Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • June 2023
    M T W T F S S
     1234
    567891011
    12131415161718
    19202122232425
    2627282930  
  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

Posts Tagged ‘ኢትዮጵያዊ’

ፍራንክፈርት | አንድ ዘረኛ ጀርመን ከመኪና ወርዶ በኢትዮጵያዊው ላይ ሽጉጡን ተኮሰበት

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on July 23, 2019

ፍራንክፈርት ከተማ አቅራቢያ በምትገኘው ቬችተርስባህ መንደር አምሳ አምስት አመት የሞላው ጀርመናዊ መኪናውን አቁሞ መንገድ ላይ ወዳየው የሃያ ስድስት ዓመቱ ኢትዮጵያዊ (ኤርትራ) በማምራት ሽጉጡን አውጥቶ በመተኮስ ከፉኛ አቆሰለው። ኢትዮጵያዊው ወዲያው ወደ ሆስፒታል ተወስዶ ከሞት ሊተርፍ ችሏል (እንኳን አዳነው!)። ከድርጊቱ በኋላ ተኳሹ ጀርመናዊ እርሱን በራሱ ሽጉጥ ገድሏል። የድርጊቱ መንስዔ ዘረኝነት እንደሆነ እና ጀርመናዊውም እራሱን ከማጥፋቱ በፊት በመጀመሪያ ቆዳው ጠቆር ያለ ሰው መንገድ ላይ ፈልጎ በማግኘት ለመግደል አቅዶ እነደነበር መርማሪዎች ካገኙት የሰውየው ጽሑፍ ለመረዳት እንደበቁ ገልጸዋል።

ግን አየን፤ በጀርመን ሃገር አንድ ሰው መንገድ ላይ ሲገደል ፖሊስም ሜዲያውም ለጉዳዩ ትልቅ ቦታ ይሰጠዋል። ስለዚህ ጉዳይ ሁሉም ብሔራዊ ሜዲያዎች ሪፖርት አቅርበዋል። ለምሳሌ እዚህ በአሜሪካ ሰው በየመንገዱ መግደል የተለመደ ስለሆነ ብዙ ባይወራ አይገርመንም፤ እሁድ ዕለት ዋሽንግተን ከተማ በሚገኝ አንድ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ጥቁር አሜሪካውያን ገብተው በምዕመናኑ ላይ ተኩስ እንደከፈቱባቸው ሰምተናል፤ ጉዳዩ ግን ብዙ ትኩረት አልተሰጠውም።

ወደ ሃገራችን ስንመለስ በሲዳማ ክፍለ ሃገር በተዋሕዶ ልጆች ላይ የተካሄደው ጂሃዳዊ ዘርተኮር ጭፍጨፋ እስካሁን የመንግስትን፣ የገዳይ አልአብይን፣ የሜዲያውን እንዲሁም የቤተ ክህነትን አትኩሮት ሊያገኝ አልቻለም። ሁሉም እስካሁን ጭጭ ብለዋልለምን? ወገን እያለቀ ተረጋጉ!?„

ጀርመኖች አብዛኞች አሁንም በብዙ ነገሮች ጥሩ ሰዎች ናቸው፤ ነገር ግን፤ ለመለወጥ ትንሽ ነገር ነው የሚበቃቸው ስለዚህ ሁኔታዎች፡ ቀስበቀስ እየተቀየሩ ነው። ለዚህም ብዙ ምኪኒያቶች አሉ፤ እርግማን ለሜርከል ይድረስና፡ በቅድሚያ ተጠያቂው ሥልጣኑን የያዘው እርጉሙ ኢስታብሊሽመንት/ አመራሩ ነው።

እግዚአብሔርን እየከዳ የመጣው የምዕራቡ አለም እራሱ በፈጠረው ችግር ከባድ ሁኔታ ላይ ወድቋል። ጀርመን ስንል አንድ የሆነች ጀርመን የለችም የተክፋፈለች እንጅ፣ ብሪታኒያ ስንል አንድ የሆነች ብሪታኒያ የለችም የተከፋፈለች እንጅ፣ አሜሪካ ስንል ፥ አንድ የሆነች አሜሪካ የለችም የተከፋፈለች እንጅ። እነዚህ በጎሳ አንድነን የሚሉ ሃገራት እኛን ከፋፈለው ለመግዛት ሲታገሉ እነርሱ እራሳቸው ተከፋፈልው በመውደቅ ላይ ናቸው። ይህን አንድ ወጥ በሆነው የሶማሊያ ሕዝብ ዘንድም አይተነዋል።

የኢሉሚናቲዎቹ ገረድ አንጌላ ሜርከል ከ አራት ዓመታት በፊት መስከረም ወር ላይ በሚሊየን የሚቆጠሩ በጥባጭ መሀመዳውያንን ወደ ጀርመን ጋብዛ ስታመጣቸው በሃገሪቱ ህውከት እና ሽብር ለመፍጠር፣ ሕብረተሰቡን አስቆጥቶ በውጭ ዝርያ ባላቸው ነዋሪዎች ላይ ለማነሳሳት ታስቦ እንደሆነ በጊዜው ጠቁመን ነበር። በተለይ ቆዳቸው ጠቆር ያለ ነዋሪዎች በቅድሚያ ጥቃት እንደሚፈጸምባቸው ግልጽ ነበር። ያው አሁን እያየነው ነው፤ ገና መጀመሩ ነው።

በጣም የሚያሳዝነው፤ እነዚህ ሉሲፈራውያን በሃገሮቻችን የሃገራችንን አየር እየሳብን፣ ፀሐይዋን እየሞቅን፣ ጤናማ የሆኑትን ምግቦች እየተመገብን፣ በየአብያተ ክርስትያናቱ እየተሳለምንና በፀበል እየተጠመቀን ከሕዝባችን ጋር በሰላም መኖር እንዳንችል ሃገር ወዳድ የሆኑትን መሪዎቻችን በመበከልና በመግደል እነርሱ የሚፈልጓቸውን መሪዎች መረጥው ሥልጣን ላይ በማስቀመጥ እንዲህ በስደት ጠፍተን እንድንቀር ይገፋፉናል። ያሳዝናል!

__________________

Posted in Ethiopia, Infos | Tagged: , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

መታየት ያለበት | የመካን ካዕባ ጥቁር ድንጋይ የሚያፈራርሰው በአላህ የተጠላውና ቀጫጫ እግር ያለው ኢትዮጵያዊ ነው

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on February 25, 2019

ይህን የተነበየው የኢስልምና ነብይ መሀመድ ነው

[የዮሐንስ ራዕይ ፲፮÷፲፫፡፲፮]

ከዘንዶው አፍና ከአውሬው አፍ ከሀሰተኛው ነብይ አፍ ጓጉንቸር የሚመስሉ ሶስት እርኩሳን መናፍስት ሲወጡ አየሁ ምልክት እያደረጉ የአጋንንት መናፍስት ናቸው።

ተከታዩ ክፍል አስተያየት ከሰጠን ከአንድ ወንድማችን የተወሰደ ነው። መልካም ንባብ፦

ራዕ ፲፮÷፲፫፡፲፮ ከዘንዶው አፍና ከአውሬው አፍ ከሀሰተኛው ነብይ አፍ ጓጉንቸር የሚመስሉ ሶስት እርኩሳን መናፍስት ሲወጡ አየሁ ምልክት እያደረጉ የአጋንንት መናፍስት ናቸው ። በታላቁም ሀሉን በሚገዛ በእግዚአብሔር ቀን ወደ ሚሆነው ጦር እንዲያስከትቷቸው ወደ ዓለም ሁሉ ነገስታት ይወጣሉ ። እነሆ እንደ ሌባ ሁኘ እመጣለሁ ራቁቱን እንዳይሄደና እፍረቱን እንዳያዩ ነቅቶ ልብሱን የሚጠብቅ ብፁእ ነው ። በዕብራይስጥ አርማጌዶን ወደ ሚባል ስፍራ አስከተቱአቸው ።

ጌዶን ማለት መሰብሰቢያ መከማቻ መዲና ማለት ነው።እስራኤሎች ከግብፅ አርነት ነፃ ሆነው በባህር መካከል ወጥተው የሰፈሩበት ቦታ ሜጌዶል ይባላል ። ይህ መሰብሰቢያ ሰፈር ማለት ነው ።

ማጌዶሎ ( ዘፍ 14፲፬÷፩፡፫) ሰልፍ አደረጉ እነዚህ ሁሉ በሲዲም ሸለቆ ተሰብስበው ተባበሩ ይኸው የጨው ባህር ነው . . .ኤር ፵፬÷፩ በግብፅ ምድር በሚግዶል.. .ኤር ፵፬÷፲፬ በሚግዶል. . . ሰይፍ በዙሪያህ ያለውን በልቶታልና ተነስ ተዘጋጅም በሉ ) ኢየሱ የእስራኤል ልጆች ለጦርነት ያሳለፈበት ቦታ ጌዶን ብሎ ጠራው።በሰማርያና በናዝሬት መካከል በየጊዜው ደም የሚፈስበት ቦታ መጊዶ ይባላል ።

፩ኛ ነገ ፳፪÷፲፱ ሚኪያሰም እንግዲህ የእግዚአብሔር ቃል ስማ እግዚአብሔር በዙፋኑ ተቀምጦ የሰማይ ሰራዊት ሁሉ በቀኝ እና በግራ ቆመው አየሁ ። እግዚአብሔርም በሬማት ዘገለዓድ ይወድቅ ዘንድ አካአብን የሚያሳስት ማን ነው ? አለ ። አንዱ እንዲህ ያለነገር ሌላውም እንዲያ ያለ ነገር ተናጋረ ። መንፈስ ወጣ በእግዚአብሔር ፊት ቆሞ እኔ አሳስተዋለሁ አለ ። እግዚአብሔር በምን? አለው። እርሱም ወጥቸ በነብያቶች ሁሉ አፍ የሀሰት መንፈስ እሆናለሁ አለ ። እግዚአብሔርም ማሳሳትስ ታሳስተዋለህ ይሆንልሀልም ውጣ እንዲህም አድርግ አለ ። አሁንም እነሆ እግዚአብሔር በእነዚህ በነቢያትህ ሁሉ አፍ ሀሰተኛ መንፈስ አድርጓል እግዚአብሔርም በላይህ ክፉ ተናግሮብሀል ።

አርማጌዶን= አረብ + መካ +ጌዶን =አረብ መሰሰብሰቢያ መካ መዲና ሳውዲ አረቢያ ሀሰተኛው ነብይና አርማጌዶን [ራዕ ፲፮÷፲፫፡፲፮]

አርማጌዶን የጥፋት እርኩሰት መናፍስት የተቆጣጠራቸው የሚሰሰበሰቡበት ስፍራ ፣የሀሰት አባት፣ በሆነው በቀድሞ ስሙ ሣጥናኤል በአሁኑ ስሙ ዲያብሎስ=ወራዳ=ዉዳቂ በተባለው ነው ። ለዚህ ለስሙ ሲል ለውርደቱ ለውድቀቱ ሲል የሰው ዘር አባት አዳምን ለመግደል ከሰማይ የወረወረው ጥቁር ድንጋይ ይገኝበታል ። ለዚህ ጥቁር ድንጋይ ወደ ወደቀበት እንዲሰግዱ እንዲዘይሩ በሀሰተኛው ነብይ ላይ አድሮ ያናገረውን እስካሁን እየፈፀመ ነው ። እግዚአብሔር እስከወሰነለት ድረስ ይከናወንለታል ። አስተውሉ ዲያብሎስ አዳም የዲያብሎስ ባሪያ ነው ። ሄዋን የዲያብሎስ ባሪያ ናት ብሎ ያስፈረመበት ሁለት ድንጋዮች አንዱን በዮርዳኖስ ሌላውን በሲኦል አኖረው ። ጌታ አምላክ ኢየሱስ ክርስቶስ አንዱን በዮርዳኖስ ሲጠመቅ አቀለጠው።ሌላውን በአፀደ ነፋስ ሲኦል ወርዶ ደመሰለው ።

ዲያብሎስን ምርኮውን ለቀቀ ተቀጠቀጠ ። ሲኦል ተበረበረች ባዶዋን ቀረች ። ወደ ሶስተኛው ጥቁር ድንጋይ ተዙሮ ዛሬም እስማኤላውያን ይሰግዳሉ ÷ይሰበሰባሉ ÷ ይከማቻሉ ።

፩ኛ ዮሀ፬÷.ወዳጆቸ ሆይ መንፈስን ሁሉ አትመኑ ነገር ግን መናፍስት ከእግዚአብሔር ሆነው እንደ ሆነ መርምሩ ፤ ብዙወች ሀሰተኛ ነብያት ወደ ዓለም ወጥተዋልና ።

ኤር፮÷፲፮ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል መንገድ ቁም ተመልከቱትም የቀደመችዋን መንገድ ጠይቁ መልካሚቱም መንገድ ወዴት እንደሆነች እወቁ በእርሷም ላይ ሂዱ ለነፍሳችሁ እረፍት ታገኛላችሁ እነርሱግን አንሄዱባትም አሉ ።

የአዳም ፣ የሂኖክ ፣ የአብርሀም ፣ የይሳቅ ፣የያዕቆብ ፣ የነብያት የሀዋርያት ፣ የሰማዕታት ፣ የፃድቀን የአበው ሀይይማኖት ። ልብስ የተባለች ተዋህዶ ኦርቶዶክስ ሀይማኖት ናት ። ORTHO +DOX= የመጀመሪያ የበፊት ቀጥተኛ + እምነት መንገድ

ተዋህዶ ሀይማኖታችሁን ጠብቁ!!!

በቪዲዮው ላይ ከተላኩት ግሩም የተመልካች አስተያየቱች መካከል፦

  • የተባረኩ ኢትዮጵያውያን!”
  • በምድር ላይ ትልቁን ጣዖት ለማጥፋት ኢትዮጵያውያን ጎን እሰለፋለሁ”
  • መቼስ ያ ጥቁር ሰውዬ ጀግናዬ ነው የሚሆነው”
  • አንድ ሰይጣንን የሚመስል ጥቁር ሰው ጥቁሩን ድንጋይ ያፈርሰዋል”
  • ይፈለጋል፦ ቀጫጫ እግር ያለው ጥቁር ሰው ከኢትዮጵያ!”
  • ሀይሌ ገብረ ሥላሴን እና የኢትዮጵያ አትሌቶች ሠራዊትን ልብ በል
  • እኔ ከኢትዮጵያ ነኝ ቀጫጫ እግር ነው ያለኝ፤ ምናልባት እኔ የተመረጥኩ እሆን?”
  • ለኢትዮጵያ መዋጮና ድጎማ ማድረግ አለበን!”
  • መሀመድ ጠላቶቹ የሆኑትን ክርስቶስ ተከታዮችን እና ጥቁሮችን ለመግደል እስልምናን መሠረተ
  • ይህን ቪዲዮ ከተመለከትኩ በኋላ ለጥቁር ህዝቦች ትልቅ አክብሮት ሰጠሁ”
  • ባካችሁ ይህን ቀጭን እግር ያለውን ጥቁር ሰው ኢትዮጵያ ሄደን እንፈልገው
  • ጥቁር ሰው ካዕባን ያጠፋል ትምህርት ደግሞ እስልምናን ያጠፋል
  • ይህን ጉድ የሚያውቅ አንድ ጥቁር ሰው እንዴት እስላም ይሆናል?”
  • ኢትዮጵያ ጥንታዊት የክርስትና አገር ናት
  • ኢትዮጵያ? የቃል ኪዳኑ ታቦትም እዚያ ነው የሚገኘው፤ በአጋጣሚ?”
  • ምናለ ቀጭን እግር ያለው ኢትዮጵያዊ ብሆን”
  • በቅርቡ ኢትዮጵያን እጎበኛለሁ”
  • መሀመድ አንድ ቀን እውነቱ እንደሚወጣ አውቋል፤ እኔ ቀጭን እግር ካለው ኢትዮጵያዊው ጋር አብሬው ነኝ
  • በተግባር ላይ የሚውል የመሀመድ ብቸኛ ትንቢት”
  • ኢትዮጵያዊ ጓደኛይህን ሰምቶ መሳቁን ቆም በኋላእንሂድ፤ እናድርገው!” ለኝ”
  • ከሳምንታት በፊት በረሮና አንበጣ በካዕባው ድንጋይ ላይ ጥቃት ስነዝረው ነበር”
  • ካዕባን የሚያጠፋው ኢትዮጵያዊ ምን ያህል የታደለ ቢሆን ነው!”
  • ኢትዮጵያዊያን ህይወት በጣም ጠቃሚ ናት!!!”
  • ለኢትዮጵያውያን እርዳታ መስጠት አለብን”
  • ካዕባ የሰይጣን ምሽግ ነው
  • አንድ ቀን ከኢትዮጵያ የመጣ አንድ ጦረኛ ካዕባን ያጠፋል፤ ዓለማችንም እርሱን በጉጉት እየጠበቀ ነው
  • ታዲያ አሁን ሳውዲ አረቢያ ቀጭን እግር ያለውን ኢትዮጵያዊ አታስገባም ማለት ነው”
  • ባራክ ኦባማ ጥሩ እድል አመለጠው”
  • ለኢትዮጵያውያን የከበረ ሰላምታ
  • ካዕባ የሰይጣን ቤት ነው
  • ካዕባ በአለም ዙሪያ የሽብርተኝነት ሁሉ ማዕከል ነው ካዕባው ከጠፋ የሽብርተኝነት ሥራ እና እብሪት በሙሉ ይጠፋል፤ እግዚአብሔር ሆይ፡ ቀጭን እግር ያለውን ኢትዮጵያዊ ቶሎ ላክልን”
  • በጣም የሚገርመኝ ነገር ኢትዮጵያውያን ጥንቱ ኢስላማዊ ህብረተሰብ እርዳታ አደረጉ፤
  • ከዚያ በኋላ የሙስሊሞች ቁጥር ከፍ ሲል ኢትዮጵያውያንን በጂሃድ ለመግደል ተመለሱ። በእርግጥ ኢትዮጵያውያ በተደጋጋሚ ጊዜያት የደረሰባን ጥቃት መክታለች፤ ለዚህም ነው እስካሁን ድረስ ኢትዮጵያ በዋነኛነት የክርስትያን ሃገር ሆና የቆየችው።”

_________

Posted in Curiosity, Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

መታወቅ ያለበት ስለ እስልምና ሊቆች | “ጥቁሮች ከእንስሶች አይበልጡም”፣ “ጥቁር ሴት ወረርሽኝ ታመጣለች”

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on June 28, 2018

ጥቁር ቀለም ከሰይጣን ነው | መሀመድ ስለውሻ፦

ውሾች ከፍጥረታት መኻል ባይሆኑ ኖሮ ሁሉም እንዲገደሉ አዝ ነበር፤ ጥቁር ውሾችን ግን ሁሉንም አሁኑኑ ግደሏቸው፤ ጥቁር ውሾች ሰይጣኖች ናቸውና”

! ! የሚያሰኝ ነገር ነው፤ ብዙዎቻችን ይህን እስካሁን አልሰማንም፤ ዲያብሎስ ሥራውን እንዳናውቅበት ዓይናችንን ጋርዶብናል፣ ጆሮአችንን ደፍኖብናልና! ግን እውነት አትደበቅም፣ አትሸነፍም፤ ፈጠነችም ዘገየችም መውጣቷ አይቀርም።

በተለይ የአፍሪቃ ትምህርት ቤቶችና ዩኒቨርሲዎች ይህን ጉድ በማጋላጥ ለተማሪዎቻቸው በትምህርት መልክ ማሳወቅ አለባቸው።

እንግዲህ እራሱ መሀመድን ጨምሮ፡ ይህን የሚናገሩት እነዚህ ሰዎች፡ በእስልምና ታሪክ አሉ የሚባሉትና በሙስሊሞች ዘንድ በጣም የሚከበሩት “ሊቃውንትና መምህራን” ናቸው። እንግዲህ እነዚህ ናቸው ታላላቅ የሚባሉት የእስልምና ሊቆች! ታዲያ አምላክ እውነት በእነዚህ ሰዎች በኩል ሊናገር ይችላልን? በጭራሽ!

እስኪ ሁላችንም ይህን ደጋግመን እንጠይቅ፦

ስለዚህ ትልቅ ቅሌት የሚያውቅ አንድ ጥቁር ወይም አንድ ኢትዮጵያዊ እንዴት እስላም ሊሆን ይችላል?

______

Posted in Curiosity, Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

ኢትዮጵያ የምዕራባውያን ቆሻሻ ማራገፊያ መሆን የለባትም

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on August 5, 2014

EthioChild

(ሪፖርተር ጋዜጣ – ከተቆርቋሪ ዜጋ)

ምንም እንኳን በሚዲያዎች በግልጽ ባይነገርም በአዲስ አበባ የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን አዳራሽ ከመስከረም 20 እስከ 25 ቀን 2006 .ም የተደረገ ስብሰባ ነበር፡፡ ይህም የዓለም አቀፍ የሥነ ሕዝብና የዕድገት ኮንፈረንስ (አይሲፒዲ) ከፍተኛ ግብረ ኃይል ያልተቋጨ አጀንዳ በተለያዩ አገሮች እ..አ ከ2014 ጀምሮ ሊተገበር የሚገባ ብሎ ያስቀመጣቸውና በስብሰባው በስተመጨረሻ ለጉባዔው ይፋ የተደረጉና በዋናነት የተቀመጡ ነጥቦች አሉ፡፡ ከእነዚህም መካከል ከአገራችን ሕግ፣ ደንብና ባህል እንዲሁም እሴቶቻችን ጋር ፈጽሞ አብረው ሊሄዱ የማይችሉ ጉዳዮች ነበሩበት፡፡

የመጀመሪያው የወሲብና ተዋልዶ መብቶችን ማክበር፣ መንከባከብና ተፈጻሚ ማድረግ የሚል ነው፡፡ ለዚህም ሕጋዊ ውርጃን ማስፋፋትና ማዳረስ፣ የወሲብና የተዋልዶ መብትን ከሌሎች መብቶችና ከተዛማች ሕጐች ጋር በማያያዝ ማስተማር፣ ግለሰቦች ያላቸውን የወሲብ ዝንባሌያቸውን በሚፈልጉት ሁኔታ ከተመሳሳይ ፆታም (ሆሞሴክሸዋሊዝም) ጋር ቢሆን ያለምንም ገደብ መብታቸውን እንዲለማመዱ ያበረታታል፡፡

ከጋብቻም ውጪ ቢሆን ማንኛውንም የወሲብ ኅብረቶች በፈቃደኝነት ላይ የተመሠረተ እስከሆነ ድረስ መብታቸውን የሚከለክሉ ድንጋጌና ሕጐች እንዲነሱ ይጠይቃል፡፡ የወሲብና የተዋልዶ ጤና መረጃና ትምህርት ማቅረብና ተደራሽነቱን ማረጋገጥ ሌላኛው ዓላማው ነው፡፡ ለዚህም በዋናነት ወጣቶችን በተለይም አፍላ ወጣት ሴቶች ላይ ያነጣጠረ መረጃ በትምህርት ቤቶችና ከትምህርት ቤቶችም ውጪ በመስጠት አጣዳፊ የእርግዝና መከላከያና ሌሎች የወሊድ መቆጣጠሪያ (ሕጋዊ ውርጃንም ጭምር) የሚያገኙበትን ሁኔታ ያመቻቻል፡፡

እንዲሁም ትምህርቱን በመቅረፅና በማዘጋጀት የሕግና ፖሊሲ ማዕቀፍ እንዲያገኝ ማድረግ የሚል ሲሆን፣ ይህንንም ለማድረግ የብሔራዊ ጤና ፕሮግራም አካል ሆኖ የራሱ በጀት እንዲኖረውም በማድረግ በአንዳንድ በውርጃ ሥራ ላይ በተሰማሩ ድርጅቶች የሚከናወን ነው፡፡ (ለምሳሌ በሪፖርተር ጋዜጣ ሐምሌ 2005 .ም በሜሪስቶፕስ ቃለ ምልልስ ላይ በወር 42 ሺሕ ሴቶች ለፅንስ ማቋረጥ ወደ እኛ ይመጣሉ ሲሉ ያለዕፍረት ተናግረዋል) ይህ እንግዲህ አንዱ ድርጅት ብቻ ነው፤ ሙሉ በሙሉ ሕጋዊነቱ ሲዳረስ ምን ሊሆን እንደሚችል መገንዘብ ያሻል፡፡

እስቲ ፍረዱ እኛ በልተን ያልጠገብንና ለማደግ የምንፍጨረጨር ዜጐች፣ የአውሮፓውያንና የምዕራባውያን ቆሻሻ ማራገፊያ የምንሆንበት ምክንያት ምንድን ነው? ይሄ ኢትዮጵያ ነው፡፡ እኛም ኢትዮጵያዊያን ነን፤ ሁለተኛ ዜጋ አይደለንም፡፡ ስለአገራችን ሁኔታ ያገባናል፡፡ ይህ ድብቅ በሆነ መንገድ ቀስ በቀስ ገጽታችንን የሚያጠፋ ጉዳይ ነው፡፡ በጣም የሚያሳፍረው ደግሞ ከግብረ ኃይሉ አባላት ውስጥ አስፈጻሚ ሆነው ልጆቻችንን የመሸጥ ያህል በመሯሯጥ ላይ ያሉት ባለሥልጣኖቻችን መሆናቸው ነው፡፡ እንርሱን ታሪክም ትውልድም ይጠይቃቸው፡፡ ዛሬ ከውጭ ለሚገኘውና በልማት ስም ለሚመጣ ገንዘብ ብለው ጤናማ ትውልድ ሊያሳጡን ነው፡፡ እኛ ኢትዮጵያዊያን ወደ ሌሎች አገሮች እንኳን ስንሄድ የምንኮራበት የራሳችን የሆነ ባህልና ሞራል እንዲሁም ታሪክ ያለን ሕዝቦች ሆነን፣ በዕድገትም ስም ተቀበሉ እያሉ በገንዘባቸው እያስፈራሩና እየደለሉን ነው፡፡ እኛ የምንመርጠው ከድህነታችን ጋር ጤናማ ኅብረተሰብና ታሪካችንን ነው፡፡

ታዲያ የአባቶቻችንና የቀደሙት መሪዎችቻችን ድፍረትና ወኔ ወዴት ነው ያለው? የአሁኖቹ መሪዎች ካደጉ አገሮች በልማት ስም ለሚገኘው ገንዘብ አሳልፈው ይሰጡን ይሆን? ሕጋችንን፣ ባህላችንንና ታሪካችንን ያከብሩልን ዘንድ እባካችሁ ጠይቁልን!

ግብረሰዶማዊነትና ልቅ የወሲብ መብቶች ከትምህርት ቤት ጀምሮ እንደ ዳቦ ሲታደል ምን ዓይነት ቀጣይ ትውልድ ይኖረናል ብለን ተስፋ እናደርጋለን? ጠቃሚ ስለሆኑት መመርያዎች ቅሬታ አይኖረንም፡፡ ነገር ግን በተከበረች አገራችን ላይ የተመሳሳይ ፆታ ጋብቻ/ግንኙነት እንዲሁም ልቅ ወሲባዊ መብት ልንሸከመው የምንችለው አይደለም፡፡ እንኳን ይህ ሁኔታ ተመቻችቶ ሚዲያዎች መጤና አጉል ልማዶችን እያስተዋወቁን ይገኛሉ፡፡ ታዲያ የሥነ ምግባርና የሞራል ውድቀት ሲጨመርበት ምን ሊሆን ይችላል? መንግሥት በዚህ ለተማሪዎች ሥነ ምግባር አሳቢ እየመሰለ በዚያ ለሺሻ ቤት ፈቃድ እየሰጠ የሚጣረስ ነገር በመሥራት ላይ ነው፡፡ እንደ እውነቱ ከሆነ ዛሬ ለአንድ ወላጅ ተማሪ ጥሩ ውጤት አምጥቶ ዩኒቨርሲቲ ሲገባ የነበረው ደስታ ጠፍቶ ልጄ ምን ይገጥመው/ይገጥማት ይሆን በሚል ሥጋት መወጠር ጀምሯል፡፡

ፍረዱ ይህ ለችግሮች መፍትሔ ነው እየተባለ በየቀኑ ኢቲቪ የሚነግረን እውን መፍትሔ ነው? ውርጃን በየክሊኒኩ ማስፋፋትና አጣዳፊ የእርግዝና መከላከያ አቅርቦት ለወጣቶቻችን መፍትሔ ነው?

ቀደም ሲልም ግብረሰዶማዊነትን ለማውገዝ የእምነት አባቶች በተነሱ ጊዜ እንዳንድ የመንግሥት ባለሥልጣናት መከልከላቸውን እናውቃለን፡፡ ይህ ታሪክ ከማጥፋትና ትውልድ ከመሸጥ አይተናነስም፡፡ በመስከረሙ ሥነ ሕዝብና አኅጉራዊ ስብሰባ ላይ ይህንን የተቃወሙ አገሮች አሉ፡፡ እንደ ቻይና ያሉ አገሮችም በጭራሽ እንዳልተቀበሉት ከኢንተርኔት ለማየት ችለናል፡፡ የእኛስ መሪዎች የተቀበሉት በልማት ስም ትውልድን መረን ለመልቀቅ ነው? ስለዚህ በጦርና መሳሪያ ለማንበርከክ/ቅኝ ለመግዛት ያልቻሏትን አገር፣ ዛሬ አንገት የሚያስደፋንን ውሳኔ መሪዎችን እንዳያስተላልፉ ሥጋት አድሮብናል፡፡

እንደ ኢትዮጵያዊና እንደ ወላጅ የነገን ጤናማና ፍሬያማ ትውልድ እንደሚናፍቅ ዜጋ ይህንን ጽፌያለሁ፡፡ ለነገም ትልቅ የማኅበረሰብ ቀውስ ነውና መንግሥታችንም ሆነ የሚመለከተው ክፍል ዛሬ አንድ በሉልን፡፡ የሕግ ያለህ! የፈጣሪ ያለህ!

__

 

Posted in Ethiopia, Infos, Life | Tagged: , , , , , , , | Leave a Comment »

 
%d bloggers like this: