Posts Tagged ‘አባ ዘ-ወንጌል’
Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on December 19, 2021
😠😠😠 😢😢😢
‘ክርስቲያን ነኝ! ኢትዮጵያዊ ነኝ!’ የሚል ወገን እንዴት ከአህዛብ ቱርክ ጋር አብሮ ክርስቲያንና ኢትዮጵያዊ የሆነውን ወንድሙን ይወጋል? ከአምስት መቶ ዓመታት በፊት፤ በዘመነ ግራኝ ቀዳማዊ፤ ኦሮሞዎችና/ጋሎችና ሶማሌዎች ልክ እንደዛሬው ከክርስቶስ ተቃዋሚ ቱርክ ጋር መሰለፋቸው የሚታወቅ ነው፤ ግን “አማራ” የተባሉትስ በወቅቱ ተመሳሳይ ክህደት ፈጽመዋልን? ታሪክ እኮ የዛሬው እና የወደፊቱ መስተዋት ነው! እግዚኦ መሐረነ ክርስቶስ!!!
😈 በአማራዎች፣ በሶማሌዎች እና በኦሮሞዎች የሚደገፈው የፋሺስቱ ኦሮሞ እና ቤን–አሚር ኤርትራ አገዛዝ አህዛብ ሰአራዊት እንዲህ ነበር አባቶቻችንን እናቶቻችንን የጨፈጨፋቸውና ✞ የቤተ ክርስቲያኑንም ሕንፃ ያፈራረሰው! ዋይ! ዋይ! ዋይ!
❖ በትግራይ አሲምባ ተራሮች ላይ የሚገኘው እንዳ መስቀለ ክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን ❖
Enda Meskel Kristos Church in the Asimba Mountains
❖[፩ኛ የዮሐንስ መልእክት ምዕራፍ ፬፥፳]
“ማንም። እግዚአብሔርን እወዳለሁ እያለ ወንድሙን ቢጠላ ሐሰተኛ ነው፤ ያየውን ወንድሙን የማይወድ ያላየውን እግዚአብሔርን ሊወደው እንዴት ይችላል?”
❖❖❖[የማቴዎስ ወንጌል ምዕራፍ ፯፥፳፩፡፳፫]❖❖❖
“በሰማያት ያለውን የአባቴን ፈቃድ የሚያደርግ እንጂ፥ ጌታ ሆይ፥ ጌታ ሆይ፥ የሚለኝ ሁሉ መንግሥተ ሰማያት የሚገባ አይደለም። በዚያ ቀን ብዙዎች። ጌታ ሆይ፥ ጌታ ሆይ፥ በስምህ ትንቢት አልተናገርንምን፥ በስምህስ አጋንንትን አላወጣንምን፥ በስምህስ ብዙ ተአምራትን አላደረግንምን? ይሉኛል። የዚያን ጊዜም። ከቶ አላወቅኋችሁም፤ እናንተ ዓመፀኞች፥ ከእኔ ራቁ ብዬ እመሰክርባቸዋለሁ።”
✞✞✞[መዝሙረ ዳዊት ምዕራፍ ፻፲፱]✞✞✞
፩ በተጨነቅሁ ጊዜ ወደ እግዚአብሔር ጮኽሁ፥ ሰማኝም።
፪ ከዓመፀኛ ከንፈር ከሸንጋይም አንደበት፥ አቤቱ፥ ነፍሴን አድናት።
፫ ስለ ሽንገላ አንደበት ምንም ይሰጡሃል? ምንስ ይጨምሩልሃል?
፬ እንደ በረሃ እንጨት ፍም የኃያላን ፍላጾች የተሳሉ ናቸው።
፭ መኖሪያዬ የራቀ እኔ ወዮልኝ፤ በቄዳር ድንኳኖች አደርሁ።
፮ ሰላምን ከሚጠሉ ጋር ነፍሴ ብዙ ጊዜ ኖረች።
፯ እኔ ሰላማዊ ነኝ፤ በተናገኋቸው ጊዜ ግን በከንቱ ተሰለፉብኝ።
__________
__________
Like this:
Like Loading...
Posted in Ethiopia, Faith, War & Crisis | Tagged: Aba Zewengel, Abel, Abiy Ahmed, Amhara, መስቀለ ክርስቶስ, መንፈሳዊ ውጊያ, መከራ, ቃኤል, ቅዱስ ዑራኤል, ቤተክርስቲያን, ቤን-አሚር, ትግራይ, አማራ, አባ ዘ-ወንጌል, አባቶች, አቤል, አዲስ አበባ, ኢትዮጵያ, ኤርትራ, ኦሮሞ, ክህደት, ክርስትና, የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነት, የክርስቶስ ተቃዋሚ, ደመና, ጂሃድ, ፀሎት, ፈተና, ፪ሺ፲፪, Ben Amir, Betrayal, Cain, Ethiopian Orthodox Tewahedo Faith, Meskele Christos, Oromo | Leave a Comment »
Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on May 7, 2021
💭 ሚያዝያ ፪ሺ፲፫/ 2013 ዓ.ም
አዲስ የዓለም ስርዓት ኢሉሚናቲ የዘመን መጨረሻ ሰይጣናዊ “ችግር – ምላሽ – መፍትሔ /”
(NWO Illuminati Endtime Satanic “Problem – Reaction – Solution )
“ዶ/ር ወዳጄነህ በምስጢር ይዞት የነበረውንና ከ አባ ዘ–ወንጌል የደረሰውን ትንቢት ተናገረ”
በእንግሊዝኛ ስለተኮላተፉ፣ ‘ዶ/ር’ የሚል ማዕረግ ስላጠለቁና ፊታቸውንም ለፈረንጅ ስላስመቱ ብቻ ለሕዝባችን የሚያሳዩት ንቀትና አሰልቺው ፍዬላዊ ድፍረታቸው ተወዳዳሪ የለውም። እንደው ይህ ተግባራቸው መቅሰፍቱን እንደሚያመጣባቸው ማወቅ ተስኗቸዋልን? አዎ! ፈሪሃ እግዚአብሔር በጭራሽ የላቸውም እኮ።
አባታችን አባ ዘ-ወንጌል ዶ/ር ወዳጀነህን የሚያውቁት ከሆነ እንኳን፤ አዎ! ብዙ ኢትዮጵያውያንን ወደ ገደል ይዞ እየገባ ነውና በተለይ አሁን በደንብ ነው የሚያውቁትና የሚያሳድዱት፤ ከዚያ ውጭ “ንስሐ ግባ! ገሃነም እሳት ይጠብቅሃል” ከማለት ውጪ መለኮታዊ ትንቢትና ማስጠንቀቂያ በጭራሽ ሊልኩለት አይችሉም። የአባ ዘ-ወንጌል መልዕክቶች መጀመሪያ ማስተላለፍ የጀመሩት እነ ዘመድኩን በቀለ ናቸው። ዘመድኩን በቀለ እራሱ አይታመንም፤ ምንም እንኳን አባ ዘ-ወንጌል ብዙ ያስተላለፏቸው መልዕክቶች ቢኖሩም ቅሉ፤ ዘመድኩን በቀለ እንደሚያመቸው አድርጎ መልዕክቶቹን እየቆራረጠ ሲያሰራጭ ሳይ በወቅቱ ይህ ግለሰብ ከጋንኤል ክስረት እና ግራኝ አብዮት አህመድ ጋር ሆኖ የአውሬው አገዛዝ በትግራይ ሕዝብ ላይ፣ በጥንታውያኑ ዓብያተ ክርስቲያናት እና ገዳማት ላይ ያቀደውን የጭፍጨፋ ጂሃድ ይደግፍለት ዘንድ በተለይ የትግራይ ተዋሕዷውያንን ህሊና ለማለማመድ ታስቦ የተዘጋጀ መልዕክት ሊሆን እንደሚችል ነው። የትግራይ ተዋሕዷውያን ሲጨፈጨፉ ፣ አክሱም ጽዮንን እና ደብረ ዳሞን ጨምሮ በጥንታውያኑ ገዳማትና ዓብያተ ክርስቲያናት ላይ ከፍተኛ ውድመት ሲደርስ ቤተ ክህነት እና በተለይ የአማራ ተዋሕዷውያን እስከ ዛሬዋ ዕለት ድረስ ጸጥ ማለታቸው የእነ ዘመድኩንን መል ዕክት በጽኑ እንደጠራጠራው አድርጎኛል። በተለይ አሁን መናፍቁ ዶ/ር ወዳጄነህ ሲታከልበት ሁሉም ነገር ግልጽ እየሆነ የመጣ ይመስለኛል። ለማንኛውም ጉዳዩ በትግራዋያን ተዋሕዷውያን መጣራት ይኖርበታል፤ በተቀሩት ላይ ተስፋ ቆርጫለሁ!
_____________________________________
Like this:
Like Loading...
Posted in Curiosity, Ethiopia, Faith | Tagged: #TigrayGenocide, 666, Aba Zewengel, Abiy Ahmed, ሃሜት, ህፃናት, መናፍቃን, ቅሌት, ቤተክርስቲያን, ትንቢት, ትግራይ, አቢይ አህመድ, አባ ዘ-ወንጌል, ኢሉሚናቲ, ኦርቶዶክስ, ዶ/ር ወዳጄነህ, ጂሃድ, ጥላቻ, ጦርነት, ጭፍጨፋ, ፀረ-ተዋሕዶ, ፀረ-ትግራዋይ, ፀረ-ኢትዮጵያ, ፕሮቴስታንት, Dr.Wodejeneh, Evil, Genocide, Prophecy, Protestantism, Tigray, War | Leave a Comment »
Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on January 1, 2021
የመሰቀለ ኢየሱስን ገዳም አስመልክቶ አንዳንድ አስደንጋጭ ዜናዎች እየወጡ ነው፤ እውነት አድርገውት ይሆንን? አንበሣውን ንጉሥ ቴዎድሮስን ቀሰቀሱትን?
ሁሉም ፀረ–ኢትዮጵያ እንቅስቃሴዎችና ቡድኖች ጦርነቶችን በጣም ይፈልጓቸዋል።
👉 በትግራይ ላይ በተከፈተውና ከሱዳን፣ ከሶማሊያ እና ጂቡቲ ጋር በታቀዱት ጦርነቶች ለጊዜውም ቢሆን የተጠቀሙት አካላት (ፍዬል)፦
☆ ፩ኛ. ኦሮሙማ
☆ ፪ኛ. አህዛብ
☆ ፫ኛ. መናፍቃን
☆ ፬ኛ. አረብ ሊግ፣ ግብጽ እና ሱዳን
☆ ፭ኛ. የኢሳያስ አፈቆርኪ ሻእቢያ
☆ ፮ኛ. ህወሃት
☆ ፯ኛ. የስጋ ማንነትና ምንነት ያላቸው የኢትዮጵያ ጠላቶች
👉 በጦርነቱ የተጎዱት (በግ)፦
❖ ፩ኛ. ኢትዮጵያ
❖ ፪ኛ. ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን
❖ ፫ኛ. የትግራይ ኢትዮጵያውያን
❖ ፬ኛ. የአማራ ኢትዮጵያውያን
❖ ፭ኛ. ኦሮሞ ያልሆኑት ደቡብ ኢትዮጵያውያን
❖ ፮ኛ. የመንፈስ ማንነትና ምንነት ያላቸው የኢትዮጵያ ወዳጆች
ለማስታወስ ያህል፤ በጣም የሚገርመው፤ ሰይጣን ከቤተክርስቲያን እና ገዳማት አካባቢ አይርቅምና ከ “ጀብሃ፣ ሻዕቢያ፣ ሀወሃት፣ ኢህአፓ፣ መኤሶን፣ ኦነግ ወዘተ” እያንዳንዱ የሉሲፈራውያኑ ቅጥረኛ፣ እያንዳንዱ የፀረ-ኢትዮጵያ ፀረ-ተዋሕዶ መጤ የግራ-ክንፍ አህዛባዊ ርዕዮተ ዓለም ተከታይ ሁሉ እዚህ በአሲምባ ተራሮች በመስቀለ ኢየሱስ ገዳም አካባቢ ነበር ተደራጅቶ ወደ ጥፋት መንገድ ያመራው። ይገርማል፤ ግን ወዮላቸው!
_________________________
Like this:
Like Loading...
Posted in Conspiracies, Ethiopia, Faith, Infos | Tagged: Abiy Ahmed, ሽብር, ብንብ ድብደባ, ትግራይ, አሲምባ, አቢይ አህመድ, አባ ዘ-ወንጌል, ኢሳያስ አፈወርቂ, ኦሮሙማ, የጦር ወንጀል, ግራኝ አህመድ, ጥላቻ, ጥቃት, ጦርነት, ጭፍጨፋ, ፀረ-ኢትዮጵያ, ፋሺዝም, War | Leave a Comment »
Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on December 11, 2019
፪ሺ፲፪ ዓ.ም – ዘመነ ዮሐንስ
[፩ኛ የዮሐንስ መልእክት ምዕራፍ ፬፥፳]
“ማንም። እግዚአብሔርን እወዳለሁ እያለ ወንድሙን ቢጠላ ሐሰተኛ ነው፤ ያየውን ወንድሙን የማይወድ ያላየውን እግዚአብሔርን ሊወደው እንዴት ይችላል?”
+_________________________________+
Like this:
Like Loading...
Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: መስቀለ ክርስቶስ, መከራ, ምጥ, ሰሜን ኢትዮጵያ, ስንብት, አሲምባ ተራራ, አባ ዘ-ወንጌል, ኢትዮጵያ, የመከራ ዘመን, የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን | Leave a Comment »
Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on November 7, 2019
በጣም የሚያስደንቅ ዕለት ነበር። እነ አባ ዘ–ወንጌል ይሆኑ ይሆን? አልኩ።
በቅዱስ ዑራኤል ቤተክርስቲያን በአጠገቤ ከነበሩ ከአንዲት ደስ ከሚሉ እናት ጋር ስለ አዲስ አበባ የጸጥታና ሰላም ሁኔታ እያወራን ነበር። ብዙ ነገር ነበር ያጫወቱኝ፤ ለምሳሌ፦ የሚኖሩባቸውንና በእርሳቸውና በጎረቤቶቻቸው ስም የተመዘገቡትን መኖሪያ ቤቶች ወራሪዎቹ ቄሮ ኦሮሞዎች ደባል አድርገው በአድራሻቸውና በቁጥራቸው መታወቂያ እንዳወጡባቸው፣ ለመሰለል በየጊዜው ብቅ እንደሚሉ ወዘተ. ከሃዘን ጋር አወሱኝ። ቀጥለውም፦ “ወራሪዎቹ የአዲስ አበባን ሕዝብ ለመጨፍጨፍ እየተዘጋጁ ነው፤ ነገር ግን አያሳካላቸውም፡ ምክኒያቱም ብዙ የገዳም አባቶች በስውር ወደ አዲስ አበባ በመግባት ላይ ናቸው።” አሉኝ። ልክ በዚህ ጊዜ ነበር ደምናው ላይ አፋቸውን ከፍተው የሚጸልዩና የሚያለቅሱ አባት ቁልጭ ብለው የታዩኝ። ለእናታችን ቪዲዮውን ቀድቼ እንዳሳየኋቸው ዓይኖቻቸው በደስታ እምባ ተሞልተው አየሁ። እግዚአብሔር የተመሰገነ ይሁን!
ስውር የሆኑ እና ለመለየት ከባድ የሆኑ የገዳም አባቶች ወደ አዲስ አበባ በመግባት ላይ መሆናቸውን ከሌሎች ወገኖችም ደግሜ ሰምቻለሁ። አዎ! አዲስ አበባ በአጠቃላይ ተኝታለች፤ ህዝቡ እንዲያንቀላፋና እየተካሄደ ስላለው የዘር መተከታት ዘመቻ ምንም እንዳያውቅ ሚዲያዎችን እንደ የእንቅልፍ ታብሌት ይጠቀምባቸዋል። ከሰሜኑ የኢትዮጵያ ክፍል (ጎጃም፣ ትግራይ፣ ኤርትራ) በመጡ የተዋሕዶ ልጆች እየተደገፈ ያለው የአዲስ አበባ ክርስቲያን በጣም በሚያስደንቅና በሚያኮራ መልክ እምነቱን በየአብያተክርስቲያናቱና አድባራቱ ሲኖር ይታያል።
በሌላ በኩል ግን፤
***ኢ–አማንያኑ፣ አሕዛብ የዋቄዮ–አላህ ልጆችና መናፍቃን ጴንጤዎች፦
-
– የኢትዮጵያን አምላክ በመክዳታቸው፣
-
– ለባዕዳውያኑ ጣዖት አምልኮዎች በመገዛታቸው፣
-
—ገንዘብን በማምለካቸው፣
-
– ወገንን ለባዕድ አሳልፈው በመስጠታቸው፣
-
– የየዋሁን ሕዝብ ንብረት በመስረቃቸው፣
-
– በድፍረት ህፃናትን በመመረዛቸው፣ በመድፈራቸው
-
– እናቶችን በማፈናቀላቸው፣
-
– የግመልና ፍየል ስጋ በመብላታቸው፣
-
– ኢትዮጵያዊ ያልሆኑትን አመጋገቦችን በማስገባታቸው፣
-
– ምድሩን፣ አየሩን፣ ውሃውን እና ምግቡን በመበከላቸው፣
-
– ያለቅጥ ቡና በመጠጣታቸው፣ ጥንባሆና ሺሻ በማጨሳቸው፣ ጫት በመቃማቸው፣
-
– በተዋሕዶ ላይ ሰይፍ በመምዘዛቸው፣
-
– ካህናትንና ምዕመናንን በመግደላቸው፣
-
– አብያተክርስቲያናትን በማቃጠላቸው
-
– በሰንበት ዕለት ሳይቀር በመጯጯህ ሰላም በመንሳታቸው፣
-
– በመሳከራቸው፣ ዳንኪራ በመርገጣቸው፣
-
– እስኪታመሙ ድረስ በማመንዘራቸው፣
-
– ግብረሰዶማዊነትን በማስፋፋታቸው
-
– ሜዲያዎቻቸው ነዋሪውን እውነትንና እውቀትን እንዲነሷቸው በማድረጋቸው
ባጠቃላይ፤ በመንፈሳዊ ሥነ ምግባር በፈሪሐ እግዚአብሔር እየተጓዘች በኖረችው አገራችን እነዚህን ድርጊቶች ለመፈጸም የሚንቀሳቀሱ ሰዎች መነሳታቸው እጅግ ያሳዝናል፤ ሰዎችን የሚያምኑና ሥነ ምግባር የጎደለውን አኗኗር የመረጡ እነዚህ ከሃዲዎች የሰዶምን ሥራ በመሥራታቸው ዛሬ ለአዲስ አበባ ከተማ በሰዶምና ገሞራ ላይ የታየው ዓይነት ቅጣት ሊያመጡባት ይችላሉ።
ውጊያው የመንፈሳዊ ውጊያ ነውና የገዳም አባቶች ወደ አዲስ አበባ በስውር መግባት ነጣቂ አውሬ የክርስቶስን ልጆች እንዳይወጣባቸው ያደርጋል። እግዚአብሔር ይጠብቀን!
እግዚኦ መሐረነ ክርስቶስ!!!
_______________________________
Like this:
Like Loading...
Posted in Curiosity, Ethiopia, Faith | Tagged: መንፈሳዊ ውጊያ, መከራ, ቅዱስ ዑራኤል, ቤተክርስቲያን, አባ ዘ-ወንጌል, አባቶች, አዲስ አበባ, ኢትዮጵያ, ክርስትና, የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነት, ደመና, ፀሎት, ፈተና, ፪ሺ፲፪, Ethiopian Orthodox Tewahedo Faith | Leave a Comment »
Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on October 22, 2019
እግዚአብሔር የአባታችንን ነፍስ ከቅዱሳን አበው ነፍስ ጋር ይደምርልን!!!
✦አባ ዘ–ወንጌል✦
አባታችን አባ ዘ–ወንጌል በሰሜን ኢትዮጵያ፡ ኢሮብ በሚባል መድኃኒያለም ገዳም ላይ የሚገኙ ሲሆን የ610 አመት እድሜ ባለ ፀጋ እንደነበሩ ይነገርላቸዋል። እንደ እውነቱ ከሆነ በኛ ዘመን ሰው እንደ ቅጠል በሚረግፍበት፣ የደሀ እንባ እንደ ጎርፍ በሚፈስበት ወቅት እንዲህ ያሉ አባቶች በዚህ ጊዜ መገኘታቸው እጅግ በጣም የሚገርምና የሚያስደስትም ነው። እድሜ እንደ ማቱሳላ ይሉሀል ይህ ነው።
ስለ አባ ዘ–ወንጌል ብዙ አለመስማታችንና ዓለማችንም ስለ አባታችን የእድሜ ፀጋና (በዚህ ዓለም ያልተሰማ) ሲፈጽሟቸው በነበሯቸው ተዓምራት ላይ አለመነጋገሩ እጅግ በጣም አሳዛኝ ጉዳይ ነው። እኔ እራሴ፡ “አልተፈቀደልኝም ነበርና”፡ ገና አሁን መስማቴ ነው። ሌሊቱን ሙሉ ሲያስገርመኝ ነው ያደረው!
ታታሪው ወንድማችን ዘመድኩን በቀለ የሚከተለውን አካፍሎናል፦
በትግራይ ክፍለ ሃገር አዲግራት አቅራቢያ በምትገኘው ኢሮብ ከተማ ውስጥ የሚገኙት አባታችን አባ ዘ–ወንጌል በምድር ላይ ከ300 አመት በላይ የኖሩ ሲሆን እጅግ በጣም የሚያስደንቁ ተአምራትን እንደሚፈጽሙ ይነገራል።
አባ ዘ–ወንጌል የአሲምባ መስቀለ ኢየሱስ ቤተ ክርስቲያን ከተመረቀ በኋላ ወደ አምላኬ እሄዳለሁ ብለው አስቀድመው በተናገሩት መሠረት እንደ ቃላቸው ወደ አምላካቸው ተጠርተዋል።
★ አሁን እንደተነገረው የኢትዮጵያ መከራዋ ይጀምራል። ትንሣኤዋም ይቀርባል። የቀረውን የበረኸኞቹን ትእዛዝ በቀጣይ ጊዜ እንነጋገራለን። [ፈጥነን ንስሐ እንግባ]።
“መእምዝ ሶበ ፈጸመ ሑረቶ ሠናየ ወአሥመሮ ለእግዚአብሔር ወአዕረፈ በሰላም ”
“ ከዚህም በኋላ መልካም ጉዞውን በፈጸመ ጊዜ እግዚአብሔርንም አገልግሎ በሰላም አረፈ። ”
“ ወስብሐት ለእግዚአብሔር ኪያነኒ ይምሐረነ በጸሎቱ ለዝንቱ አብ ወበረከቱ ተሀሉ ምስሌነ ለዓለመ ዓለም አሜን።”
ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን። እኛንም በዚህ አባት ጸሎት ይማረን። በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር። ለዘላለሙ አሜን።
ይህ ከመፈጸሙ በፊት ቀደም ብዬ ከበረኸኞቹ በተነገረኝ መሠረት መስከረም 18/2012 ዓም የጻፍኩላችሁን ማስታወሻም እነሆ፦
*★★★* በበረኸኞቹ ሲጠበቅ የቆየው ዕለት
መስከረም 18/2012 ዓም
#ETHIOPIA | ~ ከትንሣኤ በፊት ያለው የኢትዮጵያ ኅማማት ከዛሬ ዕለት በኋላ ይጀምራል የሚሉት ቀን ዛሬ ነው። ለአጨዳ የተዘጋጀ … … …

በብዙ በረኸኞች የቅዳሴ ቤቱ ምረቃ በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው በትግራይ ክፍለ ሀገር በአሲምባ በረሃ የሚገኘውና በአዲስ መልክ የተሠራው የመስቀለ ኢየሱስ ህንፃ ቤተክርስቲያን ይህ ነው።
መስቀለ ኢየሱስ ቤተ ክርስቲያን ከአዲግራት 80 ኪ ሜ ተጉዘው በትግራይ ክልል ኢሮብ ወረዳ አሲምባ ተራራ ላይ የሚገኝ ቤተ ክርስቲያን ነው።
እንደሚታወቀው አሲምባ ማለት የዛሬዋን ኢትዮጵያ ትርምስምሷን ያወጡ የዘመኑ ወጣቶች የተሰባሰቡባት፣ የብዙዎችም ደም የፈሰሰበት አካባቢ ነው። በበረሃው ስፍር ቁጥር የሌላቸው ቅዱሳን መኖሪያም ነው። የመስቀለ ክርስቶስ በስፍራው የነበረ ቢሆንም ይሄኛው በአዲስ መልክ እግዚአብሔር ፈቃዱ የሆነላቸውና ያሳሰባቸው ባለ ተስፋ ምእመናን ያሠሩት ቤተ ክርስቲያንም ነው።
ዕድሜያቸው በትክክል ይህን ያህል ዘመን ነው ብሎ ለመግለጽ ያልተቻለ አባ ዘ–ወንጌል የተባሉ ፀጋ እግዚአብሔር የበዛላቸው አባትም ያሉበት ስፍራም ነው። ይህ ቤተ ክርስቲያን በዛሬው ዕለት መስከረም 18/2012 ዓም በታላቅ መንፈሳዊ ሥነ ሥርዓት ይመረቃል።
ከዚህ ቤተ ክርስቲያን ምረቃ በኋላ አረጋዊው አባ ዘ–ወንጌል ይሰወራሉ። የኢትዮጵያም መከራ ይጀምራል። እስከ 2015 ዓ.ም ድረስ ደስ አይልም። ረሃብ፣ የእርስ በእርስ ጦርነትና ክፉ ገዳይ በሽታም ይከሰታል ይላሉ በረኸኞቹ። ታቦተ ኢየሱስ ያለበት ገዳምም ሆነ ቤተ ክርስቲያን መትረፊያ ነውም ይላሉ።
ከዚያ በኋላ የኢትዮጵያ ትንሣኤ ይጀምራል። የዓለም መከራዋም ይጀምራል። ኃያላኑ ራሳቸው በሠሩት መሣሪያ እርስ በእርሳቸው ይጫረሳሉ። በውጭ ሀገራት የተሠሩ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን አብያተ ክርስቲያናት የብዙ ሀበሾች መትረፊያ ይሆናሉ። ስደት ወደ ኢትዮጵያ ይሆናል። በተዋሕዶ ሃይማኖት አምኖ ለመጠመቅ በባህርና በየብስ የሰው ዘር ይጎርፋል። እና ሌሎች ከበድ ከበድ ደግሞም መጨረሻው ደስ የሚል ነገር ይናገራሉ።
እንደወረደ ለመናገር ቢጨንቀኝ ጊዜ ነው ቆንጠር ቆንጠር ማድረጌ። 7 ተላላቅ ገዳማት ይቃጠላሉ፣ ይወድማሉ። በዳር ሀገር ያሉ ክርስቲያኖች በተለይ ወጣቶቹ በሰይፍ፣ በመሃል ሀገር ያሉት በጦርነትና የሚበዛው በረሃብ ይጎዳሉ። ከላይ እና ከታች እሳት ይዘንባል። የማይነቅዝ እህል እና ጨው በብዛት ወደ ገዳማት ይላክ ይቀመጥ። ከጦርነቱ ረሃቡ ይከፋል። ስለ ቅዱሳኑ ሲል ዘመኑ ያጥራልም ይላሉ።
••• አክሱም ጽዮን፣ ማኅበረ ሥላሴ፣ ጉንድ ተክለሃይማኖት፣ አሰቦት ሥላሴ፣ ደብረ ሊባኖስ
________________________
Like this:
Like Loading...
Posted in Ethiopia, Faith, Life | Tagged: 610 ዓመት, መስቀለ ኢየሱስ ቤተ ክርስቲያን, መከራ, ትንሣኤ, ትግራይ, አሲምባ, አባ ዘ-ወንጌል, ኢትዮጵያ, እረፍት, ክርስትና, የመቱሳላ ዕድሜ ፪ሺ፲፪, የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነት, ገዳም, Ethiopian Orthodox Tewahedo Faith | Leave a Comment »