Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • March 2023
    M T W T F S S
     12345
    6789101112
    13141516171819
    20212223242526
    2728293031  
  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

Posts Tagged ‘ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን’

የቅድስት ሥላሴ ዓመታዊ ክብረ በዓል

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on July 14, 2020

ጊዜው የሚያዘናጋ፣ የሚያዘልል፣ የሚያስፈነጭ የሚያስጨበጭብ ጊዜ አይደለም ፥ ለፀሎት የምንነቃበት ጊዜ እንጂ: ሕዝብ ሲያምጽ፣ ኃጢዓት ሲበዛ፣ ጽዋ ሲሞላ እምቢ ለሚል እግዚአብሔርን ለሚገዳደር በተናጠል ይቀጣል

[መጽሐፈ መክብብ ምዕራፍ ፫፥፩፡፰]

ለሁሉም ነገር ጊዜ አለው፤ ከሰማይ በታች ለሚከናወነው ለማንኛውም ነገር ወቅት አለው፤ ለመወለድ ጊዜ አለው፤ ለመሞትም ጊዜ አለው፤ ለመትከል ጊዜ አለው፤ ለመንቀልም ጊዜ አለው፤ ለመግደል ጊዜ አለው፤ ለማዳንም ጊዜ አለው፤ ለማፍረስ ጊዜ አለው፤ ለመገንባትም ጊዜ አለው፤ ለማልቀስ ጊዜ አለው፤ ለመሣቅም ጊዜ አለው፤ ለሐዘን ጊዜ አለው፤ ለጭፈራም ጊዜ አለው፤ ድንጋይ ለመጣል ጊዜ አለው፤ ድንጋይ ለመሰብሰብም ጊዜ አለው፤ ለመተቃቀፍ ጊዜ አለው፤ ለመለያየትም ጊዜ አለው፤ ለመፈለግ ጊዜ አለው፤ ለመተው ጊዜ አለው፤ ለማስቀመጥ ጊዜ አለው፤ አውጥቶ ለመጣልም ጊዜ አለው፤ ለመቅደድ ጊዜ አለው፤ ለመስፋትም ጊዜ አለው፤ ለዝምታ ጊዜ አለው፤ ለመናገርም ጊዜ አለው፤ ለመውደድ ጊዜ አለው፤ ለመጥላትም ጊዜ አለው፤ ለጦርነት ጊዜ አለው፤ ለሰላምም ጊዜ አለው።

የሰይፈ ሥላሴ ፀሎት ከክፉ ነገር ሁሉ ይጠብቀን!

_______________________________________

Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

የኢትዮጵያ ልጆች ሰንደቅ ዓላማችሁን በየቤታችሁ ስቀሉ

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on January 22, 2020

+_________________________________+

Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , | Leave a Comment »

የማርያም መቀነት በሐዋሳ ጥምቀት | ገዳይ አብይ እስኪ ውጣና መቀነቱን በሜንጫህ አውርደው

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on January 21, 2020

እኛ እግዚአብሔር አምላካችንን እንዲህ ስለምነወድደው ከዚህ የተነሳ ሰይጣን በቅናት፣ በጥላቻ እና በእብደት ይሞላል። ዲያብሎስ ሁሉም እግዚአብሔርን የሚወዱትንና የሚያገለግሉትን ፍጥረታት መግደል እና ማጥፋት ይፈልጋል።

ያው እንግዲህ ዲያብሎስ በሸቀ፣ አበደ፣ ቅጥል አለ። ዲያብሎስ ሰይጣን ወደ እኛ የማለፍ ፈቃድ ካገኘ ይሰርቃል፣ ይገድላል እንዲሁም ያጠፋል። መስረቅ፣ መግደል እና ማጥፋት የእርሱ የደመ ነፍስ ስራዎች ናቸውና እግዚአብሔርን የሚወዱትን ለመግደል ወደ ሐረርና ድሬዳዋ አመራ።

_________________________________

Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

ቅድስት ሥላሴ ኢትዮጵያን እና ኢትዮጵያውያንን ይባርኩ

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on January 16, 2020

እንኳን ለአግዓዚተ ዓለም ቅድስት ሥላሴ ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሰንየአብርሃሙ ሥላሴ ሀገራችንን ኢትዮጵያን ይጠብቅልን። ሕዝባችንንም በሰላም በፍቅር በአንድነት ያኑርልን

ወደ መጨረሻ ላይ ያለውን መልዕክት እናዳምጥና እራሳችንን እንጠይቅ፤ “እንደው በዚህች ዓለም ላይ እንደ ኢትዮጵያ ተዋሕዶ ክርስቲያኖች ወደ ቤተክርስቲያን አዘውትሮ የሚሄድ፣ በጾምና በጸሎት የሚተገባ ሕዝብ ይኖራልን? እኔ መመስከር እችላለሁ፤ የለም! የትም ሃገር የለም። ሃጢአተኞች ሁላችንም ሃጢአተኞች ነን፤ ነገር ግን ቤተክርስቲያን እየተቃጠለ ያለው እኛ ከዓለም ሁሉ የከፋ ሃጢአት ሰርተን ሳይሆን ክርስቲያን ወገናችንን እና ቤተክርስቲያናቱን ለመከላከል ዝግጁ ባለመሆናቻን፣ የእኛና የአምላካችን ጠላት ከሆኑት አህዛብ ጋር በመደባለቃችን፣ የሃገር ጠላት ከሆነው መንግስት ጋር በመደመራችን ብሎም እንደ ቀደሙት አባቶቻችን መንግስትን በቁጣ ለመገሰጽና ለማስጠንቀቅ ባለመድፈራችንና በራድ ወይ ትኩስ ስላልሆንን ነው። ስለዚህ መንግስትን ለመቃወም “ሰልፍ አትውጡ፡ እኛ እንደራደራለን!” ቅብርጥሴ የሚለው መልዕክት የትም አያደርሰንም። እንዲያውም የተዋሕዶ አርበኞች በቁጣ ወደ አራት ኪሎ ቤተመንግስት አምርተው ባለሥልጣናቱ ሁሉ እንዲወገዱ መጮኽና አጥሩን መነቅነቅ ይኖርባቸዋል። ለሁሉም ጊዜ አለው፤

ከወዳጆችህ ጋር ብቻ ሳይሆን ከጠላቶችህም ጋር እንኳ ሳይቀር በሰላም ኑር፤ ነገር ግን እንዲህ የምልህ ካንተ ከግል ጠላቶችህ ጋር እንጂ ከእግዚአብሔርና ከቤተ ክርስቲያን ጠላቶች ጋር አይደለም፡፡አንድ ገዳማዊ አባት

ሰውን ከእግዚአብሔር ከሚለየው አጉል ሰላም ይልቅ ከእግዚአብሔር የማይለየው ጦርነት ይሻላል፤ ስሜታዊ ከሆነና ለቤተ ክርስቲያን ዘለቄታዊ ጉዳት ከሚኖረው ስምምነትና አንድነት ይልቅ ስለ ሐይማኖት መጠበቅ ዘለቄታዊ ጠቀሜታ የሚኖረውና ለዚህ ሲባል የሚሆን አለመስማማት ይሻላል፡፡ቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘኑሲስ

በዚህ የጥምቀት በዓል ከአባቶች የምጠብቀው መልዕክት፦

ሴት ልጆቼ በደምቢዶሎ ጫካ ውስጥ የጥምቀት በዓልን እንዲያሳልፉ አልሻም፤ ስለዚህ ጠቅላይ ሚንስትር አብይ በቃህ፡ ስልጣኑን አስረክብና በሥላሴ ስም ተጠመቅ!”

የሚለውን መልዕክት ነው።

እስኪ እናስበው፤ አቡነ ማትያስ ይህን ቢናገሩ፤ ምንም ጥርጥር የለኝም ብዙ እንቅስቃሴ ሊታይ ይችል ነበር።

የቤተክርስቲያን አገልጋዮች፡ በቃን! ስሜታዊ አትሁኑ!” እያላችሁ ሰውን አታስተኙት፤ ወኔውን አትንጠቁት! እንዲያውም “ምርጫ” የተባለው ነገር የሚካሄድ ከሆነ በመጭዎቹ ሳምንታት ምእመናኑን ለእነ አብዮት አህመድ፣ ለእነ ብርሃኑና ስብሐት ነጋ፣ እንዲሁም ለሌሎቹ አቋምየለሽ ልክስክስ ፓርቲዎች በጭራሽ ድምጽ እንዳይሰጡ ማስጠንቀቅ፤ በተቃራኒው ደግሞ ለእስክንድር ነጋ ድጋፋቸውን እንዲሰጡ ግልጽ የሆነ ቅስቀሳ ማካሄድ አለባቸው።

ሜዲያው ሁሉ በኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያዊነት ላይ አሉታዊ በሆነ መልክ 24 ሰዓት ቅስቀሳ በሚያደርጉባት ሃገራችን ለሕዝበ ክርስቲያኑ በጣም አመች የሆነው የቅስቀሳ እና የትምህርት መድረክ በቤተክርስቲያን ነው የሚገኘው።

_________________________________

Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

ሕዝብ ሲያምጽ፣ ኃጢዓት ሲበዛ፣ ጽዋ ሲሞላ እምቢ ለሚል እግዚአብሔርን ለሚገዳደር በተናጠል ይቀጣል

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on November 17, 2019

[መጽሐፈ መክብብ ምዕራፍ ፫፥፩፡፰]

ለሁሉም ነገር ጊዜ አለው፤ ከሰማይ በታች ለሚከናወነው ለማንኛውም ነገር ወቅት አለው፤ ለመወለድ ጊዜ አለው፤ ለመሞትም ጊዜ አለው፤ ለመትከል ጊዜ አለው፤ ለመንቀልም ጊዜ አለው፤ ለመግደል ጊዜ አለው፤ ለማዳንም ጊዜ አለው፤ ለማፍረስ ጊዜ አለው፤ ለመገንባትም ጊዜ አለው፤ ለማልቀስ ጊዜ አለው፤ ለመሣቅም ጊዜ አለው፤ ለሐዘን ጊዜ አለው፤ ለጭፈራም ጊዜ አለው፤ ድንጋይ ለመጣል ጊዜ አለው፤ ድንጋይ ለመሰብሰብም ጊዜ አለው፤ ለመተቃቀፍ ጊዜ አለው፤ ለመለያየትም ጊዜ አለው፤ ለመፈለግ ጊዜ አለው፤ ለመተው ጊዜ አለው፤ ለማስቀመጥ ጊዜ አለው፤ አውጥቶ ለመጣልም ጊዜ አለው፤ ለመቅደድ ጊዜ አለው፤ ለመስፋትም ጊዜ አለው፤ ለዝምታ ጊዜ አለው፤ ለመናገርም ጊዜ አለው፤ ለመውደድ ጊዜ አለው፤ ለመጥላትም ጊዜ አለው፤ ለጦርነት ጊዜ አለው፤ ለሰላምም ጊዜ አለው።

የሰይፈ ሥላሴ ፀሎት ከክፉ ነገር ይጠብቀን!

___________________________

Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

አቤቱ ወደ አንተ መልሰን ፥ እኛም ወዳንተ እንመለሳለን ፥ ዘመናችንን እንደ ቀድሞው አድስልን

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on October 20, 2019

________________________

Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , | Leave a Comment »

የበገና ዜማ በ ቅዱስ በዓለ ወልድ ቤ/ ክርስቲያን

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on April 7, 2019

እንኳን አደረሰን!

የመንበረ ጸባዖት ቅዱስ በዓለ ወልድ ቤተ ክርስቲያን በ፲፰፹፫ / 1883 .ም በዳግማዊ አፄ ምኒልክ ዘመነ መንግሥት የተመሠረተ ሲሆን ቤተ ክርስቲያኑ የ፻፳፰/ 128 ዓመት ዕድሜ ባለቤት ነው።

የቅዱስ በዓለወልድ /መካነ ሥላሴ/ ቤተ ክርስቲያን የተመሠረተው በ፲፰፹፫ / 1883 .ም በዳግማዊ አፄ ምኒልክ አማካይነት ሲሆን ለምሥረታው የተነሳሱበትም ዋናው ምክንያት አንድ ባሕታዊ መነኩሴ ከቤተ መንግሥትዎ በስተቀኝ ባለው ከፍታ ቦታ ላይ ሦስት ነጫጭ ርግቦች መጥተው ሲያርፉ በራዕይ አይቻለሁና (መካነ ሥላሴ) የሚል ጽሕፈት ያለበት ጽላት አስፈልገው በማምጣት እንዲተክሉ እግዚአብሔር አዟልና እንዲተከል ይሁን።ስለተባሉ በዚሁ መነሻነት መካነ ሥላሴ የሚል ጽሕፈት ያለበት ጽላት ሲያስፈልጉ ቆይተው ከአዲስ ዓለም በላይ ፉየታ ከሚባለው ቦታ እንዳለ በጥቆማ ስለደረሱበት ለቦታው ሌላ ጽላት ተፈልጎለት በንጉሡ ትእዛዝ በአለቃ ወልደ ያሬድ ኤላሪዮን አስመጭነት በወቅቱ የኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳሳት በነበሩት በግብፃዊው ሊቀ ጳጳስ አቡነ ማቴዎስ እጅ ከተረከቡ በኋላ ዳግማዊ አፄ ምኒሊክ ንጉሠ ሸዋ በተባሉ በ25ኛው ዓመት የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት ሆነው በነገሡ በአንደኛው ዓመት ታህሣሥ ፳፪ / 22 ቀን ፲፰፹፫ / 1883 /ም የአዛዥ ዘአማኑኤል እልፍኝ ተባርኮ በዚሁ ቅዱስ ሥፍራ በመቃኞ /በመቃረቢያ/ ቆይቶ ይህ አሁን ለዕድሳት የበቃው ሕንፃ ቤተ ክርስቲያን ለ12 ዓመታት በግንባታ ላይ ከቆየ በኋላ በ ፲፰፺፭ / 1895 /ም በመጠናቀቁ መስከረም ፯ / 7 ቀን ፲፰፺፭ / 1895 /ም ታቦተ ሕጉ ከነበረበት መቃረቢያ ወጥቶ በዓለ ንግሥ ተደርጎለት አዲስ ወደ ታነፀው ሕንፃ ቤተ ክርስቲያን ገብቷል

በዚሁ አጋጣሚ ሳይጠቀስ የማይታለፈው ዐቢይ ጉዳይ ደግሞ ቀደም ሲል ጽላቱ ከግራኝ መሐመድ ወረራ በፊት ወረኢሉ ደሴ የነበረ ሲሆን በግራኝ ወረራ ምክንያት ካህናቱ አሽሽተው ወግዳ ወስደው አኑረው ለብዙ ዘመናት ከቆየ በኋላ የራስ ጎበና ባለቤት ወ/ሮ አየለች ከወሎ ወግዳ አስመጥተው አዲስ ዓለም በላይ ፉየታ ከተባለው ቦታ ላይ አስተክለው እንደነበርና ታሪኩ እንደሚያስረዳው በአፄ ምኒልክ ትዕዛዝ ወደ አዲስ አበባ መጥቶ በዚሁ ቦታ ላይ የተተከለ ሲሆን መካነ ሥላሴ የሚለው የደብሩ ስያሜም የተሰጠው ከጽላቱ ላይ ከተገኘው ጽሕፈት በመነሳት እንደሆነ ከታሪኩ ለመረዳት ተችሏል።

የድንግል እናታችን ልጅ ስሞቹ ፦ ቃል ወልድ አማኑኤል ኢየሱስ ክርስቶስ መድኃኔ አለም ሆኑ ትርጓመያቸውም፦

#ቃል ማለት፦ አንደቤት መናገርያ ማለት ስሆን ከ3ቱ አካላት አንዱ እግዚአብሔር #ወልድ በህልውነት/በመሆን ግብሩ የ #አብ እና የ #መንፈስ ቅዱስ ቃላቸው ስሆን የእግዚአብሔር ቃል ይባላል። ራእይ 1913 “በደም የታለሰ ልብስም ለብሶአል ስሙንም ቃል እግዚአብሔርአሉት። ቍላስ.116 “በእርሱ ቃልነት እግዚአብሔር ሁሉን ፈጥሮአልና….”

#ወልድ ማለት፦ ከ3ቱ አካላት ፩(1)ዱ ወልድ ስሆን ልጅ ማለት ነው የ #ወልድ አካላዊ ግብሩ መወለድ ማለት ነው የ #አብ የባሕርይ ልጅ ስለሆነ እግዚአብሔር ወልድ ይባላል። ገላ.44,, ዮሐ.516,, ማቴ 317…

#አማኑኤል ማለት፦ እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ሆነ ማለት ነው። ማቴ 123። ይህን በት.ኢሳ 714 ላይ ስሙን እናገኛለን። ይህ ማለት ከድንግል በተዋህደው ተዋህዶ አምላክ ሰው ሆነ ዮሐ.114 …….. 1ኛ ቆሮ 1521 አዳምን የመጀመርያው ሰው ይላል ክርስቶስን ደግሞ ሁለተኛው ሰው ይለዋል።

#ኢየሱስ ማለት፦ መድሃኒት ማለት ነው ይህን መጽሐፍ ቅዱስም ይናገራል ሉቃስ 211 “እነሆ ዛሬ በዳዊት ከተማ መድኃኒት ተወልዶላችኃልእንዳለ መልአኩ ለእረኞች….

#ክርስቶስ ማለት፦ ቅቡ /የተቀባማለት ነው። በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስትያን እና በመሰሎቿ አብያተ ቤተክርስትያናት የተዋሃደተብሎ ይተረጉማል።

#መድኃኒአለም ማለት፦ የአለም መድኃኑት ማለት ነው። በእርሱ አለም ስለዳነ (በሞቱ አለምን ስላዳነ) መድኃኒአለም የአለም መድሃኒት እንለዋለን። ሉቃስ 211 ላይ እኔሆ ለሕዝብ ሁሉ የምሆን መድኃኒት እንዳላለ ሉቃስ፤ ዮሐ.129 ላይ መጥምቁ ዮሐንስ እነሆ የአለምን ኃጢአት የምያስወግድ የእግዚአብሔር በግእንዳለው እንደገና በሮሜ 512-21 ስናነብ በአንድ ሰው በአዳም ምክንያት ሞት ወደ አለም እንደመጣ ሁሉ በአንዱ በኢየሱስ ክርስቶስ ሞትም አለም እንደዳነ ይናገራል…………..እኛ ኦርቶዶክሳዊያን በነዚህ ስሞች አምላካችን ጌታችንና መድኃኒታችንን እናከብረዋለን እንጠራዋለን እናመልከዋለን ። ኢየሱስ ብቻ ስሙ ነው ሌሎችን ከየት አመጣችሁ ለምን ባለወልድ አማኑኤል መድሃኒአለም እያላቹ ትጠሩታላችሁ ኢየሱስ ማለት ብቻ እንጅየምሉ ወገኖቻችን አሉና እነዚህን ስሞችን እኛ ኦርቶዶክሶች ፈጥረንለት ሳይሆን መጽሐፍ ቅዱሱ እራሱ እንደምጠራው መገናዘብ ይገባናል።

ለስም አጠራሩ ክብርና ምስጋና ይድረሰው የእኛ ጌታ የድንግል ማርያም ልጅ ጌታችን መድኅኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ። ክብር ለወለደችው ለድንግል!!!

_________

Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

አቡነ አረጋዊ | እንጀራ ሻጩ ወጣት ቤተክርስቲያኗን በአረንጓዴ፣ ቢጫና ቀይ እንዲቀባ በራዕይ ታዘዘ

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on November 24, 2018

ትዕዛዙንም በሥራ ላይ አዋለው። ይህችን ውብ ቤተክርስቲያን በቀለሞቻችን እንዲቀባት ራዕይ የታየው ወንድማችን እንጀራ ጋግሮ በመሸጥ የሚተዳደር ወጣት ነው። ቤተክርስቲያኗን እና አካባቢዋን ከቀባ በኋላ በዚሁ በሳሪስ አቦ ኮረብታ ላይ በ አዲስ መልክ ለሚሰራው ለ አቡነ አረጋዊ ቤተከርስቲያን ህንፃ የግንብ አጥር በመገንባት ላይ ይገኛል።

በእውነት የእግዚአብሔር ሥራ ድንቅ ነው!

____________

Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , | Leave a Comment »

 
%d bloggers like this: