Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • June 2023
    M T W T F S S
     1234
    567891011
    12131415161718
    19202122232425
    2627282930  
  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

Posts Tagged ‘አባ ፓይስዮስ’

ጀግናው የግሪክ ኦርቶዶክስ ጳጳስ ለሮማው ጳጳስ ፍራንሲስኮ፤ “ፓፓ፤ መናፍቅ ነህ!”

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on December 6, 2021

👉ገብርኤል 👉ማርያም 👉ኡራኤል 👉 ጊዮርጊስ 👉 ተክለ ሐይማኖት 👉ዮሴፍ 😇መድኃኔ ዓለም

አቴንስ ከተማ ፤ ቅዳሜ ዕለት የሮማው ጳጳስ ጉብኝት በኦርቶዶክስ ግሪክ፤ አንድ የግሪክ ኦርቶዶክስ አባት ለሮማው ጳጳስ ፍራንሲስኮ፤ “ጳጳስ አንተ መናፍቅ ነህ! ሰላሳ ሺህ ሕፃናትን (በፈረንሳይ ብቻ) ደፍራችኋል!” ብለው ጮኹ።

ጀግናው የግሪክ ኦርቶዶክስ ሊቀ ጳጳስ የሮማውን ጳጳስ ፍራንሲስኮን በዚህ መልክ ከገሰጿቸው በኋላ እንዲህ አሳዛኝ በሆነ መልክ በፖሊስ ተወስደዋል።

መናፍቁ ጳጳስ ፍራንሲስኮ የምስራቅ እና ምዕራባዊ አብያተ ክርስቲያናትን “አንድ ለማድረግ/ለመጠቅለል” በሚያደርጉት ሥራ የግሪክን የሮማ ካቶሊኮችን ለመጎብኘት ቅዳሜ እለት ግሪክ ገብተዋል።

እንዲህ ያሉ ጀግና አባት መድኃኔ ዓለም ይስጠን። ዓለም ተስፋ ያደርግባቸው የነበሩት “ትሁቶቹ” የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ “አባቶች”ተገቢ ባልሆነ ዝምታቸው አውሬውን ነው እያገለገሉ ያሉት።

👉 የሚገርም ነው፤ በትናንትናው ዕለት ይህን በድጋሚ አቅርቤው ነበር፤

💭 Elder Paisios’ Amazing Prophecies About Turkey | ግሪካዊው በረኸኛ ጻድቅ አባ ፓይስዮስ፤

“አብዛኛዎቹ ቱርኮች ይጠፋሉ፤ ያለ እግዚአብሔር በረከት የተገነባ ሕዝብ ስለሆኑ ይደመሰሳሉ”

💭 ትንቢተኛው የግሪኩ አባ ዘወንጌል‘ | ቱርክ የምትባል አገር አትኖርም፤ በቅርቡ ትፈራርሳለች

✞✞✞“ኦርቶዶክስ በመሆናችን እግዚአብሔር ይረዳናል” አባ ፓይሲዮስ✞✞✞

በረኸኛው/ደገኛው ቅዱስ ኣባታችን ኣባ ፓይሲዮስ (..1924-1994)ቅድስናቸው በሁሉም ግሪኮች ዘንድ የታወቀው፤ ፖለቲከኞች ፣ አገልጋዮች ፣ ዓለማውያን ፣ መነኮሳት ፣ ካህናት ፣ ጳጳሳት በኤጂያን ባሕር ዙሪያ ስለሚሆነው ነገር ሁሉ ከእያንዳንዱ ሰው ጋር ተነጋግረዋል።

የወደፊቷን ግሪክ እጣ ፈንታ ለማየት እስኪበቁ ድረስ አባታችን ቀናትን እና ሌሊቶችን በጸሎት ያሳለፉ ነበር። ለግሪክ ፣ ለግሪካዊነትና ለኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ትልቅ፣ ልባዊና ጥልቅ ጭንቀት እንዳላቸው ለሚቀርቧቸው ሁሉ ያወሱ ነበር።

💭 በቪዲዮው ከተካተቱት የአባታችን ትንቢታዊ መልዕክቶች መካከል የሚከተሉት ይገኙበታል፦

👉 ቅዱስ ኮስማ እንደተነበዩት ሩሲያውያን ከላይ ጣልቃ ይገባሉ፤ ግሪኮች ቁስጥንጥንያን/ኢስታምቡልን በአምላክ ፈቃድ ያስመልሳሉ።

👉 ቱርክ በአጋሮቿ ትፈራርሳለች፤ ቱርኮች የተቀቀለውን ስንዴ በወገባቸው ዙሪያ አኑረዋል፤ የግሪክ ሠራዊት ወደ ቁስጥንጥንያ/ኢስታምቡል ያመራል

👉 ቱርክ በ፮/6 ማይሎች ርቀቶች(የግሪክን የክልል ውሃ)መቃረቧን በዜና ሲሰሙ ከዚያ ጦርነት ይከተላል፤ መርከቦቿም ይደመሰሳሉ።

👉 ይህ የእግዚአብሔር ፈቃድ ነው ። የቱርክ መጨረሻ መጀመሪያ ይሆናል።

👉 ቁስጥንጥንያ/ኢስታምቡል ለግሪክ ትመለሳለች፤ በሩሲያ እና በቱርክ መካከል ጦርነት ይከሰታል፤ በመጀመሪያ ቱርኮች ያሸንፉ ይመስላቸዋል ነገር ግን ይህ የእነሱ መጥፊያቸው ይሆናል።

👉 ቱርኮች ይጠፋሉ ። እነሱ ያለ እግዚአብሔር በረከት የተገነባ ህዝብ ስለሆኑ ይደመሰሳሉ።

አንድ ሦስተኛው ቱርኮች ወደ መጡበት የቱርክ ጥልቀት ይመለሳሉ። አንድ ሦስተኛ የሚሆኑት ክርስቲያን ስለሚሆኑ ይድናሉ ፣ ሦስተኛው ደግሞ በዚህ ጦርነት ይገደላሉ። ግሪኮች፣ አርመኖችና ኩርዶች ቱርክን ይከፋፈሏታል።

👉 የቀደመው የቱርክ ትውልድ በአዲስ የፖለቲከኞች ትውልድ ይተካል። በእግዚአብሔር ላይ እምነት እና ተስፋ እስካለ ድረስ ብዙ ሰዎች ይደሰታሉ። በእነዚህ ሁሉ ዓመታት ውስጥ የሚሆነው ሁሉ ይህ ነው። ጊዜው ደርሷል።

👉 እንግሊዞች እና አሜሪካውያን ለራሳቸው ጥቅም ሲሉ ቁስጥንጥንያን ለግሪክ ይሰጧታል። ቱርኮች ግሪክን ይተናኮላሉ፤ ማዕቀብ ይከተለላል፤ ዘመነ ረሃብ ይመጣል። ግሪኮች ይራባሉ።

👉 ከቱርክ ትንኮሳ በኋላ ሩሲያውያን ወደ ቢስፎረስ ባሕር ይወርዳሉ፣ እኛን ለመርዳት ሳይሆን፣ ሌሎች ፍላጎቶች ስላሏቸው እንጂ።

👉 በሩሲያውያን እና በአውሮፓውያን መካከል ታላቅ ጦርነት ስለሚኖር ብዙ ደም ይፈስሳል። ግሪክ በዚያ ጦርነት ውስጥ የመሪነት ሚና አለመጫወቷ ትልቅ በረከት ነው። ምክኒያቱም በአውሮፓውያን መካከል በሚደረግ ጦርነት የሚሳተፍ ሁሉ ይጣፋልና ነው።

👉 ቱርኮች ይመቱናል ግን ግሪክ ከፍተኛ ጉዳት አይደርስባትም፤ ቱርኮች በአገራችን ላይ ከፈፀሙት ጥቃቶች ብዙም ሳይቆይ ሩሲያውያን ቱርኮችን ይመቱና ያፈርሷቸዋል፤ ልክ አንድ ወረቀት ተቀዳደደው ይፈራርሳሉ።

👉 ሩሲያ ቱርክ ከወደመች በኋላ እስከ ፋርስ ባሕረ ሰላጤ ድረስ ጦርነቱን ትቀጥላለች፣ ወታደሮቿም ከኢየሩሳሌም ውጭ ይቆማሉ።

👉 ከዚያ የምዕራባውያኑ ኃይሎች ሩሲያውያን ወታደሮቻቸውን ከእነዚህ ቦታዎች እንዲያስወጡ ማሳሰቢያ ይሰጣሉ።

👉 ግን ሩሲያ ኃይሏን አታወጣም ፣ ከዚያ የምእራባዊያን ኃይሎች እነሱን ለማጥቃት ወታደሮችን መሰብሰብ ይጀምራሉ።

👉 የሚፈነዳው ጦርነት ዓለም አቀፋዊ ይሆናል እናም የሩሲያውያንን ኪሳራ ያስከትላል፤ ግዙፍ መተራረድ ይኖራል ፣ ከተሞቹ የፈራረሱ መንደሮች ይሆናሉ።

👉 ግሪክ በዚያ ጦርነት ውስጥ አትሳተፍም፤ የቁስጥንጥንያው ገዢ በእኛ በኩል ፖለቲካዊ እና ወታደራዊ ይሆናል።

የቱርክ መጥፋት ለግሪኮች ትልቅ እርካታ ይሆናል፤ ቁስጥንጥንያ ለግሪኮች ትመለሳለች።

የፀሎት እና ቅዳሴ ሥነ ስርዓት በቅድስት/ሃጊያ ሶፊያ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ እንደገና ይጀምራል።

ልክ እንደ ዛሬዎቹ ‘ኢትዮጵያውያን’ባዮች ኢትዮጵያ ዘ-ስጋ፤ አርሜኒያውያንም ከ፻ ዓመታት በፊት ከሚበላቸው አውሬ ጎን ተሰልፈው ነበር

__________________

Posted in Ethiopia, Faith, War & Crisis | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

 
%d bloggers like this: