Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • June 2023
    M T W T F S S
     1234
    567891011
    12131415161718
    19202122232425
    2627282930  
  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

Posts Tagged ‘አይ ኤስ’

እስላሞቹ የአይሲስ ሽብር ፈጣሪዎች ወደ ኢትዮጵያ ለመዝመት በመዘጋጀት ላይ ናቸው

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on August 20, 2019

ከጅማ በባድሜ በኩል ወደ ሲዳማ ፥ ለኢትዮጵያ ኩነኔን ለጠላቶቿ በረከትን ይዞ መጥቷል

የግራኝ አብዮት አህመድ እባባዊ መንገድ ይህን ይመስላል፦ በበሻሻ (ሲገለበጥ ሻሻባ = አልሻባብ)ጅማ ተወለደ፤ ይገርማል፤ ልክ በተወለደበት ዓመት የመንግስቱ ኃይለማርያም ቀይ ሽብር ጀመረከዚያም በባድሜው ዕልቂት አስፈላጊውን ልምድ ከሰበሰበ በኋላ ዛሬ በየቦታው እየተካሄዱ ያሉትን ጅሃዳዊ እና የዳግማዊ ቀይሽብር ዘመቻዎችን በመምራት ላይ ነው።

ኢትዮጵያውያን እንደ ቅጠል በሚረግፉበትና በተዋሕዶ ልጆች ላይ ታይቶ የማይታወቅ ጥቃት በሚፈጸምበት በዚህ ዘመን አብዮት አህመድ፡ በሬ ሆይ ሳሩን አየህና ገደሉን ሳታይእያለ የኢትዮጵያን በረከት ለጠላት አሳልፎ ለመስጠት እየሞከረ ነው። ሰውየው እንደ መተተኛዋ ሱዳን ጎረቤታማ ወደሆኑት ሃገራት በመመላለስ ላይ የሚገኘው የተጠነሰሰ ሴራ ስላለ ነው። የኢትዮጵያን በረከት በመንጠቅ ኢትዮጵያ ውስጥ ሁከትና ጦርነት እንዲቀሰቀስ ፥ በሱዳንና ሶማሊያ ግን ሰላምና መረጋጋት እንዲሰፍን ለማድረግ በመጣር ላይ መሆኑን እያየነው ነው። በረከቱን ለኢትዮጵያ ጠላት፤ ልክ የኢሳያስ ሻዕቢያ እና ህዋሃት የአክሱም ጺዮንን ኃይል፣ ፀጋና በረከት ለዋቄዮአላህ የኢትዮጵያ ጠላቶች አሳልፈው ለመስጠት እንደሚሞክሩት።

እንደ አልሸባብ፣ አይሲስ እና ቦኮ ሃራም የመሳሰሉት እስላማዊ ጽንፈኛ ቡድኖች በኢትዮጵያ እየታየ ያለውን የአመራር ድክመትና በጣም እየጨመረ የመጣውን የጎሳ እና የፖለቲካ አለመግባባት በመጥቀም በቀላሉ አዲስ አበባ ድረስ ለመግባት እንደሚሞክሩ ባለፈው ዓመት ላይ አስጠንቅቄ ነበር። ሁለት አንበሶች እርስበርስ ሲታገሉ የጅብ እራት ይሆናሉ። እርስበርስ በመናቆር የደከሙትን የኢትዮጵያ አንበሶች ለመብላት አያ ጅቦ ያው አሁን በሶማሊያና በሱዳን በኩል ሰርጎ ለመግባት ተዘጋጅቷል። በዚህም ላለፉት ሃያ ዓመታት በአዲስ አበባ ሰፍረው የሚኖሩት እስከ መቶ ሺህ የሚቆጠሩ“ስደተኛ ሶማሌዎች” ቁልፍ ሚና ይጫወታሉ። እንደ ቦሌ ሚካኤል አካባቢ በመሳሰሉ አካባቢዎች የሠፈሩት እነዚህ ሶማሌዎች ይህን ጂሃዳዊ ጥሪ አዋጅ የሚነገርበትን ቀን እየተጠባበቁ መሆናቸውን ከአስር ዓመታት በፊት በጦማሬ ለመጠቆም ሞክሬ ነበር።

ልብ በል ወገን፤ ይህን ዜና አሁን ያቀረበልን የአሜሪካ ድምጽ፡ ቪኦኤ ነው። እያንዳንዱ ሰው አስፈላጊውን መረጃ በቀላሉ አግኝቶ በስማርት ስልኩ ተነቀሳቃሽ ምስሎችን መቅረጽ በሚችልበት በዚህ ዘመን፤ ዛሬም ቁልፍ የሆኑትን መረጃዎች እያቀረቡልን ያሉት የአሜሪካ ድምጽየጀርመን ደምጽ እና ቢቢሲ ራዲዮዎች ናቸው። እንዴት? ለምን? ብለን እራሳችንን ስንጠይቅ ሁሉም ነገር በእነዚህ ሃገራት የተቀነባበረ መሆኑን እንረዳለን።

እነዚህ የሳጥናኤል ሃገራት የሚፈልጉትን አገርወዳድ ያልሆነ መሪ ስልጣን ላይ ያስቀምጣሉ፤ ሃገሪቱንም በማድከም ችግርና ግጭት እንዲፈጠር ያደርጋሉ፣ ስለችግሩ የሜዲያ እና መንግስታዊ ያልሆኑተቋማቶቻቸው ኡ!! በማለት እንዲያበስሩ ያደርጋሉ፤ ከዚያም ወታደሮቻቸውን (የተባበሩት መንግስታትን ጨምሮ፟) ወደ ሃገራችን ይልካሉ፤ ልክ እንደ ባደሜው ግጭት። መመሪያውን፡ “ችግርምላሽ መፍትሔ / “Problem – Reaction – Solution” ብሎት የለ ተንኮለኛው ፈላስፋ ጆርጅ ሄገል።

_____________________

Posted in Ethiopia, Faith, Infos | Tagged: , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

 
%d bloggers like this: