Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

Posts Tagged ‘አፄ ቴዎድሮስ’

የብሪታኒያ ቅሌት | የኢትዮጵያ ቀሳውስት የተሠረቀውን ቅዱስ ታቦት መጎብኘት ተከለከሉ

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on June 2, 2019

ከመቶ ሃምሳ ዓመታት በፊት በመቅደላ ጦርነት ወቅት ከኢትዮጵያ በብሪታኒያ ጄነራል ናፒይር የተሠረቀው ቅዱስ ታቦት ወደ ኢትዮጵያ እንዲመለስ ጥረት ቢደረግም እንግሊዛውያን ግን ዛሬም ለመመለስ ፈቃደኞች አይደሉም።

በሃገረ ብሪታኒያ በጣም ቁልፍ እንደሆነ በሚነገረለትና በነጻ ግንበኞች በተገነባው ህንጻ፡ በዌስትሚኒስተር አቤይ ውስጥ ከመንበሩ ጀርባ ተደብቆ ይገኛል። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሊቀጳጳሳት ዌስትሚንስተር ቤተክርስቲያን በሚገኘው ታቦት አቅራቢያ ቅዳሴ ለማድረግ ይችሉ ዘንድ ፈቃድ እንዲያገኙ ለንደን የሚገኙ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቀሳውስት ብዙ ሙከራ አድርገዋል፥ ግን አልተሳካላቸው።

ዲያቆን ሳሙኤል ብርሃኑ የዌስትሚንስተር አቤይ አስተዳዳሪዎች የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሊቀጳጳሳትን ጉብኝት ሊያስትናግዱ ባለመቻላቸው የተሰማቸውን ሃዘኔታ እንደሚከተለው ገልጠዋል፦

በ ፳፩ ኛው መቶ ዘመን የባህላዊና ሃይማኖታዊ ጉዳዮችን በተመለከተ ይህን ያህል ግድየለሾች ይሆናሉ፤ እንዲህ የመሰለ አመለካከት ሊኖራችሁ ይችላል ብዬ አላምንም ነበር። ለመወያየት እንኳ ፈቃደኞች አይደሉም

እንደሚታወቀው ታቦቱ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን መሠረት ሲሆን የቤተክርስቲያንን ሕንፃ የሚባርክና የሚቀድስ ነው።

እንደ ክርስቲያን ይህን ዓይነት አስተያየት እንዴት ይይዛል?የቤተክርስቲያን በር እንዴት ይዘጋብናል? የዌስትሚንስተር አቤይ አቀራረብ በጣም አሳፋሪነው – በተለይ የዌስትሚንስትር ቤተክርስቲያን እራሷ ለመጸለይ ፈቃድ አለመስጠቷ ተጨማሪ ቅሌት ነው።

ይሁን! ለጊዜው ግድየለም፡ አባቶች! ብሪታኒያ ቅዱስ ታቦታቱን ለኢትዮጵያ ሀገራችን መመለስ ፈርታለች፤ ምክኒያቱም ራቁቷን ትቀራለችና፣ ታላቋ ብሪታኒያ ታንሳለችና፤ ተስጥቷት የነበረውን ኃይልና ሞገስ ትነጠቃለችና። እንደ እኔ ከሆነ ብሪታኒያ ታላቅ ለመሆንና አብዛኛውን የዓለማችንን ክፍል ለመቆጣጠር የበቃችው፣ እንግሊዝኛ ቋንቋዋ የዓለም ሁሉ መነጋገሪያ ቋንቋ ለመሆን መቻሉ እንዲሁም ብሪታኒያ በአንደኛውና ሁለተኛው የዓለም ጦርነቶች ድል አድራጊ ለመሆን የተቻላት የተዋሕዶ ታቦታትን በእጆቿ ስላስገባቻቸው ነው።

በአፄ ቴዎድሮስ ዘመን ሀገራችንን የወረረችው፥ በትምህርት ቤት ለመማር እንደተገደድነው ፥ የታሠሩትን ዜጎቿን ለማስፈታት(ማታለያ False Flag Operation ነበር)ሳይሆን፤ እነዚህን ታቦታት ለመስረቅ ነው። መጽሐፈ ሄኖክን ከኢትዮጵያ ሰርቆ የሄደውን ሌባውን ነፃግንበኛ ጀምስ ብሩስን ቀደም ሲል ለስለላ ልከውት ነበር።

ግን የብሪታኒያ እና አጋሮቿ የክብርና ታላቅነት ዘመን ኢየሱስ ክርስቶስን መክዳት ከጀመሩበት ሰዓት አንስቶ ቀስበቀስ እየመነመነ መጥቷል። ለዚህም ነው እስልምና እንደ መቅሰፍት ሆኖ እየተላከባቸው ያለው። እባቦቹ ትውልደ ፓኪስታን የለንደን ከንቲባ እና የአገር ውስጥ ሚንስትር እስከመሆን በቅተዋል። በቅርቡ ደግሞ የክርስቶስ ተቃዋሚ ከሆነችው ቱርክ የመጀመሪያው የብሪታኒያ ጠቅላይ ሚንስትር ይሾማል። ለንደንንን ለፓክሲታን መንፈሳዊ ወንድሙ አስርክቦ ገለል ያለው የቀድሞው የለንደን ከንቲባና የቱርኩ ፖለቲከኛ አሊ ከማል የልጅ ልጅ የሆነው ቦሪስ ጆንሰን ወስላታዋን ተሪዛ ሜይን ይተካት ይሆናል።

ካሁን በኋላ የምዕራባውያኑ ምርጫ በኮሌራ እና ወረርሽኝ መሃከል ነው፤ ንስሐ ገብተው እካልተመለሱ ድረስ ሃገራቱን የሚያጠነክርና የሚጠቅም ሰው ከእንጊድህ አያገኙም።

___________________

Posted in Conspiracies, Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , | Leave a Comment »

በመቅደላ ውጊያ ከኢትዯጵያ የተዘረፉትና በለንደን የሚገኙት ፲፩ ታቦታት “በውሰት” ሊመለሱ ነው

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on May 20, 2019

የብሪቲሽ ብሄራዊ ሙዚየም ከመቶ ሃምሳ ዓመታት በፊት በነበረው የመቅደላ ውጊያ በእንግሊዝ ወታደሮች ተዘርፈው የተወሰዱት እነዚህ ታቦታት በውሰት ሊመልስ ነው።

የሙዚየሙ ሀላፊዎች ጽላቶቹን በመመለሱ ረገድ ሀሳቡን እንደሚጋሩትና የህግ ጉዳይ ሆኖ በነፃ ለመመለስ መወሰን ባይችሉም ታቦቶቾን በረጅም ጊዜ ብድር ለኢትዮጵያ አሳልፎ እንደሚሰጥ በቦታው ለተገኙት ለባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር ዶክተር ሂሩት አስታውቀዋል።

ሚኒስትሯ በሙዚየሙ የሚገኙ ታቦታት ለኢትዮጵያውያን ኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች ልዩ ክብርና ቦታ ያላቸው ከፈጣሪያቸው ጋር የሚገናኙባቸው ህያው በመሆናቸው ወደ ትክክለኛ ቦታቸው እንዲመለሱ ጠይቀው ነበር

ከእነዚህ ፲፩ ታቦታት መካከል ፱ኙ ከእንጨት ሲሆኑ ፪ቱ ደግሞ ከድንጋይ ናቸው። ሁሉም በእዚህ የብሪቲሽ ሙዚየም ድብቅ የዕቃ ቤት ውስጥ ተዘግቶባቸው እንደተቀመጡና እስከ ዛሬ ድረስ፤ ኃላፊዎቹንም ጨምሮ፤ ማንም ከፍቶ እንዳላያቸው ተጠቁሟል። ታቦታቱ ላይ ምናልባት የተቀረፀ መስቀል ሳያርፍባቸው አይቀርም ተብሏል።

በሌላ በኩል የሙዚየሙ ሃላፊዎች ኢትዮጵያን መጎብኘትና አብረው ለመሥራት እንደሚፈልጉ፣ ወደፊት ወደ ኢትዮጵያ ሲመጡም የመግባቢያ ሰነድ እንደሚፈራረሙ ገልጸዋል

የኢትዮጵያ ቅርሶች በአብዛኛው በእንግሊዝ፣ በጀርመንና በጣልያን አገር ነው የሚገኙት።

መቅደላ ወይም በአሁኑ ስሙ አምባ ማርያም የሚባለው አምባ፣ ወሎ ውስጥ የሚገኝ በአጼ ቴወድሮስ ዘመን ለዋና ከተማነት ታጭቶ በመካከሉ በእንግሊዞች ጦርነት ወቅት የተቃጠለ ከተማ ነው።

የእንግሊዝ ጦር ውድ ብራናዎችን፣አክሊሎችን፣መስቀሎችን፣የወርቅ ዋንጫዎችን፣የንጉሳዊያንና የቤተ ክርስትያን ቁሳቁሶችን ጋሻና የመሳሰሉትን ቅርሶችን በመዝረፈ ፲፭ ዝሆኖችንና ፪፻ በቅሎዎችን ለማጓጓዣነት ተጠቅመው እንደነበር መረጃዎች ያመለክታሉ። ወሰዱ።

በጣም ይገርማል! እግዚአብሔር የሰጠንን የራሳችንን ንብረት በብድር መልክ ሊሰጡን ነው። ለመሆኑ ይህን ኢትዮጵያ የተረሳችበትን ቀውጥ ጊዜ ለምን መረጡ? ዓብያተክርስቲያናት በሚቃጠሉበትና በሚዘረፉበት ዘመን? ይህ ንብረት የመንግስት ሳይሆን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቅርስና ንብረት ስለሆነ በቀጥታ የሚመለከታት ቤተክርስቲያንን ነው፤ ለምንድን ነው መንግስት ወይም የባሕል ሚንስቴር እዚህ ላይ እጁን የሚያስገባው? ምን ዓይነት ተንኮል ታስቦ ይሆን?

ወይስ ያለፈውን እና መጪውን “ቴዎድሮስን” ፈርተው ይሆን? የአፄ ቴዎድሮስ ልጅ ልዑል አለማየሁ በዊንድሶር ቤተመንግሥት በሚገኘው ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ነው የተቀበረው። ከሁለት ሣምንታት በፊት የስሴክስ ልዑልን የወለደችው የእንግሊዝ ንጉሣዊ ቤተሰብ አዲስ ደም፡ ልዕልት ሜጋን ሜርክል ባለፈው ዓመት ልክ በዚህ ጊዜ የጋብቻ ሥነ ሥርዓቷን የፈጸመችው የልዑል አለማየሁ አጽም በሚገኝበት በዚሁ በውንድሶር ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ነው።

ባለፈው ሣምንት ኢትዮጵያዊ ዝርያ ያለባት የብሪታኒያ ንግሥት ኤልሳቤጥ የልዑል አለማየሁን አጽም ለኢትዮጵያ አልመልስም ብላ ነበር። ይገርማል! እዚህ ያንብቡ

ለማንኛውም ቅዱስ ታቦታቱን ይመለሱልን እና ሕዝባችንን አደንዝዞና አሥሮ ያለውን እርኩስ መንፈስ ካገራችን ያጥፉልን! እነርሱ ለክፋት አስበውት ሊሆን ይችላል እግዚአብሔር ግን ለበጎ ያደርገዋል

የመልአኩ የቅዱስ ሚካኤል ተራዳኢነት አይለየን!

__________________

Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

እህተ ማርያም | በጣና ሐይቅ ቅዱሳን ገዳማት፡ ነጮች ማደር አይፈቀድላቸውም፡ ቅርሶቻችንን ይሠርቃሉና

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on April 21, 2018

ከጥቂት አመታት በፊት አክሱም ላይ ትንሽ ሃውልት ሰርቆ በጉያው አስገብቶ ለመውጣት ሲል አንድ አባት የያዙት የአንድ አውሮፓ ቤተ መዘክር አስተዳዳሪ ታሪክ ትዝ ይለኛል። ታሥሮ እንደነበር አስታውሳለሁ።

ትክክል ነው፤ ወደ አገራችን የሚጓዙትና እኛን የሚቀርቡን ነጮች ለእኛ በፍጹም በጎ ነገር አያስቡልንም፣ አያደርጉልንም። በእርግጥ እንደ መልአክ የሆኑ ነጮች አሉ፤ ነገር ግን ወደ እኛ የመቅረብ እድሉ የላቸውም፤ 90% የሚሆነው ነጭ ግን ለፀረ-ክርስቶሱ መንግሥት የተዘጋጀ ኤዶማዊ ነው፤ በመሪዎቹ በቀላሉ የሚነዳ ነው፡ የእኛ ጠላት እንዲሆን ተደርጎ የተኮተኮተ ነው፣ “የአፍሪቃውያን ድኽነት የእኛ ኃብት ነው፣ እነርሱ ኃብታም ከሆኑ እኛ እንደኽያለን” የሚለውን መርኾ ተቀብሎ የሚኖር ነው ።

ነጮቹም ቢሆኑ “ብሔራዊ” በሚሏቸው ቁልፍ ቁልፍ ቦታዎች ላይ አፍሪቃውያንን ማሳደር ቀርቶ፡ ለጉብኝት እንኳን አያስገቧቸውም። በየላብራቶሪው እንኳን፡ እራሳቸውን ሙሉ በሙሉ ከሸጡት ወገኖቻችን በቀር፡ ጥቁሩን አስገብተው ለማሠራት ፈቃደኞች አይደሉም። ምስጢራት ናቸው የሚሏቸውን ነገሮች ለጥቁር ሕዝቦች አያካፍሉም።

ለምሳሌ፡ በጥቁር ሰው አካል ላይ በተፈጥሮ በብዛት እንድተቀበረ የሚነገርለትን “አምላካዊ የሜላኒን ቅመም” በተመለከተ በአውሮፓ፣ አሜሪካና አውስትራሊያ በየዓመቱ ምስጢራዊ ስብሰባዎች ይካሄዳሉ፤ ነገር ግን አንድም ጥቁር በስብሰባዎቹ ተካፍሎ አያውቅም። የኢሉሚናቲዎቹ የቢልደርበርግ ስብሰባም ጥቁሮችን ያገለለ ነው። በሌላ በኩል፤ በረጅሙ የጠፈር ምርመራ ታሪክ፡ ይህን ሁሉ ዘመን፡ አንድም “አፍሪቃዊ” ወደ ጠፈር ተልኮ አያውቅም፤ አንድም! ሁሌ ተፎካካሪዎች መስለው እርስበርስ የሚጠዛጠዙትና ለጦርነት የሚዘጋጁት አውሮፓውያን፣ አሜሪካውያንና ሩሳውያን ጠፈር ላይ ቤት ሠርተው እስያዊውንና አረቡን እየጋበዙ በሕብረት “ምርምሮችን” ያካሂዳሉ። አፍሪቃውያን ግን አይጋበዙም፤ ለጠፈር ብቁ የሆነ አፍሪቃዊ ጠፍቶ ነውን? አይደለም!

የጣና ሀይቅ ገዳማት አባቶች ለሌላውም “ፈረንጅ አምላኪ” ወገናችን ትልቅ አርአያ ሊሆኑ ይገባቸዋል።

______

Posted in Conspiracies, Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , | Leave a Comment »

 
%d bloggers like this: