እንቁጣጣሽ መልካም አዲስ ፪ሺ፲፩ ዓመት
ዘመነ ሉቃስ
ዘመን አልፎ ዘመን ሲተካ
ሳር ቅጠሉ ሁሉ ሲፈካ
ዝናም በሙቀት ሊተካ
ብርሃን ጨለማን ሲተካ
እንቁጣጣሽ፡ እንቁጣጣሽ!!
ደህና ጊዜን ይዘሽ ደግሞ ደግሞ ያምጣሽ።
እርቅ ነው ፍቅር ነው ለኛ አዲስ ዘመን፡
የሚታረቀውን እናቀናለን፡ አረሙን እንነቅላለን።
፪ሺ፲ የውዲቷ ኢትዮጵያ ጠላቶች የሚያፍሩበት፡
ልዩ ዘመን ሕዝባችን የሚነቃበት።
እንቁጣጣሽ በያመቱ ያምጣሽ!
መልካም አዲስ ፪ሺ፲፩ አመት!
Happy Ethiopian New 2011 Year!
መጭው የ ፪ሺ፲፩ አመት፡ የሰላም፣ የፍቅር፣
የጤና እና የደስታ ዘመን ይሁንልን !!!
“ኢትዮጵያ በእግዚአብሔር የመሰረተችና በቅዱሳን ቃል ኪዳን የተጠበቀች፤ ከሁል በላይ ደግሞ የእመቤታችን አስራት አገር ስለሆነች እንኳን በአገር ዉስጥ ለጥፋቷ የተሰለፉ አይደለም፤ እርሷን ለማጥፋት የተሰለፉ የዉጭ መንግሥታት በሙሉ በእግዚአብሔር ቁጣ ይጠፋሉ፤ ከምድር ይጠረጋሉ። እርሷ ግን በእግዚአብሔር መንግሥትነቷ እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ ትቆያለች። ታዲያ አሁን ቢሆን “የአዲሲቷ ኢትዮጵያ መሪዎች ነን” እያሉ በኢትዮጵያና በኢትዮጵያዊነት ላይ የሚያላግጡ ሆኑ እርሷን ለማጥፋት የተሰለፉ የተለያዩ ቡድኖችና ድርጅቶች እንዲሁም መንግሥታትና ግለሰቦች ዛሬ ነገ ሳይሉ በእዉነተኛ ንስሐ ለእግዚአብሔር እጃቸዉን ቢሰጡና ወደማንነታቸዉ ወይንም ወደ ኢትዮጵያዊነታቸዉ ቢመለሱ የሚበጃቸዉ እንደሆነ በዚሁ አጋጣሚ መልእክቱን አቀርባለሁ።
ኢትዮጵያ እንኳን ዜጎቿን “ኢትዮጵያዉያን ነን” የሚሉትን ቀርቶ የዓለምን ሕዝብ ትመራለች ብንላችሁ “ኡ!ኡ!“ልትል ስለምትችህሉ የንስሐ እድሜ ካገኛችሁ ተፈጽሞ እንደምታዩ እንነግራችኋለን።”
ንቡረ እድ ኤርምያስ ከበደ ወልደ ኢየሱስ