ቻሉ? ለምን ይህን ወቅት መረጡ? ምን የተዘጋጀልን ነገር ይኖር ይሆን?

የመጨረሻው የዲያብሎስጦርነት በጋብቻ እና ቤተሰብ ላይ ነው

supreme-court-rainbow-flag

የየል ዩኒቭርሲቲ ቅል እና አጥንቶችምስጢራዊ ቡድን አባል የሆኑትና በኢትዮጵያ ክርስትና ላይ ቀስታቸውን ያነጣጠሩት ጆን ከሪ፡ ለኢትዮጵያ የብሔራዊ ቀን የደስታ መግለጫ ከላኩ በኋላ፡ ከብስክሌት ወድቀው እግራቸው ተሰበረ ተባለ። በክርስትና እና ክርስቲያኖች ላይ በተደጋጋሚ አሽሟጣጭ የሆነ ንግግራቸውን ሲያሰሙ የነበሩት ፕሬዚደንት ኦባማ ደግሞ፡ ባለፈው ወር ላይ ከሙስሊሞች ጋር ረመዳን የገባበትን ቀን አብረው ሲያከብሩ፤ በነጩ ቤታቸው ደግሞ ለሰዶማውያኑ የተለየ አቀባበል አድርገዋቸዋል፡ ሕንፃውንም የማርያምን መቀነትን (ቀስተደመናን) ቅዱስ ክብርን በሚያንቋሽሸውና ባንዲራችንንም በሚያራክሰው ቀለማቸው አሸበረቁበት።

ፕሬዚደንት ኦባማ እ..አ በ2008 .ም በነጩ ቤተመንግሥት ዙፋን ላይ ከተቀመጡትበት ጊዜ ጀምሮ ለሦስት ታላላቅ ወንጀሎች ተጠያቂ ናቸው፦

1. በአሜሪካም ሆነ በአፍሪቃ በጥቁርሕዝቦች ላይ ግድያዎች (በጥይት፥ በማስወረድ) መጨመራቸው

2. በመላው ዓለም ታይቶ የማይታወቅ ጭፍጨፋ ክርስቲያን በሆኑ ሕዝቦች ላይ መካሄዱ

3. የሰዶማውያን መስፋፋት፤ ሰዶማውያን እና እስላሞች በክርስትና ላይ ዘመቻ እንዲያካሂዱ በር መከፈቱ

እነዚህ ወንጀሎች ኦባማን በእግዚአብሔር ዘንድ ተጠያቂ ያደርጋቸዋል፤ የአሜሪካ ፕሬዚደንት ሆኑ ከፍተኛ ባለሥልጣን፣ ከተጠያቂነት አያመልጡም።

የኢትዮጵያ ሕዝብ ታላቅ ነው!

ProudEthiopian

ፕሬዚደንት ኦባማ ወደ ኢትዮጵያ መሄዳቸው እሳቸው እንጂ እንድለኛው ኢትዮጵያ ወይም ኢትዮጵያውያን አይደሉም እድለኞቹ። የምዕራባውያን መሪዎች፡ በግል ሆነ በአገር ደረጃ የሚፈጽሟቸው አስክፊ ድርጊቶች ምናልባት በእስልምና ሕግ በሚተዳደሩ አገሮች ከሚፈጸሙት አጸያፊ ድርጊቶች ጋር የሚወዳደሩ ናቸው። ለብዙዎቻችን የማይታዩን በጣም አስከፊ የሆኑ በደሎችን ነው የሚፈጽሙት።

የእናት አገራችንን ምድር ሲረግጡ፤ በሕዝባችን ላይ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ የሠሩትን በደል በመገንዘብ ንስሓ ለመግባት ፈቃደኛ መሆን ይኖርባቸዋል። ያኔ ነው፡ እንኳን ደኽና መጡ! የምንለው። አሊያ፡ እንደወትሮው የኢትዮጵያ ክርስትናን ባለማክበር ምዕመናኗን በመውቀስ፡ ሰዶማዊ የሆነ ቅስቅሳ የሚያካሂዱ ከሆነ፡ አንጠራጠር፡ መቅሰፍቱ በሄዱበት ሁሉ ነው የሚከተላቸው። ሳዑዲ፣ ቱርክ እና ግብጽ ሲመላለሱ፡ ይህን አስመልክቶ አንዲትም ቃል አልተነፈሱም ነበር፤ ስለዚህ፡ ለራሳቸው ጥቁርሕዝብ ሳይቆሙ ወደኛ መጥተው ሕዝባችንን የሚወቅሱበት ወይም የሚኮንኑበት ህሊና አይኖራቸውም።

ኦባማ በኢትዮጵያውያን ላይ ምን በደል ሠርተዋል?

ObamaAfricaምስሉ፡ የኦባማ ተወዳጅነት በአፍሪካ

1. አይኤስ የተባለውን እስላማዊ ቡድን የመሠረቱት ኦባማ ናቸው፤ በዚህ ቡድን ክርስቲያን ኢትዮጵያውያን ወደ ሜዲትራንያን ባሕር ደማቸው ፈሷል፣ በሲናይ በረሃ ኩላሊቶቻቸው ተወስደውባቸዋል፥ ተሽጠዋል፥ ተደፍረዋል ተገድለዋል

2. በተለያዩ ተቋሞቻቸው አማካይነት በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ክርስቲያን ኢትዮጵያውያን እህቶቻችን ፡ አንዳንዶቹ መኻን እንዲኾኑ ሌሎቹ ደግሞ ልጆቻቸውን እንዲያስወርዱ (እንዲገድሉ) ተደርገዋል

3. በባሕላችን፣ በቋንቋችንና በእምነታችን ላይ ጦርነት ከፍተውብናል፤ ዓየራችንን ፥ ምግባችንና መጠጣችንን በመበከል የኢትዮጵያዊውን መልክ ለመቀየርም ጥረት እያደረጉ ነው

4. ዛሬም የምናገረው ነው፤ ለቀድሞው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ፓትርያርክ እና ለጠቅላይ ምኒስትር መለስ ዜናዊ ሞት ፕሬዚደንት ባራክ ሁሴን ኦባማ፥ መሀመድ አላሙዲን፥ መሀማድ ሙርሲ የሚያውቁት ነገር እንዳለ ነው።

ኃጢአት የማይሠራ የለም፤ ሁላችንም ኃጢአተኞች ነን። ሆኖም፡ እንደምናየው ፕሬዚደንት ኦባማ ብዙ ውሸት ዋሽተዋል፥ ገድለዋል/አስገድለዋል፥ ሰዶማዊነት እንዲስፋፋ ከፍተኛ ሚና ተጫውተዋል. ወዘተ. ባጠቃላይ፡ ምናልባት 10ቱን የእግዚአብሔር ትዕዛዛት አላከበሩም። በእግዚአብሔር ፊት እየፈጸሟቸው ያሏቸው ወንጀሎች ከ3ሺህ ዓመታት በፊት የሰዶም እና ገሞራ ነዋሪዎች ከፈጸሟቸው ወንጀሎች የከፉ ናቸው። ሰዶም እና ገሞራ አጸያፊ ድርጊቶቻቸውን እዚያው በሚኖሩበት ከተማ ነበር የፈጸሙት፤ እነ ኦባማ ግን ከከተማዎቻቸውና አገሮቻቸው ድንበር አልፈው በመላው ዓለም ነው ኃጢአታቸውን በግዴታ ለማስፋፋት እየሞከሩ ያሉት። ይህ ትልቅ፣ በጣም ትልቅ ወንጀል ነው! በእውነት ኦባማ በፈጸሟቸው የተለያዩ ወንጀሎች ተጸጻች ቢሆኑና ትልቅ ሰው ቢሆኑ ኖሮ ከሥልጣናቸው ከዓመታት በፊት በፈቃዳቸው በወረዱ ነበር።

fflag

ሰዶማዊነትን የሚደግፉትን እና ወንድሞቻቸው፡ ኦባማ በፈጠሯቸው የአይሲስ ገዳዮች እንደ በግ የታረዱባቸው ክርስቲያን ኢትዮጵያውያን ፕሬዚደንት ባራክ ሁሴን ኦባማን ባደባባይ ከመቀበል መቆጠብ ይኖርባቸዋል። አልያ ትልቅ ጸረክርስቶሳዊ ቅሌት ነው የሚሆነው!

ኢትዮጵያን ቀዳሚ ከሆኑት የጸረሰዶማውያን አገሮች ሰሞኑን መመደባቸው በአጋጣሚ አይደለም። ሰዶማውያኑ የባንዲራችንን ቀለማት በመዘቅዘቅ አገራችን ዋና ጠላታቸው እንደሆነች እየጠቆሙን ነው። ሕዝባችን ከሁሉም አቅጣጫ ለውርደትና ለውድቀት መብቃት እንዳለበት ፊርማቸውን ካሰፈሩ ውለው አድረዋል። ምናልባት በኦባማ ጉብኝት ወቅት የታሰበ ተንኮል ይኖር ይሆን? ኦባማ በኢትዮጵያ ቆይታቸው አደጋ ነገር ቢገጥማቸው፤ ጸረሰዶማዊ የሆኑትን የቀጥተኛ ተዋሕዶ ክርስቲያኖች ለመኮነን፡ ኢትዮጵያንም ለመውረር ዕቅድ ይኖራቸው ይሆን? አገራችንን ከከበቧት ውለው አድረዋል። በጅቡቲ ምን እየሠሩ ይሆን? ከዚህ በፊት የኔቶ ወታደሮች በድርቅና ረሃብ ሳቢያ ኢትዮጵያ ሠፍረው ብዙ ወንጀሎችን በአገራችን መፈጸማቸውን እናስታውስ።

መቼስ እውነትን ለዘላለም ደብቆ መያዝ አይቻልምና፡ ነጋም ጠባም፡ ምስጢራዊ የሆኑ ነገሮች ሁሉ አንድ ቀን መገለጣቸው አይቀርም። አንጋፋ ለውጦችን ልብ ብለን ሳንታዘባቸው ያልፋሉ፡ ነገር ግን ለሰብዓዊ እድገታችን ከፍተኛ ሚና ስለሚጫወቱ፡ እውነትን ያቀፉ ለውጦችን በስሜት መከታተል ይኖርብናል፤ በጨለማው ቡድኖች የተደበቁት ምስጢሮች የሚጋለጡበት ዘመን ላይ ደርሰናልና።

እዚህ ድህረገጽ በሚገኘው ቪዲዮ ላይ የቀረበው ቃለመጠይቅ በጣም የሚያስገርምና ለማመን የሚያስቸግር ነው። ኬይ ግሪግስትባላልቸ፤ የአሜሪካ ሠራዊት ሜሪን ኮሎኔል ሚስት ናት። ባሏ፡ በአገር ውስጥ እና በዓለም ዓቀፍ ደረጃ በሁሉም አቅጣጫ ከፍተኛ ተጽእኖ ያለው የአሜሪካ ሠራዊት የስለላ ቡድን አባል የነበረ ሲሆን፡ ባለቤቱን፡ ኬትን፡ ሰክሮ ሲመጣ፡ ብዙ ምስጢሮችን ያካፍላትና አልፎ አልፎም ይደበድባት እንደነበር ገልጣለች። ኬይ፡ አጋላጭ ፊሽካ ነፊየሆነችው እ..አ በ1996 .. ነበር። ከዚህ ጊዜ ጀምሮ የግድያ ዛቻዎችን ስትቀበል ኖራለች።

... 1998 .. ኬይ ግሪግስ የክርስቲያን ኤፍ. ኤም አቅራቢ ከሆነው ከ ፓስተር ሪክ ስትሮውከተር ጋር የ 7 ሰዓት ቃለ መጠይቅ አድርጋለች። ምንም እንኳን አንዳንድ አሻሚና ጭፍን የሆኑ ነገሮችን ብትናገርም (ለምሳሌ፡ በአይሁዳውያን ላይ ብቻ በይበልጥ ትኩረት ማድረጓ፡ ጸረእስራኤል የሆነ አቋም መያዟና ለተንኮለኞቹ ፍልስጤሞች መራራቷይህ የብዙ ምዕራብ ሴቶች ችግር ነው፤ ሁኔታዎችን ከታሪክ ጋር የማገናዘብ ድክመት አላቸው) አብዛኛው ግን እውነት መሆኑ የሚያጠራጥር አይደለም።

በዚህ ኢንተርቪው፦

  1. — ብዙ ባለሥልጣኖች በወንጀለኞችና አረመኔዎች እጅ እንደወደቁ

  2. —ከበስተጀርባ ሆነው ሥልጣኑን የያዙት እነዚህ ምስጢራዊ ኃይሎች ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣኖችን ለመቆጣጠር ያስችላቸው ዘንድ ከሚጠቀሙባቸው ዘዴዎች መካከል አጸያፊ በሆኑ ወሲባዊ ተግባራት ላይ እንዲሰማሩ መገፋፋት (ድርጊቱ ለስም ማጥፊያነት በኋላ ስለሚረዳ። ቢል ኮዝቢ ላይ እያየነው ነው)

  3. —ከፍተኛ የፖለቲካ፣ የባንክና መንግሥታዊ ተቋማት፣ የጦር ሠራዊቱና የስለላ ድርጅቶች ሥልጣን ላይ የተቀመጡ ግለሰቦች እንደ ነፃ ግንበኞች” ፣ ካባላእና ቅል እና አጥንቶችበብዛት ሰዶማውያን፥ ሕፃናት ደፋሪዎች፥ ሽርሙጥና ላይ የተሰማሩ መሆናቸውን።

  4. ከነዚህም መካከል ታዋቂው ሄንሪ ኪሲንጀር እንደሚገኙበት

  5. —ልክ ጀርመን በናዚዎች ጊዜ ሴቶችን እና እናቶችን የማግለል ፖሊሲ እንደምትከተለው እነዚህም ሰዶማውያን ቱጃሮች ሴቶችን እንደሚያረክሱ፣ እንደሚኮንኑ እና እንደሚያንቋሽሹ

  6. —ሰዶማውያኑ ከተመረጡ የአውሮፓ አገሮች፣ ከቱርክ፣ ከእስራኤልና ከሳዑዲ አረቢያ ከመጡ ቡድኖችና ግለሰቦች ጋር በመተባበር አጸያፊ ዓለምአቀፋዊ እንቅስቃሴዎችን እንደሚያደርጉ፡ በገዳይ ኮማንዶዎቻቸው አማካይነት የግድያ ተግባራትን በየቦታው እንደምፈጽሙ

  7. —ጥቁር ሕዝቦች – እንደነ ኮሊን ፓወልጀሲ ጃክሰን ወይም ባራክ ኦባማ እራሳቸውን የሸጡ አሻንጉሊቶች ካልሆኑ በቀር – ከእነዚህ ቱጃሮቹ ጋር አብረው እንደማይሰሩ

ኬይ ግሪግስ። በ2015 .ም ምን እንደተናገረች ለመስማት በጣም ጓጉቻለሁ።

__

Posted in Curiosity, Ethiopia, Faith, Infos | Tagged: , | Leave a Comment »

በስልጤ ዞን ክርስቲያኖች የድረሱልን ጥሪ እያሰሙ ነው፤ ‹‹ወረዳው ሊቢያ ኾኖብናል፤ ለእኛም አልቅሱልን›› እያሉ ነው

Posted by addisethiopia on May 13, 2015


ክርስቲያን መምህራን እና የመንግሥት ሠራተኞች ተመርረው እና ተሠቃይተው ወረዳውን እንዲለቁ ከሥራ ማባረርን ጨምሮ እስራት፣ ያለበቂ ምክንያት የደመወዝ ቅጣት፣ ያልተገባ የሥራ ምደባ እና ዝውውር እንዲኹም ‹‹እናርዳችኋለን›› በሚል የግድያ ዛቻ ይደረግባቸዋል፤

የሚያስቀድሱበት እና የሚቀበሩበት ቤተ ክርስቲያን መሥሪያ ቦታ ያገኙት በብዙ ውጣ ውረድ ነው፤ የቂልጦ ጎሞሮ ቅድስት ማርያም ሕንፃ ቤተ ክርስቲያንን ለመሥራት በኮሚቴ የተሰባሰቡ ምእመናን በአንድነት ባሉበት ቤት በምሽት ቤንዚን በማርከፍከፍ እሳት ተለቆባቸዋል፤

እየተሠራ ባለው ሕንፃ ቤተ ክርስቲያን ላይ ‹‹ጉልላት ለምን አስቀመጣችኹ›› ሦስት ጊዜ የማቃጠል ሙከራ ተደርጓል በዞኑ ባለሥልጣናት በተደጋጋሚ የሚወቀሱት የወረዳው አስተዳደርና ልዩ ልዩ አደረጃጀቶች ጉዳዩን በውይይት ስም እያድበሰበሱ ክርስቲያኖችን በማይመለከታቸው ጉዳይ በደመወዝ ከመቅጣት፣ ከሥራ ከማባረር እና ከመኖርያቸው ከማሳደድ ውጭ መፍትሔ ሰጭ የእርምት ርምጃ እየወሰዱ አይደለም፤

የሚደርስባቸውን በደል ለዞኑ ያሳወቁ እና በጠንካራ ሠራተኝነታቸው ከዐይን ያውጣችኹ የተባሉ የወረዳው ክርስቲያን መምህራን እና የመንግሥት ሠራተኞች ‹‹አስወቅሳችኹን›› ባሉ የወረዳው አስተዳደር እና የድርጅት ጉዳይ ሓላፊዎች፥ ያለበቂ ምክንያት ከሥራ ተባርረዋል፤ የትምህርት ዝግጅታቸውን እና የሞያ ልምዳቸውን በማይመጥን ቦታ በማዛወር ሞራላዊ ጥቃት ተፈጽሞባቸዋል፤ ‹‹ሀገራችኹ ሥራ ቢኖር እዚኽ አትመጡም ነበር›› በሚል ተዘብቶባቸዋል፤

በዛሬው ዕለት ለሦስተኛ ጊዜ ከቤቱ ተወስዶ የታሰረው የሕንፃ ቤተ ክርስቲያኑ አሠሪ ኮሚቴ ሰብሳቢ እና ምስጉኑ የቂልጦ ኹለተኛ ደረጃ መሰናዶ ት/ቤት መምህር የማርያም ወርቅ ተሻገር በፖሊስ ጣቢያ እንግልት እና ድብደባ እየተፈጸመበት እንዳለ ተዘግቧል፡፡ የዋስ መብቱ ተጠብቆ ሊፈታ እንደማይችልም ከወረዳው ኢንስፔክተር መገለጹን የዓይን እማኞች ተናግረዋል፡፡

ይህ መልእክት የደረሳችኹ ወገኖቻችን፤ የሃይማኖት አባቶች፣ የመንግሥት አመራሮች እና መሥሪያ ቤቶች፣ ጋዜጠኞች፣ ለሊቢያ ወንድሞቻችን ብቻ አይደለም ለእኛም አልቅሱ፤ እነርሱ ከአገር ወጥተው ነው፤ እኛ ግን በአገራችን ከአዲስ አበባ 220 .. ርቀት ላይ ነው የምንገኘው፡፡ ፍጹም መሮናል፤ ተሠቃይተናል፤ በጭንቀት እና በስጋት ላይ ነን፤ መቼ ምን እንደምንኾን አናውቅምና ድረሱልን ! ! !

ሙሉ መልዕክቱ እዚህ ይገኛል

__

Posted in Ethiopia, Faith, Infos | Tagged: , , , , , , , | Leave a Comment »

 
%d bloggers like this: