Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on October 7, 2020
👉 መድኃኔ ዓለም ነሐሴ ፳፯ / 27 / ፪ሺ፲፪ ዓ.ም
እጄ ያለወትሮው እየተንቀጠቀጠ ካሜራውን መያዝ እኪያቅተኝ ድረስ፤ ጌታችንን ኢየሱስ ክርስቶስን፣ ክቡር መስቀሉን፣ ላሊበላ ቤተ ጊዮርጊስን ቀለማቶቻችንን እና ኢ‘ት‘ዮጵያን ያየሁ መሰለኝ፤ የተሰማኝም ይህ ነው።
ጨረቃዋ እንደ መስተዋት ሆና ጌታችንን፣ እመቤታችንን፣ ክቡር መስቀሉን፣ ኢትዮጵያችንን፣ ቀለማቶቻችንን፣ የላሊበላን መስቀል (ያለፈውን የፀሐይ ግርዶሽ እናስታውሳለን?) ለመላው እያሳየች እኮ ነው። ኢትዮጵያኛው እና መስቀለኛው “ት” ፊደል እኮ በግልጽ ይታያል፤ በጣም ይገርማል! ይህ ተዓምር ቀላል ነገር አይደለም። በዚሁ ዕለት በአዲስ አበባ ኮተቤ ሚካኤል አካባቢ ከተከሰተው ከፍተኛ የእሳት ቃጠሎ ጋር ምን ሊያገናኘው እንደሚችል አላውቅም። ግን የሆነ ነገር አለ።
👉 ባለፈው የሆሳዕና ዕለት እመቤታችንን እና ልጇን ጌታችንን ነበር የታዩኝ፤
____________________________
Like this:
Like Loading...
Posted in Curiosity, Ethiopia, Faith | Tagged: ላሊበላ, መስቀል, መድኃኔ ዓለም, ቤተ ጊዮርጊስ, አረንጓዴ፣ ቢጫና ቀይ, ኢትዮጵያ, ኢትዮጵያና ቀለማቷ, እመቤታችን, የኢትዮጵያ ካርታ, ደም ጨረቃ, ጨረቃ, Full Moon | Leave a Comment »
Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on February 12, 2020
ጾመ ነነዌ (የኢትዮጵያ ጾም) ዘመነ ዮሐንስ፤ ዛሬ ረቡዕ ፬ – ፪ሺ፲፪ ዓ.ም ነው፤ ሐዋርያው ቅዱስ ዮሐንስ ወልደ ነጎድጓድ ነው።
ነቢዩ ዮናስ ነነዌ መሬት ላይ እንደደረሰ ባወቀ ጊዜ ከእግዚአብሔር መሸሽ አለመቻሉን ተረዳ። የነነዌ ሰዎችንም ንስሐ ግቡ እያለ መስበክ ማስተማር ጀመረ፡፡ የነነዌ ሰዎችን የዮናስን ትምህርት ሰምተው ንስሐ በገቡ ጊዜ እግዚአብሔር አምላክ ይቅር ብሎ ከጥፋት አድኗቸዋል፡፡ነቢዩ ዮናስም ሐሰተኛ እንዳይባል እሳቱ እንደ ደመና ሆኖ ከላይ ታይቷል።
ዮናስ ማለት የስሙ ትርጉም ርግብ ማለት ነው።
በጾማችን እግዚእብሔር አምላክ መዓቱን በምሕረቱ ቁጣውን በትዕግስቱ መልሶ በኃጢአት ለጠፋው ዓለም ይቅርታውን ይላክልን፡፡
___________________________
Like this:
Like Loading...
Posted in Curiosity, Ethiopia, Faith | Tagged: ነብዩ ዮናስ, አረንጓዴ፣ ቢጫና ቀይ, ኢትዮጵያና ቀለማቷ, የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነት, የኢትዮጵያ ካርታ, የካቲት ፫, ደመና, ጨረቃ, ጾመ ነነዌ | Leave a Comment »