በግብጻውያን ክርስቲያን ወገኖቻችን ዘንድ ተወዳጅ የሆኑትና የዝነኛው የአባ መቃርስ ገዳም – የመጥምቁ ቅዱስ ዮሐንስ እና የነብዩ ኤልሳዕ አጽሞች የተቀበሩበት ገዳም ነው – አስተዳዳሪ የሆኑት አባ ኤፒፋኒዮስ ባለፈው እሑድ ዕለት በካይሮ ሰሜን ምዕራብ በሚገኘው በዚህ በረሃ ገዳም ውስጥ በአሰቃቂ ሁኔታ ተገድለው ተገኝተዋል። የአባ ኤፒፋኒዮስ አካል ተወጋግቶ፣ ደማቸው ፈስሶ እና አንጎላቻውም ከተፈረካከሰው ራስ ቅላቸው ወጥቶ ተገኝቷል።
እግዚአብሔር ነፍሳቸውን ከቅዱሳን ይደምርልን!
ዑራኤል + ጊዮርጊስ + ተክለ ሐይማኖት + መርቆሪዎስ
የአባይ ሤራ…
ይህን ጭካኔ የተሞላበት ግድያ ከወንድማችን ስመኘው በቀለ አገዳደል ጋር የሚያገናኙት አንዳንድ ነገሮች አሉ፦
- 1ኛ. ሁለቱም የተገደሉት ባንድ ወቅት ነው
- 2ኛ. ሁለቱም ደማቸው ፈሶባቸዋል
- 3ኛ. ሁለቱም ከአባይ ጋር የተያያዘ ሥራ ነበራቸው፤ ከአባይ ወንዝ እየጠጡም ኖረዋል
- 4ኛ. ሁለቱም የተገደሉት በ መሀመዳውያን ሳጥናኤል ወኪሎች ነው
- 5ኛ. ሁለቱም ቅዱስ በሆኑ ቦታዎች ላይ ነው የተገድሉት፤ ስመኘው በ “መስቀል” አደባባይ፣
- አባ ኤፒፋኒዮስ በቅዱስ መቃሬ ‘ጽድቅ ገዳም
ስለ ፃድቁ አባ መቃርስ ከቀረበ ትዕይንት የተወሰደ፦
አባ መቃርስ፡– አንተ እርኩስ መንፈስ፡፡ እነሆ በእግዚአብሔር ስም ይዤሃለሁ እንዳትንቀሳቀስ! … ለመሆኑ ከየት ነው የምትመጣው;
ሳጥናኤል፡– በረሀ ላይ ያሉትን መነኮሳት እየተፈታተንኩ ነው፡፡ ከዛው ነው የምመጣው
አባ መቃርስ፡– አንተ ዲያቢሎስ አንተ ክፉ ለበረሃ ካሉት መነኮሳት ጋር በምታደርገው ውጊያ ዙሪያ ስራህ እንዴት ነው;
ሳጥናኤል፡– በጣም መጥፎ ነው፡፡ ምንም እንኳን መነኮሳቱን ክፉ ኃጥያት እንዲሰሩ ባሳስባቸውም ሁሉም ያሳሰብኳቸውን ኃጥያት ለንሰሐ አባታቸው ይናገራሉ፡፡ አንዱ ግን ለንሰሐ አባቱ ስለማይናገር ከኔ ጋር ተወዳጅቷል፡፡
አባ መቃርስ፡– አንተ ርኩስ‘ አንተ አስመሳይ ዘላለምህን ትዕቢተኛ‘ ሀሰተኛ‘ ቅናተኛ የጠላህና የተዋረድክ ነህ። ክፉ‘ ነፍሰ ገዳይ‘ እውነት እንዲሰማ የማትሻ‘ ለጥፋት አነሳሽ‘ ጌተን እንኳን ያልፈራህ ፈታኝ ነህ። መልካምን ወደ ክፉ የምትለውን‘ ለክፋት የምታነሳሳና የምትመራ‘ አታላይ‘ አስመሳይ ከበጎ የምታዘገይ እንቅፋት ነህ። በምትሃት ተዓምር እያደረግህ ነገር የምታባብስ ሰዎችን በሕመም በምታሰቃይ‘ መንቻካና ምቹ ጊዜን የምትጥብቅ ባለጋራ ነህ። አሁን በመስቀሉ ሳላስርህ ካጠገቤ ራቅ። (ሰይጣን ይሰወራል) (ከጥቂት ዝምታ ቦሃላ) አዎን ያን የተሳሳተ መነኩሴ ማግኘት አለብኝ።