Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • March 2023
    M T W T F S S
     12345
    6789101112
    13141516171819
    20212223242526
    2728293031  
  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

Posts Tagged ‘አንግሊካን’

የደቡብ አፍሪቃው ሊቀ-ጳጳስ ስለ ጽዮን ዝም አላሉም | ግን የኛዎቹ በሰው ፊት ከፈሩ በእግዚአብሔር ፊት ምን ያህል ማፈር ይኖርባቸው ይሆን?

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on March 7, 2021

ደቡብ አፍሪቃዊው የአንግሊካን ቤተ ክርስቲያን ሊቀ-ጳጳስ ታቦ ማክጎባ በኢትዮጵያ ‘የሰብአዊ አደጋን’ ለማስቆም እርምጃ እንዲወሰድ ጥሪ አቀረቡ፡፡

Archbishop Thabo Makgoba calls for action to stop ‘humanitarian catastrophe’ in Ethiopia.

❖❖❖[ወደ ኤፌሶን ሰዎች ምዕራፍ ፭፥፲፩፡፲፫]❖❖❖

ፍሬም ከሌለው ከጨለማ ሥራ ጋር አትተባበሩ፥ ይልቁን ግለጡት እንጂ፥

እነርሱ በስውር ስለሚያደርጉት መናገር እንኳ ነውር ነውና፤

ሁሉ ግን በብርሃን ሲገለጥ ይታያል፤ የሚታየው ሁሉ ብርሃን ነውና።”

❖❖❖[ትንቢተ ሕዝቅኤል ምዕራፍ ፫፥፲፰፡፲፱]❖❖❖

እኔ ኃጢአተኛውን። በእርግጥ ትሞታለህ ባልሁት ጊዜ፥ አንተም ባታስጠነቅቀው ነፍሱም እንድትድን ከክፉ መንገዱ ይመለስ ዘንድ ለኃጢአተኛው አስጠንቅቀህ ባትነግረው፥ ያ ኃጢአተኛ በኃጢአት ይሞታል፤ ደሙን ግን ከእጅህ እፈልጋለሁ።

ነገር ግን አንተ ኃጢአተኛውን ብታስጠነቅቅ እርሱም ከኃጢአቱና ከክፉ መንገዱ ባይመለስ፥ በኃጢአቱ ይሞታል፥ አንተ ግን ነፍስህን አድነሃል።”

❖“ትንፋሽ የሌለው ሰው የሞተ እንደሆነ ሁሉ፣ የማትናገር ቤተክርስቲያንም የሞተች ነች” – አባ መዓዛ ክርስቶስ በየነ

***UPDATE***

የእግዚአብሔር መልአክ በዕለተ ሰንበት ሰማኝ ማለት ነው፤ የደቡብ አፍሪቃው ሊቀ-ጳጳስ ታቦ ማክጎባ አመረሩ፤ ከደቂቃዎች በፊት የወጣ መረጃ

👉 “ፕሪቶሪያም ሆኑ የአፍሪካ ህብረት (AU) በአዲስ አበባ በአብዛኛው በትግራይ ደም አፋሳሽ ግጭት አይናቸውን በመሸፈናቸው ፣ የኬፕታውን አንግሊካን ሊቀ ጳጳስ ታቦ ማክጎባ ሌላ ሩዋንዳን የመሰለ የዘር ፍጅት ለመከላከል እርምጃ እየጠየቁ ናቸው፡፡”

❖ ዋው! ለዚህ እኮ ነው “የጽዮን ማርያም ስዕል ያለበትን የጽዮን ሰንደቅ ብንይዝ 1000% እርግጠኛ ነኝ ዛሬ በአክሱም ጽዮን ላይ ከባድ ግፍ በመፈጸም ላይ ያሉት የዋቄዮአላህአቴቴ ወራሪዎች በአንድ ቀን እንደ በረዶ ቀልጠው በጠፉ ነበር” የምለው።

Anglican Archbishop of Cape Town intervenes to prevent Rwanda-like genocide in Ethiopia

With both Pretoria and the African Union (AU) in Addis Ababa largely turning a blind eye to the bloody conflict in Tigray, Anglican Archbishop of Cape Town Thabo Makgoba has taken up the cudgels, demanding action to prevent another Rwanda-like genocide.

______________________________

Posted in Ethiopia, Faith, Infos, Life | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

ልብ ብለናል? | በእንግሊዙ ልዑላውያን ሠርግ ላይ “አቡነ ዘበሰማያት” ያደረሱት የግብጽ ኦርቶዶክስ ሊቀ ጳጳስ ነበሩ

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on May 20, 2018

የ “የዓመቱ ሠርግ” ነው በተባለለትና የእንግሊዙ ልዑል ሃሪ ከ አሜሪካዊቷ ከሜጋን ሜርክል ጋር በ ዊንዘር ቅ/ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ውስጥ ባደርጉት የጋብቻ ስነሥርዓት ላይ የአቡነ ዘመሰማያት ጸሎት እንዲያደርሱ የተጋበዙት በግብጽ ኮፕቲክ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን የለንደን ሊቀ ጳጳስ የሆኑት አቡነ አንጌሎስ ነበሩ። ሙሽራዎቹን ጨምሮ ሁሉም ባንድ ላይ ፀሎት ያደረሱበት ብቸኛ ሥነስርዓት ነበር።

እኔ የምጠየቀው፦

1. እንግሊዛውያኑ ሠርገኞች የተጋቡት በ አንግሊካን ቤተክርስቲያን ሥርዓት መሠረት ነው።

2. ሙሽራዋ ከዚህ በፊት አግብታ የፈታች ናት።

ታዲያ እንዴት ነው አንድ የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን አገልጋይ” በዚህ መላው ዓለም ሁሉ በተከታተለው የሠርግ ሥነስርዓት ላይ፡ ጸሎት ለማድረስ የበቃው ወይም የተፈቀደለት? ኤፒስኮፓሎቹስ አንግሊካውያን ናቸው፤ ግን ካቶሊክን ጨምሮ ሌሎች ዓብያተክርስቲያናት ሳይጋበዙ፤ እንዴት የግብጽ ኦርቶዶክስ ወንድሞቻችን ተጋበዙ?

በጣም የሚገርም ነገር ነው!

______

Posted in Ethiopia, Faith, Infotainment | Tagged: , , , , , , , , , | Leave a Comment »

 
%d bloggers like this: