Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • June 2023
    M T W T F S S
     1234
    567891011
    12131415161718
    19202122232425
    2627282930  
  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

Posts Tagged ‘ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን’

ስለ ሃይማኖታቸው ሲሉ በሙስሊሞች ሕይወታቸውን በግፍ ለተነጠቁት 30 ኢትዮጵያውያን ሰምዓታት ቤተክርስቲያን መሠራት ይኖርበታል

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on April 23, 2018

______

Posted in Ethiopia, Faith, Life | Tagged: , , , , , , , , , | Leave a Comment »

በሊቢያ በረሃ በሙስሊሞች የታረዱት 12ቱ የቂርቆስ ሠፈር ሰማዕታት ፡ በሁለት ህገወጥ መስጊዶች መካከል የፈለቀውን እጹብ ድንቅ ጸበል አፍልቀውት ይሆን?

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on October 12, 2017

ከቪዲዮው የተወሰደ| ስለ ጸበሉ ጥሩ እውቀት ያላቸው ወንድሞች ያካፈሉኝ አስገራሚ መረጃ በከፊል እነሆ፦

+ ግንቦት ፴፡ ፪ሺ፱ ዓ.ም አዲስ የመድኃኔ ዓለም ፍልውሃ ጸበል ቂርቆስ ቤ/ክርስቲያን አካባቢ ፈለቀ

+ እስካሁን ግማሽ ሚሊየን የሚጠጋ ሕዝብ በጸበሉ ተጠምቋል

+ የኪዳነ ምህረት፣ የአርሴማና የዮሐንስ ጸበሎች በተጨማሪ እንደሚፈልቁ ተጠማቂዎች መስክረዋል

+ አራቱም ጽላቶች በዚህ ቦታ ላይ እንደሚገኙ፡አባቶች በ1976 .ም ጠቁመው ነበር

+ በሊብያ በረሃ ከሁልት ዓመታት በፊት በሙስሊሞች ታርደው ሰማዕትነት ተቀበሉት ኢትዮጵያውያን መካከል 12የቂርቆስ አካባቢ ነዋሪዎች ነበሩ

+ በጸበሉ መፍለቅ የሚያነገራግሩት ሙስሊሞች “ዘምዘም” ነው ብለው ወደ ሳዑዲ ነፍስ አባቶቻቸው ይመላለሳሉ

+ ብዙ “የጠፉ በጎች” ሙስሊሞች በጸበሉ ሲጠመቁና ሲድኑ የኢየሱስ ክርስቶስን መድኃኔ ዓለምነት በቦታው ይመሰክራሉ፤

ኧረ መድኃኔ ዓለም ተው!ኧረ መድኃኔ ዓለም ተው!ይህ ለኛ ለሙስሊሞች ውርደት ነው!”በማለት ይጮሃሉ

+ በጸበሉ ተዓምራዊነት አጋንንቱ እራሳቸው መስካሪዎች ናቸው

+ የጴንጤ መንፈስ አለብን ብለው የሚጮሁና አላህ ስይጣን ነው፣ ክርስቶስ አዳኝ አምላክ ነው የሚሉ ብዙ ናቸው

+ እስልምና ከጥንቆላ ብዙ የከፋ ጣዖታዊ አምልኮት መሆኑን እና ቅዱስነትንም ፈጽሞ እንደማያውቅ አጋንንቱ ይመሰክራሉ

+ እንደዚህ ቀሚስ ለባሽ የአረብ ወኪሎች እየተቅነዘነዙና ጋኔናዊ የአረብኛ ቃላትን እየለፈለፉ፤ ለመጠመቅ የሚጎርፉትን

ኢትዮጵያውያን በየጊዜው ያውካሉ

+ ዓለማውያኑ “የጠፉት በጎች“፤ (”ሸገር ራዲዮ”፣“ኢቢሲ”፣”ሙስሊም ፖሊሶች”)በቦታው ተገኝተው፤ “ውሃው በኬሚካል የተበከለ ነው”በማለት የሃሰት ምስክርነት መስጠታቸውንና በየጊዜው በሚፈወሱት ሰዎች ብዛትም ለማፈር በቅተዋል

+ ተተኩሶ የወጣው ፍልውሃ ጸበል ያቃጠለው ዛፍ ጉድጓዱን ሲቆፍር የነበረው ቻይናዊ መሀንዲስ በፍልውሃው አንድ ዓይኑ ጠፋ፤ በኋላም ራእይ ታይቶት በጸበሉ ተፈውሶ ዓይኑ በርቷል (የረር መድኃኔ ዓለም)

+ ሰማዕታቱን በማስብ በደማቸው ያጸኑትን የእምነት በረከት ተካፋዮች ለመሆን መድኃኔ ዓለም ያብቃን

______

Posted in Ethiopia, Faith, Infos | Tagged: , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ: ከግማሽ ክፍለ ዘመን በላይ ያስቆጠረ ታቦተ ቅዱስ ሚካኤል ተገኘ

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on December 10, 2016

  • የመንበረ ልዑል ቅዱስ ማርቆስ ቤተ ክርስቲያን ከዩኒቨርሲቲው በአደራ ተረክቦታል
  • በዐፄ ኃይለ ሥላሴ ጥያቄ እንደተቀረፀና ከ68 ዓመት በላይ እንዳስቆጠረ መረጃ አለ
  • ነገሥታት፣ ታቦት በቤተ መንግሥታቸው ሥዕል ቤት የማስቀመጥ ልምድ ነበራቸው
  • ለብዙኃን መገናኛና ለሕዝብ ይፋ ለማድረግ፣ የፊታችን ጥር 8 ቀን፣ ቀጠሮ ይዟል

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ 6 ኪሎ ካምፓስ ሙዝየም ውስጥ፣ ከግማሽ ክፍለ ዘመን በላይ ያስቆጠረ ታቦት የተገኘ ሲኾን፤ ታቦቱ ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን እንደተመለሰ ታውቋል፡፡

በዩኒቨርሲቲው ግቢ ታቦት ስለመኖሩ፣ “ራእይ ታይቶኛል” የሚሉ ባሕታዊ፣ ለጠቅላይ ቤተ ክህነት ባስታወቁት መሠረት፣ ጥናት ተደርጎ መኖሩ በመረጋገጡ፤ ከዩኒቨርሲቲው ጋር ብዙ ድርድር ከተደረገ በኋላ፣ ኅዳር 10 ቀን 2009 ..፣ ታቦቱ ለጠቅላይ ቤተ ክህነት መመለሱን በጉዳዩ ተሳታፊ የነበሩት መጋቤ ምሥጢር ቡሩክ አሣመረ ለአዲስ አድማስ ተናግረዋል፡፡

ታቦቱ በዐፄ ኃይለ ሥላሴ ጥያቄ እንደተቀረፀና የቅዱስ ሚካኤል ታቦት መኾኑን የሚገልጽ ማስታወሻ ተገኝቷል፡፡ ታቦቱ ከ68 ዓመት በላይ ዕድሜ እንዳለውም ታውቋል፤” ብለዋል – መጋቤ ምሥጢር ቡሩክ፡፡

ታቦቱ በዩኒቨርሲቲው ስለመኖሩ፣ ባሕታዊ በለጠ ዘነበ የተባሉ በራእይ ታይቶኛል በሚል በተደጋጋሚ ሲናገሩ እንደነበር የጠቆሙት መጋቤ ምሥጢር ቡሩክ፤ “ቅዱስ ሚካኤል ሚዛንና ሰይፍ ይዞ በዩኒቨርሲቲው ካምፓስ አንደኛ በር በኩል እየወሰደ ያሳየኛል፤” እያሉ ይናገሩ እንደነበርና፣ ይህንንም በ2003 .. አካባቢ ለፓትርያርክ አቡነ ጳውሎስ መግለጻቸውን፤ ነገር ግን ትኩረት የሚሰጣቸው ሳያገኙ መቅረታቸውን ያስታውሳሉ፡፡

ባሕታዊው፣ በ2007 .. ይህንኑ ራእይ ለብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ አቡነ ማትያስ ማሳወቃቸውንና የሚመለከታቸው የጠቅላይ ቤተ ክህነቱ የሥራ ሓላፊዎች ጉዳዩ እንዲጠና ማዘዛቸውን መጋቤ ምሥጢር ቡሩክ አውስተው፣ በጥናቱም ጽላቱ በዩኒቨርሲቲው ውስጥ መኖሩ መረጋገጡን ገልጸዋል፡፡ ይህን ተከትሎም ታቦቱ ለቤተ ክርስቲያንዋ እንዲመለስ ከዩኒቨርስቲው ጋር በርካታ የደብዳቤ ልውወጦች ተደርገዋል፡፡

መጀመሪያ ላይ ዩኒቨርሲቲው የጥናትና ምርምር ተቋም እንደመኾኑ፣ ቅርሶችን ተከባክቦ የመያዝና ለትውልድ የማስተላለፍ ሓላፊነት እንዳለበት በመግለጽ፣ ታቦቱን ለቤተ ክርስቲያንዋ ለመመለስ በእጅጉ ተቸግሮ ነበር፤ ይላሉ መጋቤ ምሥጢር ቡሩክ፡፡ ኾኖም ጽላት ለቱሪስቶች(ለጉብኝት) ክፍት ኾኖ መታየት የሌለበት የሥርዓተ አምልኮ መፈጸሚያና መግለጫ በመኾኑ፣ በዩኒቨርሲቲው ሙዝየም ውስጥ ቢቀመጥ ትርጉም እንደሌለው ስምምነት ላይ በመደረሱ፣ የመንበረ ልዑል ቅዱስ ማርቆስ ቤተ ክርስቲያን በአደራ ተረክቦ እንዲያስቀምጥ መደረጉን ለማወቅ ተችሏል፡፡

ታቦቱ፣ አልተረስቶን በሚል ስያሜ፣ በመዝገብ ቁጥር 1761 ተመዝግቦ የተገኘ ሲኾን፣ ሚስተር ስቴፈን ራይት በተባለ ሰው፣ እ..አ ሰኔ 12 ቀን 1961 ወደ ሙዝየም መግባቱን መጋቤ ምሥጢር ይናገራሉ፡፡ ነገሥታት ታቦት አስቀርፀው በቤተ መንግሥታቸው በሚገኙ አብያተ ጸሎታት(ሥዕል ቤቶች) የማስቀመጥ ልምድ እንደነበራቸው የጠቀሱት መጋቤ ምሥጢር ቡሩክ፤ ምናልባትም ዐፄ ኃይለ ሥላሴ ይህን የቅዱስ ሚካኤል ታቦት ሳያስቀርፁት እንዳልቀረ ግምት መኖሩን አመልክተዋል፡፡ “ታቦቱ በዩኒቨርሲቲው ሙዝየም 3ኛ ምድር ቤት ለብቻው በተሠራ ቤት ውስጥ ተደብቆ ነው የተገኘው፤ የሙዝየሙ ሠራተኞች እንኳን ታቦት መኖሩን አያውቁም ነበር፤” ብለዋል መጋቤ ምሥጢሩ፡፡

ከሰኔ 12 ቀን ጀምሮ፣ ከመልአኩ ቅዱስ ሚካኤል ጋር ይገናኙ እንደነበር የገለጹት ባለራእዩ ባሕታዊ በለጠ ዘነበ፣ በተደጋጋሚ ወደ ፓትርያርኩ ጽ/ቤት እየሔዱ ቢናገሩም ትኩረት አለማግኘታቸውን ጠቅሰው፣ በኋላ የቤተ ክርስቲያኒቱ የልማትና ክርስቲያናዊ ተራድኦ ኮሚሽንና የቤተ መዛግብትና ቅርስ ክፍል ሓላፊዎች ባደረጉት ከፍተኛ ጥረት ታቦቱን ከዩኒቨርስቲው ለመረከብ መቻሉን ለአዲስ አድማስ አስረድተዋል፡፡

በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የታሪክ ምሁር የኾኑትን ፕ/ር አሕመድ ዘካርያን ስለ ጉዳዩ ጠይቀናቸው ምላሽ ለመስጠት ፈቃደኛ ሳይኾኑ ቀርተዋል – “አኹን ብዙም የምገልጸው ነገር የለም፤” በማለት፡፡

በዩኒቨርሲቲው ሙዝየም የተገኘውን የቅዱስ ሚካኤል ታቦት አስመልክቶ፣ ለብዙኃን መገናኛ እና ለሕዝብ ይፋ ለማድረግ፣ ለጥር 8 ቀን 2009 .. መርሐ ግብር መያዙን መጋቤ ምሥጢር ቡሩክ አስታውቀዋል፡፡

አኹን በ6 ኪሎ የሚገኘው የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ዋናው ግቢ፣ የግርማዊ ቀዳማዊ ንጉሠ ነገሥት ዐፄ ኃይለ ሥላሴ ገነተ ልዑል ቤተ መንግሥት የነበረ ሲኾን፣ ታቦቱን በአደራ የተረከበው የመንበረ ልዑል ቅዱስ ማርቆስ ቤተ ክርስቲያንም፣ የንጉሠ ነገሥቱና ቤተሰቦቻቸው ሥዕል ቤት(ጸሎት ቤት) ኾኖ ያገለገለ ነው፡፡ የ1953 .. መፈንቅለ መንግሥት ተከትሎ የንጉሡ ቤተ መንግሥት ወደ ኢዮቤልዩ በመዛወሩ፣ የገነተ ልዑል ቤተ መንግሥትን ለትምህርት ተቋምነት በስጦታ አበርክተዋል፤ ጸሎት ቤት የነበረው የመንበረ ልዑል ቅዱስ ማርቆስ ቤተ ክርስቲያንም ለሕዝብ አገልግሎት የሚሰጥ ኾኗል፡፡

ምንጭ

__

Posted in Curiosity, Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , | Leave a Comment »

 
%d bloggers like this: