Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • June 2023
    M T W T F S S
     1234
    567891011
    12131415161718
    19202122232425
    2627282930  
  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

Posts Tagged ‘አንድነት’

ወደ ኤፌሶን ሰዎች ፬ | እርስ በርሳችሁም ቸሮችና ርኅሩኆች ሁኑ ፥ እግዚአብሔርም ደግሞ በክርስቶስ ይቅር እንዳላችሁ ይቅር ተባባሉ

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on August 14, 2022

  • ❖ ትሕትና
  • ❖ የዋሕነት
  • ❖ ቸርነት
  • ❖ እውነተኛነት
  • ❖ ርኅሩሕነት
  • ❖ ትዕግሥት
  • ❖ ፍቅር
  • ❖ ሰላም
  • ❖ አንድነት

❖ አንድ ጌታ አንድ ሃይማኖት አንዲት ጥምቀት፤ ❖

በእውነት ይህ የሐዋርያው የቅዱስ ጳውሎስ መልዕክት በጣም ድንቅ ነው። ለዚህ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ክርስቲያኖች ትውልድ የተላለፈ ሆኖ ነው ያገኘሁት።

በትግራይ በኩል አንዳንድ ግብዞች ባይጠፉም፤ ግን ዛሬ ይህ ሁሉ ግፍና በደል ደርሶባቸው እንኳን ለሰላም፣ ለይቅርታና ለአንድነት እየሰሩ ያሉት የትግራይ ጽዮናውያን ብቻ ናቸው። እስኪ በዙሪያችን እንመልከት! ሜዲያዎቹን እንዳስስ፤ በተለይ “በአማራ” ስም “ለኢትዮጵያና ተዋሕዶ ክርስትናዋ እንታገላለን፣ ስለ ጽዮን ዝም አንልም!” የሚሉትን ግብዞች እንታዘባቸው። እውነቱን ተጋፍጠው እራሳቸውን ለይቅርታና ንስሐ ዝግጁ በማድረግ ፈንታ፤ በፈርዖናዊ ልበ-ደንዳናት “እግዚአብሔር አያውቀውም!” በሚል እርጉም እራስን የማታለያ አካሄዳቸው ዛሬም ከቸርነት፣ ከሰላም፣ ከፍቅርና ከአንድነት ይልቅ የጸበኝነትን፣ የጥላቻንና የውንጀላን እኩይ ተግባር አሰልቺ በሆነ ግትረኝነት፣ እልኸኝነትና በስንፍና ሲፈጽሙት የሚታዩት/የሚደመጡት። እስኪ ለመናዘዝ፣ ለመጸጸትና ይቅርታ ለመጠየቅ ዝግጁ የሆነ አንድ የአማራ ልሂቅ እንፈልግ። አሉ የተባሉትን “መምህራኑን” እና የሜዲያ ሰዎችን ጨምሮ አንድም አስተዋይ ሰው አይታይም/አይሰማም! ከዚህ ሁሉ ጉድ በኋላ እንኳን አማራው ከትግራይ ክርስቲያን ወንድሞቹ ጎን ከሚቆም ይልቅ ዛሬም ከአረብ፣ ከቱርክ፣ ከሱዳን፣ ከግብጽ፣ ከአፋር፣ ከሶማሌ ወይም ከኦሮሞ አህዛብ ጎን ለመቆም የመረጠ ይመስላል። ቅዱስ ጳውሎስ “እርስ በርሳችሁ ቸሮች ርኅሩሖች ሁኑ” አለን እንጅ “ለአሳዳጆቻችሁና ገዳዮቻችሁ አብልጣችሁ ቸሮች ርኅሩሖች ሁኑ!” አላለንም። እያየን ያለው ግን ሁሉም ሰሜናውያን እርስ በርስ አብልጠው ቸርና ርኅሩሕ በመሆን ፈንታ ገዳይ ጠላቶቻቸውን ሲያስቀድሙ ነው። የራሳቸውን ሕዝብ ከማዳን ይልቅ በጠላት ዘንድ መሞገሱን ይሻሉ። በጣም ያሳዝናል! እንደው ምን ያህል በአህዛብ ተጽዕኖ ሥር እንደወደቁና በተግባርም እንደ አህዛብ እየኖሩ ነው። አንዳቸውም እነዚህን ወርቃማ ክርስቲያናዊ ባሕርያት እንደማይከተሉ ዛሬ በግልጽ እያየነው ነው። እኔ በግሌ ምናልባት ከዲያቆን ቢንያም ፍሬው በቀር ሌሎቹ ሁሉ የእነዚህ ክርስቲያናዊ ባሕርያት ተጻራሪዎች ናቸው።

እነዚህን ክርስቲያናዊ የሆኑትንና መንፈሳዊ ማንነትን የሚያንጸባርቁትን ባሕርያት ሁሉ ያላሟላ እንዴት “ቄስ፣ ዲያቆን፣ ካህን ወይም ጳጳስ ነኝ” ለማለት ይደፍራል?! በእውነት ክርስቶስን እንደዚህ ስላልተማሩ ነውን? ወይንስ የቅዱሳኑ አባቶቻችን እርግማን?

❖❖❖ ወደ ኤፌሶን ሰዎች ምዕራፍ ፬ ❖❖❖

  • ፩ እንግዲህ በጌታ እስር የሆንሁ እኔ በተጠራችሁበት መጠራታችሁ እንደሚገባ ትመላለሱ ዘንድ እለምናችኋለሁ፤
  • ፪ በትሕትና ሁሉና በየዋህነት በትዕግሥትም፤ እርስ በርሳችሁ በፍቅር ታገሡ፤
  • ፫ በሰላም ማሰሪያ የመንፈስን አንድነት ለመጠበቅ ትጉ።
  • ፬ በመጠራታችሁ በአንድ ተስፋ እንደ ተጠራችሁ አንድ አካልና አንድ መንፈስ አለ፤
  • ፭ አንድ ጌታ አንድ ሃይማኖት አንዲት ጥምቀት፤
  • ፮ ከሁሉ በላይ የሚሆን በሁሉም የሚሠራ በሁሉም የሚኖር አንድ አምላክ የሁሉም አባት አለ።
  • ፯ ነገር ግን እንደ ክርስቶስ ስጦታ መጠን ለእያንዳንዳችን ጸጋ ተሰጠን።
  • ፰ ስለዚህ። ወደ ላይ በወጣ ጊዜ ምርኮን ማረከ ለሰዎችም ስጦታን ሰጠ ይላል።
  • ፱ ወደ ምድር ታችኛ ክፍል ደግሞ ወረደ ማለት ካልሆነ፥ ይህ ወጣ ማለትስ ምን ማለት ነው?
  • ፲ ይህ የወረደው ሁሉን ይሞላ ዘንድ ከሰማያት ሁሉ በላይ የወጣው ደግሞ ያው ነው።
  • ፲፩ እርሱም አንዳንዶቹ ሐዋርያት፥ ሌሎቹም ነቢያት፥ ሌሎቹም ወንጌልን ሰባኪዎች፥ ሌሎቹም እረኞችና አስተማሪዎች እንዲሆኑ ሰጠ፤
  • ፲፪-፲፫ ሁላችን የእግዚአብሔርን ልጅ በማመንና በማወቅ ወደሚገኝ አንድነት፥ ሙሉ ሰውም ወደ መሆን፥ የክርስቶስም ሙላቱ ወደሚሆን ወደ ሙላቱ ልክ እስክንደርስ ድረስ፥ ቅዱሳን አገልግሎትን ለመሥራትና ለክርስቶስ አካል ሕንጻ ፍጹማን ይሆኑ ዘንድ።
  • ፲፬ እንደ ስሕተት ሽንገላ ባለ ተንኮል በሰዎችም ማታለል ምክንያት በትምህርት ነፋስ ሁሉ እየተፍገመገምን ወዲያና ወዲህም እየተንሳፈፍን ሕፃናት መሆን ወደ ፊት አይገባንም፥
  • ፲፭ ነገር ግን እውነትን በፍቅር እየያዝን በነገር ሁሉ ወደ እርሱ ራስ ወደሚሆን ወደ ክርስቶስ እንደግ፤
  • ፲፮ ከእርሱም የተነሣ አካል ሁሉ እያንዳንዱ ክፍል በልክ እንደሚሠራ፥ በተሰጠለት በጅማት ሁሉ እየተጋጠመና እየተያያዘ፥ ራሱን በፍቅር ለማነጽ አካሉን ያሳድጋል።
  • ፲፯ እንግዲህ አሕዛብ ደግሞ በአእምሮአቸው ከንቱነት እንደሚመላለሱ ከእንግዲህ ወዲህ እንዳትመላለሱ እላለሁ በጌታም ሆኜ እመሰክራለሁ።
  • ፲፰ እነርሱ ባለማወቃቸው ጠንቅ በልባቸውም ደንዳንነት ጠንቅ ልቡናቸው ጨለመ፥ ከእግዚአብሔርም ሕይወት ራቁ፤
  • ፲፱ ደንዝዘውም በመመኘት ርኵሰትን ሁሉ ለማድረግ ራሳቸውን ወደ ሴሰኝነት አሳልፈው ሰጡ።
  • ፳ እናንተ ግን ክርስቶስን እንደዚህ አልተማራችሁም፤
  • ፳፩ በእርግጥ ሰምታችሁታልና፥ እውነትም በኢየሱስ እንዳለ በእርሱ ተምራችኋል፤
  • ፳፪ ፊተኛ ኑሮአችሁን እያሰባችሁ እንደሚያታልል ምኞት የሚጠፋውን አሮጌውን ሰው አስወግዱ፥
  • ፳፫ በአእምሮአችሁም መንፈስ ታደሱ፥
  • ፳፬ ለእውነትም በሚሆኑ ጽድቅና ቅድስና እንደ እግዚአብሔር ምሳሌ የተፈጠረውን አዲሱን ሰው ልበሱ።
  • ፳፭ ስለዚህ ውሸትን አስወግዳችሁ፥ እርስ በርሳችን ብልቶች ሆነናልና እያንዳንዳችሁ ከባልንጀሮቻችሁ ጋር እውነትን ተነጋገሩ።
  • ፳፮ ተቆጡ ኃጢአትንም አታድርጉ፤
  • ፳፯ በቁጣችሁ ላይ ፀሐይ አይግባ፥ ለዲያብሎስም ፈንታ አትስጡት።
  • ፳፰ የሰረቀ ከእንግዲህ ወዲህ አይስረቅ፥ ነገር ግን በዚያ ፈንታ ለጎደለው የሚያካፍለው እንዲኖርለት በገዛ እጆቹ መልካምን እየሠራ ይድከም።
  • ፳፱ ለሚሰሙት ጸጋን ይሰጥ ዘንድ፥ እንደሚያስፈልግ ለማነጽ የሚጠቅም ማናቸውም በጎ ቃል እንጂ ክፉ ቃል ከአፋችሁ ከቶ አይውጣ።
  • ፴ ለቤዛም ቀን የታተማችሁበትን ቅዱሱን የእግዚአብሔርን መንፈስ አታሳዝኑ።
  • ፴፩ መራርነትና ንዴት ቁጣም ጩኸትም መሳደብም ሁሉ ከክፋት ሁሉ ጋር ከእናንተ ዘንድ ይወገድ።
  • ፴፪ እርስ በርሳችሁም ቸሮችና ርኅሩኆች ሁኑ፥ እግዚአብሔርም ደግሞ በክርስቶስ ይቅር እንዳላችሁ ይቅር ተባባሉ።

______________

Posted in Ethiopia, Faith, War & Crisis | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

ኢትዮጵያን ከፍ የሚያደርጓት እነ ቅዱስ ያሬድ እየመጡ ነውና ተዋሕዷውያን ወደ አንድ እንሰባሰብ

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on March 5, 2022

👉 ገብርኤል 👉 ማርያም 👉 ኡራኤል 👉 ጊዮርጊስ 👉 ተክለ ሐይማኖት 👉 ዮሴፍ 😇 መድኃኔ ዓለም

💭 ሁሉም ከጸዳ በኋላ ቅዱስ ያሬድ በስውር እያሰለጠናቸው ያሉት ትክክለኛዎቹ ካህናት ይወጣሉ፤ እውነተኞቹን ተዋሕዶ ክርስቲያኖችን የሚሰበስብ፣ ክርስቶስን የሚወድና እስልምናን የሚጠላ አንድ ቅዱስ ሰው በእግዚአብሔር ተቀብቶ ይወጣል። ያኔ የእስልምና አምልኮ ከምድረ ገጽ ይጠፋል። እውነተኞቹ ኢትዮጵያን የሚያውቋት ያውቁታልና ወደ አንድ ይሰባሰባሉ። መቶ ሚሊየን የሚሆነው ነዋሪ ኢትዮጵያን አያውቃትምና ሁሉም ይጠፋል። በአፋቸው ሳይሆን በህሊናቸው ኢትዮጵያንና ተዋሕዶን ከልባቸው የያዙት፣ ደሞዝ እየተከፈላቸው ካህናት የሆኑት ሳይሆኑ፣ በደሞዙ የሚንጠራሩት ሳይሆኑ፣ በዘረኝነት የተለከፉት ሳይሆኑ፣ ዘረኛ፣ ዘማዊና ጉቦኛ ያልሆኑት፣ ዘረኛ ያልሆኑትንና በፍቅር የሚመላለሱትን ምዕመናንን ጨምሮ ሁሉም በቅዱሱ ሰው ዙሪያ ተሰባስበሰው ኢትዮጵያን ይኖሩባታል።

†††[ትንቢተ ኢሳይያስ ምዕራፍ ፲፩፥፮]†††

ተኵላ ከበግ ጠቦት ጋር ይቀመጣል፥ ነብርም ከፍየል ጠቦት ጋር ይተኛል፤ ጥጃና የአንበሳ ደቦል ፍሪዳም በአንድነት ያርፋሉ፤ ታናሽም ልጅ ይመራቸዋል።”

❖❖❖ይህ ዓለም ካዘጋጀልን ወጥመድና መከራ ሰውሮ ወደ አንድነት ይሰብስበን!❖❖❖

†††[ትንቢተ ኢሳይያስ ምዕራፍ ፲፩]†††

፩ ከእሴይ ግንድ በትር ይወጣል፥ ከሥሩም ቍጥቋጥ ያፈራል።

፪ የእግዚአብሔር መንፈስ፥ የጥበብና የማስተዋል መንፈስ፥ የምክርና የኃይል መንፈስ፥ የእውቀትና እግዚአብሔርን የመፍራት መንፈስ ያርፍበታል።

፫ እግዚአብሔርን በመፍራት ደስታውን ያያል። ዓይኑም እንደምታይ አይፈርድም፥ ጆሮውም እንደምትሰማ አይበይንም፤

፬ ነገር ግን ለድሆች በጽድቅ ይፈርዳል፥ ለምድርም የዋሆች በቅንነት ይበይናል፤ በአፉም በትር ምድርን ይመታል፥ በከንፈሩም እስትንፋስ ክፉዎችን ይገድላል።

፭ የወገቡ መታጠቂያ ጽድቅ፥ የጎኑም መቀነት ታማኝነት ይሆናል።

፮ ተኵላ ከበግ ጠቦት ጋር ይቀመጣል፥ ነብርም ከፍየል ጠቦት ጋር ይተኛል፤ ጥጃና የአንበሳ ደቦል ፍሪዳም በአንድነት ያርፋሉ፤ ታናሽም ልጅ ይመራቸዋል።

፯ ላምና ድብ አብረው ይሰማራሉ፥ ግልገሎቻቸውም በአንድነት ያርፋሉ፤ አንበሳም እንደ በሬ ገለባ ይበላል።

፰ የሚጠባውም ሕፃን በእባብ ጕድጓድ ላይ ይጫወታል፥ ጡት የጣለውም ሕፃን በእፉኝት ቤት ላይ እጁን ይጭናል።

፱ በተቀደሰው ተራራዬ ሁሉ ላይ አይጐዱም አያጠፉምም፤ ውኃ ባሕርን እንደሚከድን ምድር እግዚአብሔርን በማወቅ ትሞላለችና።

፲ በዚያም ቀን እንዲህ ይሆናል፤ ለአሕዛብ ምልክት ሊሆን የቆመውን የእሴይን ሥር አሕዛብ ይፈልጉታል፤ ማረፊያውም የተከበረ ይሆናል።

፲፩ በዚያም ቀን እንዲህ ይሆናል፤ የቀረውን የሕዝቡን ቅሬታ ከአሦርና ከግብጽ፥ ከጳትሮስና ከኢትዮጵያ፥ ከኤላምና ከሰናዖር ከሐማትም፥ ከባሕርም ደሴቶች ይመልስ ዘንድ ጌታ እንደ ገና እጁን ይገልጣል።

፲፪ ለአሕዛብም ምልክትን ያቆማል፥ ከእስራኤልም የተጣሉትን ይሰበስባል፥ ከይሁዳም የተበተኑትን ከአራቱ የምድር ማዕዘኖች ያከማቻል።

፲፫ የኤፍሬምም ምቀኝነት ይርቃል፥ ይሁዳንም የሚያስጨንቁ ይጠፋሉ፤ ኤፍሬምም በይሁዳ አይቀናም፥ ይሁዳም ኤፍሬምን አያስጨንቅም።

፲፬ በምዕራብም በኩል በፍልስጥኤማውያን ጫንቃ ላይ እየበረሩ ይወርዳሉ፥ የምሥራቅንም ልጆች በአንድነት ይበዘብዛሉ፤ በኤዶምያስና በሞዓብም ላይ እጃቸውን ይዘረጋሉ፥ የአሞንም ልጆች ለእነርሱ ይታዘዛሉ።

፲፭ እግዚአብሔርም የግብጽን ባሕር ያጠፋል፤ በትኩሱም ነፋስ እጁን በወንዙ ላይ ያነሣል፥ ሰባት ፈሳሾችንም አድርጎ ይመታዋል፥ ሰዎችም በጫማቸው እንዲሻገሩ ያደርጋቸዋል።

፲፮ ከግብጽም በወጣ ጊዜ ለእስራኤል እንደ ነበረ፥ ለቀረው ለሕዝቡ ቅሬታ ከአሦር ጐዳና ይሆናል።

______________

Posted in Ethiopia, Faith, War & Crisis | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

የኖቤል የሰላም ተሸላሚው ግራኝ አሕመድ አሊ ጥቁሩ አዶልፍ ሂትለር ነው | የአህዛብ ርኩሰት

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on July 21, 2021

M & M

👉 Hitler’s Book: ‘Mein Kampf/My Struggle’ = Abiy Ahmed’s Book : Medemer/ Synergy

🆚

M & M ☆ = 👉 Mohammad + Martin Luther

👉 Senator Jim Inhofe, Presbyterian Protestant Guardian of Pentecostal-Muslim Protestant Abiy Ahmed Ali

# ትግራይ የዘር ማጥፋት ወንጀል | የኖቤል የሰላም ተሸላሚ ጠ / ሚ አሕመድ ጥቁር አዶልፍ ሂትለር?

&

👉 የሂትለር መጽሐፍ ማይን ካምፍ / ትግሌ” = የአብይ አህመድ መጽሐፍ መደመር

🆚

& ☆ = ሀመድ + ርቲን ሉተር

👉 ፕሬስበቴሪያን ፕሮቴስታንቱ ሴናተር ጂም ኢንሆፌ = የፔንጠቆስጤሙስሊሙ ፕሮቴስታንት አቢይ አህመድ አሊ ጠባቂ

Mohammed Amin al-Husseini / መሀመድ አልሁሴይኒ☆

ሂትለር አይሁዶችን ለማባረር እንጅ ለመግደል አልፈለገም ነበር ፥ ግን ፍልስጤማዊው ሙስሊም፤ ሙፍቲ አልሁሴይኒ ነበር አይሁዶችን እንዲጨፈጭፍ የአሳመነው” ይላሉ የቀድሞው የእስራኤል ጠ/ር ናታንያሁ።

Mufti Mohammed Amin al-Husseini / ሙፍቲ መሀመድ አል-ሁሴይኒ ከናዚው አዶልፍ ሂትለር ጋር☆

የኔዘርላንድሱ ፖለቲከኛ ጌርድ ቪልደርትስ፤

አደገኛው ቁርአን መታገድ አለበት፤ ከሂትለር መጽሐፍ ጋር ተመሳሳይ ነውና”

ይህ የአህዛብ ርኩሰት ያመጣው ጣጣ ነው፤ ለዲያብሎስ ተላልፈው የተሰጡት ሕዝቦች አህዛብ ይባላሉ፤ እነዚህ አህዛብ ናቸው ዛሬ አማራውን፣ ኦሮሞውን፣ ኤርትራዊውን/ቤን አሚር፣ ሶማሌውን ብሎም ከላይ እስከታች የቤተ ክርስቲያን “አገልጋይ” የተባለውን ሁሉ (የዋቄዮ-አላህ-ዲያብሎስ ጭፍሮች) በመንፈስ የተቆጣጠሯቸው።

በትግራይ ላይ የሚካሄደው ጂሃድ አህዛብ የትክክለኛዎቹን ተዋሕዶ ኢትዮጵያውያን ተፈጥሯዊ ጸጋና በረከት ለመስረቅና የራስ ለማድረግ የሚሰሩ የጥፋትና የሞት አሰራር ይዘው የመጡ የዲያብሎስ ጭፍሮች ናቸው። ምክኒያቱም የዲያብሎስ ልጆች ሁሉ ስምና ክብራቸው የሚሠሩት ተፈጥሯዊ ጸጋና በረከት ያለውን ሌላ አንድ አካል በመግደል፣ በማፍዘዝ፣ በማሰር፣ በማሳበድ፣ በሽተኛ በማድረግ ነውና። ስጋ ተፈጥሯዊ ጸጋና በረከት የለውም፤ የመንፈስን ስምና ክብር ነው የራሱ የሚያደርገው። ስለዚህም ደግሞ ያ መንፈሳዊ አካል ሊሞት የግድ ይሆናል። የስጋ ስምና ክብር አንጻራዊ ስለሆነ የግድ አንድን መንፈሳዊ አካል መስዋዕት አድርጎ ያቀርባል። ገድሎ፣ አጥፍቶ፣ ሠርቆ፣ አጭበርብሮነው ስሙንና ክብሩን የሚሠራው። ስዚህም ነው ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስለ ዲያብሎስ ዓላማ ሲናገር፤ “ሌባው ሊሰርቅና ሊያርድ ሊያጠፋም እንጂ ስለ ሌላ አይመጣም”[የዮሐንስ ወንጌል ምዕራፍ ፲፥፲] ያለው። አስቀድሞም ራሱ ዲያብሎስ በዚህች ምድር ላይ ገዥና መንግስት የሆነው የራሱ ያልሆነውን የአዳምን(ሰው)ተፈጥሯዊ

ጸጋና በረከት የጥፋትን ዕውቀት፣ ጥበብና ኃይል በመጠቀም ለራሱ ማድረግ በመቻሉ ነበር። ዲያብሎስ በምድርና በውስጧ ባሉት ሁሉ ላይ ገዥ እንዲሆን አልተፈጠረም። እርሱ በዚህች ምድር ላይ ገዥ የሆነውን የሌላን አካል የአዳምን ጸጋና በረከት የርሱ ማድረግ በመቻሉ መሆኑን ማወቅ አለብን። አዳም የሞትን ፍሬ እንዲበላ ማድረግ በመቻሉ ነበር በምድርና በውስጧ ያሉትን ሁሉ እንዲገዛ የተሰጠውን ሥልጣን የነጠቀውና የራሱ ያደረገው። ልጆቹም እንዲሁ ናቸው። ዲያብሎስ በሌላ ሰው ጸጋና በረከት የሚኖርን፣ የሚገለጥና የሚነግስ የምኞት አካል ነው። ይህም ደግሞ ስጋ የምንለው የሞትና የባርነት ማንነትና ምንነት ነው፤ የስጋ ስምና ክብር። የዲያብሎስን ዕውቀት፣ ጥበብና ኃይል ለተፈለገው ዓላማ ለጥቅም ለማዋል ደግሞ እነዚህን የርኩሰትና የጥፋ አሠራሮችን መፈጸም የግድ ይሆናል።

[ኦሪት ዘዳግም ምዕራፍ ፲፪፥፴፩]

እግዚአብሔር የሚጠላውን ርኵሰት ሁሉ እነርሱ ለአማልክቶቻቸው አድርገዋልና፥ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻቸውን ደግሞ ለአማልክቶቻቸው በእሳት ያቃጥሉአቸዋልና አንተ ለአምላክህ ለእግዚአብሔር እንዲሁ አታድርግ።”

በዲያብሎስ የሚያምን ለእርሱም የሚገዛ ሁሉ ይህን የርኩሰት አሠራር የመፈጸም ግዴታ አለበት። አህዛብ የዋቄዮ-አላህ-ዲያብሎስ ልጆች በትግራይ ተዋሕዶ ክርስቲያን ሕዝብ ላይ እየፈጸሙት ያሉትም ይህን የርኩሰት አሠራር ነው። የዋቄዮ-አላህ-ዲያብሎስ ልጆች በተለይ ከምኒልክ ፪ኛው መምጣት አንስቶ ላለፉት መቶ ሠላሳ ዓመታት በትግራይ ላይ የሚያካሂዱት ጂሃዳዊ ዘመቻ ዋናው ተልዕኮ፤ እግዚአብሔር ለትግራይ ኢትዮጵያውያን የሰጣቸውንና ከአዳም ዘመን አንስቶ ተከላከሎ ያቆየላቸውን ተፈጥሯዊ ጸጋና በርከት መስረቅና የራሳቸው ማድረግ ነው። አይሳካላቸውም እንጂ!

______________________________________

Posted in Ethiopia, Faith, War & Crisis | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

Stop The Genocide in Tigray | Back to The Roots

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on July 20, 2021

_____________________________________

Posted in Ethiopia, Infos, Music, War & Crisis | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

መላዋ ፈረንሳይ እና ፕሬዚዳንቷ በሙስሊሞች አንገቱን ለተቀላው መምህር ብሔራዊ ክብር ሰጡ | እኛስ?

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on October 24, 2020

ሳሙኤል ፓቲይ የተባለው መምህር በክፍሉ ውስጥ አወዛጋቢ የነብዩ መሐመድ የካርቱን ስዕሎችን ለተማሪዎቹ ካሳየ በኋላ ከትናንት በስቲያ አንድ የ፲፰ ዓመት ወጣት ትምህርት ቤት አቅራቢያ አንገቱን መቅላቱ ይታወሳል።

ሳሙኤል ፓቲይ የሚያስተምርበት ትምህርት ቤት መምህራንን ጨምሮ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች “እኔም መምህር ነኝ” “እኛ ፈረንሳይ ነኝ” የሚሉ መፈክሮችን ይዘው አደባባይ ወጥተዋል።

ጥቃቱ ከተፈጸመ በኋላ የፈረንሳዩ ፕሬዝደንት ኢማኑኤል ማክሮን መምህሩ አንገቱ ተቀልቶ የተገደለው “በእስላማዊ የሽብር ጥቃት ነው” ብለው ነበር።

አሸባሪው ግራኝ አብዮት አህመድ አሊ የኢትዮጵያ መሪ እንዳልሆነና የሃገራችን ጠላት እንደሆነም በተደጋጋሚ አይተነዋል ስለዚህ በዋቄዮ-አላህ ልጆች በመገደል ላይ ስላሉት ኢትዮጵያውያን የተዋሕዶ ልጆች እንኳን ብሔራዊ የመታሰቢያ ቀን ሊያውጅ የማይሰማውን “ሃዘኑን” እንኳን እንደ ፖለቲከኛ ለመግለጥ እንደማይሻ ከአንዴም አሥር ጊዜ አይተነዋል። በሌላ በኩል ግን የተደራጁ ኢትዮጵያውያን ተቋማት ለምሳሌ ቤተ ክህነት ለምንድን ነው ተዋሕዶ ኢትዮጵያውያን በጎቿን “ወደ መንገድ እንውጣና ሃዘናችንን እንግለጥ! ታግተው የተሰወሩት ሴት ተማሪዎች የት እንደደረሱ እንጠይቅ!” የማትለው?

____________________________

Posted in Curiosity, Ethiopia, Infos | Tagged: , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

ከኮሙኒዝም ሲዖል የተረፉት ኦርቶዶክስ ሩሲያውያን በኦሮሞ ሲዖል እየተካሄደ ስላለው የክርስቲያኖች ጭፍጨፋ

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on October 14, 2020

በዚህ የሩሲያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ቴሌቬዥን ባቀረበው ድንቅ ሪፖርት የተካተቱት ጽሑፎች፦

የሚያሳዝነውና ለማመን የሚያስቸግረው ነገር ደግሞ፤ ይህ ሁሉ ጭፍጨፋ የሚካሄደው ከአፍሪቃ በጣም ክርስቲያናዊት ሃገር በሆነችው በኢትዮጵያ መሆኑ ነው።”

እነዚህ ቃላት ብዙ ነገር ይነጉርናል!

+++የኢትዮጵያ መስቀል+++

👉 ኦሮሚያ በተባለው የኢትዮጵያ ክልል አብያተ ክርስቲያናት ተቃጥለዋል፣ ተዘርፈዋል፣ ብዙ ካህናትና ምእመናን ተገድለዋል።

👉 ፪ ሚሊየን ኢትዮጵያውያን በገዛ አገራቸው ስደተኞች ለመሆን ተገድደዋል።

👉 በተዋሕዶ ክርስቲያኖች ላይ መንግስታዊ የሆነ ስደት እና በደል እየተካሄደ ነው።

👉 ይህ መንግስታዊ ስደት በጣም ጭካኔ የተሞላበትና ብዙ ደም የፈሰሰበትም ነው።

👉 መሀመዳውያኑ ማህተብና መስቀል ያደረጉ ክርስቲያኖችን እያሳደዱ በድንጋይ ወግረው፣ በሜንጫና በጠርሙስ ሳይቀር አርደው ይገድሏቸዋል።

👉 የዚህም ስደት ተቀዳሚ ዓላማ ክርስቲያኑ መስቀሉን እንዳያደርግ፣ ማንነቱን እንዲቀይርና አካባቢውን ለቅቆ እንዲሄድ ለማስገደድ ነው።

👉 ጋሎቹ ክርስቲያኖችን በእንደዚህ ዓይነት ሜንጫ ያሳድዳሉ፤ ይህ ሁሉ ጉድ ህልም አይደለም፡ እውነታ እንጅ።

👉 በኦሮሚያ የሚካሄደው ጭካኔ የምታዩት ነው፤ በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ተዋሕዶ ክርስቲያኖች በሜንጫ፣ በካራ፣ በዱላና በጥይት ተቀጥቅጠው ተገድለዋል።

👉 የሚያሳዝነውና ለማመን የሚያስቸግረው ነገር ደግሞ፤ ይህ ሁሉ ጭፍጨፋ የሚካሄደው ከአፍሪቃ በጣም ክርስቲያናዊት ሃገር በሆነችው በኢትዮጵያ መሆኑ ነው።

👉 በኢትዮጵያ ክርስቲያኖችና ሙስሊሞች ለዘመናት በአንፃራዊ ሰላም ኖረዋል፤ ዛሬ ግን ሁሉም ነገር

ተቀይሯል፤ ሙስሊሞቹ ስለ እምነታቸው በግልጽ ማወቅ ሲችሉ ክርስቲያኖችን ማሳደድ ጀምረዋል።

👉 የእስልምና መሪዎች ከመንግስትና ፖሊስ ጋር በመናበብና በማበር ክርስቲያኖችን እያጠቁ ነው፤ ገዳዮችን እየደበቁ ነው፤ ስለ ግድያውና ስደቱ መረጃ እንዳይወጣም አፍነውታል።

👉 መንግስት ክርስቲያኖችን አይረዳም፤ አይጠብቅም፤ እስካሁን በብዙ ሺህ ክርስቲያኖች ተገድለዋል፤

በጣም ብዙዎች ቆስለዋል፣ ተሰድደዋል።

👉 የኦሮሞ ጽንፈኞቹ ዓላማቸው የገደሉትን ገድለው የተረፉትንም አካለስንኩል ማድረግና ማኮላሸት ነው።

👉 የሚገርመው፤ ዋና ዋናዎቹ ዓለም አቀፋዊ የመገናኛ ብዙሃን በኢትዮጵያ ክርስቲያኖች ላይ ስለሚካሄደው ጭፍጨፋ አንድም ቃል ለመተንፈስ አለመቻላቸው/አለመፈለጋቸው ነው።

👉 ጭፍጨፋው የቀጠለው ሜዲያዎቹ ፀጥ በማለታቸው ነው፤ ይህ ሁኔታ መቀየር አለበት፤ እኛ መናገር አለብን!

👉 የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያንን መስበር ማለት፤ ሃገሪቷን ማፈራረስ በአካባቢው ያሉትን ሃገራትንም ማተረማመስ ማለት ነው።

👉 በኢትዮጵያ ተዋሕዷውያን ከ ፷/60 በመቶ በላይ መሆናቸው አገዛዙን አላስደሰተውም።

👉 በጎንደር አካባቢ ያሉ ክርስቲያኖች ከሩሲያ እና ከመላው ኦርቶዶክሱ ዓለም ዕርዳት ማግኘት ይሻሉ።

👉 ስለ ኢትዮጵያ ክርስቲያኖች በማስታወሳችን ብቻ ተዋሕዷውያን ምስጋናቸውን እየገለጡልን ነው።

👉 ኢትዮጵያ ክርስቲያን የሆነችው በአንደኛው ክፍለ ዘመን ሐዋርያው ፊሊጶስ የኢትዮጵያን ጃንደረባ ካጠመቀበት ዘመን አንስቶ ነው።

👉 ዛሬ በኢትዮጵያ አብዛኛዎቹ የዓለማችን ጽኑ ክርስቲያኖች የሚኖሩባት ሃገር ናት፤ ተዋሕዷውያን ከ፷፭/65 ሚሊየን በላይ እንደሆኑ ይገመታል።

👉 እንደ እኔ ግንዛቤ ከሆነ ኢትዮጵያውያን በግለሰብ ደረጃ ከክርስቶስ ጋር ጽኑ ግኑኝነት ያላቸው ክርስቲያኖች ሆነው ይታያሉ፤ ይህ በእኛ ሃገር በሩሲያ እንኳን አይታይም።

👉 በክብረ በዓላቱ ወቅት፤ በተለይ ደግሞ በጸሎትና ሥርዓተ ቅዳሴ ወቅት ከእግዚአብሔር ጋር ምን ያህል ጥልቅ ግኑኝነት እንዳላቸው ለምታዘብ በቅቻለሁ።

👉 የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ የበላይ ሓላፊ ከሩሲያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስትያን ፓትሪያርክ

ከብፁዕ ወቅዱስ ኪሪል ጋር በሩሲያ አብረው ተምረዋል።

👉 ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ በሩሲያ።

👉 የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ለብዙ ዘመናት ለውጩ ዓለም ዝግ ሆና በመቆየቷ ሌሎች የጠፋባቸውን

በጣም ክቡርና ውድ የሆኑ ነገሮችን ሁሉ ለመጠበቅ ችላለች።

👉 ለኢትዮጵያውያን ክርስቶስ ሕይወት ነው፤ ለክርስቶስ ባላቸው እምነት ሕይወታቸውን ለመስጠት ዝግጁዎች ናቸው።

👉 እስከ ቅርብ ጊዜ በኮሙኒዝም ሥርዓት ሲበደሉ፣ ሲሰደዱና ሲሰቃዩ የነበሩት ሩሲያውያን ዛሬ በኢትዮጵያውያን ክርስቲያኖች ላይ የደረሰውን ህመም በቀላሉ መረዳት ይችላሉ።

__________________________

Posted in Ethiopia, Faith, Infos | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

ልዩነት ውበት መሆኑን ቤተክርስቲያን ብቻ ነች የምታሳየው

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on September 20, 2019

_____________________

Posted in Ethiopia, Faith, Life, Love | Tagged: , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

 
%d bloggers like this: