Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on February 4, 2020
ይህን የአንበሳ ግልገል ሳይ የደምቢዶሎ እህቶቻችን ናቸው ብልጭ ብለው የታዩኝ።
እህቶቻችን የታገቱት በአላጋጩ እና ተሳላቂው አብዮት አህመድ ነው። 100%። ያው እያያችሁት ነው፤ የም ዕራባውያኑን ርካሽ የስነ–ልቦና ጨዋታ በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ በሙከራ መልክ ለማዋል አማካሪዎቹ እነ ዶ/ር ወዳጄነህ የሰጡትን “አበባ” በማንሳት (ችግኙ አበበ) የታገቱትን ሕፃናትና እናቶች ሰቆቃ ለማረሳሳት፣ የሕዝቡን ቁጣ ለማቀዝቀዝ ሞክሯል። ይህ ጨካኝና አላጋጭ ግለሰብ ለሁለት ወራት ያህል ኢትዮጵያውያን ዝም ማለታቸውን ዝም ብሎ በመታዘብ ከቆየ በኋላ አሁን “አሉታዊውን” “በአዎንታዊ” የመተካት የስነ–ልቦናዊ ሙከራዎች በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ ለማካሄድ በመድፈር ላይ ነው። “ምንም አታመጡም!” ነው ጨዋታው።
“ኢትዮጵያዊ ነኝ” የሚል ሁሉ ያለምንም ቅድመ ዝግጅት ወደ አራት ኪሎ በማምራት ይህ ወራዳ ከምኒሊክ ቤተ መንግሥት እስካልወጣ ድረስ የግቢውን አጥር በቁጣ መነቅነቅ ይኖርበታል።
_______________________________
Like this:
Like Loading...
Posted in Curiosity, Ethiopia, Infos | Tagged: መንግስት, ሽብር, አብይ አህመድ, አንበሳ, አንቱ አንተ, አውሬው መንግስት, ኢትዮጵያ, ዝንጀሮ, የሰብዓዊ መብት ጥሰት, የታገቱ ተማሪዎች, ደምቢዶሎ, ግልገል | Leave a Comment »
Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on January 31, 2020
በዋሽንግተን ዲሲ የተቃውሞ ሰልፍ ላይ ነበር ይህ ክስተት የተፈጠረው። መፈክሮቹ ጥሩዎች ናቸው። ግን በአንዳንዶች ዘንድ ይህን ወራዳ ግለሰብ “አንቱም” “ዶክተረም” ብሎ ለመጥራት የተደረገው ሙከራ ተገቢ አይደለም። እስኪ ይታየን፤ ለአሜሪካ ብልጽግና እና ደህንነት ተግቶ በመሥራት ላይ ያሉትንና በሕዝብ የተመረጡትን ሃገር–ወዳዱን ፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕን “አንተ” ይሏቸዋል፤ ለኢትዮጵያ ውድቀት ተግቶ በመሥራት ላይ ያለውንና ያልተመረጠውን ፀረ–ኢትዮጵያ ግለሰብ ግን “አንቱ”። ምን ዓይነት ቅሌት ነው?! እኔ እንደተረዳሁት፤ ይህን እራስ አፍቃሪ/ ናርሲስት ግለሰብ በ“አንቱ” እና “ዶ/ር” መልክ የሚጠራ ወገን ልክ እንደ ግብዝ ደጋፊዎቹ ነፍሱን ቀስ በቀስ ቆርሶ በመጣልና በማድከም የአብዮትን የሥልጣን እድሜ ለማራዘም ብሎም ሰውየው በሕዝብ ላይ የሚሳለቅበትን ዘመን ለማስቀጠል አስተዋጽኦ እንደሚያበረክት ከወዲሁ ሊያውቀው ይገባል። በአለፉት ሁለት ዓመታት በሃገራችን ሕዝብ ላይ ያን ሁሉ ታይቶና ተሰምቶ የማይታወቅ ሰቃይና መከራ ያመጣውንና የኢትዮጵያ ጠላት ሆኖ በግልጽ የሚሠራውን ይህን ወሮበላ ግለሰብ ማክበርና መፍራት ተገቢ አይደለም፤ ኢትዮጵያዊነትን ማርከስ ነው የሚሆነውና ፥ ጠቅላይ ሚንስተርነቱንም ሕዝብ የሰጠው አይደለምና።
ሌላው አስገራሚ ክስተት፦ ጉግል አስተርጓሚ ገብታችሁ በእንግሊዝኛው “Abiy Ahmed“ ብላችሁ ብትጽፉ በአማርኛው “ዶ/ር አብይ አህመድ” በሚል መልክ ተተርጉሞ ይነበባል። ይህ በአማርኛው ቋንቋ ብቻ እንጂ በሌሎች ቋንቋዎች የለም። ይህን እንግዲህ ለአውሬው የጉግል ተቋም ተቀጥረው የሚሠሩ የአማርኛ ቋንቋ ተናጋሪዎች የሆኑ የገዳይ አብይ ደጋፊዎች ፕሮግራም ያደረጉት መሆኑ ነው። በአፋጣኝ ብታርሙት ይሻላችኋል!
__________________________
Like this:
Like Loading...
Posted in Curiosity, Ethiopia, Infos | Tagged: መንግስት, ሽብር, አብይ አህመድ, አንቱ አንተ, አክብሮት, አውሬው መንግስት, ኢትዮጵያ, ክብር መስጠት, ዋሽንግተን ዲሲ, የሰብዓዊ መብት ጥሰት, የተቃውሞ ሰልፍ, የታገቱ ተማሪዎች | Leave a Comment »