Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • June 2023
    M T W T F S S
     1234
    567891011
    12131415161718
    19202122232425
    2627282930  
  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

Posts Tagged ‘አባ ኪዳነ ማርያም ተከስተ’

የኢሳያስ እና ዶ/ር አህመድ ሤራ | የታላቁ ደብረ ቢዘን ገዳም አምስት አባቶች ታሠሩ

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on July 7, 2019

[የማቴዎስ ወንጌል ምዕራፍ ፲፰፥፲፰]

እውነት እላችኋለሁ፥ በምድር የምታሥሩት ሁሉ በሰማይ የታሠረ ይሆናል፥ በምድርም የምትፈቱት ሁሉ በሰማይ የተፈታ ይሆናል።

በኤርትራ ክፍለ ሃገር(አዎ! ካሁን በኋላ ሁሉንም የኢትዮጵያ ግዛቶች ክፍለ ሃገራት ነው የምላቸው) ከተመሠረተ ስድስት መቶ ሃምሳ ዓመታትን ያስቆጠረው ታላቁ የደብረ ቢዘን ገዳም ጣሊያን ኤርትራን እያስተዳደራት እያለም ቢሆን በኢትዮጵያ አስተዳደርና ንብረት ሥር ነበር (በውጫሌ ስምምነት ውስጥ ተጠቅሷል)

ላለፉት አሥራ ሦስት ዓመታት በፕሬዚደንት ኢሳያስ አፈወርቂ ወኅኒ የሚንገላቱት(ውሸት ነው አልተፈቱም)የቀድሞው የኤርትራ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ፓትሪያርክ የዘጠና ሁለት ዓመቱ አዛውንት አቡነ አንጦኒዮስ እንዲፈቱላቸውና የኢሳያስ መንግስት በቤተክርስቲያን ጉዳይ የሚያደርገውን ጣልቃገብነት በመቃወም ድምጻቸውን ሲያሰሙ የነበሩት የታሪካዊው ደብረ ቢዘን ገዳም መነኮሳት(ባለፈው ዓመት የተቀረጸው ቪዲዮው ላይ ይታያሉ)የሚከተሉት ናቸው፦

፩ኛ. አባ ክብረአብ ተክሌ

፪ኛ. አባ ማርቆስ ገብረ ኪዳን

፫ኛ. አባ ገብረ ትንሣኤ ተወልደ መድሕን

፬ኛ. አባ ኪዳነ ማርያም ተከስተ

፭ኛ. አባ ገብረ ትንሣኤ ዘሚካኤል

ነገሮችን ሰፋ አድርገን ከተመለከትን ይህ በዶ/ር አብዮት አህመድ እና በፕሬዚደንት ኢሳያስ አፈወርቂ የተቀነባበረው ፀረክርስትና ዘመቻ መሆኑን እንረዳለን።

ለአንድ የሰሜን ኢትዮጵያውያን ትውልድ መጥፋት ተጠያቂ የሆነውን ኢሳያስ አፈወርቂን ወድቆበት ከነበረው የማዕቀብና መገለል ጉድጓድ ያወጡት ዶ/ር አብዮት አህመድ እና ሉሲፈራውያኑ ደጋፊዎቹ ናቸው። ኢሳያስ ኦነጎችን እና ብርሃኑ ነጋዎችን እየቀለበ ሲያሳድግለት ስለነበር እንዲሁም ወጣት የተዋሕዶ ልጆች እየተሰደዱ እንዲያልቁ ትልቅ አስተዋጽዖ ስላበረከተ የ ዶ/ር አብይም የሉሲፈራውያኑ ደጋፊዎችም ባለውለታቸው ነበርና ነው። አሁን ሁለቱ የተዋሕዶ ጠላቶች በተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ላይ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ጥቃት በመፈጸም ላይ ይገኛሉ።

በጅጅጋ የተዋሕዶ ልጆች ላይ የተካሄደው ጭፍጨፋ እንደ ማንቂያ ደወል ሊሆነን በተገባ ነበር። ዛሬ እየታዘብን ያለነው፤ ወንጀለኞች እየነገሡ፥ እውነተኞች እየኮሰሱ፤ ዘራፊዎች እየፋፉ፥ ከልብ አገልጋዮች እየተገፉ፥ መንፈ ሳውያኑ ሊቃውንት ሜዳ ላይ እየተጣሉ የመጡበትን ዘመን ነው። እስኪ በአሁኑ ሰዓት እየተሰደደ፣ እየታሠረና እየተገደለ ያለው ማን እንደሆነ እንመልከት። ሃፍረተቢሱ ገዳይ አልአብይ ገና ሃዘኗን ያልጨረሰችውን የጄነራል አሳምነውን ባለቤትና የልጆቹ እናትን ለማሠር ደፍሯል፤ ይህ እንዴት ይሆናል? በኢትዮጵያ ታሪክ ይህን መሰሉን ጽንፈኛ ተግባር የምናውቀው መንግስቱ ኃይለ ማሪያም የኃይለ ሥላሴንና ሚንስትሮቹን ቤተሰቦች አንድ ባንድ እየለቃቀመ ሲገድል በነበረበት ዘመን ብቻ ነው። ወያኔ እንኳን የ ብርሃኑ ነጋንና መሰሎቹን ቤተሰቦች ያንገላታበት ግዜ አልነበረም። ገዳይ አልአብይ እንደ ሞኞቹ ወያኔዎች በማሠር ብቻ አልተወሰነም፤ ተቃዋሚ የሚላቸውን እየመነጠረ ወዲያው ይገድላል።

ሰሞኑን ከታሠሩት ሺህ የሚሆኑ ኢትዮጵያውያን መካከል አንድም ጴንጤ ወይም ሙስሊም አለመኖሩ ብዙ ሊጠቁመን የሚችል ነገር አለ። አዎ! በተዋሕዶ ልጆች የግራኝ አህመድ እና የመንግስቱ ኃይለማርያም ቀይ ሽብር ዘመን ተመልሶ መጥቷል።

ቤተክርስቲያናችን ከታሠሩት ጋር የታሠረች፥ ከተገረፉት ጋር የተገረፈች፥ ከተገደሉትም ጋር አብራ የሞተች ናት፤ ደግሞም የካህን ሐዘንና ዕንባ ከባድ ነው፥ ውዳሴ ማርያምና ዳዊት ስለሚደግም ስር ይነቅላልና ለጉዳዩ ቤተክህነትም ምዕመናንም ተገቢውን አትኩሮት እንስጠው

እግዚአብሔር ሁሉንም ከእሥራታቸው ይፈታቸው ዘንድ ስለ ታሠሩ ሰዎች እንማልዳለን!

__________________

Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

 
%d bloggers like this: