Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

Posts Tagged ‘አንበጣ’

“ናግራን” ሳውዲ አረቢያ በአንበጣ መንጋ ተወረረች

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on May 2, 2019

ሰማዕታተ ናግራን

ከኢትዮጵያ (ኤርትራ + ሱዳን) አካባቢ የተነሳው የአንበጣ መንጋ በሳውዲ እና የመን መዋሰኛ የምትገኘውን የናግራን ከተማ ወርሯል። በ፮ኛው መቶ ክፍለ ዘመን የኢትዮጵያ (የአክሱም) መንግሥት

ቀይ ባሕርን ተሻግሮ እስከ ደቡብ ዓረብ (የመን) ድረስ ግዛቱን አስፍቶ እንደነበር የሚታወቅ ነው። ከ495-525 .. የነገሠው የሀገራችን ንጉሥ አጼ ካሌብ በየመን (ናግራን/Najran) አካባቢ የሚገኙ ክርስቲያኖች፡ ድሁ ንዋስ (ፊንሐስ) በተባለ አይሁዳዊ ከደረሰባቸው ጥቃት ለመከላከል መቶ ሃያ ሺህ ሠራዊት በ፷ መርከቦች አዝምቶ ከጥቃት ታድጓቸዋል።

ለሰማዕታቱም መታሰቢያ ይሆን ዘንድ በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን የሐዋርያነት ታሪክ በዐረቢያ ምድር የመጀመሪያው ድንቅ ቤተ ክርስቲያን ከ1400 ዓመታት በፊት በዚሁ በናግራን ታንጾ ነበር፤ ይህም የቅድስት ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን ነበር። ነገር ግን እርኩሱ መሀመድ (በገሃነም እሳት ይቃጠል) 622 .ም ጀምሮ በዲያብሎሳዊው ጂሃዱ እና “ሁለት ሃይማኖቶች በአረቢያ ጎን ለጎን መኖር የለባቸውም” በሚል መርሆው እዚያ የነበሩትን ተዋሕዶ ክርስቲያኖችን (ደካማ በነበረበት ዘመን መጠለያ ሰጥተውት የነበሩትን) በመጨፍጨፍ ቤተክርስቲያናቸውን አፈራርሶባቸዋል። ከዚያ ጊዜ ጀምሮ ዛሬ ሳውዲ አረቢያ ተብሎ በሚጠራው ሃገር በምትገኘዋ በናግራን ከተማ ክርስቲያኖች አይኖሩም።

የመጀመሪያ ማሰንቀቂያ የሆነው ይህ የአንበጣ መንጋ በሚቀጥሉት ሳምንታት ወደ አረብ ኤሚራቶች፣ ኢራን እና ግብጽ ያመራል። እኛ ዝም ብንል የሰማዕታት ደም ዝም አይልም፤ ይጮኻል፣ ይጣራልፈስሶ አይቀርምሊቢያና የመን ውጥንቅጣቸው እየወጣ እንደሆነ እያየን ነው፣ ግብጽና ሳውዲም አንበጣ ብቻ ሳይሆን ገና እሳት ይወርድባቸዋል።

[ኦሪት ዘጸአት ምዕራፍ ፲፡፬፥፭]

አንበጣዎች

ሕዝቤን ለመልቀቅ እንቢ ብትል ግን፥ እነሆ ነገ በአገርህ አንበጣዎችን አመጣለሁ፤ የምድሩንም ፊት ይሸፍኑታልና ምድሩን ለማየት አይቻልም፤ ከበረዶውም አምልጦ የተረፈላችሁን ትርፍ ይበሉታል፥ ያደገላችሁንም የእርሻውን ዛፍ ሁሉ ይበሉታል

__________________

Posted in Curiosity, Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , | Leave a Comment »

የለገጣፎ እንባ | ግብጽ እና ሳውዲ አረቢያ በመጪዎቹ ወራት ታይቶ የማይታወቅ የአንበጣ መቅሰፍት ይመጣባቸዋል

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on February 24, 2019

የአንበጦቹ መነሻም ከኢትዮጵያ(ኤርትራ)እና ሱዳን ነው

የግራኝ አህመድና ዋቄዮ አላህ ልጆች ሞግዚቶች ሳውዲ አረቢያ፣ ግብጽ፣ ኤሚራቶች፣ ቱርክ፣ አሜሪካ እና አውሮፓ ናቸው። ሁሉም የአውሬው ፍየል አገሮች ናቸው፤ ወዮላቸው! ንፍጣቸውን እንኳን ያልጠረጉ ውርንጭላዎች በአገራችን ላይ ሲሳለቁና ሲሳሳቁ የእኛ ደካማ ትውልድ በዝምታ ማለፉን ቢመርጥና በከንቱ የእባቡን ጅራት ለመያዝ ቢደክምም፤ እግዚአብሔር ግን ዝም አይልም፤ አይዘገይም፤ የእባቡን እራስ ነው የሚቀጠቅጠው።

አንዳንዴ እንዲያውም የጣናው እንቦጭ መብቀል እና በአንዳንድ ገዳማቱ ቅዳሴ ማቆም ምናልባት እግዚአብሔር ግብጽን ለመቅጣት ያዘጋጀው ቅድመ ሁኔታ ሊሆን ይችላል የሚል ሃሳብ አለኝ። እስራኤላውያን ግብጽን ለቀው ከወጡበት ዘመን አንስቶ የአባይን ውሃ በመባረክ ላይ ያተኮረው የአባቶቻችን የፀሎት ሥራ የጠቀመው የእግዚአብሔር እና የኢትዮጵያ ጠላት የሆኑትን ግብጻውያን ብቻ ነውና። እግዚአብሔር ለአባቶቻችን “ሂዱ! ግብጽ አይገባትም!“ እያለን ይሆን?

በጊዜው ፈርዖን የዓለም ተፈሪ ንጉሥ ነበር፡፡ ግብጽ የዚያኛው ዘመን ልዕለ ኃያል አገር ነበረች፡፡ ይህን ትልቅ አገዛዝ እግዚአብሔር በቅማልና በአንበጣ ነበር ያንበረከከው።

 

_________

Posted in Curiosity, Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , | Leave a Comment »

 
%d bloggers like this: