Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • March 2023
    M T W T F S S
     12345
    6789101112
    13141516171819
    20212223242526
    2728293031  
  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

Posts Tagged ‘ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነት’

ቅ. ሥላሴ | እናንተም የክርስቶስ ከሆናችሁ እንኪያስ የአብርሃም ዘር እንደ ተስፋውም ቃል ወራሾች ናችሁ

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on December 16, 2021

💭 እንጦጦ መንበረ ስብሃት ቅድስት ስላሴ ቤተክርስትያን ፲፱፻፴፰ ዓ ም ተመሠረተ

ውብ እና ማራኪ የሆነው የቅድስት ሥላሴ ቤተከርስቲያን ግቢ፤ አዲስ አበባ እንጦጦ/ሽሮ ሜዳ መስከረም ፳፻፲ ወ ፩ ዓ.ም

✞✞✞[ወደ ገላትያ ሰዎች ምዕራፍ ፫፥፳፱]✞✞✞

እናንተም የክርስቶስ ከሆናችሁ እንኪያስ የአብርሃም ዘር እንደ ተስፋውም ቃል ወራሾች ናችሁ”

ጥቅምት ፳፬/24 በፃድቁ አባታችን አቡነ ተክለ ሐይማኖት ዕለት የጀመረውን ይህን በትግራይ ላይ እየተካሄደ ያለውን የዘር ማጥፋት “ዘመቻ ፀረአክሱምጽዮን” ጂሃዳዊ የጥቃት ጦርነትን የደገፉትና የሚደግፉ ከእንስሳ ዘር የተገኙት የዋቄዮአላህዲያብሎስ ጭፍሮችና የተታለሉት “ሃጋር/ አጋሮቻቸው እንዲሁም በመላው ዓለም የሚገኙትና የእባቡ ዘር የሆኑት ኤዶማውያን እና እስማኤላውያን ሁሉ፤ ”ጽዮናውያንን ከምድረ ገጽ ካላጠፋን ብለው ዛሬም ሆነ ለብዙ ዘመናትም በተለያየ መንገድ የዘር ማጥፋት ጦርነቱን የከፈቱበት ዋናው ምክኒያት ጥንታዊውን፣ የመጀመሪያውን የሴቲቱን የሰው ዘር፣ እስራኤል ዘነፍስ የተባለውን የአዲስ ኪዳኑን ኢትዮጵያዊ ሙሉ በሙሉ አጥፍተው ምድርን ሙሉ በሙሉ ለብቻቸው በመቆጣጠር “ኬኛ” እያሉ ዋቄዮአላህዲያብሎስን ለማንገስ ስለሚሹ ነው። ተግባራቸው ፀረ ሥላሴ፣ የክርስቶስ ተቃዋሚ፣ ፀረጽዮን፣ ፀረአቡነ አረጋዊ፣ ፀረአቡነ ተክለ ሃይማኖት፣ ባጠቃላ ፀረቅዱሳን፣ ፀረተዋሕዶ ክርስትና፣ ፀረኢትዮጵያ፣ ፀረሰንደቅ፣ ፀረግዕዝ፣ ፀረሰሜናውያን፣ ፀረተጋሩ፣ ፀረሰላም፣ ፀረፍቅር፣ ፀረፍትህ፣ ፀረእውነት መሆኑን ያለፉ አስራ አራት ወራት ቁልጭ አድርገው አሳይተውናል።

ቅዱስ ዮሐንስ በራዕዩ ”ዲያቢሎስ ጥቂት ዘመን እንዳለው አውቆ በታላቅ ቁጣ ወደ እናንተ ወርዷልና” ብሎ ስለነገረን ወደ ሕይወታችን በቅናት ቁጣ እየመጣ የሚያመሰቃቅለንን፣ ግራ የሚያጋባንን፣ የሚያባክነንን፣ የእኛ የሆነውን የሚነጥቀንን ዲያቢሎስ በሰይፈ ሥላሴ ጸሎት ልናርቀው እና ልንርቀው ይገባል። [ራዕ. ፲፪÷፲፪]

✞✞✞በመለኮት ቅድስት ሥላሴ፤ የሚተነኳኰለን፣ ወንድማማቾችን እርስበር የሚያባለው፣ ቀጣፊው፣ አጭበርባሪው፣ አታላዩ፣ ጠበኛው፣ የዲያብሎስ ጭፍራ አብዮት አህመድ አሊ የተባለው አረመኔ ጠላታችን ይጠፋልን ዘንድ የእግዚአብሔር ቃል ይውጋው፣ በተሳለ የመለኮት ሰይፍ አንገቱን ያጣጋው በአምልኮትና በፍጹም ምስጋና በሥላሴ ስም አሜን!✞✞✞

___________________

Posted in Ethiopia, Faith, War & Crisis | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

የሩሲያው መሪ ጥምቀትን በኦርቶዶክሷ ሰርቢያ ሲያከብሩ፡ የኛዎቹ ደግሞ ‘፫ኛውን ሂጂራ’ ወደ ኢትዮጵያን በማመቻቸት ላይ ናቸው

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on January 19, 2019

መዝሙረ ዳዊት ምዕራፍ ፻፴፫]

ወንድሞች በኅብረት ቢቀመጡ፥ እነሆ፥ መልካም ነው፥ እነሆም፥ ያማረ ነው።

ከራስ እስከ ጢም እንደሚፈስስ፥ እስከ አሮን ጢም፥ በልብሱ መደረቢያ እንደሚወርድ ሽቱ ነው።

ኦርቶዶክሱ ፕሬዚደንት ፑቲን ለጉብኝት እህት አገር ወደ ሆነችው ወደ ሰርቢያ አምርተዋል። በሚሊየን የሚቆጠሩ ኦርቶዶክስ ክርስቲያኖች በዝነኛው የቅዱስ ሳቫ (የሰርቢያ ቅዱስ) ቤተክርስቲያን የሞቀ አቀባበል አድርገውላቸዋል።

በሉሲፈራዊያኑ የቱርክ፣ የናዚዎች እና በቅርቡም የኔቶ ሠራዊት በታሪኳ ብዙ ጥቃት የደረሰባት ኦርቶዶክስ ሰርቢያ መጀመሪያ በእርሷ እርዳታ ኃያል ለመሆን የበቃችውን ዩጎዛላቪያን በታትነው አደከሟት፤ ከዚያም፡ በቅርቡ፡ የክርስትና ስልጣኔዋ ታሪካዊ ቦታ የሆነችውን ኮሶቮን ገንጥለው ወሰዱባት።

..አ በ1999 .ም እሑድ በትንሳኤ በዓል ወቅት የአሜሪካው ፕሬዚደንት ቢል ክሊንተን ዋና ከተማዋን ቤዖግራድን በከፋ መልክ በቦምብ ማስደብደቡን አንረሳም፤ በኦርቶዶክስ ትንሳኤ ዕለት! እዚህ ያንብቡ

ያው እንግዲህ፤ ሉሲፈራውያኑ ከዚያ ጊዜ ጀምሮ ጦርነቱን ኦርቶዶክስ ክርስቲያን በሆኑት ሰርቢያ፣ ማኬዶኒያ፣ አርሜኒያ፣ ጆርጂያ፣ ሩሲያ፣ ዩክሬይን ቆጵሮስ፣ ሶሪያ፣ ግብጽ እና ኢትዮጵያ ላይ በማጧጧፍ ላይ ናቸው።

____________

Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

የሩሲያ መሪዎች በቤተክርስቲያን | አንድ የአገራችን መሪ ግን ለመጨረሻ ጊዜ ቤተክርስቲያን የሄደው ከ፵፭/ 45 ዓመታት በፊት ነበር

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on January 13, 2019

እስኪ አስቡበትአብረን እናስብበትአንድ የኢትዮጵያ መሪ የክርስቶስ የሆነችውን እናት ቤተክርስቲያን የጎበኘው ከአርባ አምስት ዓመታት በፊት ነበር። ዋው!

የኮሙኒዝምን ሥርዓት ሲያገለግሉ የነበሩት የሩሲያው ፕሬዚደንት ቭላዲሚር ፑቲን የሉሲፈራውያኑን ርዕዮተ ዓለም እርግፍ አድርገው በመተው ወደ ክርስቶስ መጥተዋል። በሶቪየት ኮሙኒዝም ጊዜ የቭላዲሚር ፑቲን እናት በቅዱስ ፒተርስቡርግ ከተማ ወደሚገኘው ቤተክርስቲያን በድብቅ ቭላዲሚር ፑቲንን አምጥተዋቸው አስጠምቀዋቸው ነበር። (ቤተክርስቲያን የሚሄዱ ሩሲያውያን ክትትልና አድሎ ይደረግባቸው ነበርና)

በአንድ ወቅት፤ “አንገቴ ላይ ያደርግኳት ይህች መስቀል ሕይወቴን አድናታለች” በማለት መስክረው የነበሩት ፕሬዚደንት ፑቲን በዚሁ በተጠመቁበት ቤተክርስቲያን ነበር ባለፈው እሑድ የገና በዓልን ተመስጠው ሲያከብሩ የሚታዩት። ጠቅላይ ሚንስትር ሚድቪዴም ለፀሎት ሦስት ጊዜ ሲያማትቡ ይታያሉ።

ወደ አገራችን ስንመጣ፤ ቪዲዮው ላይ እንደሚታየው፡ አንድ የአገራችን መሪ ለመጨረሻ ጊዜ ኢትዮጵያዊቷን ቤተክርስቲያን የጎበኘው ከአርባ አምስት ዓመታት በፊት ነበር። እንዴት ነውይህ ክስተት እርርይ! ! ! አያሰኘንምን። ምን ዓይነት ኃጢዓት ብንሠራ ነው ኢትዮጵያን እና አምላኳን የሚጠሉ መሪዎች የተሰጡን?! እንደ መስቀል፣ ገና እና ጥምቀት በመሳሰሉት አንጋፋ የኢትዮጵያውያን ክብረ በዓላት (ሰባ ሚሊዬን ኢትዮጵያውያን የሚያከብሯቸው) ላይ ለመሳተፍ ፈቃደኛ የሆኑ መሪዎች እንኳን የሉንም። በመስከረሙ የመስቀል ደመራ በዓል ወቅት ዶ/ር አብይ በመስቀል አደባባይ ይገኙ ይሆናል የሚል ጭምጭምታ ነበር፤ ነገር ግን እርሳቸውም ያው ከ666ቱ ስለሆኑ ሳይሳተፉ ቀሩ።

ባለፈው ጊዜ፡ በዚምባብዌ፡ ለገዳዩ መንግስቱ ኃይለማርያም የሰገዱት የቀድሞው ጠ/ሚንስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ከስልጣን ከመውረዳቸው በፊት በኢየሩሳሌም የምትገኘውን የኢትዮጵያ ቤትከርስቲያን በእስራኤል መንግስት ግፊት ለመጎብኘት ሲገደዱ ጫማቸውን እንኳን ሳያወልቁ ነበር የገቡት፤ አቤት ድፍረት! አቤት ትዕቢት አቤት ቅሌት!

! ለሉሲፈራውያኑ ወኪሎች፤ ሕዝባችንን ኋለኞች ለማድረግ ተግተው ለሚሠሩት፤ ዋ!

እኛ የተዋሕዶ ልጆች ግን በገዢዎች ተስፋ ከማድረግ ይልቅ በእግዚአብሔር ተስፋ ማድረጉን እንመርጣለን፦

[ ፪ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች ምዕራፍ ፮፥፩፡፲]

አብረንም እየሠራን የእግዚአብሔርን ጸጋ በከንቱ እንዳትቀበሉ ደግሞ እንለምናለን፤ በተወደደ ሰዓት ሰማሁህ በመዳንም ቀን ረዳሁህ ይላልና፤ እነሆ፥ የተወደደው ሰዓት አሁን ነው፤ እነሆ፥ የመዳን ቀን አሁን ነው። አገልግሎታችንም እንዳይነቀፍ በአንዳች ነገር ማሰናከያ ከቶ አንሰጥም። ነገር ግን በሁሉ እንደ እግዚአብሔር አገልጋዮች ራሳችንን እናማጥናለን፤ በብዙ መጽናት፥ በመከራ፥ በችግር፥ በጭንቀት፥ በመገረፍ፥ በወኅኒ፥ በሁከት፥ በድካም፥ እንቅልፍ በማጣት፥ በመጦም፥ በንጽህና፥ በእውቀት፥ በትዕግሥት፥ በቸርነት፥ በመንፈስ ቅዱስ፥ ግብዝነት በሌለው ፍቅር፥ በእውነት ቃል፥ በእግዚአብሔር ኃይል፥ ለቀኝና ለግራ በሚሆን በጽድቅ የጦር ዕቃ፥ በክብርና በውርደት፥ በክፉ ወሬና በመልካም ወሬ ራሳችንን እናማጥናለን፤ አሳቾች ስንባል እውነተኞች ነን፤ ያልታወቁ ስንባል የታወቅን ነን፤ የምንሞት ስንመስል እነሆ ሕያዋን ነን፤ የተቀጣን ስንሆን አንገደልም፤ ኀዘንተኞች ስንሆን ዘወትር ደስ ይለናል፤ ድሆች ስንሆን ብዙዎችን ባለ ጠጎች እናደርጋለን፤ አንዳች የሌለን ስንሆን ሁሉ የእኛ ነው።”

__________________

Posted in Curiosity, Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

ኮፕት አባታችን በላሊበላ የገና በዓል | “ግሩም ታሪክና ሃይማኖታዊ ሥርዓት ስላላችሁ ልትኮሩበት ይገባል”

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on January 6, 2019

ይህን ያሉት በጀርመን የኮፕት ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ጳጳስ የሆኑት አንባ ዳሚያን ናቸው። (ቪዲዮው ላይ “ዳንኤል” ያለው በስህተት ነው)። ግልጽና ቀጥተኛ የሆነ ቃል የሚናገሩና የማደንቃቸው አባት ናቸው። ቃለ ሕይወት ያሰማልን! ለኮፕት ወገኖቻችንም ይህን የልደት በዓል በሰላም እንዲያከብሩት እንመኝላቸዋለን!

ብሩክ ገና!!!

______________

Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , | 1 Comment »

ድንግል ፈጣሪዋን ወለደችው | ብሩክ የልደት በዓል

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on January 5, 2019

ይህ የልደት በዓል ታኅሣሥ ፳፰ / ጃንዋሪ 7 በ፤

  • + ኢትዮጵያ (ኤርትራን ጨምሮ)

  • + እስራኤል

  • + ግብጽ

  • + አርመኒያ

  • + ጆርጂያ

  • + ሩሲያ

  • + ዩክሬን

  • + ቤላሩስ

  • + ሞልዶቫ

  • + ካዛክስታን

  • + ሰርቢያ

  • + ማኬዶኒያ

  • + ሞንቴኔግሮ

በቆንጆ መልክ ይከበራልእንኳን አደረሰን!

________________

Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , | Leave a Comment »

ቅዱስ ገብርኤል ሆይ፥ ሕዝባችንን በመተናኮል ላይ ያለውን ዘንዶ እና የአገራችንን ጠላቶች ሁሉ በሰይፍህ ቀጥቅጠህ ጣላቸው

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on December 30, 2018

[ትንቢተ ዳንኤል ምዕራፍ ፰]

፲፭ እኔም ዳንኤል ራእዩን ባየሁ ጊዜ ማስተዋሉን ፈለግሁ፤ እነሆም፥ የሰው ምስያ በፊቴ ቆሞ ነበር።

፲፮ በኡባልም ወንዝ መካከል። ገብርኤል ሆይ፥ ራእዩን ለዚህ ሰው አስታውቀው ብሎ የሚጮኸውን የሰውን ድምፅ ሰማሁ።

፲፯ እኔም ወደ ቆምሁበት ቀረበ፤ በመጣም ጊዜ ፈርቼ በግምባሬ ተደፋሁ፤ እርሱም። የሰው ልጅ ሆይ፥ ራእዩ ለፍጻሜ ዘመን እንደ ሆነ አስተውል አለኝ።

፲፰ ሲናገረኝም ደንግጬ በምድር ላይ በግምባሬ ተደፋሁ፤ እርሱም ዳሰሰኝ ቀጥ አድርጎም አቆመኝ።

፲፱ እንዲህም አለኝ። እነሆ፥ በመቅሠፍቱ በመጨረሻ ዘመን የሚሆነውን አስታውቅሃለሁ፤ ይህ ለተወሰነው ለፍጻሜ ዘመን ነውና።

____________

 

Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , | Leave a Comment »

እናንተም የክርስቶስ ከሆናችሁ እንኪያስ የአብርሃም ዘር እንደ ተስፋውም ቃል ወራሾች ናችሁ

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on December 24, 2018

ዘራችን ማን እደሆነ፣ ያወረሰን፡ የወረሰን ማን እንደሆነ፣ በዚህ በሚያልፈው፡ በሚጠፋው፣ ሰዎች በፈጠሩልን፣ ጠላት በሠራልን፡ በቀደደልን ቦይ እየፈሰስን፣ እንደው በቅጡ እንኳን ለይተን በማናውቀው፡ በዚህ ምድራዊ በሆነው ዘር ከምንነካከስ፡ ከምንጠፋፋ ትውልድንም ከምናጠፋ ይልቅ፥ ዋናው ምንጫችን፡ ወርሶ ያወረሰን ኢየሱስ ክርስቶስ እንደሆነ ማወቅ ይገባናል።

____________

Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , | Leave a Comment »

የግራኝ አህመድ ጊዜ እንዳያገረሽ – ቤተ ክርስቲያናችን ዘመቻ ፊልጶስን ልታውጅ ይገባታል

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on December 5, 2018

ሞኙ ሕዝባችንን፡ ላይ ላዩን በድራማዎች እና በ “አዲስ ዜና” ፕሮፓጋንዳዎች እያታለሉ ውስጥ ውስጡን ግን የመቶ ዓመት ህልሞቻቸውን በሥራ ላይ በማዋል ላይ ናቸው።

በጅጅጋ፣ በአምቦ፣ በጅማና በመሳሰሉት የደቡብ ከተሞች ተዋሕዶ ክርስቲያኖች ተመንጥረው ቀስበቀስ በመገደል ላይ ናቸው፤ ክርስቲያን ሕፃናቱ ደክመው ሕይወታቸው እንድታጠር መርዝ እየተሰጣቸው ነው። አዲስ አበባም ከደቡብ በመጡ አማርኛ ተናጋሪ ባልሆኑ የኢትዮጵያ ጠላቶች ተወርራለች (ይህ የማፈናቀያ ዘመቻ በደንብ መጧጧፍ የጀመረው፡ በተለይ አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ ሥልጣን ላይ ከወጡ በኋላ ነው፤ የደቡብ ሰዎችና ሙስሊሞች በብዛት ወደ አዲስ አበባ እንዲገቡና የንግድ ቦታዎችን እንዲከፍቱ፣ በየጎረቤቱ ተሰግሰው እንዲገቡ፣ ወላይታዎች ደግሞ ጉራጌዎችን በመተካት እንደ ጫማ ጠረጋ በመሳሰሉት የስራ መስኮች ላይ እንዲሰማሩ፤ በሌላ በኩል ክርስቲያኖች (“አማራና ትግሬ) የእኔቢጤዎች ሆነው በየቦታው እንዲለምኑ፤ በተለይ በቤተክርስቲያን አካባቢ። ይህ ማንም የሚያየው የአዲስ አበባ ገጽታ ነው።

አሁን ደግሞ በመካሄድ ላይ ያለውን ለው ተከትሎ ወይም ተገን አድርጎ የሚነሣ ፀረ ክርስትና ቡድን በሚወስደው ኢክርስቲያናዊ ርምጃ ምክንያት የአምልኮተ እግዚአብሔር መፈጸሚያ የኾኑት የተዋሕዶ አብያተ ክርስቲያን ሲደፈሩና ሲወድሙ፤ በአገልጋዮቿ ካህናትና በተከታዮቿ ምእመናንም ላይ እስከ ኅልፈተ ሕይወት ጉዳት ሲደርስ፣ ሌላ አቅም ባይኖራትም የተከታይ አቅም እያላት፣ “ዝም በሉ የእኔን እግር ነው የሚበላው” እንደተባለው ዐይነት ነገር የደረሰባትን ጉዳትና ችግር ኹሉ በትዕግሥት፣ በአርምሞና በጽሞና ማሳለፍ ከጀመረች እነኾ ወደ ግማሽ ምእት ዓመት አጋማሽ ተጠግቷታል፡፡

ይህን በማስመልከት ሐራ ዘተዋሕዶ የሚከተለውን ዘገባ አቅርቦልናል፦

የሩቁን ለታሪክ እንለፈውና በቅርቡ የተደረገውን ስናስታውሰው፣ በ1997 .. በአርሲ ሀገረ ስብከት በኮፈሌ ወረዳ ውስጥ የምትገኘው የአይሻ ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን፣ በወቅቱ በተፈጠረው የምርጫ ግርግር ምክንያት፣ ፀረ ክርስትና አቋም ባለው ቡድን ስትቃጠልና አገልጋዮቿ ካህናት በቤተ መቅደስ ውስጥ ሲታረዱ ዝም ብላ አሳልፋለች፡፡ እንደገናም በ1999 .. በጅማ ሀገረ ስብከት የበሸሻ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ቤተ ክርስቲያን ጥቅምት 5 ቀን በዕለተ በዓሉ በፀረ ክርስትና ኃይሎች ሲቃጠልና አገልጋዮቿ ካህናትና ተከታዮቿ ምእመናንም በቤተ መቅደሱ ውስጥ እንደ በግ ሲታረዱ አሁንም ለኅብረተሰቡ የከፋ እልቂት እንዳይደርስ በማሰብ በብዙኃን ተከታዮቿ ዘንድ እየታማች ጉዳቷን ጉዳት አድርጋ ድምፅዋን ሳታሰማ በትዕግሥት አሳልፋለች፡፡

አሁን ደግሞ በቅርቡ፣ ባሳለፍነው በ2010 .. መገባዳጃ ላይ፣ አገር የኾነችውን ወይም ኹለንተናዊ ጠቃሜታዋና ትሩፋቷ ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ባለውለታ የኾነችውን አንጋፋዋን ቤተ ክርስቲያን ከሌላው ነጥሎ ለመምታትና የተከታዮቿ ምእመናንን አሻራ ከገጸ ምድር ለማጥፋት ወይም አሳምኖ የራሱ ተከታዮች ለማድረግ፣ የረዥም ጊዜ ዕቅድ ባለው የሱማሌ ክልል ፀረ ክርስትና ቡድን በፈጸመው ጥቃት፣ በክልሉ ውስጥ የሚገኙ አብያተ ክርስቲያንን በሙሉ አውድሟቸዋል፤ ሀብታቸውን፣ ንብረታቸውንና ቅርሶቻቸውንም ዘርፏቸዋል፤ አገልጋዮቿ ካህናትንም እንደ ካህኑ ዘካርያስ በየቤተ መቅደሳቸው ውስጥ አርዷቸዋል፡፡

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ላይ ብቻ በማነጣጠር በተከታታይ የተፈጸመው ይህ ዐይነቱ ጥቃት ወይም ኢክርስቲያናዊ ድርጊት ከትዕግሥት በላይ ቢኾንም፣ ቤተ ክርስቲያኒቱ አገር እንደ መኾኗ መጠን፣ አሁንም በቤተ ክርስቲያንም ኾነ በሕዝብ ላይ የበለጠ ጉዳት እንዳያደርስ በማሰብ ብዙ መጎዳቷንና መጠቃቷን ለመንግሥትና ለሕዝብ ይፋ ያደረገችው ከብዙ ጉዳትና ትዕግሥት በኋላ ነው፡፡ ሌላው ቢቀር ከዓመታት በፊት በሊቢያ በረሓ ላይ በአይኤስኤስ ፀረ ክርስትና ቡድን ለተሠዉት ኢትዮጵያውያን ወጣቶች የሰማዕትነት ክብርና ማዕርግ እንደሰጠቻቸው ኹሉ ይልቁንም፣ በራሳቸው አገር በቤተ መቅደስ አገልግሎት ላይ እንዳሉ ለተሠዉት ለራሷ ካህናትና ምእመናን የሰማዕትነት ክብርና ማዕርግ መስጠት ነበረባት፤ ከአሁኑ የቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ የሚጠበቀውም ይህ ውሳኔ ነበር፤ ወደፊትም ቢኾን የሰማዕትነት ክብርና ማዕርግ እንዲያገኙ ውሳኔ መስጠት ይገባታል፡፡

በአጠቃላይ በአሁኑ ጊዜ፣ ለኹሉም በተሰጠው ገደብ የለሽ የእምነት ነጻነት መሠረት፣ ኹሉም የራሱን እምነት በሰላም ማራመድ ሲገባው በተቃራኒው ፀረ ኦርቶዶክስ ዘመቻ በኹለት ግንባር በመካሔድ ላይ ይገኛል፡፡ በአንድ በኩል ቀደም ሲል በዝርዝር እንደተገለጸው፣ ፀረ ክርስትና አቋም ያለው ቡድን፣ በአንዳንድ አካባቢዎች የሚገኙትን የኦርቶዶክስ አብያተ ክርስቲያን እያቃጠለ ነው፤ ካህናትንና ምእመናንንም እያረደ ነው፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ፣ እንደእነ ፓስተር ኢዩ ጬፋን የመሳሰሉት የእነ ሬንሐርድ ቦንኬ ደቀ መዛሙርት፣ በቡድን ተሰማርተው ሕዝቡን በወንጌል ሳይኾን በመናፍስት መንፈስ በማስገደድና በካራቴ በግድ በማሳመን የእነርሱ ተከታይ ለማድረግ እየተጣጣሩ ነው፡፡

ስለዚህ የብሉይ ኪዳን እምነትና የሐዲስ ኪዳን እምነት መሠረት የኾነችው ሀገረ አምላክ ኢትዮጵያ፣ የእነ ሬንሐርድ ቦንኬ ሠራዊት መፈንጫ አገር ከመኾኗም ባሻገር ኹለተኛዋ ሊብያ እንዳትኾንና የግራኝ አሕመድ ጊዜ እንደገና እንዳያገረሽ፣ ቤተ ክርስቲያናችን ዘመቻ ፊልጶስን ልታውጅ ይገባታል፡፡ በስሟ ተጠቃሚዎች የኾኑት አንጋፋ ማኅበራትም፣ ከቤተ ክርስቲያኒቷ ጋራ በአቻነት ለመሰለፍ የሚያደርጉትን ግብግብ ለጊዜው አቁመው በሚቻላቸው ኹሉ ሊያግዟት ይገባቸዋል፡፡ በአሁኑ ጊዜም ትዕግሥትዋ ያለቀ በመኾኑ፣ ከጥቅምት 11 እስከ 22 ቀን 2011 .. ድረስ ባደረገችው ሲኖዶሳዊ ጉባኤ ባሳለፈችው ውሳኔ፣ ከጦርነት ኹሉ የሃይማኖት ጦርነት ስለሚከፋ፣ የከፋ ችግር ከመፈጠሩ በፊት በሀገሪቱ ምሥራቃዊ እና ደቡብ ምዕራብ ክልሎች እየተፈጸመ ያለው ኢክርስቲያናዊ ድርጊት በአስቸኳይ እንዲገታ መንግሥት የራሱን አፋጣኝ ርምጃ እንዲወስድ ያቀረበችው አቤቱታና ከኅዳር 1 እስከ 7 ቀን 2011 .. 7 ቀናት ያህል በመላ ኢትዮጵያ ጸሎተ ምሕላ እንዲደረግ የዐወጀችው ዐዋጅ የሚደገፍ ነው፡፡

______

Posted in Ethiopia, Faith, Infos | Tagged: , , , , , , , | Leave a Comment »

ቅዱስ ጊዮርጊስ | አንዳንዱ አባት እንደዚህ እየቀሰቀሰ ቤተክርስቲያን ቢያሠራ ዛሬ መናፍቃን እንደቁጫጭ ባልወረሱንም ነበረ፤ በስንፍናችን ተኝተን ነው አሳልፈን የሰጠነው

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on December 2, 2018

ቤተክርስቲያኑን እንዲህ ውብ አድርገው ለሚንከባከቡት አባቶችና እናቶች፣ እህቶችና ወንድሞች ሞቅ ያለ ምስጋና ይድረሳቸው።

እንኳን ለዚህ አበቃን!

________________

Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , | Leave a Comment »

የማርያም እህቶች በጣና ሐይቅ ላይ የኖኅን መርከብ አዩ

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on March 11, 2018

[የማቴዎስ ወንጌል ምዕራፍ ፳፬፥፴፯]

የኖኅ ዘመን እንደ ነበረ የሰው ልጅ መምጣት እንዲሁ ይሆናልና።”

ድንቅ ነው፤ እግዚአብሔር በደመናዎች ላይ ብዙ ምልክቶችን እያሳየን ነውና ወደ ታች ሳይሆን ወደላይ መመልከቱን ማዘውተር ሊኖርብን ነው።

በእኛ በኢትዮጵያውያን ዘንድ “ሰባቱ ኪዳናት” ተብለው የሚታወቁትና የቅዱሱ ኪዳን አካላት የኾኑት፡ የኢትዮጵያዊነት ተዋህዶ ሃያማነኖታችን መሠረቶች፡ መደበኛ ስማቸውና መለያ ምልክታቸው ተለይቶና ተዘርዝሮ ይገኛል። እነዚህም፦

  1. ኪዳነ አዳምና ሔዋን፥

  2. ኪዳነ ኖኅ፥

  3. ኪዳነ መልከ ጼዴቅ፥

  4. ኪዳነ አብርሃም፥

  5. ኪዳነ ሙሴና

  6. ኪዳነ ዳዊት፥ በመጨረሻም

  7. በድንግል ማርያምና በኢየሱስ ክርስቶስ የተገኘው “ኪዳነ ምሕረት

የሚባሉት ናቸው።

______

Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , , | 1 Comment »

 
%d bloggers like this: