የዓለም መንግስታት የሚባሉት ትንሽ ግጭት በዓለም ላይ ቢከሰት ወዲያው ተሰብሰበው ማውገዙ፣ ማዕቀቡ፣ ማሳደዱ ይቀጥል ነበር። ሆኖም ማንኛቸውም ሃገራትና መንግስታት በኢትዮጵያ ጉዳይ አንድ አቋም ነው ያላቸው፤ የድሃ ሆነ የበለጸጉ ሃገራት መንግስት፣ አፍሪቃዊ ሆነ እስያዊ፣ አሜሪካዊ ወይም አውሮፓዊ ሁሉም ህልማቸው ኢትዮጵያ እንድትጠፋ ብቻ ነው። ምክኒያቱ አንድ እና አንድ ነው፤ በኢትዮጵያ ሃገራችን ከአባቶቻችን ዘመን ጀምሮ በጽናት የቆመች የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነታችን በእግዚአብሔር መወደድ እና መመረጥ ዲያብሎስን እና ምድርን የከደኑ አለቃ እና አመንዝሮቹ እጅግ ስላበሳጨ፣ ስላወከና የህልውናቸው ሁሉ አደጋ ስለሆነ ነው። ስለዚህ ዛሬ ገዢዎች ሁሉ በዓለም ላይ በዚሁ ክፉ ጠላታችን በዲያብሎስ ተመርቀውና ጸድቀው ስልጣን ላይ የተኮለኮሉና ለጥፋት የተሰማሩ ስለሆኑ ኢትዮጵያን ቢጠሉ፣ ኢትዮጵያን ለማፈራረስ ቢደክሙ፣ እምነታችንን እና የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን ለማጥፋት ቢተጉ ፥ የተሰጣቸው የጨለማው ኃይላት ስራ ነውና፤ እነሱም ወደው ለሱ የተገዙ ናቸውና እኛ ልንገረም አይገባንም።
ቃል ሕይወት ያሰማለን፤ ወንድማችን!