Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

Posts Tagged ‘አፄ ዮሐንስ’

ሰንደቃችንን እና አማርኛን ብሔራዊ ያደረጓቸው ታላቁ አፄ ዮሐንስ በአዲስ አበባ ለምን መታሰቢያ የላቸውም?

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on March 11, 2020

መጋቢት ፩ አፄ ዮሐንስ ፬ኛ ንጉሠ ነገስት ዘኢትዮጵያ የፅዮን ጠባቂ ፻፴፩/131ኛው የመስዋዕት ቀን።

እኔ ዮሐንስ እንደሆንኩ ሐሳቤም፡ ነፍሴም፡ ሃይማኖቴም አንዲት ናት!!! የሀገሬን መደፈር የሕዝቤን መዋረድ በሕይወቴ ቁሜ አላይም፤ አልሰማም!!! የሚንቁኝንና አንበገርልህም የሚሉኝን እገጥማለሁ ብዬ ጦሬን ወደ ወንድሞቼ አላዞርምአንገቱን የሰጠው ንጉሣችን ዩሐንስ ፬ኛ።

ይህ ጉዳይ ቀላል ጉዳይ አይመስለኝም፤ ሃገርንና እያንዳንዱን ግለሰብ የሚመለከት ወቅታዊ ጉዳይ ነውና ኢትዮጵያዊ ነኝ የሚል በግልጽና በንጹሕ ልብ ሊነጋገርበት የሚገባው ጉዳይ ነው። ጠላት ከብዙ አቅጣጫ እየተለሳለሰ መጥቷል።

ባለፈው ጊዜ መገናኛ ላይ ሆኜ ወደ ኮተቤ የሚሄዱትን ታክሲዎች እጠብቅ ነበር። ዕለቱ ሐና ማርያም ስለነበር ወደ ኮተቤ ሐና ማርያም መሄድ ፈልጌ ነበር። መንገዱ በመሃል እየተሠራ ስለነበር ወደዚያ የሚሄድ በቂ ታክሲ ስላልነበር ብዙ አስጠበቀኝ። በአጠገቤ አንዲት የሃገር ልብስ የለበሰች ወጣት እናት አብራኝ ትጠብቅ ነበር። የሆነ ሰዓት ላይ አንድ ታክሲ የመንግስቱ ኃይለማርያምን ፎቶ ለጥፎ ሲያልፍ አየሁትና ለሴትዮ በሀዘን እያየሽ ነው ዘመዶቼን በአሰቃቂ ሁኔታ የገደለው፣ የብዙ አዲስ አበባ ነዋሪዎችን ሕይወት የቀጠፈውን የመንግስቱ ኃይለማርያምን ፎቶ ሙሉ አዲስ አበባ በየታክሲውና ሎንቺናዎች ላይ ተለጣጥፎ ሳይ ደሜ ይፈላል።ስላት በሃዘን ተሞልታ ከዚሁ ጋር በተያያዘ የክርስትና አባቷ አቡነ ተክለ ሃይማኖት እንደሆኑና በግል ሕይወቷ ብዙ ተዓምረኛ የሆኑ ነገሮች እንዳደረጉላት እያጫወተችኝ ወደ ሐና ማርያም አብረን አመራን።

ሀገሬ ኢትዮጵያ ሞኝ ነሽ ተላላ የሞተልሽ ቀርቶ የገደለሽ በላ!” የሚለውን አባባል ስታነሳለኝ የታየኝ፤ እንዴ ሙሉ አዲስ አበባን ብትዘዋወሩ አንድም የአፄ ዮሐንስን ወይም የራስ አሉላ አባ ነጋን ፎቶ የለጠፈ ታክሲ አታዩም። (የአፄ ቴዎድሮስ፣ የአፄ ምኒልክ፣ የአፄ ኃይለ ሥላሴ፣ የመንግስቱ ኃይለ ማርያም፣ የአብይ አህመድና ለማ መገርሳ፣ የቼጉቬራ ወዘተ ፎቶዎች በብዛት ተለጥፈው ይታያሉ)። እንዲያውም ጠለቅ ብዬ ስሄድ በኢትዮጵያ ዋና ከተማ ለ አፄ ዮሐንስ እና ራስ አሉላ መታሰቢያነት ይውል ዘንድ በስማቸው የቆመ ሃውልት፣ የተሰየመ መንግድ፣ አደባባይ፣ ትምህርት ቤት ወይም ሆስፒታል አንድም የለም። ቅዱስ ያሬድ እንኳን ከሙዚቃው ትምህርት ቤትና ዘንድሮ ለይስሙላ ከተመረቀው አደባባይ በቀር መንገድም ሆነ ሰፈር አልተሰየመለትም። የቤተ ክርስቲያን አባት ለሆነው ቅዱስ ያሬድ በስሙ የተሰየመው ቤተ ክርስቲያንም አንድ ብቻ ነው። የሚገርም ነገር አይደለም? ቁልፍ የሆኑ የከተማዋ ቦታዎች ካርል አደባባይ፣ ሃይሌ ጋርሜንት፣ ጀርመን፣ ፈረንሳይ፣ ውንጌት፣ ቸርቺል ጎዳና፣ ጆሞ፣ ፉሪ፣ ጉለሌ ወዘተ እየተባሉ በባዕዳውያኑ ስም ይጠራሉ፤ ለኢትዮጵያና ተዋሕዶ እምነቷ የሞቱላት ግን የሚያስታውሳቸው እንኳን የለም። ለእነ ቦብ ማርሊ እና ካርል ህይንስ ቡም ኃውልት ቆሞላቸዋል በመንግስቱ ኃይለ ማርያም በሲባጎ ታንቀው ለተገደሉት አቡነ ቴዎፍሎስ የተሠራው ኃውልት ግን በአደባባይ እንዳይቆም ተደርጓል። በእርኩስ ቱርክ ለተሰዉት ለእነ አፄ ዮሐንስማ የማይታሰብ ነው።

እስኪ ይህ ለምን እንደሆነ እራሳችንን በንጹህ ልብ እንጠይቅ?

  • 1. ደገኛ የሰሜን ሰው ስለሆኑ?

  • 2. ምርጥ የተዋሕዶ አርበኞች ስለነበሩ?

  • 3. ጥልቅ የሆነውን ኢትዮጵያዊነትን ስለያዙ?

  • 3. ሰንደቃችንን እና አማርኛን ብሔራዊ ስላደረጉ?

  • 4. ባዕዳውያኑ የኢትዮጵያ ጠላቶች ስለማይፈልጓቸው?

  • 4. ቆላማዎቹ ኦሮሞዎች እና ሙስሊሞች ስለሚጠሏቸው?

  • 5. ብዙ አብሮ ከመኖር የተነሳ ሰው በዋቄዮአላህ መተት ስለተያዘ?

በክርስቶስ ተቃዋሚዎቹ ቱርኮች የተጨፈጨፉት አባቶቻችን እንባቸውን እያረገፉ ነው! በቱርክ ሰይፍ የታረዱት አፄ ዮሐንስ መቃብራቸውን እይገለበጡ ነው! እግዚአብሔርም በትውልዱ እያዘነበት ነው።

በዛሬዋም ኢትዮጵያ ከአቡነ ተክለ ሃይማኖት እና አፄ ዮሐንስ ችግር ያለው ከፍተኛ ችግር ያጋጥመዋል!


ይህን ድንቅ ጽሑፍ ከዘጠኝ ዓመታት በፊት በጦማሬ አቅርቤው ነበር፦

የአፄ ዮሐንስ እና የንጉሥ ምኒልክ ዕርቅ


*ከማሞ ውድነህ*

የእስበሳችን ነገር ያለ ማክረሩ ነው የሚሻለው። ጠንካራ ክንድና ብርቱ ትኩረት የሚገባው ግን እንደ አዞ ከውሀ ውስጥ ብቅ የሚለው ነው“ (አሉላ አባነጋ)

አፄ ዮሐንስ ከጉራዕ ጦርነት በኋላ ሐማሴን ውስጥ ሰነባብተው ወደ ዐደዋ ከመመለሳቸው በፊት የሰሜን ኢትዮጵያ በር የተከበረና የታፈረም እንዲሆን ሲሉ ደጃዝማች ኃይሉ ተወልደ መድኅንና ራስ ባርያውን በገዥነት ሲሾሙ፡ ስመ–ጥሩውን አዋጊያቸውን ሊጋባ አሉላን በራስነት ማዕረግ አስኮፍውሰና አስጊጠው ከመረብ ማዶ ያለውን አገር በጦር አበጋዝነት እንዲጠብቁ ሾሙዋቸው። ከዚያ በኋላም የአፄ ዮሐንስ ትልቁ የሥራ ምዕራፍ የኢትዮጵያን የውስጥ ጉዳይ ማደላደልና ማለሳለስ አንድነቷን ማጽናትና ሕዝቡ ፍትሕ አግኝቶ አርሶና ነግዶ እንዲተዳደር የማድረጉ ጉዳይ ነበር።

ይህን ዓላማቸውን ሊያደናቅፉባቸው እንደሚችሉ አሥግተዋቸው ከነበሩት ሁኔታዎችም ጋር መፋጠጡን ተያያዙት። በሰሜን ኢትዮጵያ በኩል የውስጡን ተቀናቃኝ ቀርቶ የውጭውንም ወራሪ ጠላት ከአንዴም ሁለቴ ኃያሉ ክንዳቸውን ስለአሳረፉበት ለጊዜው ረጭ ብሎላቸዋል። በምዕራብና በመካከል ኢትዮጵያም በኩል የቤገምድር የወሎና የጐጃም ሁኔታ ጋብ ብሎላቸዋል። የጥርጣሬና የሥጋት ትኩረታቸውን የሳበባቸው ግን ሸዋ ሆነ። የወጣትነት ጓደኛቸውና ምስጢረኛቸው ምኒልክ “አፄ” ተብለው ቁጥሩ እስከ ሰባ ሺህ በሚደርስ ሠራዊት ጐልብተው፡ ከሸዋም አልፈው ወሎንና ጐጃምን ለመደረብ ከሚያስፈራሩበት ደረጃ ላይ ወጥተዋል።

አፄ ዮሐንስ ግን፡ የምኒልክን ሁኔታ አንሥተው ከመኳንንቶቻቸውና ከጦር አበጋዞቻቸው ጋር በሚወያዩበት ሰዓት ሁሉ ደጋግመው የሚያነሡት ጉዳይ ነበራቸው።

ዋናው ሥጋቱና ችግሬ የሠራዊቱ ብዛት አይደለም። ለዚህ ለዚህስ እኔም ላቅ ያለ እንጅ ከእርሱ ዝቅ ያለ ሠራዊት የለኝም። ግን እንደዚያ ማሳያ እንደሚሉት የሰይጣን መልእክተኛ የመሰለ ፈረንጅ ከአጠገቡ አስቀምጦ፡ ከነሙንዚንገር ጋርም የሚያደርገው መላላክና መስማማት ነው።

ከዚያ ሌላ ደግሞ እነዚህ ሚሲዮኖችም በዚያ በኩል ገብተዋል፡. ዋናው ዓላማቸውም ምኒልክን አሳስተውና ጦር አስመዝዘው ከኔ ጋር ለማጋጨት መሆኑን አላጣሁትም። ግዴለም የማደርገውን ዐውቃለሁ” እያሉ ዛቻ አዘልና ትካዜ–ለበስ አነጋገር ያሰሙ ነበር። እርግጥም ነው በዚያ ዘመን ፒዬር አርኖ የተባለ ፈረንሳዊ በዘይላ በኩል ወደ ሸዋ ገብቶ የምኒልክ ባለሟል ሆኖ የእርሳቸውንም መልእክት ይዞ ወደ ግብጽና ፈረንሣይ እየሔደ ‘ዮሐንስን ለመጣል ትልቅ መሣሪያ ይሆናችኋል‘ እያለ ያሽቃብጥ ነበር። ከእርሱም ሌላ ደግሞ በምሕጻረ ቃል “አባ ማስያስ” እየተባለ የሚጠራው ሎሬንዞ ጉልየሞ ማሳያ የሚባለው የሮማ ካቶሊክ ሚሲዮን አባል በሸዋና በከፋ ውስጥ ድርጅቱን አቋቁሞ የምኒልክን ባለሟልነትም አትርፎ ከሚሲዮናዊነቱ ይልቅ በዲፕሎማቲክና በስለላው ሙያ ተሠማርቶ ዮሐንስንና ምኒልክን ለማራራቅና ለማጋጨት በመካከላቸው ገብቶ ነበር።

እነዚሁ ሁለቱ አውሮጳውያን የምኒልክን ጉልበት ከዮሐንስ ጉልበት የጠነከረ ለማድረግ ሲያደርጉት የነበረውን ጥረት ሲከታተሉት የነበሩት ዮሐንስም ክንዳቸውን በቀላሉ የማይታጠፍ ለማድረግና ምኒልክንም ለማስገበር ሲሉ የሠራዊታቸውን ቁጥር እስከ አንድ መቶ ሺህ ከአደረሱት በኋላ፥ ክዚሁ ውስጥ እስከ ዐርባ ሰባት ሺህ

የሚደርሰውን ልዩ ልዩ መሣሪያዎች አስታጠቁት። ከጉንደትና ጉራዕ ጦርነቶች የተገኘው ቀላል መካከለኛና ከባድ መሣሪያም የበላይነታቸውን ያረጋገጡበት ዋናው ትጥቃቸው ነበር።

ከመሣሪያው ጥራትና ብዛትም ሌላ በአጼ ተክለ ጊዮርጊስና በግብጾች ላይ ያገኙት ድል ዝናቸውንና ጥንካሬያቸውን “አበሻ መሬት አውጥቶ በአፍሪቃ፡ በእስያና በአውሮጳ ውስጥ አስተጋብቶላቸው ነበር። በአሜሪካም ውስጥ ቢሆን፡ “የኛ የጦር መኮንኖች ያዘመቱትን የግብጽን ጦር ድል ያደረገ ብርቱ ንጉሥ” የሚል ጸጸት–ለበስ ታዋቂነት አትሮላቸው ነበር።

ታዲያ እንደዚያ ሆኖ ስሙ የገነነ ሠራዊት ሸዋ የገባ እንደሆነ ሊያደርስ የሚችለውን ብርቱ ጉዳት አስቀድመው የተረዱትና የተጠነቀቁበት ከጐልማሳው ምኒልክ ይልቅ አዛውንቱ አጐታቸው ዳርጌ ንበሩ። “ጉዳዩን በቀላሉ አትዩት፤ በየልቦናችሁ ምከሩበትና በእርቅ ይለቅ” ሲሉ አዛውንቱ “ጦር ጠማኝ” ይሉ የንበሩት የምኒልክ የጦር አበጋዝ ግን፤

ወይ እሳቸው መጥተው፥ ያለዚያ እኛ ዘምተንባቸው ሳንሞካከር እንዴት አስቀድመን እንገብራለን” እያሉ ምኒልክን ይወተዉቱ ነበር።

በዮሐንስ ቤተ መንግሥት እንደአባት ይታዩ የንበሩት ራስ አርአያም በበኩላቸው፤

የሁለት ወንድማማች ጠብ ማንን ጐድቶ ማንን ይጠቅም ይመስላችሁ? ኢትዮጵያን እኮ ነው የሚያዳክማት! ኢትዮጵያን እኮነው የሚያሳንሳት! ኢትዮጵያን እኮ ነው የጠላቶቿ መሳቂያ የሚያደርጋት! ታሪክ ይወቅሰናል፤ ትውልድ ያፍርብናል፤ ታቦትና መስቀል አስይዘን ካህናትን ወደ ምኒልክ እንስደድ እንጂ ጦር መምዘዙን አልስማማበትም” እያሉ የእህታቸውን ልጅ ከነጦር አበጋዞቻቸው ይቆጡ ነበር።

እዚህ ይቀጥሉ

___________________________________

Posted in Curiosity, Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , | Leave a Comment »

ለኢትዮጵያና ተዋሕዶ የተሰውትን ጀግናውን አፄ ዮሐንስን የሚያሳድደው አቶ ታየ በመጋቢ ተግሳፅ ቦግ አለ

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on October 19, 2019

በዘመነ ዮሐንስ፡ እንዲያውም እንደ አፄ ዮሐንስ የመሰለ ተዋሕዶ መሪ ነው ለሃገራችን የሚያስፈልጋት!

አቶ ታየ ቦጋለን ይህን ያህል እብሪተኛና ቁጡ ያደረገው የትግሬ ጥላቻ ይሆን? ወይስ የአንድ ዓለም ጣዖታዊ አምልኮንለመመስረት አፄ ዮሐንስና ተዋሕዶ ልጆቻቸው መሰናክል ስለሆኑበት? አቶ ታየ እና ፕሮፌሰር ፍቅሬ ቶሎሳ ግማሽ ሐቅ ይዘው እባባዊ በሆነ መልክ ታሪክን ለመከለስ በመታገል ላይ ናቸው። ጉድ እኮ ነው፤ የታሪክ ሊቆቹ ሁሉ ኦሮሞነን የሚሉት ታሪክ አልባዎች ናቸው። በትግሬዎች ላይ ያላቸው ጥላቻ በዘር የሚተላለፍ ወይም ጄኔቲካዊ ይመስላል። ለእነዚህ አደገኛ ሰዎች የሚያጨበጭብ ኢትዮጵያዊ ግብዝ የሆነ ወገን ብቻ ነው፤ ዘጠኝ መድኃኒት ሰጥተውት አንድ መርዝ ጠብ እያደረጉለት መሆኑ አይታወቀውም።

ማን ከማን ጋር መዋለዱ/መወላለዱ የስጋ ነገር ነውና እንደ ኢትዮጵያውያን ላሉ መንፈሳዊ ሕዝቦች ብዙ ትኩረት ሊሰጠው የሚገባው ነገር አይደለም። የስጋውን ነገር ከረጅም ጊዜ በፊት አልፈነዋል! ዋናው የኑሯችን ጉዳይ ከመንፈሳዊ ሕይወት ጋር የተያያዘ ነው፤ ስለዚህ ከመንፍሳዊ ማንነታችን ጋር በተያያዘ በዚህ በጉ ከፍየሎች በሚለይበት ዘመን ወይ ከክርስቶስ ጋር ወይ ከዲያብሎስ ጋር፣ ወይ ከቅዱስ መንፈስ ጋር ወይ ከእርኩስ መንፈስ ጋር፣ ወይ ከመስቀሉ ጋር ወይ ከጨረቃ ጋር፣ ወይ ከበጉ ጋር አሊያ ደግሞ ከፍየሉ ጋር መደመር ግድ ነው። ከፍየሉ ጋር ከሆንክ የኢትዮጵያና ክርስቶስ አምላኳ ጠላት ነህ ማለት ነው።

ኢትዮጵያ ማለት ክርስትና ማለት ነው፤ ወደድንም ጠላንም፡ ከዚህ ውጭ ሌሎች አምልኮዎች በሃገረ ኢትዮጵያ ምንም ዓይነት ሚና ሊጫወቱ አይገባቸውም።

እነ አቶ ታየ ቦጋለና ፕሮፊሰር ፍቅሬ ቶሎሳ ኩሽ፣ ዋቀፌና ቅብርጥሴ እያሉ ክንቱ የሆነ ዝባዝንኬ ነገር ከሚቀበጣጥሩ ሕዝቤ ነውየሚሉትን ኦሮሞየተባለውን ሕዝብ አባቶቹ በኢትዮጵያ ላይ ከሠሩትና ከተረገሙበት አስከፊ በደል ተጸጽተው ለንስሐ እንዲበቁ በቅንነት ቢያስተምሩት የተሻለ ነው። የሚያስዝን ነው፤ የኦሮሞ ልሂቃንዘመን ያለፈበትን የነገስታት ታሪክ ሌት ተቀን እያነሱ ባለፈበትና በሞተ ነገር ሲጨቀጭቁን ነው እሚውሉት ፥ ታሪክ ከመስራት ይልቅ ታሪክ በማውራት ዘመናቸው ሊያበቃ ነው።

ኦሮሞ ነን” የሚሉት ምስጋናቢሶች ሰፊውን ጠልተው ጠባቡን፣ የሚያኮራውን ንቀው የሚያቀለውን፣ የሚያስከብረውን አውግዘው የሚያዋርደውን፣ ግዕዝን ትተው ላቲኑን፣ ክርስቶስን ትተው ዲያብሎስን፣ የማርያም መቀነትን ትተው የዘንዶውን ቀበቶ፣ እውነቱን ትተው ውሸቱን መርጠዋልና በቅርቡ ክፉኛ ይቀጣሉ። መዳን የሚፈልጉ ወገኖች ግን ዲያብሎስ የሰጣቸውን ኦሮሞነታቸውን በመካድ ከአምልኮተ ጣዖት መላቀቅ አለባቸው፣ ዋቄዮ አላህን እርግፍ አድርገው በመተው ንስሃ ገብተው ከሌሎች ኢትዮጵያውያን ጋር ቶሎ ቢቀላቀሉ ይሻላቸዋል።

[የሉቃስ ወንጌል ምዕራፍ ፲፬፳፮፳፯]

ማንም ወደ እኔ የሚመጣ ቢኖር አባቱንና እናቱን ሚስቱንም ልጆቹንም ወንድሞቹንም እኅቶቹንም የራሱን ሕይወት ስንኳ ሳይቀር ባይጠላ፥ ደቀ መዝሙሬ ሊሆን አይችልም። ማንም መስቀሉን ተሸክሞ በኋላዬ የማይመጣ፥ ደቀ መዝሙሬ ሊሆን አይችልም

_____________________________

Posted in Curiosity, Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

ሞኝነት እስከ መቼ?

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on August 23, 2012

    PS: Republished Post from July

መቅበጥበጥ ላይ የምትገኘዋ ቱርክ ከመቶ ዓመታት በኋላ እንደገና ወደ አፍሪቃው ቀንድ፡ ወደ ኢትዮጵያችን ጠጋ ጠጋ በማለት ላይ ትገኛለች። በንግሥት ዘውዲቱ ዘመነ መንግሥት (ራስ ተፈሪ/አፄ ኃይለሥላሴ አልጋወራሽ ነበሩ)በሐረር ከተማ እ...1910-1912 .ም ድረስ የኦቶማን ንጉሥ ነገሥት ግዛት በሐረር ከተማ አንድ ቆንሲል ከፍቶ ነበር። የዚህን ቆንሲል ህንፃ ያሁኗ ቱርክ ለማደስ ዝግጁ እንደሆነች ሰሞኑን አስታወቃለች። ከዚህ በተጨማሪ የእስላሞችን ነበይ የሙሀመድን ባላጋሮች በኢትዮጵያ ተቀብሎ ያስተናገዳቸውና በስህተትአልነጃሺየሚሉትን ክርስቲያን የኢትዮጵያ ንጉሥ ፡ አርማሕን ፡ እንዲሁም የሙሀመድን ባላጋሮች የሚያስታውሱ ሃውልቶች በትግራይ ውስጥ ለማቆም ከጥቂት ቀናት በፊት ከስምምነት ደርሳለች። ሕዝበ ዲያስፐራ ይህን ዜና በቸልተኝነት ማለፉ አሳሳቢ ነው!

የኢትዮጵያ ነገሥታት ከመጽሐፍ ቅዱስ የተማሩትን ክርስቲያናዊ ሥነምግባር በመከተል፤ ጻድቁ አብርሃምም እንግዳን የመቀበል ልማዱ እግዚአብሔርን ለመቀበል አብቅቶት ስለነበር፤ ኢትዮጵያውያን ለሚመጣው እንግዳው ሁሉ(ለጠላቶቻቸውም ጭምር)ተመሳሳይ አቀባበል ሲያደርጉ ቆይተዋል። ሕዝባችን በእንግዳ ተቀባይነቱ ምናልባት የዓለም ቻምፒዮን ሊሆን ይችላል። ነገር ግን ይህ በጐ ተግባር ብዙውን ጊዜ ከጥቅሙ ጉዳቱንና መዘዙን ነው ይዞብን የመጣው። ይህን እንግዳ ተቀባይነታችንን እንደሞኝነት አድርገው የቆጠሩት፤ ግብጾች፣ አረቦችና ቱርኮች አገራችንን በየጊዜው እየተተናኮሉ ለውድቀት እንድትጋለጥ አድርገዋታል። የማሽኮርመም ጥበቡን የተካነችው ቱርክ ታሪካዊ ጠላታችን ነች፤ እስከ መጥፊያዋ ጊዜም(ተቃርቧል)ወደድንም ጠላንም አደገኛ ጠላታችን ሆና ነው የምትቀርበን። በ16ኛው መቶ ክፍለ ዘመን፡ ግራኝ አህመድ ኢትዮጵያን በወረረ ጊዜ የአክራሪ እስልምና እንቅስቃሴ ተስፋፍቶ የነበረው በቱርኮች ደጋፊነት ነበር። በ19ኛውም መቶ ክፍለዘመንም ቱርኮች ግብጾችንና የሱዳን መሀዲስቶችን በመደገፍ አያሌ ጥንታውያን አብያተ ክርስቲያናትን አቃጠሉ፣ ሕዝቡን አረዱ፣ ቅርሶችን አወደሙ፣ ከዚህም አልፈው ለዐፄ ዮሐንስ ኅልፈት ምክንያት ሆኑ።

ታዲያ ይህን ሁሉ በደልና ጥፋት በሕዝባችን ላይ ደግመው ደጋግመው ሲያደርሱ የነበሩት ቱርኮች በንግሥት ዘውዲቱ ጊዜ እንዴት ቆንሲል በሐረር ከተማ ሊከፍቱ ቻሉ? በጊዜው ቱርክ በ አናቶሊያ ግዛቷ የሚኖሩትን አርመናውያን፣ ግሪኮችና አሹር ክርስቲያኖችን ለመጨፍጨፍ የተዘጋጀችበት ጊዜ ነበር። ባሁኑ ጊዜም በክርስቲያኖችና በኩርዶች ላይ ግልጽ የሆነ በደል በመፈጸም ላይ ናት። አሁን ቱርክ የምትባለዋ አገር የአርመኖችና የግሪኮች ምድር ናት ወደፊትም ትሆናለች። ቱርኮች ከመካከለኛው እስያ በወራሪነት እስከ ቁንጥንጥንያ ከመግባታቸው በፊት ቦታው የክርስትና ማዕከል ነበር። ታዲያ ባሁን ጊዜ የዚህን የክርስቲያናዊ ሥልጣኔ የሚያንጸባርቁትንና የ2ሺህ ዓመታት ያህል ታሪክ ያላቸውን ዓብያተ ክርስቲያናት፣ ገዳማትንና የትምሕርት ማዕከላት ለማደስ በቱርክ የቀሩት ጥቂት አርመኖችና ግሪኮች ፈጽሞ አይፈቀድላቸውም። አዲስ ቤተክርስቲያን መስራት ጭራሽ የማይታሰብ ጉዳይ ነው።

በአገራቸው ይህን ዓይነት ግልጽ ኢሰብዓዊ ድርጊት የሚፈጽሙት ቱርኮች እንዴት ወደ ኢትዮጵያ ገብተው የእስልምና ቅርሶችን እንዲያድሱ ፀረክርስቲያን የጥላቻ ትምህርት ቤቶችና ተቋማትን ለመሥራት ተፈቀደላቸው? ማን ነው ይህን ዕድል የሰጣቸው? ይህን የጥፋት በረከት ለቱርኮች የሰጠ በኢትዮጵያና በሕዝቧ ላይ ከፍተኛ በደል እየፈጸመ መሆኑን በኋላም እንደሚያስጠይቀውና እንደሚያስቀጣው አይገነዘብምን?

በጐረቤት አገር፤ በሶማሊያምየተራበውን የሶማሊያ ወንድማዊ ሕዝብ እንረዳለንበማለት ብዛት ያላቸው ቱርካዊ እርዳታ ሰጪዎች ወደ ሶማሊያ በመጉረፍ ላይ ይገኛሉ። ሁልጊዜ የመጀመሪያው መግቢያቸው በሶማሊያ በኩል ነው። አሁን የግራኝ መሀመድ መንፈስ እንደገና እየጠራቸው ይሆን? ከሃያ የጥፋትና የእልቂት ዓመታት በኋላ የሉሲፈር ዋና መሃንዲስ የሆነችውም እንግሊዝ ለሶማሊያ አሳቢ በመምሰል ስብሰባዎችን በመጥራት ላይ ናት። ለካውካስ ሕዝቦች በመቆርቆር በአፍጋኒስታንና ኢራቅ ከፍተኛ የገንዘብና የዲፕሎማሲ መስዋዕት የሚያደርጉትና የሚደሙት አውሮፓውያንና አሜሪካውያንም የሶማሊያ ነገርከእንቅልፋቸው የቀሰቀሳቸው ይመስላል አንድ ነገር ማድረግ አለብንበማለት ላይ ናቸው። ለመሆኑ ሶማሊያ ውስጥ ምን ተገኝቶ ይሆን? ወይስ ሌላ ያሰቡት ነገር አለ?

የሰሜኑ አትላንቲክ የጦር ቃልኪዳን(ኔቶ)አባል የሆነችው ቱርክ በዚህ በፍጻሜው ዘመን የጎግ ማጎግን ሚና ለመጫወት የተዘጋጀች አገር የሆነች ትመስላለች። ቱርክ፡ ልክ እንደ አረቦቹ አገራት፡ ዓለማችንን ወደ አንድ መንደር ለማምጣት ቆርጠው በተነሱት የምዕራባውያን ኃይሎች እየተረዳች ነው። ወደ ምዕራባውያኑ ዓለም ላለፉት 60 ዓመታት በብዛት ተሰደው የሚኖሩት ቱርኮች ለአገራቸው እድገትዓይነተኛ አስተዋጽኦ በማድረጋቸውም ገና ድህነት ላይ የምትገኘው ቱርክ፡ አለሁ አለሁ፤ ጠገብ ጠገብ በማለት ላይ ትገኛለች። ቱርክ እንደ ኢትዮጵያ ላሉ አገሮች ፈጽሞ ወዳጅ ልትሆን አትችልም። ቱርክ ለኢትዮጵያ ዲያብሎሳዊ ተልዕኮ እንዳላት ሁኔታዎቹ ሁሉ በግልጽ ያሳዩናል። አሁንም ቢሆን የኢትዮጵያን ማንነት ለማጥፋት ከኢትዮጵያ ሕዝብና መንግሥት ዙሪያ የክፋት ድሯን በዝግታ በመጠንጠን ላይ ትገኛለች። የመጥፊያ ጊዜዋ የተቃረበው ቱርክ በየቦታው ብቅ ጥልቅ በማለት የሌላትን ጉልበት ለማሳያት ትሞክራለች፤ ባንድ በኩል እስራኤልን ትተናኮላለች፣ በሌላ በኩል ደግሞ ከሱኒ እስልምናው ዓለም ጋር በማበር ፀረሺዓ የሆነ ትግል በኢራን፣ የመንና ሶርያ ላይ ታካሂዳለች። በቅርቡም ከ አዘርበጃን ጎን በመቆም በአርመኒያ ላይ ልትዘምት በመዘጋጀት ላይ ነች። በዓለም የመጀመሪያዎቹ ክርስቲያን ሕዝቦች እንደሆኑ ለሚታወቁት አርመንያኖች እና ኢትዮጵያውያኖች ቱርኮች ታሪካዊ ጠላቶቻቸው ናቸው። አሁን ቱርክ ተብላ የምትታወቀው ግዛት የአርመንያኖች አገራቸው ነበረች። አርምንያኖች አሁን ልክ እንደ ኢትዮጵያ የባሕር መውጫ እንኳን የላቸውም። በነገራችን ላይ፣ 22ቱ የአረብ አገሮች፣ እንድያውም ከአፍጋኒስታን በስተቀር ሁሉም እስላም ነን የሚሉትና 54 የሚጠጉት አገሮች የባሕር አዋሳኝ ግዛት አላቸው። እንደ ኢትዮጵያና አርመኒያ የመሰሉት ሞኝ የክርስቲያን አገሮች ግን ያላቸውን ለጠላት እያስረከቡ በስቃይ ይኖራሉ። አይበቃንም? መቃድሹን እንኩ፣ በርበራን እንኩ፣ ጅቡቲን እንኩ፣ አሰብና ምጽዋን እንኩ፡ ውሰዱ እያለች ግዛቷን ለባዕድ ሸርሸረን በመስጠት በየጊዜው ተታለልን፡ አሁን ሁሉ ግልጽ ሆኖ በሚታይበት ዘመን ተመሳሳይ ስህተት (ኃጢአት)ስንሠራ ወደ እንስሳነት እንደተለወጥን ሆኖ አይሰማንምን?

ባሁኑ ጊዜ ባካባቢያችን እየተካሄደ ያለውን ሁኔታ በሚገባ አጠንቅቀን ልናገናዝብ ይገባናል። የኤርትራ ሁኔታ ቸል መባል የለበትም። በኢትዮጵያ ስም አንድ ሆነው በተፈጠሩ ሕዝቦች መካከል ልዩነት እንዲኖር ሰውሰራሽ የሆነው የጥላቻ መንፈስ የተገኘው ከዲያብሎስ መሆኑ መታወቅ ይኖርበታል። ስለዚህ አጋንንታዊው የጎሰኝነት መንፈስ የፈጠረውንና ከያቅጣጫው የሚነዛውን የጥላቻ ፕሮፓጋንዳ መግታት ይኖርብናል። ከኤርትራ ጋር እንደገና አንድነት ፈጥሮ መኖሩ የያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ዓላማ መሆን አለበት፣ እናንት እና እኛመባባሉ ጠላታችን ዲያብሎስን ብቻ ነው የሚጠቅመው። ሱዳን ለሁለት ተከፍላለች፣ ከደቡብ ሱዳን ጋር የጠበቀ ግኑኝነት ሊኖረን ይገባል፡ እንዲያውም ሁለቱ ሕዝቦች ወደ ኮንፌደረሽን ደረጃ ለማምራት ቢበቁ የጠላቶቻቸው ዓላማ ሁሉ ከንቱ ይሆናል፣ ደቡብ ሱዳናውያንም ከዕልቂት ሰይፍ ይተርፋሉ። ቀይ ባሕርንም ተሻግሮ፤ የመን ውጥንቅጧ ይወጣል፤ እንደገና ለሁለት የመከፋፈል እጣ ይደርሳታል። የዲያብሎስ መዲናዋ ሳዑዲ ዓረቢያም ያልተጠበቀ የውጥንቅጥ ማዕበል ይዟት እንደሚሄድ እርግጠኛ ነኝ።

ከጥቂት ወራት በፊት አንድ የወታደሮች አሰልጣኝ አሜሪካዊ ፡ ሳዑዲ ዓረቢያን የተመለከተና አወዛጋቢ ሆኖ የተገኘ ትምህርታዊ መግለጫ ወታደራዊ በሆኑት የአሜሪካ ተቋማት ለማቅረብ በቅቶ ነበር። በዚህም መግለጫው ላይ፤ አሜሪካ ጦርነት ማካሄድ ያለባት ከ አክራሪ ጂሃዲስቶች ጋር ብቻ ሳይሆን ከእስልምና ጋርም መሆኑን ይጠቁማሉ። እንደሰውየው ከሆነ አሜሪካ መካና መዲናን ሙሉ በሙሉ ማውደም ይኖርባታል፤ ሳውዲ አረቢያም ለረሃብና ዕልቂት መጋለጥ አለባት፡ እንደሁኔታውም፡ በብዙ ሚሊየን የሚቆጠሩ ሙስሊሞችን መቅጣት አማራጭ የሌለው እርምጃ ነው። ባጠቃላይ በጃፓኖቹ ሂሮሺማና ነጋሳኪ የተደረገው ዓይነት የአቶም ቦምብ ጥቃት በመካና መዲና መውረድ ይኖርበታል ያላሉ። ይህም በርግጥ በጣም ሊቀፈንና ሊረብሽን ይችል ይሆናል፡ እኔንም ረብሾኝ ነበር። ሙሉውን መልዕክት ለመመልከት እዚህች ይጫኑ

ነገር ግን ታሪክ እንደሚያስተምረን ይህ ላይ የቀረበው የጥቃት ፕላን ፈጠነም ዘገየም አንድ ቀን እንደሚፈጸም አንጠራጠር። የኒው ዮርኩ የመስከረም 11 ሽብርተኞች ሳውዲዎችና ግብጾች ነበሩ፡ ታዲያ ተመሳሳይ ጥቃት በአሜሪካ ምድር በድጋሚ የሚፈጸም ከሆነ አሜሪካ ሳውዲ ዓረቢያን ከምድረበዳው ሥር ለመቅበር እንደምትነሳ አንጠራጠር። እነዚህ አትኩሮት ፈላጊ የሆኑት የእስላም አገሮች እና አክራሪ እስላሞች አገራቸው ባልሆኑት አገሮች ሳይቀር ጠግበው በመፈንጠዝ ያዙን ልቀቁን በማለት ላይ ይገኛሉ፣ ባሁን ጊዜ ያላመሱትና ያልበጠበጡት የዓለም ክፍል የለም። መንግሥታቱና የዜና ማሰራጫዎቹ ለዘብ ያሉ ቢመስሉንም፡ ከአፍሪቃ እስከ እስያ፡ ከአውሮፓ እስከ አሜሪካ ያሉ ሕዝቦች ትዕግስታቸው እያለቀና በመቆጣት ላይ ይገኛሉ። ከሰዶማውያን ቀጥሎ በዓለም ላይ የጥላቻ መርዛቸውን በመርጨት ላይ የሚገኙት የአክራሪ እስልምናው ተከታዮች ናቸው። እነዚህ እኛ ብቻ እንናገርባይ ኃይሎች አሁን ግድ ነው መታየት፣ መታወቅ ይኖርባቸዋልና ለዓለም ማህበረሰብ በፈቃዳቸው እራሳቸውን እያጋለጡ ነው፤ ከሁሉም የተለየ ልብስ በመልበስ፣ የተለየ መማሪያ ቦታ በመክፈት፣ የተለየ የጸሎትና የመመገቢያ ቦታ እንዲሰጣቸው በመጠየቀ እራሳቸውን ከሌላው በማግለል ላይ ይገኛሉ። ይህ አልበቃቸውም፣ የሌላውን መብት ሁሉ በመጋፋት፤ አይሁዶችንና ክርስቲያኖችን በመሳደብ በማንቋሸሽ ላይ ናቸው። ኮፕት ክሪስትያኖችን ለመጨፍጨፍ እጆቹን በማሻሸት ላይ ያለው አዲሱ የግብጽ እስላማዊ መንግሥትም የእስልምና ጠበቃ በመሆን በኢትዮጵያ ላይ ተንኮሉን በፍጥነት ጀምሮታል። ሊንኩ ክርስቲያንና ሙስሊም ኢትዮጵያውያን በካይሮ ሰልፍ ወጡ በኢትዮጵያ የሙስሊሞችን ጭቆና አወገዙ ይላል። ይህ በእንግሊዝኛው ‘projection’ የሚሉት ነገር ነው። ይታየን አዲስ አበባ ክርስቲያኑና ሙስሊሙ በአንድነት ወጥቶ በኮፕቶች ላይ የሚካሄደውን በደልና ግድያ ሲቃወም። ጨምላቆች! እባቡ መሪያቸው፡ ሙርሲ አዲስ አበባ ከመግባቱ በፊት ጥቁሩን ድንጋይ ለመሳለም፡ ዘይቱንም ለመቅመስ መጀመሪያ ወደ ሳውዲ ዓረቢያ ጎራ ማለት ግድ ነበረበት። (ፕሬዚደንት ኦባማ ወደ ኢትዮጵያ ባይመጡም ተመሳሳይ የሆነ ጉዞ መጀመሪያ በግብጽ ከዚያም በሳውዲ አረቢያ አድርገው ነበር።)

ባንዳንድ የአውሮፓ አገሮች ሙስሊሞች ከአገሬው ተወላጅና ከጸጥታ አስከባሪዎች ጋር መጋጨቱን አዘውትረዋል። ሕንፃዎችን ያበላሻሉ፣ ፈረንጅ ያልሆኑትን ክርስቲያኖች በግልጽ ይሳደባሉ፣ ዓብያተ ክርስቲያናት ውስጥ በሚገኘው የጠበል ውሃ ላይ ይተፋሉ፣ ይሸናሉ፤ ልጃገረዶችን በየመንገዱ እያስገደዱ ይደፍራሉ፤ በትውልድ አገሮቻቸው ደግሞ ክርስቲያኖችን፣ ሂንዱዎችን፣ ቡድሃውያንን ይገድላሉ የአምልኮ ቦታዎቻቸውንና ቤቶቻቸውን ያቃጥላሉ። ታዲያ ይህ ሁሉ እንደው ዝም እንደተባለ የሚቀጥል ይመስለናልን? በፍጹም፤ ለእነዚህ መዳንእምቢላሉ ሰዎች መጥፊያቸው እየተዘጋጀላቸው ነው። የሚጠፉትም ለአጭር ጊዜ ከነርሱ ጋር በመተባበር ሲረዷቸው በነበሩት ፀረክርስቶሳውያን የምዕራብ ኃይሎች አማካኝነት ነው። ሳውዲ ዓረቢያ በኢትዮጵያ ታይቶ ከነበረው የረሃብ ቸነፈር የከፋ ስቃይ የምታይበት ጊዜ ሩቅ አይደልም፡ ያው ረሃቡም የመን ገብቶ ዳርዳር እያለ ነው፤ ፈጣሪ ይርዳቸው፡ ግን እንደ ኢትዮጵያ ረሃቡን ድል አድርገው ለማገገም የሚችሉ ሕዝቦች አይደሉም።

እየተራበች እየተጠማች ስደተኛውን ሁሉ እንደ ወንድሞቿና እህቶቿ፤ እንደ እናቶቿና እንደ አባቶቿ አድርጋ የምታስተናግደው ኢትዮጵያስ እጆቿን ወደ እግዚአብሔር የመዘርጋት እድል ተሰጥቷታል፤ በትዕቢት የተወጠረችው፡ በነዳጅ ዘይት ገንዘብ የምትዋኘውና በኢትዮጵያውያን ላይ አስከፊ በደል የምትፈጽመው ሳውዲ ግን እጣዋ ሲዖል ካልሆነ ሌላ ሊሆን አይችልም።

የኢትዮጵያ ልጅ ሆይ ልብ አድርገህ ተመልከት። ኢትዮጵያ የተባለች አንደኛ እናትህ ናት፣ ሁለተኛ ዘውድህ ናት፣ ሦስተኛ ሚስትህ ናት፣ አራተኛ ልጅህ ናት፣ አምስተኛ መቃብርህ ናት። እንግዲህ የእናት ፍቅር፣ የዘውድ ክብር፣ የሚስት ደግነት፣ የልጅ ደስታ፣ የመቃብር ከባድነት እንደዚህ መሆኑን አውቀህ ተነሣ።(አፄ ዮሐንስ ፬ኛ)

_______________________________________________

Posted in Ethiopia | Tagged: , , , , , , , | Leave a Comment »

 
%d bloggers like this: