Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • April 2023
    M T W T F S S
     12
    3456789
    10111213141516
    17181920212223
    24252627282930
  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

Posts Tagged ‘አውሮፓውያን’

የክርስቶስ ተቃዋሚ ቱርክ ኢትዮጵያውያንን በማሳረድ ዛሬም መሪነቱን ይዛለች | የሰው ቄራ

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on September 29, 2020

ወገን በሃገሩ መፈናቀሉ፣ መታገቱና መጨፍጨፉ አልበቃውም፤ እነ ግራኝ ኩላሊቱንና መቅኒውን ይዘርፉበት ዘንድ ለቱርኮችና አረቦች አሳልፈው በመስጠት ላይ ናቸው። ይገድሉሃል፣ ኩላሊትህን ይሰርቁብሃል ከዚያም አካልህን ወደ በርሃ ለጥንብ አንሳ ይጥሉታል።

ወንድማችን እየነገረን ያለው ነገር ሁሉ ትክክል ነው፤ ይህ እጅግ በጣም አንገብጋቢ የሆነ ጉዳይ ነው።

ከሁለት ዓመታት በፊት ባቀረብኳቸው ጽሑፎች “ኢትዮጵያውያን በዓለማችን ካሉ ጥቂት ጤናማ ሕዝቦች መካከል እንደሚመደቡ እንደሚከተለው አውስቼ ነበር፦

“ኢትዮጵያውያን በዓለም በጣም ጤናማ ከሆኑ 10 ሕዝቦች መካከል ተመድበዋል”

“ክሊኒክ ኮምፔር የተባለው የእንግሊዝ ድህረገጽ ባወጣው መረጃ እንደ መለኪያ አድርጎ የወሰደው፦

1. አልኮሆል መጠጣት

2. ሲጋራ ማጤስ

3. ውፍረት

አልፎ አልፎ ጤናማ የሆኑ ሊቃውንት አይታጡም፤ ይህ ሙሉ በሙሉ የምስማማበት ጥናት ነው። ስጋዊውን ጤንነት የተመለከተ ነው፤ መንፈሳዊውን ጢንነት ያካተተ ቅን ጥናት ቢያካሂዱማ አገራችን የመጀመሪያውን ደረጃ እንደምትይዝ የሚያጠራጥር አይደለም።

የጥንቶቹ ግሪካውያን ረጅም እድሜ የሚያስገኘው የመጠጥ ውሃ የሚገኘው በኢትዮጵያ ነው በማለት ይናገሩ ነበር። ድንቁ የሩሲያ የእጽዋትና የጄኔቲክስ ባለሙያ እንዲሁ ዓለማቀፋዊ አሳሽ፡ ኒኮላይ ቫቪሎቭም ኢትዮጵያና አፍጋኒስታን የስልጣኔ ምንጭ መሆናቸውን ከመቶ ዓመት በፊት ጠቁሞ ነበር።

ጂም ውስጥ ዱብዱብ ማለቱ ጥሩ ቢሆንም ከዚህ ጥናት ጋር ግን የተዛመደ አይደለም።

ለማንኛውም፡ አደራ፣ የተሰጠንን ምርቃትና በረክቱን በበርገር እንዳንለውጥ፣ ዔዶማውያንና እስማኤላውያን ዳር ዳር እያሉ ነው!“

እንግዲህ አሁን እንደምናየው ዔዶማውያኑ እና እስማኤላውያኑ “ዳር ዳር” ማለቱን ተሻግረው አሁን በሃገራችንና በሕዝባችን ውስጥ ሰርገው ገብተዋል። ይህ ጉዳይ ከረጅም ጊዜ በፊት ታቅዶና በደንብ ተጠንቶበት የቆየ ጉዳይ ነው።

እንደ እኔ እይታ ከሆነ የኢትዮጵያ ውድቀት እና ውርደት የተካሄዱባቸው ዘመናት በሦስት ይከፈላሉ፦

👉 1ኛው ዘመን፦ ፮ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ፤ አረቦቹ የመሀመድ ተከታዮች ኢትዮጵያ እንዲገቡ ሲደረጉ

👉 2ኛው ዘመን፦ ፲፮ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ፤ ቱርኮቹ የመሀመድ ተከታዮች በግራኝ አህመድ በኩል ኢትዮጵያን እንዲያደክሙና አጋሮቻቸው የሆኑትን ጋሎችን ወደ ኢትዮጵያ ምድር ሲያስገቧቸው

👉 3ኛው ዘመን፦ ፲፱ኛው መቶ ክፍለ ዘመን፤ ኢትዮጵያ በብሔር ብሔረሰብ እንድትከፋፈልና የአህዛብን ጥበብ ሙሉ በሙሉ ለመቀበል ፣ ነገስታቱ እና መሪዎቹም ሁሉ በዔዶማውያኑ እና እስማኤላውያኑ ተጽዕኖ ሥር ለመሆን ሲወስኑ

ከአምስት መቶ ዓመታት በፊት ከተዘረጋው የጥፋት መንገድ ብንጀምር እንኳን የክርስቶስ ተቃዋሚ ቱርክ ግራኝን ከማሰማራቷ በፊት በደቡቡ የኢትዮጵያ ክፍል (በዛሪዎቹ ሶማሊያ እና ኬኒያ) አስቀድማ ሶማሌዎችን ከደቡብ አረቢያ/ የመን፣ ጋላዎችን ከዛሪዋ ታንዛኒያ (ታንጋኒካ + ዛንዚባር) አካባቢ በማምጣት አሰፈረቻቸው፤ ጊዜው ሲደርስ ግራኝን አህመድን አነሳስታ በክርስቲያን ኢትዮጵያ ላይ የጥፋት ጂሃዱን አካሄደች። ዛሬ እየተካሄደ ያለው ከዚያ ዘመን የቀጠለው ጂሃድ ነው። በሀሰተኛው ነብይ መሀመድ ዘመን ጀመረ፣ በግራኝ አህመድ ቀዳማዊ ዘመን ቀጠለ፣ ዛሬ በግራኝ አህመድ ዳግማዊ ዘመን በመጧጧፍ ላይ ይገኛል።

በመጀመሪያዎቹ ሁለት ዘመናት ስጋን ለመግደል የተካሄዱ ጂሃዶች ነበሩ፤ በዚህ ዘመን ጂሃድ ግን በግራኝ አህመድ አሊ የሚመሩት የዋቄዮአላህ አርበኞች ስጋን ብቻ ሳይሆን ለመግደል የተነሱት፤ እራሳቸውን “አምላክ” አድርገው ነፍስንም ለመንጠቅ፣ ከአካላትም ኩላሊትን፣ ልብን፣ መቅኒን፣ ደምን፣ ጥርሶችን ለመዝረፍ ነው።

ኢትዮጵያውያን በነፍሳቸውም በስጋቸውም በጣም ጤናማ ስለሆኑ በዔዶማውያኑ እና እስማኤላውያኑ ዘንድ በጣም ይፈለጋሉ። ለማመን የሚከብድ ነው፡ ግን፤ ፹፭/ 85 በመቶ የሚሆኑት አውሮፓውያን እና አሜሪካውያን (ዔዶማውያን) እንዲሁም ፺፭ / 95 በመቶ የሚሆኑት አረቦች፣ ቱርኮች፣ ኢራኖች (እስማኤላውያን) ከባዮሎጃዊ/ስጋዊ ማንነት አንጻር “ሰብአዊ” አይደሉም፤ ማለትም የስው ልጅ ማንነት የላቸውም፣ እጅጉን ስለተበከሉ ከሰው ዘር አይመደቡም። ዒዶማውያኑን የሚመገቧቸው ምግቦች፣ የሚጠጧቸው ውሃዎች፣ የሚወስዷቸው “መድኃኒቶች” እንዲሁም አየሩ ለውጠዋቸዋል ፥ በእስማኤላውያኑ ዘንድ ደግሞ ለረጅም ጊዜ ሰፍኖ የሚታየው የእርስበርስ/ ዝምድና ጋብቻ ሥርዓት፤ ማለትም ከወንድም ከእህት፣ ከአጎትና አክስት መወላለድ፣ (Incest) ፣ እስልምናው፣ ሃላል ምግቡ፣ በርሃው፣ ሙቀቱ፣ የሕይወት እስትንፋስ የሌለው አየሩ ሁሉ የሰው ልጅ ማንነት እንዳይኖራቸው አድርገዋቸዋል። በሁለቱም ዘንድ ግብረ-ሰዶማውያን እየበዙ መምጣታቸው አንዱ ማሳያ ነው።

የሰው ልጅ ማንነት ያላቸው ፣ የአዳም ዘር በውስጣቸው የሚገኝባቸው ሁለት የዓለማችን ሕዝቦች ኢትዮጵያውያን እና በደቡብ አፍሪቃ እና ናሚቢያ የሚገኙት ሳን/ ኮይሳን የተባሉት ሕዝቦች ብቻ ናቸው፤ ይህንም የአንትሮፖሎጂ/ጄነቲክስ ሳይንስ ሳይቀር ያረጋገጠው ነው። እንደ ዔዶማውያኑ እና እስማኤላውያኑ ከሆነ እነዚህ ጥንታውያን ሕዝቦች መጥፋት አለባቸው። ስለዚህ የሞት ፍርድ ከተፈረደብን ሰነባብቷል። የደቡብ አፍሪቃዎቹ ሳን ሕዝቦች ብዙም አልቀሩም፤ ጠፍተዋል ማለት ይቻላል፤ እስካሁን ያልተቻላቸው ኢትዮጵያውያኑን ነው፤ እነርሱንም ለማጥፋት ከውጭ ሆነው ብዙ ሞከሩ አልተሳካላቸውም፤ አሁን ግን ለአምስት መቶ ዓመታት ባዘጋጇቸውና የኢትዮጵያ አስኳል ውስጥ ሰርገው እንዲገቡ በተደረጉት ጋሎች አማካኝነት ህልማቸውን በማስተገበር ላይ ይገኛሉ።

ወንድማችን ቪዲዮው ላይ እንደሚጠቁመን፤ በጂማ እባብ ጂፋር ዘመን ሲካሄድ የነበረው የባርነት ንግድ ዛሬም በዘመነ ግራኝ አብዮት አህመድ እየተካሄድ ነው። ወደ መርካቶ ሂዱና ኢትዮጵያውያንን ለአረቦችና ቱርኮች የሚሸጡትን ወኪሎች ተመልከቱ፤ ሁሉም በዋቄዮ-አላህ ባሪያዎች የተያዙ ናቸው። ባለፈው ዓመት ላይ ይህን ለማጣራት ሄጄ ነበር፤ አንዱ ቢሮ ውስጥ ገብቼ ስጠይቀው ይናገረው የነበረው ነገር ሁሉ አንገፍግፎኝ ጠረጴዛውን ገለባብጬበት ነበር የወጣሁት። እነዚህ እርጉሞች ከፍተኛ የመንግስት ተብየው ክፍል እርዳታ ይደረግላቸዋል። ዲያብሎሳዊ ዓላማቸው ገና ብዙ ነው። ዔዶማውያኑ የህዝብ ቁጥሯ አነስተኛ የሆነውን ሊቢያን ያለምክኒያት አለመሰቃቀሏትም። ተቀዳሚው ፍላጎታቸውም የነዳጅ ዘይትና ጋዝ ለመውሰድ ሳይሆን፤ ሊቢያን አንድ ትልቅ እርሻ ማድረግ ነው፤ አዎ! የሰው ልጅ አካላት የሚመረትበት/ የሚሰረቅበት እርሻ። በግብስ ሲናይ በርሃ የሚደረገውን ነገር በጥቂቱም ቢሆን ሰምተናል፤ በሊቢያ የሚካሄደው ነገር ሁሉ ግን ታፍኗል። በሊቢያ በርሃ በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ አፍሪቃውያን ለኩላሊት፣ ጉበት፣ መቅኒ፣ እና ልብ ነጠቃ እንደ ከብት ታግተው ይገኛሉ። ቱርክ እና ግብጽም ሆን ተብሎ ወደተፈጠረው የሊቢያ ግጭት ጣልቃ እንዲገቡ መደረጉ ዋናው ለዚህ ተግባር ነው። አውሮፓውያን እያረጁና ክፉኛ እየታመሙ ነው የመጡት ስለዚህ ያገግሙ ዘንድ አንድ የአካላት መለዋወጫ ጣቢያ ለአውሮፓ ቀረቤታ ባላት በሊቢያ ማቋቋም በቅተዋል።

ኢሳያስ አፈወርቂ እና አብይ አህመድ ኢትዮጵያውያኑን በባርነት ለአረቦችና ለቱርኮች ይሸጣሉ፣ እራሳቸውን ለመሸጥ ዝግጁ ያልሆኑትንም ደግሞ ሰላምን፣ ፍቅርን እና ምቾትን በመንፈግ ከሃገራቸው እንዲወጡና እንዲሰደዱ ያደርጓቸዋል፤ ቱርኮችና አረቦች ኢትዮጵያውያኑን ተቀብለው በማረድ ኩላሊታቸውን፣ ጉበታቸውንና መቅኒያቸውን አውጥተው ለዔዶማውያኑ እና እስማኤላውያኑ እየሸጡ በብዙ ቢሊየን ዶላር ያካብታሉ። በተለይ ምንም ዓይነት የተፈጥሮ ኃብት (ነዳጅ ዘይት፣ ማዕድን) የሌላት ቱርክ አሁን ከፍተኛ የምጣኔ ኃብት ቀውጥ ላይ ነው የምትገኘው። ስለዚህ እንደ አንድ “ጥሩ” የምጣኔ ኃብት ሞተር አድርጋ የወሰደችው ይህን በጣም እርኩስ የሆነ የባርነትና የሰው ልጅ አካል ነጠቃ ንግድ ነው። ዱሮም ይህ የባርነት ንግድ ነበር መሀመዳውያኑን ሊያጠናክራቸውና በየሃገሩ እንዲስፋፉ የረዳቸው።

ምናለ በሉኝ፤ የአርመኖችና ግሪኮች ክርስቲያን ወገኖቻችን ሃገር የነበረችውና ዛሬ ቱርክ ተብላ የተጠራቸው የግራኝ አህመዶች ሞግዚት ሃገር፡ ወይ በከፍተኛ የመሬት መንቀጥቀጥ ሙሉ በሙሉ ትወድማለች፤ አሊያ ደግሞ ሩሲያ ታጠፋታለች።

____________________________

Posted in Conspiracies, Ethiopia, Health, Infos | Tagged: , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

አሳሳቢ አዲስ መረጃ | አንዳንድ የ ኢትዮጵያ ወጣቶች በገንዘብ እየተገዙ ወደ እስልምና ለመለወጥ እየተገደዱ ነው

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on November 18, 2018

ይህ ወደ ሲዖል የሚያስገባ ወንጀል ነው!

አንድ ማንንታቸውን ማሳወቅ ያልፈለጉ ክርስቲያን እንደገለጹት ከሆነ ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ ወጣት ዜጎች በገንዘብ እየተገዙ ወደ እስልምና ለመለወጥ እየተገደዱ ነው። ሥራን ትምህርትን ቤቶችን እና ሌሎች  ድጋፎችን ከሙስሊሞች በማግኘት እየተገዙ ነው።

ክርስቲያኖች ድህነትን ለማምለጥ ሲ ወደ ሙስሊም ሃይማኖ እንዲቀላቀሉ እየተደረገ ነውበማለት የካቶሊክ እርዳታ ሰጭ ድርጅት መሪ ተናግረዋል።

የሙስሊም አሠሪዎች ወጣት ታዳጊዎችን እያደኑ ነው ስኮላርሽንስ የሥራ ዕድል ወዘተ ….እንደሚሰጣቸው ቃል እየገቡላቸው ነው።”

የስራ አጥነት በኢትዮጵያ ውስጥ በጣም ከፍተኛ ነው፤ ስለዚህ ይህ ለወጣቶች በጣም ማራኪ ነው።” ስራ ከፈልግክ እንደዚህ መኖር ይኖርብሃል” ተብለው ይነገራሉ ፥ ወጣቶቹ ግቦቻቸው ናቸው።”

ሥራ ማግኘት ይችሉ ዘንድ በመንገዶች እና በመንደሮች መሻገሪያዎች ላይ በመቶዎች እንዲያውም በሺዎች የሚቆጠሩ ወጣቶች በሰልፍ በመጠባበቅ ላይ ይገኛሉ።፣

የማዕድን ማውጫ ቦታዎች ሙስሊም የሆነ ሰው ብቻ ስለሚቀጥሩ ወጣት ክርስቲያኖች ከእምነታቸው ወጥተው ቋሚ ሥራ እንደሚሰጣቸው ቃል ይገቡላቸዋል።”

በአንድ ሀገረ ስብከት የእምነበረድ ማዕድን እና የወርቅ ማዕድን ውስጥ ባለሀብቶቹ ሙስሊሞቹ ናቸው።

ስለዚህ ሥራ የሚሰጣቸው ሙስሊም የሆኑት ብቻ ናቸው።

ወጣቶች ሥራ ሲፈልጉ ወይም ቤት የሚፈልግ ከሆነ ሃይማኖታቸውን እንዲቀይሩ ይገደዳሉ።

ወደ እስልምና ከቀየሩ ቤቶችን ለመግዛት እርዳታ ይሰጣቸዋል።”

የሃይማኖት መሪዎቹ በተጨማሪ እንደገለጹት፡ “10 ሙስሊም ቤተሰቦች የሚኖሩበት አካባቢ ካለ መስጂዶች ይገነባሉ፥ አዳዲስ አብያተ ክርስቲያናትን መገንባት ግን አስቸጋሪ ነው።

ገንዘ እንደ ሳውዲ አረቢያ ሉ የውጭ አገሮች ነው የሚመጣው።

በተጨማሪም ሙስሊሞች በሃገረ ስብከቱ ውስጥ የሚኖሩትን እምነትአልባ ማሕበረሰቦች አባላትን ለመሳብ የገንዘብ ጉቦ ይሰጧቸዋል። እስልምና ውጊያውን በገንዘብ በማጧጧፍ ላይ ነው ፤ ትምህርትን፣ ስራዎች ወይም ሌሎች እገዛዎችን በማድረግ ተስፋ በመስጠት ያታሉሏቸዋል።

የክርስትያኖ መሪ እነኚህን የአገሬው ሰዎች ለመማረክ በሥራ ላይ የዋለው ገንዘብ ከውጭ አገር የሚመጣ መሆኑን ይጠቁማሉ።

በተለምዶ ክርስቲያኑ እና ሙስሊሙ ተስማምቶ በኖረባት ኢትዮጵያ አሁን የሃገሪቷ ኢስላማዊ ህብረተሰብ ላይ የአረብ አገራት ተፅእኖ እየጨመረ እንደመጣ መጥቷል፤ አሳሳቢ ነው።”

ቀጥተኛ ጥቃት ወይም ቀጥተኛ ግጭት ባይኖርም፤ ግን ይህ በጥቂት አመታት ውስጥ ሊለወጥ እንደሚችል ፈርተናል በግብፅ እና በአቅራቢያ ባሉ ሌሎች ስፍራዎች ውስጥ ያለውን ሁኔታ አይተናልና።

ብለዋል የክርስቲያኖቹ መሪ።

ምንጭ

ይህ መረጃ እንከን አይወጣለትም፤ በአገራችን እየተደረገ ያለው ይህ ነው። ቀደም ሲል በጎዴና ጂጂጋ አካባቢ የሚኖሩ የተዋሕዶ ሕፃናት ተዋሕዶ ሕጻናቱ ተገድደው እንዲሰልሙ መደረጋቸውን እዚህ ላይ አቅርቤው ነበር፦

በ አንቦ አካባቢ የተዋሕዶ ሕፃናትን በየጎረቤቱና ትምህርት ቤቱ እየበከሏቸውና እያኮላሿቸው እንደሆነ ባለፈው ሳምንት ላይ አንድ እውቀቱ ያላቸው እናት ጠቁመውኛል።

አሁንማ ጦር ያልያዘው ግራኝ አህመድ ፪ኛ ስልጣን ላይ ወጥቷል በማለት መንገዱ በሰፊው ተከፍቶላቸዋል፤ ገንዘቡም ከአረቢያና ቱርክ ይጎርፍላቸዋል ያለው።

ተዋሕዶ ክርስቲያን ወንድሞችና እህቶች ቀዝቃዛ ጦርነት ታውጆብናል፤ ንቁ እንንቃ! በአሁኑ ዘመን ወገንን ከእስልምና አደጋ ከመከላከል የበለጠ ፃድቅ የሆነ ሥራ የለም፤ አንድ ኢትዮጵያዊ እስላም ወይም ጲንጤ መሆን የለበትም፤ የውድቀት ውድቀት ነውና!

የሮማው ጳጳስ ፍራንሲስኮ ከሁለት ዓመታት በፊት ኦርቶዶክስ ጆርጂያ እና አርሜኒያን ሲጎበኙ አንድ ሃቅ ተናግረው (የተበላሸም ሰዓት በቀን ሁለቴ ትክክል ነውና) ነበር፦

ኦርቶዶክስ ክርስቲያኖችን ወደ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ቀይሩ ማለት የለብን፤ ይህ ትልቅ ኃጢዓት ነው የሚሆንብን እና”

አዎ! ኢትዮጵያ ውስጥ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶን ለመዋጋት ቀድማ ገብታ የነበረችው የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ነበረች፤ ነገር ግን በኢትዮጵያ የካቶሊክ እምነት ተከታዮች ቁጥር በጣም ዝቅተኛ ነው። ምክኒያቱ ካቶሊኮች የተዋሕዶ ልጆችን ማደን ድሮ ነው ያቆሙት፤ ይህ ድርጊት ሲዖል የሚያስገባ መሆኑን ከታሪካዊ ክስተቶች ተምረዋልና ነው። የሮማው ጳጳስም ኢትዮጵያን ጎብኝተው ከማያቁባቸው ምክኒያቶች አንዱ ይህ ይመስለኛል።

ከታሪክ አንማርም ያሉት እውሮቹና ደንቆሮዎቹ ሙስሊሞች እና ጴንጤዎች ብቻ ናቸው። የክርስቶስን ልጆች እንዲህ በገንዘብ እየደለሉ የሚመለምሉት ሁሉ የዲያብሎስ ልጆች ናቸው በሲዖል የሚጠብቃቸውም ገሃነም እሳት ብቻ ነው። ጉዟቸውን ያፋጥንላቸው!

______

Posted in Ethiopia, Faith, Infos | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

የጎዴ ጉድ | ወላጅ-አልባ የተዋሕዶ ሕፃናትን ወደ እስልምና እንዲቀይሩ የሚያስገድደው የልጆች መንደር

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on February 8, 2018

ሰለጠፉት በጎቼ ምን እንደማደርግ አላውቅም፣ ልጆቼ ተሠርቀዋል፣ ለእምነታቸው በእግዚአብሔር ፊት ተጠያቂው እኔ ነኝ!አባ ፍሬው።

ይህ አሳሳቢ ሪፖርት ሰሞኑን በአንጋፋው የስፔን ጋዜጣ፡ “ኤል ፓይስ” የወጣ ነው። መረጃው ብዙ ስፓኛውያን ክርስቲያን አንባቢዎችን አንገፍግፏል፣ አስደንግጧል።

ተዋሕዶ ሕፃናትን መስረቅ ከእግዚአብሔር እየነጠቋቸው ነው!” በማለት ሁለት የኦርቶዶክስ ቀሳውስት የድርጊቱን አሳሳቢነት ደም በሚያስለቅስ መንገድ ገልጸውታል። ይህ ጉዳይ ሁላችንንም፤ በተልይ የወንጀሉን ተባባሪዎች አውሮፓውያኑንና ኢትዮጵያውያን ጨምሮ ሁላችንንም በጥብቅ ሊያሳስበን ይገባል፤ በእግዚአብሔር ዘንድ ያስወነጅላልና፣ ያስቀጣልና።

  • ሠላሳ የሚሆኑ ተዋሕዶ ሕፃናት ወደ እስልምና እንዲቀይሩ ተገድደዋል

  • ክርስቲያን ነች” የምትባለዋ ኦስትርያ በእዚህ መንደር አንድ መስጊድ ሠርታለች

  • የመንደሮቹ አስተዳዳሪ ጣልያናዊ ነው

  • ገንዘብ ለጋሾቹ አውሮፓውያን ናቸው

እነዚህ ፃናት ወደ ሕፃናት መንደሮች ሲገቡ በአክራሪነት ውስጥ እንዲካኑ እየተደረጉ ናቸው ሠላሳ የሚሆኑ ክርስቲያን ሕፃናት እስልምናን እንዲቀበሉና በቀን እስከ አምስት ሰዓት ድረስ በመንደሩ መስጊድ ውስጥ እንዲፀልዩ ይገደዳሉ

ይህ ሁሉ ጉድ የሚፈጸመው በኢትዮጵያ ውስጥ በሚገኘው ዓለም አቀፉ መንግስታዊ ያልሆነ መንደር ውስጥ ነው

ዜናው ለመጀመሪያ ጊዜ የመጣው..አ በ ሁለት ሺህ አስራአራት ዓ.ም የበጋ መጀመሪያ ቀናት ውስጥ ነበር። አባ ፍሬው ክርስቲያን ልጆችን፣ ወጣቶችንና ጎልማሶችን እስላም ለማድረግ ሤራ መጠንሰሱን፡ ኦርቶዶክስ ቤተክርስትያን የበላይ አለቆቻቸው አስቀድመው ማስጠንቀቂያ ልከው ነበር።

አደጋው ያንዣበበው በሶማሌ ክልል በጎዴ ከተማአስራ ሁለት የ አልዲያስ ኢንፋንቲል ድርጅት መጠለያዎች ውስጥ ተከፋፍለው በሚገኙ መቶ ሃያ ህፃናት ላይ ነው።

ተንከባካቢና አሳዳጊና የእንጀራ እናት ሆነው ልጆቹን የሚነከባከቡት ሶማሊያውያን አክራሪ እስላሞች ናቸው።

በጣም የሚገርመው አንድ የኦስትሪያ መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት በእዚህ የሕፃናት መንደር መስጊድ መስራቱ ነው። በተጨማሪም መስጊዱ እንደ ቁርአን ትምህርት ቤት ወይም መድረሳ ሆኖ ያገለግላል። በዚህ መስጊድ ክርስቲያኑ ሕፃናት በቀን አምስት ጊዜ እንዲሰግዱ ብሎም የቁርአን ሱራዎችን (መቶ አስራ አራት አንቀጾች አሉት) እና ተጨማሪ ጥቅሶችን እስኪደክማቸው ድረስ እንዲያነበንቡና በቃላቸው እንዲሸመድዱ ገና ከልጅነታቸው ይገደዳሉ።

አባ ፍሬውና አጋራቸው ህይወታቸው ለአደጋ የተጋለጥች ብትሆንም፡ ስለዚህ የሕጻናቱ አሳዛኝ ሁኔታ ለሚመለከታቸው የበላዮቻቸው ከማስታወቅ ወደ ኋላ አላሉም። እንደርሳቸው ከሆነ እስከ ሠላሳ የሚሆኑ ሕጻናት በመስጊዱ ግፊት ወደ እስልምና እንዲገቡ ተገድደዋል።

የሕጻናቱ መንደር በሚገኝበት ቦታ ያሉ ባለስልጣናት መስጊድ የሚለውን ስም በይሉኝታ በማለሳለስ “የጸሎት ቤት ብለው ሊጠሩት መርጠዋል።

አባ ፍሬው ለህይወታቸው አስጊ የሆነ ሁኔታ ቢፈጠርም በጎዴ የ ኢስ..ኤስ የህፃናት መንደሮች ምን ዓይነት ጉድ እየተካሄደ እንደሆነ ያው ለሦስት ዓመታት ያህል ድምጻቸውን ከማሰማት ወደ ኋላ አላሉም። “ሰለተሰረቁት በጎቼ ምን እንደማደርግ አላውቅም፣ ልጆቼ ተሠርቀዋል፣ ለእምነታቸው በእግዚአብሔር ፊት ተጠያቂው እኔ ነኝ!„ በማለት አባ ፍሬው በደከመ መልክ እና እንባ እየተናነቃቸው ተናግረዋል። ሙስሊሞቹ አደጋ ሊጥሉብኝ እንደሚችሉ ቢሰማኝም፡ ለጠፉት በጎቼ ጥብቅና ለመቆም ደሜን ለመፈወስ ፈቃደኛ ነኝ። ልጆቼን ለመከላከል ዝግጁ ካልሆንኩ በእግዚአብሔር አምላክ ዘንድ እኔ ነኝ ለነፍሳቸው ተጠያቂ የምሆነው።”

ነገር ግን የድኽነት ስሜት ይሰማኛል፣ ጥንካሬም ጎድሎኛል፣ ማንም ሊሰማኝ ፈቃደኛ አይደለም፣ ወደ ህፃናቱ መንደ ውስጥ እንድገባና ከተዋሕዶ ልጆቼ ጋር እንድነጋገር እንኳይፈቅዱልኝም።ብለዋል፡ አባ ፍሬው።

ተዋሕዶ ክርስቲያን ሆነው ወደ ህፃናት መንደ መጡትና ወደ “እስልምና” እንዲቀየሩ የተገደዱት ወላጅ አልባ ልጆ ስም መካከል በጥቂቱ የሚከተሉት ይገኙበታል ፦

  • ንዋሜ ደጀኔ

  • ጃፈር አቢ

  • ሞሆ አቢቹ

  • ሰላም

  • ቤዛዊት

  • ሊዲያ

  • መስከረም

  • ብሩክ

  • ብርቱካን

  • ሃይማኖት

  • ሃሊ

  • ነፃነት

  • ዮርዳኖስ

  • ናርዶስ

አሁን ግን ሙስሊም ስሞች ተሰጥቷቸዋል፣ ዘራቸውን እንዲያጡ ተደርገዋል፤ ከሌሎቹ ቤተሰቦቻቸው ጋር ከአያቶቻቸው፣ ከአጎቶቻቸው እና ከሌሎች ዘመዶቻቸው ጋር ግኑኝነት እንዲያቋርጡ ተደርገዋል። ዘመዶቻቸው አልፎ አልፎ ለመጠየቅ ሲመጡ ሙስሊሞቹ “ሞግዚቶቻቸው” አይነጠሏቸውም፡ ምክኒያቱም ከክርስቲያን ዘመዶቻቸው ጋር ለብቻቸው እንዲሆኑ አይፈቅዱላቸውምና ነው።

ህፃናቱን እስላም ለማድረግ ገንዘብ ይሰጣልን?

በንዴት የቆሰሉት አባ ፍሬው እንዲህ ብለዋል፦ እርግጠኛ ነኝኤስ ኦ ኤስ (SOS) የሕፃናት መንደሮች ገንዘብ የሚሰጡ የውጭ ሰዎች በአብዛኛው ክርስቲያኖች ናቸው። ነገር ግን እነሱን የሚደግፉ ሰዎች ልጆቻቸውን ለአክራሪ እስልምና አሳልፈው እየሰጧቸው እንደሆነ የሚያውቁ አይመስለኝም።”

በእነዚህ መንግሥታዊ ልሆኑ ድርጅቶች (NGO) አማካኝነት በተቋቋሙት የሕፃናት መንደሮች ምን ዓይነት ጉድ እየተሠራ እንድሆነ ለማጣራት የስፔይን ኤስ ኦ ኤስ መንደሮች መርማሪ ወገን በቦታው ተግኝቶ ነበር። ከገንዘብ ለጋሾቹ መካከል፦

  • ስፔይን

  • አውስትርያ

  • ጣልያን

ይገኙበታል። የጎዴን የህፃናት መንደር የሚያስተዳድረው ጣልያናዊው ክላውዲዮ ክሮቼ ይባላል።

ምንጭ፦ El País

______

Posted in Ethiopia, Faith, Infos | Tagged: , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ሐዘን የማንም የቡድን ጥቅም ማራመጃ መሆን የለበትም

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on September 22, 2017

በመንግሥቴ አወቀ – ሪፖርተር ጋዜጣ 12 Aug, 2016

 

ከአንድ ዓመት ተኩል በፊት እ... በኦክቶበር 2013፣ በመቶ ቤት የሚቆጠሩ ጥገኝነት ጠያቂዎችን የያዘ ጀልባ ጣሊያን ባህር ጠረፍ ማዶ ውስጥ ሰጥሞ ከ360 በላይ ሰው ሲያልቅ፣ አገሪቷ ጣሊያን የታላላቅ የመገናኛ ብዙኃን የወሬ መተረማመሻ ሆኖ ነበር፡፡

በሰሜናዊው አፍሪካ በኩል የሜዲትራንያን ባህር አቋርጦ አውሮፓ ለመግባት እንደ ጐርፍ የሚፈሰውና ቁጥሩ እያደር የሚጨምረው ፈላሽ (መጣተኛ) ቁጥር፣ እነሆ እንደ ከሳምንት በፊት በደረሰው የ900 ሰዎች እልቂት አማካይነት ከቁጥጥር የወጣ ችግር መሆኑን በግድ እያስመዘገበ መጥቷል፡፡ ከዚህ እልቂት ሁለትና ሦስት ቀናት በፊት 550 መጣተኞች (ማይግራንትስ) ከያዘ ጀልባ ውስጥ ከ400 ያላነሱ ሰምጠው ሞተዋል፡፡

በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽን (UNHCR) መረጃ መሠረት፣ ሜዲትራንያን ባህርን አቋርጦ ወደ አውሮፓ የሚወስድ ዕድልና ሁኔታ እስኪመቻችላቸው ድረስ መከራ እየተቀበሉ የሚጠብቁና ሊቢያ ጠረፍ ላይ የሠፈሩ በግማሽ ሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች አሉ፡፡ እ... 2015 በተለመደው ስቃይና መከራ ውስጥ ጣሊያን የደረሱት 20 ሺሕ ያህል ብቻ ናቸው፡፡

አብዛኞቹም የግዞት ካምፕ ውስጥ ይገኛሉ፡፡ ከአፍሪካ በሜዲትራንያን ባህር በኩል ወደ አውሮፓ የሚደረገው ጉዞ ሦስት ጎዳናዎች (መንገዶች) አሉት፡፡ አንደኛው የመንገደኞች ምንጭ ከሴኔጋል፣ ጊኒ፣ ማሊ አድርጎ ከዚህም አጋብሶ ወደ ሰሜን አፍሪካ የሚያቀናው የምዕራቡ መንገድ ነው፡፡ የናይጄሪያ፣ የጋናና የኒጀርን ወጣት እያግተለተለ በተመሳሳይ ሁኔታ ሽቅብ ወደ ትሪፖሊ አቅንቶ ወደ ላምፔዱዛ የተዘረጋው መንገድ ማዕከላዊ ይባላል፡፡ ከሶማሊያ፣ ከኤርትራ፣ ከኢትዮጵያና ከሱዳን (ዳርፉር) አሰባስቦ በሱዳን ካርቱም፣ ከዚያም በኩርፍ አጅዳቢያ ቤንጋዚ ወይም ትሪፖሊ በኩል ወደ ባህሩ የሚሄደው ደግሞ የእኛው ምሥራቃዊ መንገድ ነው፡፡ የገዛ ራሱ ገባር ወንዝ ያለው ይህ ሁሉና እያንዳንዱ መንገድ ራሱ የሜዲትራንያን ባህር ገባር ነው፡፡

ከመነሻው ከእያንዳንዱ ቤትና ጭስ ጀምሮ የሚያስመዘግበው መከራና ግፍ፣ ጭካኔና ዝርፊያ ደግሞ የእያንዳንዱ ስደተኛ ወይም መጣተኛ ‹‹ሕይወቴና የአገሬ ዕርምጃ›› ነው፡፡ አሁን ይህንን ስጽፍ ከአፍሪካ ወደ አውሮፓ አቋራጭና አጭሩ የሜዲትራንያን ባህር በኩል ለማለፍ ተራ ወረፋና ዕድል የሚጠብቁ ከግማሽ ሚሊዮን የበለጡ መከረኞች አሉ፡፡

ከእነዚህ መካከል ነው 900 ያህሉ በግፍ ሰምጠው የሞቱት፡፡ ከእነዚህ መካከል ነው 30ዎቹ በግፍ ታርደው የሞቱት፡፡ ሁለቱም ዓይነት ሞቶች ልዩ ልዩነት አላቸው እንጂ ከግድያና ከትራጀዲ በላይ ወንጀል ጭምር ናቸው፡፡

ዛሬ ኢትዮጵያ በ30ዎቹ አረመኔያዊ ግድያ ምክንያት ብሔራዊ ሐዘን ቁጭ ብላለች፡፡ የአውሮፓ ኅብረት ግዛቱ በገፍ በግፍ የሚሞቱ ስደተኞችና መጣተኞች መቃብር መሆኑ አሳፍሮት ይይዘው ይጨብጠው አጥቶ የመከራ ስብሰባ ላይ ነው፡፡ በዘጠኝ መቶ ሟቾች ውስጥ አጠራጣሪው ቁጥራቸው እንጂ ኢትዮጵያውያን ስለመኖራቸው አይደለም፡፡ ይህም ሌላ ያልተረዳነው ሐዘን ነው፡፡ በቅጡ ያላወቅነው መርዶ ነው፡፡

እንዲህ ያለ ሐዘን ወቅት ከሚያሳስቡን ጉዳዮች መካከል በዛሬው ጽሑፌ የማነሳቸው ሁለቱን ነው፡፡ የውጭ ጉዞና ሃይማኖት፡፡

  1. ጉዳዩ ከሚያነሳው ነገሮች መካከል አንዱ የውጭ ጉዞ ነው፡፡ ወደ ዓረብ አገሮች የሚወስደውን በሰሜናዊው አፍሪካ በኩል ሜድትራንያንን አቋርጦ አውሮፓ የሚያደርሰውን፣ በምሥራቅ ኢትዮጵያ በኩል በህንድ ውቅያኖስ አድርጎ መካከለኛው ምሥራቅ የሚያስገባውን፣ በምሥራቅ አፍሪካ አድርጎ ወደ ደቡብ አፍሪካ የሚወስደውን፣ ወዘተ ይህን የውጭ ጉዞ ከነስያሜው እንኳን ገና አላወቅንበትም፡፡ አልተስማማንበትም፡፡ መንግሥትና የመንግሥት ባለሥልጣናት ራሳቸው ጭምር ሌላው ቢቀር መንግሥን ያሳጣል ብለው እንኳን ሳያጠራጥሩ ስደት ይሉታል፡፡ የመንግሥትን የፖለቲካ አጀንዳ የሚሸከም መልዕክት አክለው ማስተላለፍ ሲፈልጉ ደግሞ ሕገወጥ ስደት ይሉታል፡፡

ለነገሩ አማርኛውም በ‹‹ሬፊውጂና›› እና በ‹‹ማይግራንት›› መካከል በስያሜ ልዩነት ስለማያበጅ የመገናኛ ብዙኃን ራሳቸው ይምታታባቸዋል፡፡ ስለ “IOM” ያውሩ ስለ “UNHCR” አይታወቅም፡፡ በዚህ ረገድ በዕውቀት ላይ የተመሠረተ የሚመስል ዕርምጃ ወስዶ ያየሁትና መሰንበቻቸውን ልዩነቱ ላይ አስምሮ ተደጋግሞ የሰማሁት የአማርኛው ቪኦኤ በስደትና በፍልሰት፣ በስደተኛና በፍልሰተኛ መካከል ልዩነት አበጅቶ ሲናገር ሰምቻለሁ፡፡

እንዲህ ያለ በአገር አቀፍ ደረጃ የሚሰማና የማይደበቅ ችግር በመጣ ቁጥር ተደጋግሞ የሚሰማው፣ ሙዝዝ ተብሎ የተያዘውና በሊቢያው የሚያዝያ 2007 .. ቁጣ ውስጥ አደባባይ  የወጣው የውጭ ጉዞ ጉዳይ፣ ‹‹አገር ውስጥ ሠርቶ መለወጥ›› ሲቻል የሚል አዝማች ያለው የመንግሥት ዜማ ነው፡፡ መንግሥትና የመንግሥት ባለሥልጣናት እንዲሁም በዚህ ጉዳይ ምክንያት መንግሥትና ፓርቲው የተነካካባቸውና የተሸነፈባቸው የሚመስላቸው ደጋፊዎች፣ እንዲህ ያለ ጉዳይ በተነሳ ቁጥር በመንግሥት የኢኮኖሚ፣ የዕድገትና የልማት ፖሊሲ ወይም በተከታታይ በሚመዘገበው የዕድገት ውጤት ላይ ተፈጥሮና ታሪክ ከመደብ ጠላት ጋር ተረባርቦ የማይካድ የግፍ ማስረጃ ያቀረበባቸው ስለሚመስላቸው፣ የውጭ ጉዞን ጨርሶ የሚያወግዝ፣ እንዲከለከል የሚያደርግ፣ ከዚህ ጋር የተያያዘውን ሁሉ ለችግሩና ለወንጀሉ ጭምር ካበረከተው አስተዋጽኦና ድርሻ በላይ የሚያወግዝ፣ የሚዝትና የሚረግም መከላከያቸውን በዘመቻና ‹‹በአስቸኳይ ጊዜ ሁኔታ›› መልክ ሲለፍፉ እናያለን፡፡

ኢትዮጵያዊ በገፍ በተለያዩ አቅጣጫዎች ወደ ውጭ የሚጎርፈው የኢሕአዴግን መንግሥት ለማሳጣት አይደለም፡፡ በኢሕአዴግ የዕድገትና የልማት ፖሊሲ ላይ የሕይወትና የአካል ማስረጃ ለማቅረብ አይደለም፡፡ ኢሕአዴግ ያስመዘገበው ባለሁለት አኃዝ ዕድገትም ሙሉ በሙሉ ለማስተባበል አይደለም፡፡

የተለያዩ ጉዳዮች እየተጋገዙ የውጭ ጉዞውን የግፊት ኃይል ሲበዛ ከፍ አድርገውታል፡፡ የመንግሥት ዲስኩርና የሃይማኖት መሪዎች ስብከት ‹‹የአገር ፍቅር ስሜት›› ቅስቀሳ የፈለገውን ቢሉም፣ ግፊቱና ፈተናው ከሚታገሱት በላይ ሆኖ በየቤቱ የአዲስ ዘመን ምኞት ቃል ማሰሪያ ሆኗል፡፡ በዚህ ምክንያት መንግሥት የዚህን ችግር አተያዩን ግልጽና የጠራ ማድረግ አለበት፡፡ በተለይም ደግሞ የውጭ አገር የዜጎች ጉዞን የፖሊሲው ውድቀት ማስረጃ ሆኖ ይቀርብብኛል ብሎ እየተደናገረና እየተወናበደ የአገርን አጠቃላይ ችግር ከማየት ወደሚከለከለው ደመነፍሳዊ ራስን የመከላከል ስትራቴጂው መውጣት አለበት፡፡ እናም ኢሕአዴግ ራሱ እንደሚለው ልማት የአገር የህልውና መሠረት መሆኑን እየተገነዘበ፣ በተግባርም እያስገነዘበና እያስመዘገበ ልማቱ የሚያስመዘግበው ዕድገትና ውጤት የሥራ ሥምሪቱን እያስፋፋና እያፋፋመ መሆኑን ከማረጋገጥ ጋር፣ የውጭ ጉዞን አታንሱብኝ ከማለት አባዜው መውጣት አለበት፡፡ ‹‹በአገር ውስጥ ሠርቶ መሻሻል ሲቻል›› ማለት መፈክሩንም ‹‹የደመኛ ጠላቶቹ›› (ወደ ውጭ ሄደው በሚደርስባቸው ችግር ‹‹የሚያሳጡትን››) እና ደጋፊዎቻቸው መምቻ ከማድረግ ተራ ጨዋታ መውጣት አለበት፡፡

ኢትዮጵያና ኢትዮጵያውያን ላይ የደረሰው የ2007 .. የሊቢያ ጭፍጨፋም ሆነ ማንኛውም አጋጣሚ ደግሞ በውጭ ጉዞና በሌሎችም አርዕስቶች ላይ (ለምሳሌ አሸባሪነት፣ ሃይማኖት ወዘተ) የሚቀርቡትን አስተያየቶች ከውይይት በላይ ማድረግ የለበትም፡፡ ከውይይት በላይ የሆነ፣ አላናግርም፣ ሐሳብን መግለጽ አልፈቅድም የሚል ምንም ዓይነት የመንግሥትም ሆነ የማንም አቋምና እምነት የለም፡፡ የውጭ ጉዞው አሁን የሊቢያው ጉዳይ በቀረበበት መልክ የሚጠይቀውንና የሚያስከፍለውን የገንዘብ ወጪ እያነሱና እየጣሉ፣ ከፍተኛነቱን እያሳዩ (ይህ የቀበጡ ወይም የደላቸው ሰዎች በገዛ ራሳቸው ያመጡት ችግር ነው ዓይነት) የመንግሥትን አቋምና መከላከያ ብቻ እየወቀጡ ዜና መሥራት፣ የዚህ ተቃራኒ መከራከርያ፣ ከዚህ የተለየ ሐሳብ እንዳይቀርብ መከልከል፣ አገር ሌላው ቀርቶ የጋራ ሐዘን እንዳይኖራት የሚከለክል አለማወቅ ነው፡፡

በአጠቃላይ የውጭ ጉዞን ራሱን የዚህ ሁሉ መከራና ስቃይ ዋነኛ ምክንያት ማድረግ፣ በጉዞው ውስጥ የሚከሰከሰውን (ገና ልክና መልኩ ተዘርዝሮ ያልታወቀውን) ገንዘብ አንፃራዊ መጠን እያወሱ (ሲሉ የሰሙትን) የ‹‹ካልጠገቡ አይዘሉ፣ ካልዘለሉ አይሰበሩ›› መከራከሪያና ብያኔ መስጠት፣ በየአቅጣጫው ከኢትዮጵያ አንድ ወረዳ ወይም ዞን እስከ ሊቢያ የባህር ዳር ድረስ ያለውን የውጭ ጉዞ የደላላ መዓት ብቸኛው የወንጀል ድርጊቱ ተካፋይ አድርጎ ማሳየት፣ በሕጋዊው የውጭ ጉዞ ሰንሰለትና ፌርማታ ውስጥ በመላ መንግሥት የተዋጣለት ሥርዓት የዘረጋ ይመስል፣ መደበኛ ያልሆነውን የጉዞ መስመር ብቻ የችግራችን ምንጭ ማድረግ ሕመማችንን የሚያሳይ አካሄድ አይደለም፡፡

የውጭ ጉዞ ሲባል ሁልጊዜም የሚነሳው ይህ ዘፈኖች ሁሉ ተባብረውና ተረባርበው የሚዘምርለት፣ በጅምላ ‹‹ስደት›› የሚባለው ብቻ አይደለም፡፡ ኢትዮጵያውያን የሕክምና ባለሙያዎች ለምሳሌ ወደ ውጭ አገር የሚፈልሱት ለ‹‹ስደት›› አይደለም፡፡ በቃሉ ትክክለኛ ትርጉም አገር ወይም የፖለቲካ ሥርዓቱ አላስቆም አላስቀምጥ ብሏቸው፣ ‹‹አሳዷቸው›› አይደለም፡፡ ሲሉ እንደምንሰማው እንደ ቦትስዋና ባሉ አገሮችም በተግባር እንደሚታየው፣ የኢትዮጵያ የሕክምና ባለሙያዎች በውጭ አገር ገበያ ውስጥ ተፈላጊ ናቸው፡፡ እንደዚህ ያለና ከዚህ ዓይነት ፍላጎት የተነሳ የባለሙያ ፍልሰትም በተለይ መንግሥትን ያሳስበዋል፡፡

በዚህም የተነሳ መንግሥት ከባለሙያዎች ጋር ቢያንስ ቢያንስ የሚያሻክር፣ ከመብት ጋር አልገጥም የሚል ከከፍተኛ የትምህርት ተቋም ጀምሮ እስከ የሥራ ውል ይዘት ድረስ የማራዘም የመከላከያ ዕርምጃ ሲወስድ ይታያል፡፡ የክልከላ ዕርምጃውም፣ የዕርምጃውም ዓላማ ግን ከአገር ልማት አጠቃላይ ግብ ጋር አይጣጣምም፡፡ በርካታ ባለሙያዎች ከኢትዮጵያ ወደ ውጭ መፍለሳቸው ማስፈራትም ማሳሰብም የለበትም፡፡ ይልቁንም የኢትዮጵያ ሙያተኛ በውጭ በመፈለጉ ተደስተን በተሻለ የችሎታና የሥነ ምግባር ብቃት ገበያውን ለመሙላት፣ እንዲሁም ለማስፋፋት በአገሪቱ ውስጥ ያለውን ፍላጎትም ለመሸፈን የሚችል የሰው ኃይል በየጊዜው ማፍራት፣ ኢትዮጵያ ልትረባረብበት የሚገባ አንድ የልማት ዕቅድ መሆን አለበት፡፡

በአሪቱ ውስጥ ያለውን የባለሙያ ፍላጎት ለመሸፈን የሚችል የውስጥ የሰው ኃይል ፍላጎት ሲባል መታሰብ ያለበት የኢትዮጵያ ዜጋ ወይም የኢትዮጵያ ሕዝብ የውስጥ ፍላጎት ብቻ አይደለም፡፡ ጥራትና ደረጃቸው ከለሙት አገሮች ጋር የተመጣጠኑ የሕክምና ወይም የመዝናኛ አገልግሎቶችን በቀላል ዋጋ ማቅረብ አንዱ የውጭ ምንዛሪ መሳቢያ ነው፡፡

የተሻለ የሥራና የገቢ ዕድል ወዳለበት አገር ሄዶ መሥራትም ነውር የለበትም፡፡ ሌሎች ከእኛ የተሻሉ አገሮችም በሥራ አጥነት ማስተንፈሻ ይጠቀሙበታል፡፡ ወደ መካከለኛም ምሥራቅ ለሥራ የሚሄዱ ኢትዮጵያውያን ጉዳይም ከዚህ የተለየ አይደለም፡፡ እዚህ ውስጥ መንግሥት ሥራውን፣ ሥራው ካልሆነው ለይቶ ማወቅ አለበት፡፡ የመንግሥት ሥራ ከውጭ የሥራ ዕድሎች ዕውቀት ጋር ባህልና ሕግ ነክ መረጃዎችና የምክር አገልግሎት ተሟልተው የሚገኙበትን ሕጋዊ መንገዶች ማመቻቸት ነው፡፡

በውጭ በሚሠሩ ኢትዮጵያውያን ላይ የሚደርሱ ጥቃቶችንበአግባቡ ለመከላከልና ለመጠየቅ የሚያስችል (እዚህ አገር ቤትም ሆነ በውጭ) ሥርዓት አለመዘርጋትና ለዚህም ዝግጁና ብቁ ሆኖ አለመገኘት፣ አስጊ ወይም ጠንቀኛ ሁኔታዎች ሲኖሩም ከማሳወቅ እስከ ጉዞ ማገድና ዜጎችን እስከመጥራት የሚደርስ ዕርምጃ አለመውሰድ ማስጠየቅ አለበት፡፡

በዚህ ዘርፍ ያለው የመንግሥት ግዴታ ገና ያልተነካ መሆኑን የግል ሥራና ሠራተኛ ኤጀንሲ የሚባለው ሕግ ራሱ የተጓዘበትን ውጣ ውረድና አሁንም ድረስ የታገደ መሆኑን ማየት ብቻ ይበቃል፡፡

2. አሁን ያጋጠመው አረመኔያዊ የወንጀል ድርጊት በተፈጸመበት መልክ ‹‹በጥንቃቄ››ም ቢሆን ያነሳው የሃይማኖት ጉዳይ ነው፡፡ ሃይማኖትን ከጉዳዩ ጋር ያያያዘው ደግሞ በጭራሽ የውጭ ጉዞ አይደለም፡፡ በ30ዎቹ ወገኖቻችን ላይ የተፈጸመውን የግፍ አገዳደል ወንጀል በጥንቃቄ ከሚነሳ ሃይማኖት ጋር ያገናኘው አሸባሪነት ነው፡፡ በዚህ ምክንያት ይህን ጉዳይ እየፈሩና እየቸሩ ሳይሆን በግልጽና አፍታቶ መጋፈጥ ያስፈልጋል ብዬ አምናለሁ፡፡

‹‹አገር የጋራ ነው፣ ሃይማኖት የግል ነው፤›› ማለት ለረዥም ጊዜ በኢትዮጵያ ሕዝቦች ውስጥ የነበረ መዳከር የሌለባቸውን ሁለት መብቶች ቁልጭ አድርጎ የሚያሳይ፣ ችግሮች እንዳይፈጠሩ ሲጠብቅና ሲፈጠሩም መፍቻ ሆኖ ሲያገለግል የቆየ ቁልፍ የአብሮነት መመርያ ነው፡፡ ዛሬም ይህ መመርያ በዜጎች ግንኙነት ንቃተ ህሊና ውስጥ ያለው ዋልታነት መጠናከር አለበት፡፡ ክርስትናና እስልምና ከውጭ ወደ ኢትዮጵያ በተቀዳዳሚ ጊዜ ውስጥ የገቡ መሆናቸው ይታወቃል፡፡ የሃይማኖቶች አገባብ ከኢትዮጵያ ሕዝቦች ጥንተ አመጣጥ ጋር የተያያዘ አይደለም፡፡ ይህ እውነት እንደተጠበቀ ሆኖ ‹‹ከትውልድ ትውልድ ሲወርድ የመጣ›› የሚለው አባባል ለሁለቱም ሃይማኖቶች ማገልገል ይችላል፡፡

ነገር ግን ኢትዮጵያን ከአንድ ሃይማኖት ጋር የማዛመድም ሆነ በአካባቢ ደረጃ ያለን የቋንቋና የሃይማኖት ሥርጭታዊ ክምችትን መሠረት በማድረግ አናሳውን እንደ ባይተዋር የመቁጠር አመለካከት፣ እንዲሁም በቅርቡ የገቡ እምነቶችን ተከባሪነት ከኦርቶዶክስ ክርስትናና ከእስልምና አሳንሶ ማሰብ የተሳሳተና የሚያሳስት ነው፡፡ ኢትዮጵያ የክርስቲያኖች፣ የሙስሊሞች፣ የሌሎች እምነት ተከታዮችም አገር ናት፡፡

ኢትዮጵያ የጋራችን እምነት የግል

ከደርግ በፊት ክርስትና የመንግሥት ሃይማኖት ስለነበር እስልምና በ‹‹ክርስትያኗ›› ኢትዮጵያ ውስጥ ውሱን ሥፍራ ያለው እምነት ተደርጎ ይታሰብ ነበር፡፡ ደርግ ሃይማኖትንና መንግሥትን ከመለየት ዘሎ ሃይማኖትን የማፈንና የማዳከም ፖሊሲ ነበረው፡፡ ኢሕአዴግ ደግሞ ከደርግ በፊትና በደርግ ጊዜ የነበረውን ችግር ለማስወገድ ሞክሯል፡፡

ነገር ግን የፖለቲካ ድርጅቶች ሃይማኖቶችን በደጋፊ ማሰባሰቢያነት ወይም በማስጠሊያንት ሊገለገሉባቸው መሞከራቸው ገና አልቀረም፡፡ ከአሥር ዓመት በፊት በ1997 ምርጫ ጊዜ የግል መብቶችን ያጠበቀውን ወገን በመቃረን ኢሕአዴግ ስለቡድን መብት አስፈላጊነት ሲያስረዳ፣ ከብሔር መብት ሌላ ሙስሊሙ ወገን ያገኘውን የእምነት እኩልነት ጠብቆ የማቆየትን ጉዳይ መጠቃቀሱ፣ እንዲሁም የተቃዋሚዎች ወገኖችም ኢሕአዴግ በሙስሊሙ ላይ አደረሰ የሚሉትን በደል መቁጠራቸው ይታወሳል፡፡ ይህን የመሰለ ሃይማኖቶችን ምርኩዝ ያደረጉ ግልጽና ስውር የፕሮፖጋንዳ ቅስቀሳዎች በተለይ በሥልጣን ላይ የተቀመጠውን ፓርቲ ላንዱ ወይም ለሌላው ሃይማኖት ልዩ ተቆርቋሪነት ያለው የሚያስመስል ግንዛቤ ሊያስከትሉ ይችላሉ፡፡ መንግሥት ለዚህም ሆነ ለዚያ ሃይማኖት ያደላል የሚል አስተሳሰብ እንዳይፈጠርበት ተጠንቅቆ መሥራቱ ለተስሚነቱም ሆነ ለሃይማኖቶቹ ጤናማ ግንኙነት፣ ብሎም ለአገሪቱ ሰላም መሠረታዊ ነው፡፡ አንደኛውና ሃይማኖትን የሚመለከተው አጠቃላይ ጉዳይ ይኼው ነው፡፡

ይህን የሚደግፉ ሌሎች ዝርዝር ነጥቦችም አሉ፡፡ ሃይማኖትን መስበክ መብት ቢሆንም የሌላው መብት የሚነካበትን ወሰን አበክሮ ማወቅና ማክበር ደግሞ የግድ ነው፡፡ አንድ ሰው በአንድ ሃይማኖት ውስጥ ረግቶ የሚቆየው ከሎጂክ ይልቅ በእምነት ፅናት ነው፡፡ ዛሬ ባለንበት የመቻቻልና የመከባበር ባህል ዝቅተኛነት ደረጃ የሃይማኖት ክርክር መግጠም ከጥቅሙ ጉዳቱ ሊበልጥ መቻሉን አውቆ መቆጠቡ ይመረጣል፡፡

በእምነት ተቋምም ውስጥ ሆነ በጽሑፍና በሌላ የመገናኛ ዘዴ የሌላውን እምነት እየተቹ እምነትን ማስተማር አደገኛ ትንኮሳ አለበት፡፡ አንድ ሃይማኖት ማስተማር ያለበት ለእምነቱ ምሰሶ በሆኑ በራሱ መጻሕፍት ላይ ተመሥርቶ እንጂ፣ ከሌላው የእምነት መጻሕፍት እየመዘዘ መሆን የለበትም፡፡

የትኛውም ወገን ማንኛውንም እምነት የማረምና የመተቸት መብት የለውም፡፡ እምነቴ ስህተት ነው የሚል ሃይማኖተኛ በዓለም ላይ የለም፡፡ የእኔ ሃይማኖት ልክ ነው ባይነት ግን የሌላውን ልክ ነኝ ባይነት ከማክበር ጋር መጣመር አለበት፡፡

ስለዚህም አሁንም ‹‹አገር የጋራ ነው፣ ሃይማኖት የግል ነው፤›› የሌላውን ሃይማኖት ሳያከብሩ የራስን ማስከበር ያዳግታል፡፡ ሌላም ተጨማሪ መጤን ያለበት ጉዳይ አለ፡፡ ዛሬ፣ ‹‹ሃይማኖት›› የተለያየ ፍላጎት መሸፈኛና ማራመጃ ሆኖ የሚያገለግልበት ዘመን ላይ ደርሰናል፡፡ የዘንድሮ ሌባ ሳይቀር ሃይማኖት አጥባቂ መስሎ በመቅረብ ሙሉ ለሙሉ እስኪታመን ድረስ ጠብቆ በገፍና በእጅጉ ማጭበርበር አምጥቷል፡፡

በዓለም ውስጥ የተደራጀ ቡድንን ጥቅም ለማሟላትና ፖለቲካዊ ጥላቻንና በቀልን ለመወጣት፣ ሃይማኖት ሲያገለግል ብሎም የአዕምሮ ቀውሶች መጫወቻ ሲሆን ማየት አዲስ አይደለም፡፡

በተለያዩ ጊዜያት እንደ ክርስቶስ ሞተን እንነሳለን በማለት ራሳቸውንና ተከታዮቻቸውን በመርዝ የጨረሱ ወፈፌዎች ተከስተዋል፡፡ በኡጋንዳ ውስጥ በሕዝብ ላይ ግፍ ሲውል፣ የቆየው ሎርድ ሬዚስታንስ አርሚ (LRA) ራሱን የጌታ አምላክ ሠራዊት ብሎ የሰየመና ለኦሪት ሥርዓት ቆሜያለሁ ባይ ሆኖ ነው፡፡

በእስልምናም በኩል ታሪክን ወደኋለኛው ዘመን ሊመልሱ የሚሞክሩና የሚጥሩ አሉ፡፡ በተለያዩ ቦታዎች በተለይም በቅርቡ ሊቢያ ውስጥ የተፈጸመው ወንጀል ለእስልምና እምነት ከመቆም ጋር ፊጽሞ የማይዛመድ የታመመ ተግባር ነው፡፡

እንደዚህ ዓይነት ለእምነቱ ከመገዛትም ሆነ ከመቆም ጋር ፈጽሞ የማይገናኝ ይልቁንም የሚቃረን አደጋና ጥቃት ሲያጋጥም፣ በስሙ የተነገደበት የትኛውም ሃይማኖት ተከታዮች እንደ ‹‹ተከሳሽ›› የሚቆጠሩበት ይቅርታ የመጠየቅ ያህል ለተለያዩ ሥነ ሥርዓታዊ ግርግር የሚዳረጉበት አሠራር የትም ቦታ ጤናማ አይደለም፡፡

እስካሁን ያሳነው በመንግሥት በኩል አለ ያልነውን ነው፡፡ የመንግሥት ተቃዋሚዎችም ከደሙ ንፁህ አይደሉም፡፡ አንዳንዴ ሲታሰብ የሚያስደነግጥ ነገር የሚደገስ መሆኑ ይሸታል፡፡ ሐዘን በተቀመጠች ኢትዮጵያ ‹‹ድንኳን›› ውስጥ ድንገት ከሰላሳ በላይ ሰው ሞቶ፣ ይህን ያህል ሕዝብ አልቆ በዚህም መንግሥት ቢሳጣ፣ ቢከሰስና ቢወገዝ ተብሎ ለዚህ ውጤት የሚከናወን ሥራ ያለ ይመስላል፡፡ ይህ የጤነኛ ፖለቲካ አካሄድ አይደለም፡፡ ጨርሶ ፖለቲካም አይሆንም፡፡ ፖለቲካ በሥልጣን ላይ ያለውን መንግሥት ከማውረድና ከመተካት በላይና ከዚህ የተለየ ዓላማና ግብ አለው፡፡ መንግሥትን መቃወምና ማሳጣት ወንጀልም ነውርም አይደለም፡፡ መቃወምንና ማሳጣትን በተለይም በሕዝብ ሕይወትና ደም ዋጋ፣ ዓላማና ግብ ማድረግ ግን በጭራሽ ፖለቲካ አይደለም፡፡

______

Posted in Conspiracies, Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , | Leave a Comment »

ኢትዮጵያ የምዕራባውያን ቆሻሻ ማራገፊያ መሆን የለባትም

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on August 5, 2014

EthioChild

(ሪፖርተር ጋዜጣ – ከተቆርቋሪ ዜጋ)

ምንም እንኳን በሚዲያዎች በግልጽ ባይነገርም በአዲስ አበባ የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን አዳራሽ ከመስከረም 20 እስከ 25 ቀን 2006 .ም የተደረገ ስብሰባ ነበር፡፡ ይህም የዓለም አቀፍ የሥነ ሕዝብና የዕድገት ኮንፈረንስ (አይሲፒዲ) ከፍተኛ ግብረ ኃይል ያልተቋጨ አጀንዳ በተለያዩ አገሮች እ..አ ከ2014 ጀምሮ ሊተገበር የሚገባ ብሎ ያስቀመጣቸውና በስብሰባው በስተመጨረሻ ለጉባዔው ይፋ የተደረጉና በዋናነት የተቀመጡ ነጥቦች አሉ፡፡ ከእነዚህም መካከል ከአገራችን ሕግ፣ ደንብና ባህል እንዲሁም እሴቶቻችን ጋር ፈጽሞ አብረው ሊሄዱ የማይችሉ ጉዳዮች ነበሩበት፡፡

የመጀመሪያው የወሲብና ተዋልዶ መብቶችን ማክበር፣ መንከባከብና ተፈጻሚ ማድረግ የሚል ነው፡፡ ለዚህም ሕጋዊ ውርጃን ማስፋፋትና ማዳረስ፣ የወሲብና የተዋልዶ መብትን ከሌሎች መብቶችና ከተዛማች ሕጐች ጋር በማያያዝ ማስተማር፣ ግለሰቦች ያላቸውን የወሲብ ዝንባሌያቸውን በሚፈልጉት ሁኔታ ከተመሳሳይ ፆታም (ሆሞሴክሸዋሊዝም) ጋር ቢሆን ያለምንም ገደብ መብታቸውን እንዲለማመዱ ያበረታታል፡፡

ከጋብቻም ውጪ ቢሆን ማንኛውንም የወሲብ ኅብረቶች በፈቃደኝነት ላይ የተመሠረተ እስከሆነ ድረስ መብታቸውን የሚከለክሉ ድንጋጌና ሕጐች እንዲነሱ ይጠይቃል፡፡ የወሲብና የተዋልዶ ጤና መረጃና ትምህርት ማቅረብና ተደራሽነቱን ማረጋገጥ ሌላኛው ዓላማው ነው፡፡ ለዚህም በዋናነት ወጣቶችን በተለይም አፍላ ወጣት ሴቶች ላይ ያነጣጠረ መረጃ በትምህርት ቤቶችና ከትምህርት ቤቶችም ውጪ በመስጠት አጣዳፊ የእርግዝና መከላከያና ሌሎች የወሊድ መቆጣጠሪያ (ሕጋዊ ውርጃንም ጭምር) የሚያገኙበትን ሁኔታ ያመቻቻል፡፡

እንዲሁም ትምህርቱን በመቅረፅና በማዘጋጀት የሕግና ፖሊሲ ማዕቀፍ እንዲያገኝ ማድረግ የሚል ሲሆን፣ ይህንንም ለማድረግ የብሔራዊ ጤና ፕሮግራም አካል ሆኖ የራሱ በጀት እንዲኖረውም በማድረግ በአንዳንድ በውርጃ ሥራ ላይ በተሰማሩ ድርጅቶች የሚከናወን ነው፡፡ (ለምሳሌ በሪፖርተር ጋዜጣ ሐምሌ 2005 .ም በሜሪስቶፕስ ቃለ ምልልስ ላይ በወር 42 ሺሕ ሴቶች ለፅንስ ማቋረጥ ወደ እኛ ይመጣሉ ሲሉ ያለዕፍረት ተናግረዋል) ይህ እንግዲህ አንዱ ድርጅት ብቻ ነው፤ ሙሉ በሙሉ ሕጋዊነቱ ሲዳረስ ምን ሊሆን እንደሚችል መገንዘብ ያሻል፡፡

እስቲ ፍረዱ እኛ በልተን ያልጠገብንና ለማደግ የምንፍጨረጨር ዜጐች፣ የአውሮፓውያንና የምዕራባውያን ቆሻሻ ማራገፊያ የምንሆንበት ምክንያት ምንድን ነው? ይሄ ኢትዮጵያ ነው፡፡ እኛም ኢትዮጵያዊያን ነን፤ ሁለተኛ ዜጋ አይደለንም፡፡ ስለአገራችን ሁኔታ ያገባናል፡፡ ይህ ድብቅ በሆነ መንገድ ቀስ በቀስ ገጽታችንን የሚያጠፋ ጉዳይ ነው፡፡ በጣም የሚያሳፍረው ደግሞ ከግብረ ኃይሉ አባላት ውስጥ አስፈጻሚ ሆነው ልጆቻችንን የመሸጥ ያህል በመሯሯጥ ላይ ያሉት ባለሥልጣኖቻችን መሆናቸው ነው፡፡ እንርሱን ታሪክም ትውልድም ይጠይቃቸው፡፡ ዛሬ ከውጭ ለሚገኘውና በልማት ስም ለሚመጣ ገንዘብ ብለው ጤናማ ትውልድ ሊያሳጡን ነው፡፡ እኛ ኢትዮጵያዊያን ወደ ሌሎች አገሮች እንኳን ስንሄድ የምንኮራበት የራሳችን የሆነ ባህልና ሞራል እንዲሁም ታሪክ ያለን ሕዝቦች ሆነን፣ በዕድገትም ስም ተቀበሉ እያሉ በገንዘባቸው እያስፈራሩና እየደለሉን ነው፡፡ እኛ የምንመርጠው ከድህነታችን ጋር ጤናማ ኅብረተሰብና ታሪካችንን ነው፡፡

ታዲያ የአባቶቻችንና የቀደሙት መሪዎችቻችን ድፍረትና ወኔ ወዴት ነው ያለው? የአሁኖቹ መሪዎች ካደጉ አገሮች በልማት ስም ለሚገኘው ገንዘብ አሳልፈው ይሰጡን ይሆን? ሕጋችንን፣ ባህላችንንና ታሪካችንን ያከብሩልን ዘንድ እባካችሁ ጠይቁልን!

ግብረሰዶማዊነትና ልቅ የወሲብ መብቶች ከትምህርት ቤት ጀምሮ እንደ ዳቦ ሲታደል ምን ዓይነት ቀጣይ ትውልድ ይኖረናል ብለን ተስፋ እናደርጋለን? ጠቃሚ ስለሆኑት መመርያዎች ቅሬታ አይኖረንም፡፡ ነገር ግን በተከበረች አገራችን ላይ የተመሳሳይ ፆታ ጋብቻ/ግንኙነት እንዲሁም ልቅ ወሲባዊ መብት ልንሸከመው የምንችለው አይደለም፡፡ እንኳን ይህ ሁኔታ ተመቻችቶ ሚዲያዎች መጤና አጉል ልማዶችን እያስተዋወቁን ይገኛሉ፡፡ ታዲያ የሥነ ምግባርና የሞራል ውድቀት ሲጨመርበት ምን ሊሆን ይችላል? መንግሥት በዚህ ለተማሪዎች ሥነ ምግባር አሳቢ እየመሰለ በዚያ ለሺሻ ቤት ፈቃድ እየሰጠ የሚጣረስ ነገር በመሥራት ላይ ነው፡፡ እንደ እውነቱ ከሆነ ዛሬ ለአንድ ወላጅ ተማሪ ጥሩ ውጤት አምጥቶ ዩኒቨርሲቲ ሲገባ የነበረው ደስታ ጠፍቶ ልጄ ምን ይገጥመው/ይገጥማት ይሆን በሚል ሥጋት መወጠር ጀምሯል፡፡

ፍረዱ ይህ ለችግሮች መፍትሔ ነው እየተባለ በየቀኑ ኢቲቪ የሚነግረን እውን መፍትሔ ነው? ውርጃን በየክሊኒኩ ማስፋፋትና አጣዳፊ የእርግዝና መከላከያ አቅርቦት ለወጣቶቻችን መፍትሔ ነው?

ቀደም ሲልም ግብረሰዶማዊነትን ለማውገዝ የእምነት አባቶች በተነሱ ጊዜ እንዳንድ የመንግሥት ባለሥልጣናት መከልከላቸውን እናውቃለን፡፡ ይህ ታሪክ ከማጥፋትና ትውልድ ከመሸጥ አይተናነስም፡፡ በመስከረሙ ሥነ ሕዝብና አኅጉራዊ ስብሰባ ላይ ይህንን የተቃወሙ አገሮች አሉ፡፡ እንደ ቻይና ያሉ አገሮችም በጭራሽ እንዳልተቀበሉት ከኢንተርኔት ለማየት ችለናል፡፡ የእኛስ መሪዎች የተቀበሉት በልማት ስም ትውልድን መረን ለመልቀቅ ነው? ስለዚህ በጦርና መሳሪያ ለማንበርከክ/ቅኝ ለመግዛት ያልቻሏትን አገር፣ ዛሬ አንገት የሚያስደፋንን ውሳኔ መሪዎችን እንዳያስተላልፉ ሥጋት አድሮብናል፡፡

እንደ ኢትዮጵያዊና እንደ ወላጅ የነገን ጤናማና ፍሬያማ ትውልድ እንደሚናፍቅ ዜጋ ይህንን ጽፌያለሁ፡፡ ለነገም ትልቅ የማኅበረሰብ ቀውስ ነውና መንግሥታችንም ሆነ የሚመለከተው ክፍል ዛሬ አንድ በሉልን፡፡ የሕግ ያለህ! የፈጣሪ ያለህ!

__

 

Posted in Ethiopia, Infos, Life | Tagged: , , , , , , , | Leave a Comment »

 
%d bloggers like this: