በኡራል ተራሮች በምትገኘዋ ማግኒቶጎርስክ ከተማ ውስጥ የውበት ሳሎን ባለቤት የሆነችው ኦክሳና ዞቶቫ የውበት ውድድሮች አሸናፊ ሆና ሽልማቶች በምታገኝበት ወቅት የቄስ ሚስት እንደሆነች በማሳወቋና የማግኒቶጎርስክ ሀገረ ስብከት የሀይማኖት አባቶች ታሪኩን በመስማታቸው ቄስ ባሏ ከተሰጠው ሃላፊነት ተነስቶ ራቅ ብላ ወደምትገኝ ትንሽ መንደር በቅጣት መልክ ተልኳል።
“የአንድ ካህን ሚስት እራሷን ለትዕይንት ማቅረቧ ትልቅ ኃጢአት ነው”
“ሚስቱ ስህተቷን በመቀበል ንስሃ እስካልገባች ድረስ ባሏ ወደ ቤተክርስቲያኑ ተመልሶ አያገለግልም፣ የራሱን ቤተሰብ መቆጣጠር ካልቻለ ምን ዓይነት ቄስ ነው? እንዴትስ ምዕማኑን መቆጣጠር ይችላል?” በማለት የሃገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ገልጸዋል።
ይህ ትልቅ ትምህርት ነው!