ቦሊቪያ እንደ ጋና የሉሲፈራውያኑ ኮከብ ያረፈበትን አረንጓዴ፣ ቢጫና ቀይ ባንዲራ ስላልመረጠች ጥንታውያኑ አ‘ይ‘ማራ ነዋሪዎቿ የኢትዮጵያን ሕዝቦች ስቃይ በመጋራት ላይ ናቸው።
በጥንታዊው ክርስትና፣ በጥንታውያን ሕዝቦች እና በኢትዮጵያ የማርያም መቀነት ቀለማት ላይ የሚካሄድ የቀለም አብዮት
በጣም የሚያስገርም ዘመን ላይ እንገኛለን ፥ በርግጥ ዓለማችን ትንሽ ሆናለች።
የኢትዮጵያን ቀለማት የያዙት ቦሊቪያውያን የሉሲፈራውያኑ ተቋም ሲ.አይ.ኤ ያካሄደውን መንፈቅለ መንግሥት በጥብቅ በመቃወም ላይ ይገኛሉ። ሆን ተብሎ በርዕዮተ ዓለም እንድትከፋፈል የተደረገችው ደቡብ አሜሪካዋ ቦሊቪያ ልክ እንደ ቺሌና ቬኔዝዌላ ታይቶ በማይታወቅ የእርስበርስ ጦርነት ተናውጣለች። ብዙዎች ተገድለዋል። ሉሲፈራውያኑም በአጭር ጊዜ ውስጥ እራሳቸው ያስቀመጡትን “አብዮታዊ ዲሚክራሲያዊ” ፕሬዚደንት ኢቮ ሞራሌስን ከስልጣን እንዲወገድና እራሳቸው በመረጧት ሴት እንዲተካም አድርገዋል።
ተመሳሳይ ሁኔታም በአረንጓዴ፣ ቢጫ እና ቀይ ቀለማቱ ባለቤት በሃገረ ኢትዮጵያ በመታየት ላይ ነው።
ከሰባት ዓመታት በፊት(መለስ ዜናዊን ሲገድሉት) በኢትዮጵያ ሃገራችንም ተመሳሳይ መፈንቅለ መንግስት(መፈንቅለ ሥርዓት) በሉሲፈራውያኑ ተካሄዶ ነበር። 666ቱ ገዳይ አብዮትም የዚህ መፈንቅለ ሥርዓት ልጅ ነው። የሁለቱ መፈንቅለ ሥርዓታት ዓላማም ሃገራዊ፣ ብሔራዊ፣ ክርስቲያናዊ እና የጥንት የሆነውን ነገር ሁሉ ሙሉ በሙሉ ማስወገድ ነው። በኢትዮጵያ “አማራ እና ትግሬ” የተባሉትን ጥንታውያን ኢትዮጵያውያንን ፥ በቦሊቪያ ደግሞ ጥንታዊ የሆነውን የአ‘ይ‘ማራ ነገድ ከእናት ሃገራቸው ማጥፋት ነው። ልክ መለስ ዜናዊን እና አብዮት አህመድን በኢትዮጵያ እንዳዘጋጇቸው ፥ በቦሊቪያም ከአ‘ይ‘ማራ ነገድ የሆነውን የቀድሞ ፕሬዚደንትን ኢቮ ሞራሌስን ሤረኛ በሆነ መልክ አዘጋጅተውታል።
በደቡብ አሜሪካዎቹ ቦሊቪያ፣ ቺሌ እና ፔሩ የሚገኙትና “Pueblos Indiginas / ፑዌብሎስ ኢንዲኺናስ” በመባል የሚታወቁት ጥንታውያኑ የአገሬው ሕዝቦች መጠሪያቸው “አይማራ” ነው። 11 ሚሊየን ነዋሪዎች ባሏት ቦሊቪያ የአይማራ ሕዝብ ቁጥር 1.5 ሚሊየን ወይም 20% ይጠጋል። አብዛኛው የቦሊቪያ ነዋሪ ከአውሮፓውያን ጋር የተካለሰ ሲሆን ለረጅም ጊዜ ስልጣኑንም የያዘው እነዚህ “ሜስቲዞስ / ክልሶች” የሚባሉት ናቸው። ቦሊቪያን እንደ አይማራ ከመሳሰሉት ያገሬው ጥንታውያን ነዋሪዎች ለማጽዳት ዘር ከመከለስ እስከ ምግብና ውሃ መበከል ያልተሞከረ የዘር ማጥፋት ዘመቻ አልነበረም።
ከአሥር ዓመታት በፊት ሉሲፈራውያኑ የዓለማችን ፈላጭ ቆራጮች ለመጀመሪያ ጊዜ ከዚሁ የአይማራ ነገድ የወጣውን የአገሪቷን መሪ “ኢቮ ሞራሌስን” ሥልጣን ላይ አወጡት። ምንም እንኳን ኢቮ ሞራሌስ የአይማራ ነገድ ይሁን እንጅ ተጠሪነቱ ግን ለሉሲፈራውያኑ ነው። የአሜሪካ ተቀናቃኝ እንዲሆን (የሚቆጣጠሩት ተቀናቃኝ / Controlled Opposition) ብሎም የሶሺያሊስታዊ ሥርዓት አራማጅ እንዲሆን አዘዙት። አሁን ልክ ጊዜው ሲደርስ ከስልጣን አስወገዱት፤ በከፊሉ የቦሊቪያ ሕዝብ ዘንድ ተወዳጅነትንም እንዲያተርፍ ስላደረጉት አሁን እየታየ ያለው ህውከት ሊፈጠር ቻለ።
በሃገራችንም ከዚህ የከፋ ህውከት ከመጪው ግንቦት “ምርጫ” በኋላ ሊፈጠር እንደሚችል ለማወቅ ሊቅ መሆን አይጠበቅብንም።
ከሃያ ዓመታት በፊት በኦርቶዶክስ ክርስቲያኗ ሰርቢያ (የቀድሞዋ ዩጎዝላቪያ) የጀመረው የሉሲፈራውያኑ “የቀለም አብዮት” ጥንታውያን እና ኦርቶዶክስ ክርስቲያን በሆኑት ሕዝቦች ዘንድ እንዲቀጣጠል ነው እየተደረገ ያለው። ከኦርቶዶክስ ሰርቢያ ወደ ኦርቶዶክስ ጆርጂያ፣ ዩክሬይን እና ሩሲያ እንዲቀጥል ተደርጓል።
አዎ! የሳጥናኤል ግብ ኢትዮጵያ ነው። ዲያብሎስ ተዋሕዶ ክርስትናን እና ሰንደቅ ዓላማችን በጣም ይጠላቸዋል፣ ይፈራቸዋል። ይህን በሃገራችን እያየን አይደለም?! የክርስቶስ ተቃዋሚዋ ቱርክ እንኳን የኩርድ ሕዝብን በመጨፍጨፍ ላይ ያለቸው ኩርዶች የኢትዮጵያን ቀለማት በመያዛቸው ነው።
የአንድን ሕዝብን ዘር ሙልጭ አድርጎ በማጥፋት የሺህ ዓመታት ልምዱ ያላቸው ቱርኮች እና አረቦች ወደ ኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን ወደ ቦሊቪያ እና ቬኔዝዌላም ርቀው በመጓዝ እየሠፈሩ ነው። እነዚህ የመጥፎ ዜና እና ጥፋት መልዕክተኞች ከምዕራባውያኑ ረዳቶቻቸው ጋር በማበር የኢትዮጵያን ክርስቲያኖች ደም አፍስሰው ለዋቄዮ–አላሃቸው እንደሚገብሩት በቦሊቪያም “አ‘ይ‘ማራ የተሰኘውን ጥንታዊ ሕዝብ ለዚሁ ሰይጣናዊ ተግባር መፈጸሚያ ለማድረግ በመዘጋጀት ላይ ናቸው።
ኢቮ ሞራሊሰ ከስድስት ወራት በፊት ቱርክን በመጎብኘት የመጀመሪያው የቦሊቪያ ፕሬዚደንት ለመሆን በቅቶ ነበር።
የሚገርም ነው፤ በሃገራችን አማራ፤ በቦሊቪያ አ‘ይ‘ማራ። ሁለቱም በአሁኑ ሰዓት የተዳከሙ ሕዝቦች ናቸው። ልዩነቱ ግን የኢትዮጵያ አማራ የደከመው ኢትዮጵያዊነቱ ስላልጠነከረ/ በኢትዮጵያዊነት ስላልተጠናከረ፣ የአባቶቹን ነፍጠኛነት በመርሳቱ ሲሆን የቦሊቪያዎቹ አ‘ይ‘ማራዎች ግን በአ‘ይ‘ማራነታቸው ስላልጠነከሩ/ስላልተጠናከሩ ነው። ከአማራ በፊት ኢትዮጵያ ስትቀድም ከቦሊቪያ በፊት ግን አ‘ይ‘ማራ ይቀድማል።
በኢትዮጵያ በአማራ ላይ እየተካሄደ ያለው ጥቃት ነዋሪዎቹ “አማራ” በመሆናቸው ሳይሆን አማርኛ በመናገራቸው፣ ተዋሕዶ ክርስቲያን በመሆናቸው፣ አረንጓዴ፣ ቢጫና ቀይ ሰንደቅ ዓላማ በማውለብለባቸው፤ ባጠቃላይ ኢትዮጵያዊ በመሆናቸው ነው። “ትግሬ” የሚባለውም በትግሬነቱ ሳይሆን ጥቃት የሚፈጸምበት በጥንታዊው ኢትዮጵያዊነቱ እንጂ። እነዚህ ኢትዮጵያውያን ከዚህ ኢትዮጵያዊነታቸው እስካልተላቀቁ ድረስ ጥቃቱ ይቀጥላል። ስለዚህ በተቻለ መጠን አማራነት ኢትዮጵያዊ ባልሆነ አማራነት፣ ትግሬነት ኢትዮጵያዊ ባልሆነ ትግሬነት እንዲቀየሩና እንዲዳብሩ ይደረጋሉ። ትናንትና ኤርትራ ዛሬ ደግሞ ትግራይ እና ኦሮሞ በተባሉት የኢትዮጵያ ክፍለሃገራት የተደረገው ነገር ይህ ነው።
“አብን” የተባለው ፓርቲ ገና ሲቋቋም “ኡ! ኡ! ዋይ! ዋይ!” ብዬ ነበር። በዘውግ የተደራጀ “አማራ” የተሰኘው ሕዝብ በአማራነት ከኢትዮጵያ የሚነጥል ሤር መጠንሰሱን ከውዲሁ ይታየኝ ነበር። የደከመው አማራ ላይ ቶሎ ጥቃት የፈጸሙት፣ “መሪዎች” የሚሏቸውን ልሂቃን የገደሉትን እና የአብን አመራራትን ወደ እስር ቤት የከተቱት አማራ የሚሉት ነዋሪ ተቆጭቶና ተነሳስቶ ኢትዮጵያዊነቱን እንዲተውና ኢትዮጵያን የከዳ የአማራ ሃገር እንዲገነባ ነው።
“አብን” የተሰኘው ፓርቲ ሰሞኑን ከኢትዮጵያ ቀንደኛ ጠላት ከሆኑ ኦነጎች ጋር በአንድ ጠረጴዛ ዙሪያ መቀመጡ ይህን የፀረ–ኢትዮጵያ የሆነ አካሄድ ነው የሚጠቁመን። ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ ፓርቲዎች ሁሉም በፀረ–ኢትዮጵያ ኃይሎች የተደራጁና በጠላቶቻችን ባትሪ የሚሞሉ ሃገር አጥፊዎች ናቸው። አሁን በአብን እና በኦነጎች መካከል የተፈጠረው ግኑኝነት ከሰላሳ ዓመታት በፊት በህዋሃት እና ኦነግ መካከል ተካሂዶ የነበረውን ጋብቻ ያስታውሰኛል። ያኔም የጥፋት ኦርኬስትራውን ሲመሩ የነበሩት ምዕራባውያኑ ሉሲፈራውያን ነበሩ ፥ ዛሬም እየመሩ ያሉት እነርሱው ናቸው።
“በሠላሳ ዓመት ውስጥ ኦሮሞው እና ትግሬው ከኢትዮጵያዊነት እንዲርቅ ተደርጓል ፥ በመጭዎቹ ሰላሳ ዓመታት ደግሞ አማራው ኢትዮጵያዊነቱን እርግፍ አድርጎ እንዲተው ይደረጋል፤ ያኔ ኢትዮጵያ የምትባል ሃገር እትኖርም፣ ተዋሕዶ ትጠፋለች፣ አረንጓዴ፣ ቢጫ እና ቀይ ቀለማቱም ወደ ጥቁርነት ይቀየራሉ” የሚል ነው እቅዳቸው። ግን ብዙ መስዋዕት ያስከፍለናል እንጂ ይህ እቅዳቸው አይሳካላቸውም።
ስቃዩና ዕልቂቱ እንዲቀነሱ ግን ባፋጣኝ “አማራ” እና “ትግሬ” የተባሉት ነገዶች ልሂቃቃናቶቻቸው ለዘመናት ለፈጸሙባቸው በደሎች ብድር ከመመላለስ በመቆጠብና እርስበርስ ይቅር በመባባል ባፋጣኝ መተባበር ይኖርባቸዋል። ይህ በአማሮችና ትግሬዎች ላይ የመጣ የህልውና ጉዳይ ብቻ ሳይሆን፤ ከምጽዋ እስከ ሞያሌ ያሉትን ሌሎቹን “ደካማ” ኢትዮጵያውያን ነገዶችን አንስፍስፎ ከመጣው የዋቂዮ–አላህ ሠራዊት መከላከል ብሎም ኦሮምኛ ተናጋሪ ኢትዮጵያውያንን ከዚህ አውሬ ኃይል ማዳን መቻል ስለሚኖርባቸው ነው።
በሃገራችን፣ በቤተክርስቲያናችን እና በሰንደቅ ዓላማችን ቀለማት ላይ የተነሱትን የዲያብሎስ ቡችሎች ቅዱስ ሚካኤል በሰይፉ ቆራርጦ ከእግራችን ስር ይጣልልን!
ኢትዮጵያውያንን በተበከለ “የፈረንጅ ዶሮ” የሚመርዙት አላሙዲን እና ቢል ጌትስ በቦሊቪያም ተመሳሳይ ፕሮጀክት ለመፈጸም አቅደው እንደነበርና ቦሊቪያም ከልክላቸው እንደነበር ከሚከተለው ቪዲዮ ጋር በተያያዘ አውስቼ ነበር፦