Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • June 2023
    M T W T F S S
     1234
    567891011
    12131415161718
    19202122232425
    2627282930  
  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

Posts Tagged ‘አቡዬ’

አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ | ከጽዮናውያን ጎን ሆነው ውጊያ፣ ጦርነትና ድል እያደረጉ ያሉት ቅዱሳኑ ናቸው

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on November 14, 2021

ዛሬ በብቸኛነት ለፍትሕ እና ለሕልውናቸው እየታገሉ ካሉት ከጽዮናውያን ተጋሩ፣ አገው እና ቅማንት ኢትዮጵያውያን ጎን ያልቆመ በጭራሽ ክርስቲያንም፣ ኢትዮጵያዊም፣ የእግዚአብሔር ልጅም ሊሆን አይችልም!

✞✞✞ቤተ ክርስቲያን ቅዱሳን የምትላቸው እነማንን ነው? ✞✞✞

😇 ቅዱሳን መላእክት፡ቅዱሳን መላእክት ከማንኛውም ነገር የራቁ፣ ሥርዓታቸውን የጠበቁ፣ እግዚአብሔርን ያወቁ፣ እግዚአብሔርን የሚቀድሱ ስለሆኑ ቅዱሳን ይባላሉ፡፡

አንዱም ለአንዱ፣ ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ምድር ሁሉ ከክብሩ ተሞልታለች እያሉ ይጮሁ ነበር፡፡” [ኢሣ. ፮፥፫]ስለዚህ በባህሪዩ ቅዱስ የሆነውን እግዚአብሔርን ስለሚያመሰግኑ፣ ስለሚቀድሱ ቅዱሳን ተብለዋል፡፡

😇 ቅዱሳን አበው፡መጻሕፍት ሳይጻፍላቸው መምህራን ሳይላኩላቸው በሕገ ልቡና በቃል ብቻ የተላለፈላቸውን ይዘው እንዲሁም በሥነ ፍጥረት በመመራመር ፈጣሪያቸውን አምነው እርሱ የሚወደውን ሥራ የሠሩና በጣኦት አምልኮ ራሳቸውን ያላረከሱ አባቶች ቤተ ክርስቲያናችን ቅዱሳን ትላቸዋለች፡፡ ለምሣሌ አበው ብዙኃን አብርሃም ኩፋሌ [፶፥፵፪፡፵፬፣ ፲፩፥፩]

😇 ቅዱሳን ነቢያት፡እግዚአብሔር ከማኅፀን ጀምሮ ጠርቶ መርጧቸው ሀብተ ትንቢትን አጐናጽፏቸው ያለፈውንና ወደፊት የሚሆነውን በእርግጠኝነት እየተናገሩ ሕዝቡን ይመክሩትና ይገስጹት የነበሩ ቤተ ክርስቲያን በቅድስና ማዕረግ የምትጠራቸው አባቶች ናቸው፡፡

ትንቢት ከቶ በሰው ፈቃድ አልመጣምና፣ ዳሩግን በእግዚአብሔር ተልከው ቅዱሳን ሰዎችበ መንፈስ ቅዱስ ተነድተው ተናገሩ” [፪ኛጴጥ ፩፥፳፭] እንዲል፡፡

😇 ቅዱሳን ሐዋርያት፡በነቢያት የተነገረውን ቃለ ትንቢት መድረሱንና በዘመናቸው መፈጸሙን ለዓለም እንዲያስተምሩ ጌታችን ራሱኑ ተከተሉኝ ብሎ የጠራቸውና የመረጣቸው ናቸው፡፡

በእውነት ቀድሳቸው ቃልህ እውነት ነው፡፡ወደ ዓለም እንደላክኸኝ እንዲሁ እኔ ወደ ዓለም ላክኋቸው፤ እነርሱም ደግሞ በእውነት የተቀደሱ እንደሆኑ እኔ ራሴን ስለ እነርሱ እቀድሳለሁ“[ዮሐ. ፲፯፥፲፯፡፲፱]

😇 ቅዱሳን ጻድቃን፡ቅዱሳን ጻድቃን ጌታን አርአያ አድርገው መላ ዘመናቸውን ከጣዕመ ዓለም ተለይተው ፈቃደ ሥጋቸውን ለፈቃደ ነፍሳዋው አስገዝተው በጾም፣ በጸሎት፣ በስግደት፣ በምናኔ ጸንተው ድምጸ አራዊትን፣ ጸብአ አጋንንትን፣ ግርማ ሌሊትን ሳይሳቀቁ ዳዋ ጥሰው፣ ደንጊያ ተንተርሰው፣ ጤዛ ልሰው የኖሩ አባቶችን ቤተ ክርስቲያን በቅድስና ማዕረግ ታከብራቸዋለች፡፡

ጻድቅንም በጻድቅ ስም የሚቀበል የጻድቁን ዋጋ ያገኛል“[ማቴ ፲፥፵፪] እንዲል፡፡

😇 ቅዱሳን ሰማዕታት፡ቅዱሳን ሰማዕታት ጌታችን በጲላጦስ ፊት “እኔ እውነት ልመሰክር ስለዚህ ተወልጃለሁ ስለዚህም ወደ ዓለም መጥቻለሁ“[ዮሐ ፲፰፥፴፯] ያለውን ምስክርነት በመከተል እግዚአብሔርን አንክድም ለጣኦት አንሰግድም በማለት በዓላውያን ነገስታት ፊት ሳይፈሩና ሳያፍሩ ቆመው የመሰከሩትን ቤተ ክርስቲያን በቅድስና ትጠራቸዋለች፡፡

😇 ቅዱሳን ነገሥታት፡እንደ አሕዛብ፣ ዓላማውያን ነገሥታት በሥልጣናቸው በሀብታቸው በሠራዊታቸው ሳይመኩ ኃይማኖት ይዘው ምግባር ሰርተው የተገኙ እንደ ዳዊት ያሉ ቅዱሳን አባቶችናቸው፡፡

😇 ቅዱሳን ሊቃውንት፡ቅዱሳን ሊቃውንት ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ ያልተመሰለውን መስለው የተመሰለውን ተርጉመው በማስተማር መጻሕፍትን በመተርጐም መናፍቃንን ጉባኤ ሰርተው ረትተው ያስተማሩ ቅዱሳን ይባላሉ፡፡

መልካሙን የምስራች የሚያወሩ እግሮቻቸው እንዴት ያማሩ ናቸው” [ሮሜ. ፲፥፲፭]

😇 ቅዱሳን ጳጳሳት፡ቅዱሳን ጳጳሳት የካህናትና የምዕመናን፣ የሰማያውያንና የምድራውያን አንድነት የሆነችውን ቤተ ክርስቲያን በኃይማኖት በመምራት መንጋውን ከተኩላ በመጠበቅ የክርስቶስን ትዕዛዝ የፈጸሙ ቅዱሳን ናቸው፡፡

😇 ቅዱሳን መነኮሳት (ደናግል)ቅዱሳን መነኮሳት (ደናግል) ከሕገ እንስሳ ሕገ መላእክት ይበልጣል ብለው ራሳቸውን ለክርስቶስ አጭተው ከሴት ወይም ከወንድ ርቀው ስለ መንግሥተ ሰማያት ብለው ራሳቸውን ጃንደረቦች ያደረጉ ናቸው፡፡

😇 ቅዱሳት አንስት፡ጌታችን መርጦ ካስከተላቸው ፻፳/120ው ቤተሰብ ፴፮/36ቱ ቅዱሳት አንስት ጌታ ሲሰቀል ሳይሸሱ፣ በመቃብሩም በመገኘት፣ የትንሳኤው ምስክርም በመሆን መከራ በበዛበትና በጸናበት የክርስትና ጐዳና የተጓዙ እናቶች፣ እህቶች ሁሉ ቅዱሳት አንስት ይባላሉ፡፡

😇 ቅዱሳት መካናት፡ማለት የተለዩ፣ የተከበሩ ሥራዎች ቦታዎች እግዚአብሔር በመዝሙር፣ በቅዳሴ፣ በማኅሌት ይገለገልባቸው ዘንድ የመረጣቸው ገዳማትና አድባራት ቅዱሳት መካናት ይባላሉ፡፡

የእግዚአብሔር ሠራዊት አለቃ ኢያሱን፡አንተ የቆምክባት ስፍራ የተቀደሰ ነውና ጫማህን ከእግርህ አውልቅ አለው” [ኢያሱ ፭፥፲፭]

😇 ቅዱሳት መጻሕፍት፡ቅዱሳት መጻሕፍት የሚባሉት የብሉያትና ሐዲሳት፣ የመነኮሳትና ሊቃውንት፣ እንዲሁም አዋልድ መጻሕፍት ናቸው፡፡ ቅዱሳት መጻሕፍት ስንል የተመረጡ፣ የተከበሩ የተወደዱና የተመሰገኑ መጻሕፍት ማለት ነው፡፡

😇 ቅዱሳን መጻሕፍት ቅዱስ መሰኘታቸው የሰውን ልጅ መነሻና መድረሻ ታሪክ በሦስቱም ሕግጋት የተነሱ ቅዱሳን ጥንተ ክብራቸውን ገድላቸውን ከእግዚአብሔር የተቀበሉትን ጸጋ እግዚአብሔር ወልድ የሰውን ልጅ ለማዳን ያደረገውን ጉዞ የማዳን ሥራውን ስለያዙ ቅዱሳን ተባሉ፡፡

😇 ቅዱሳትሥዕላት፡በእግዚአብሔር ትእዛዝና ፈቃድ ተስለው የእግዚአብሔር ስም በሚጠራበት ቦታ የሚቀመጡና ከስዕሉ ባለቤት ተራዳኢነትና በረከትን ለማግኘት የሚጠቅሙ የእግዚአብሔር ልዩ ስጦታዎች ናቸው፡፡ [ዘፀ. ፳፭፥፲፰፡፳፪፣ ዘኁ.፯፥፹፱]

ሥጋዊውን ዓለም ከሚያንጸባርቁ ዓለማውያን ሥዕላት ፈጽመው የተለዩ በመሆናቸው ነው፡፡ የቅዱሳኑ ቅድስና ሥዕላቱንም ቅዱሳት አሰኝቷቸዋል። ሥዕላቱ በራሳቸው የሚያደርጉት ገቢረ ተአምራት ቅዱሳት አሰኝቷቸዋል፡፡

😇 ቅዱሳት ንዋያት፡በእግዚአሔር ቤት ውስጥ ለመንፈሳዊ አገልግሎት የሚውሉ ንዋያት ሁሉ የተቀደሱ ናቸው፡፡ ምክንያቱም አገልግሎቱ የሚፈፀመው ቅድስና የባህሪይ ገንዘቡ ለሆነ ለእግዚአብሔር ነውና፡፡

ቅዱስ መስቀል፡የጌታችን ቅዱስ መስቀል ሕያው፣ አማናዊ በሆነው በክርስቶስ ደም ከመክበሩ የተነሳ ቅዱስ ተብሏል፡፡ (ቅዱስ ያሬድ ስለመስቀሉ በድጓ ዘክረምት ላይ እንዲህ ብሏል) “የቅዱሳን ክብራቸው የጻድቃን ሞገሳቸው የዕውራን ብርሃናቸው እነሆ ይህ መስቀል ነው” ብሏል፡፡

ታቦት፡ቤተክርሲያን ቅዱስ ብላ ከምታከብራቸው አንዱ ታቦተ ሕጉን ነው፡፡

ታቦት ማለት በግእዝ ቋንቋ ማዳሪያ፣ ማዳኛ ማለት ሲሆን በዚህ ታቦት ላይ እግዚአብሔር የሚያድርበትና የሚገለጥበት የጽላት ሕጉ ማዳሪያ ነው፡፡ [ዘፀ. ፳፭፥፳፪]

________________

Posted in Ethiopia | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

ግራኝ አህመድ አሊ በተዋሕዶ ላይ ጅሃዱን የጀመረው በጅማ-በሻሻ ነው

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on October 15, 2020

[የዮሐንስ ወንጌል ምዕራፍ ፰፵፥፬]

እናንተ ከአባታችሁ ከዲያብሎስ ናችሁ የአባታችሁንም ምኞት ልታደርጉ ትወዳላችሁ። እርሱ ከመጀመሪያ ነፍሰ ገዳይ ነበረ፤ እውነትም በእርሱ ስለ ሌለ በእውነት አልቆመም። ሐሰትን ሲናገር ከራሱ ይናገራል፥ ሐሰተኛ የሐሰትም አባት ነውና።

👉 ግራኝ አብዮት አህመድ አሊ እዚህ ቦታ(ጅማ-በሻሻ) በ፲፱፻፷፰ ዓ.ም የሞት መንፈስ ይዞ ተፈጠረ። (ዘመነ ቀይ ሽብር ክርስቲያን ጀነሳይድ)

👉 ግራኝ አብዮት አህመድ አሊ በ፲፱፻፺/1990 ዓ.ም. ወደ ባድሜው ጦርነት የሞት መንፈስ ይዞ ዘመተ። (ዘመነ ባድሜ ክርስቲያን ጄነሳይድ)

👉 ግራኝ አብዮት አህመድ አሊ በ፲፱፻፺፱/1999 ዓ.ም. የሞት መንፈስ ጂሃድ በትውልድ ቦታው ቀሰቀሰየበሻሻ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ቤተ ክርስቲያን ተቃጠለ ፯/7 ካህናትና ምእመናን ባሰቃቂ ሁኔታ ታርደው ለሰማዕትነት በቁ። (ዘመነ ጅሃድ ክርስቲያን ጄነሳይድ)

👉 የበቀል፣ የጥፋትና የሞት መንፈስ ተሸክሞ የተፈጠረው ግራኝ አብዮት አህመድ አሊ ዛሬ በጅማ የጀመረውን የጄነሳይድ ጅሃዱን በግልጽ በማጧጧፍ ላይ ይገኛል፤ (ዘመነ ጅሃድ ክርስቲያን ጄነሳይድ)– ጅ + ጄ + ጅ

በ፲፱፻፺፱/1999 .ም ጅማ ሀገረ ስብከት በሻሻ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ቤተ ክርስቲያን ላይ ዘግናኝ በደል ነበር የተፈጸመው፡፡ ቤተ ክርስቲያን ተቃጥላለች፤ ካህናትና ምእመናን በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ታርደዋል፤ በገጀራ ተደብድበዋል፡፡ በበሻሻ የተፈጸመውን ግፍ በወቅቱ የነበሩትና በድብቁ ግራኝ አብዮት አህመድ አሊ የተመሩት የመንግሥት ባለሥልጣናት እንዳስተባበሩት እማኞች ተናግረው ነበር፡፡

በሌሎች ብዙ ወገኖቻችንም ላይ የተፈጸመውን ጥቃትና ጭፍጨፋ አንረሳውም፡፡

በ፲፱፻፺፱/1999 ዓ.ም ጅማ ሀገረ ስብከት በሻሻ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ቤተ ክርስቲያን ላይ ዘግናኝ በደል ነበር የተፈጸመው፡፡ ቤተ ክርስቲያን ተቃጥላለች፤ ካህናትና ምእመናን በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ታርደዋል፤ በገጀራ ተደብድበዋል፡፡ በበሻሻ የተፈጸመውን ግፍ በወቅቱ የነበሩትና በድብቁ ግራኝ አብዮት አህመድ አሊ የተመሩት የመንግሥት ባለሥልጣናት እንዳስተባበሩት እማኞች ተናግረው ነበር፡፡

የበሻሻ ቆሻሻ አብዮት አህመድ የውሸት PHD ቴሲሱንም በዚህ ጉዳይ ላይ ነበር ጻፈ የተባለው። ዋው!

ግን የበሻሻ ቆሻሻ ባለፈው ሳምንት ላይ ኢሳያስ አፈቆርኪን ወደ በሻሻ የወሰደው ለምን ይመስለናል?!

____________________________

Posted in Ethiopia, Faith, Infos | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

ሰይጣን መንገዳቸው ላይ መሰናክል አስቀመጠባቸው እግዚአብሔር ግን መሰናክሎችን እየጠረገ ዝቋላ በድል አደረሳቸው

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on October 15, 2020

እንኳን ለአቡዬ ገብረመንፈስ ቅዱስ አደረሳችሁ!

_____________________________

Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

ወደ ዝቋላ አቦ ገዳም የሚጓዙ ምዕመናን ከደብረ ዘይት አታልፉም ተባሉ

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on October 14, 2020

ግድየልም፤ አውሬው በእሳት መጠረጊያው ተቃርቧል፤ ምናለ በሉኝ!

___________________________

Posted in Ethiopia, Faith, Infos | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

ዓለም እጆቿን በሳሙና ታጥባለች ፥ ኢትዮጵያ እጆቿን ወደ እግዚአብሔር ታደርሳለች

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on March 17, 2020

ድንቅ ነው!

መጋቢት ፭ቀን ፪፼፲፪ ዓ.ም ዝቋላ የአቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ ዓመታዊ ክብረ በዓል እና በዓለ እረፍት በምድረከብድ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ አንድነት ገዳም።

ከኮሮና ቫይረስ ጋር በተያያዘ ዓለም ለስጋዋ በጣም ተጨንቃለች፤ እስያ፣ አውሮፓ እና አሜሪካ ቤተክርስቲያኖቻቸውን ዘግተዋል፣ በቫቲካን ከተማ የሮማው ካቶሊክ ጳጳስ ሰውአልባ በሆነው አደባባይ ብቻቸውን ሲቀድሱ ነበር፣ የአህዛቡም ጣዖት የመካው ጥቁሩ ድንጋይም ብቻውን ቀርቷል። ወገናችን ግን እንዲህ ተሰባስቦ ለመላው ዓለም ጸሎት እንዲያደርስ እግዚአብሔር አምላኩ ፀጋውን ሰጥቶታል። ዲያብሎስ በዚህ ቅጥል ይላል፤ ገና ብዙ ይተናኮለናል፣ ሊያስፈራራን እና ሊያሸብረን ይሻል።

የእግዚአብሔር ልጆች የወንድሞቻቸው ደም በፈሰሰበት ቦታ ላይ ለአምላካቸው እጆቻቸውን የሚያደርሱበትን ቤተ መቅደስ ይገነባሉ፤ የዲያብሎስ ልጆች ደግሞ ለዲያብሎስ የደም ግብር ባቀረቡበት ቦታ ላይ የአውሮፕላን ማረፊያ ለመገንባት ያልማሉ።

ባለፈው ዓመት የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን በተከሰከሰበት በደብረዘይት ከተማና ዝቋላ ገዳማት አቅራቢያ በሚገኝ ሰፊ ቦታ ላይ በአፍሪቃ አንጋፋ የሆነ አውሮፕላን ማረፊያ ለመገንባት ዕቅድ መኖሩን በቅርብ ልንከታተለው ይገባናል። ከዚህ ቀደም በዋልድባ ገዳም ዙሪያ ፋብሪካዎችን ለመገንባትና በመቶ ሺህ የሚቆጠሩ አህዛብን ወደዚያ ወስዶ ለማስፈር ተሞክሮ እንደነበረው እዚህም ተመሳሳይ ዲያብሎሳዊ ዕቅድ እንዳለ የተዋሕዶ ልጆች ካሁኑ መገንዘብ ይኖርባቸዋል። ዋልድባን በስኳር ፋብሪካ፣ የጣና ሐይቅ ገዳማትን በእንቦጭ፣ የዝቋላ ገዳማትን ደግሞ በአውሮፕላን። ጋኔኑ ግራኝ አህመድ “ፓርክ” በሚል ሰበብ የግቢ ገብርኤልን በኦዳ ዛፍ እንዲከበብ ካደረገ በኋላ አሁን በእንጦጦ ዓብያተ ክርስቲያናትና ገዳማት ላይ ዓይኑን ጥሏል

________________________________

Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

ቤተ ክርስቲያን ሆይ መከራሽ መብዛቱ፤ ከአንቺው አብራክ ወጥተው ጎራዴ አነገቱ፤ ተባብረው ሊወጉሽ ባንቺ ላይ ዘመቱ

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on December 15, 2019

+_________________________+

Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

ምዕመናኑን ፀጥ ያሰኘ ስብከት | ቋንቋን ለምን እንደ ሃይማኖት እንጠቀማለን? ከሆነማ ሁላችንም በግእዝ መነጋገር አለብን

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on October 15, 2018

ቋንቋን እግዚአብሔር አልፈጠረም፤ በቋንቋ መንግስተ ሰማያት አይገባም፡ ነገር ግን የመጀመሪያው አዳምም ለ ፯ ዓመታት በገነት ሳለ በፀሎት ሲተጋ የነበረውና ከሄዋን ጋር ይነጋገርበት የነበረው የመጀመሪያው ቋንቋ ግእዝ ስለሆነ እርስበርስ ለመግባባት እንችል ዘንድ ሁላችንም አሁን ግእዝ ቋንቋን ማወቅ ሊኖርብን ነው።”

ቃለ ሕይወት ያሰማልን፡ አባታችን! (የካሜራዬን ባትሪ መለወጥ ነበረብኝና ሁሉም ስብከታቸው አልተካተተም፡ ይቅርታ!)

አዎ! ዲያብሎስ በቋንቋ እርስበርሳችን እንድንጨፋጨፍና በእንግሊዝኛ ወይም በአረብኛ እንድንነጋገር ከማስገደዱ በፊት ፈጥነን ግእዝ ቋንቋን መማር አለብን።

ግእዝ የእግዚአብሔር ቋንቋ ነው ተብሎ በትዉፊት ይነገራል

ትውፊታዊ ታሪኩ

ግእዝ የእግዚአብሔር ቋንቋ ነው ተብሎ በትዉፊት ይነገራል። ፍጥረታት በሐሌዎበነቢብና በግብር የተፈጠሩ ሲሆን በተለይ ነቢቡ (ንግግሩ) ግእዝ ነበር ብለዉ የሚከራከሩና የራሳቸውን ማስረጃ የሚያቀርቡ ሊቃውንት አሉ። ግእዝ የመጀመሪያ ቋንቋ ነው ስንል አዳም ማለት ያማረ የተዋበ ማለት ሲሆን አባቶቻችን በመንፈስ ቅዱስ እየተመሩ ከጻፏቸው መጻሕፍት እና ሌሎች ድርሰቶች ተነስተን ቅዱስ ገብርኤል “ንቁም በበህላዌነ” ብሎ ሠራዊተ መላእክትን ያረጋጋው በግእዝ ነው፤ አዳምም ለ ፯ ዓመታት በገነት ሳለ በፀሎት ሲተጋ የነበረውና ከሄዋን ጋር ይነጋገርበት የነበረው ቋንቋ በግእዝ ነው በማለት ቋንቋውን የመላእክትም የሰውም መግባቢያ ያደርጉታል።

ግእዝ የአዳምና ሔዋን (የተፈጥሮ ቋንቋ) የመጀመሪያው መነጋገሪያ ልሳን መኾኑ ለማረጋገጥ ከሚያቀርቧቸው ፲ ምክኒያቶች መካከል

፩ኛ. ”ግእዝ” የጥሬ ዘሩ ቃል ትርጉም፡ “መጀመሪያ”, “ነፃ” እና “የጥንት ተፈጥሮ ጠባይ ወይም ባህሪይ” ማለት መኾኑ

፪ኛ. የእያንዳንዱ ፊደል የመጀመሪያ ቅርጽ አፍ ሳያስከፍት በድን በኾነው በተፈጥሮ ድምፅ ብቻ የሚነገር መኾኑ

፫ኛ. የፊደሉ መነሻ “አ” “አዳም” በሚል ቃል በወንድና ሴት ጾታ ለተፈጠሩት ለመጀመሪያዎቹ ሰዎች መጠሪያ መኾኑ

፬ኛ. በሰባት ብዛት የሚወሰን ቁጥር፤ የመለኮታዊ ሥራ ምሥጢር እንዳለበት ስለሚታመን፤ እያንዳንዱ ፊደል፤ በሰባት ስሞች ድምጾችና መልኮች ተለይቶ የሚታወቅና የሚነገር መኾኑ

፭ኛ. ሌሎቹ የሰዎች ቋንቋዎችና ፊደሎቻቸው በተናጋሪዎቻቸው ሕዝቦች ወይም ጎሣዎች ስም ለምሳሌ፤ ዐማርኛ፤ በዐምሓሮች፤ ትግርኛ በትግሬዎች፣ ኦሮምኛ በኦሮሞዎች፣ ሶማልኛ በሶማሌዎች፣ ዕብራይስጥ በዕብራዊያን፤ ዐረብኛ በዓረቦች፣ እንግሊዝኛ በእንግሊዞች፣ ቻይንኛ በቻይኖች ስም ሲጠሩ “ግዕዝ” ግን በራሱ ብቻ የሚጠራ መኾኑ

፮ኛ. በ ”አ” ጀምሮ በ “ኦ” የሚፈጸም ፊደል ያለው እርሱ፤ ግእዝ ብቻ ከመኾኑ ጋር “አልፋና ኦሜጋ፤ መጀመሪያውና መጨረሻው እኔ ነኝ” ብሎ፡ ኃላ “ኢየሱስ ክርስቶስ” ተብሎ፤ ራሱን በሰውነት የገለጸው “እግዚአብሔር” በዚህ ስሙ የታወቀበትና አምልኮቱ የሚፈጸምበት ቋንቋና ፊደል ኾኖ በሕያውነት እስከዛሬ መቀጠሉ

፯ኛ. በምድር ላይ የሚኖሩ የሰው ልጆች ኹሉ፡ ተወልደው በሕፃንነታቸው መናገር በሚጀምሩበት ጊዜ ቋንቋቸውና ፊዲፈላቸው የተለያዩ ሲኾኑ፤ አፋቸውን መፍታት አባቶቻቸውናና እናቶቻቸውንም ለይተው መጥራት የሚጀምሩበት “አባባ”፤ “እማማ!” የሚባሉት ቃላት “አብ አብ አብ”፤ “እም እም እም” የተባሉት፤ ትርጉማቸው፡ “አባት አባት አባት”፡ “እናት እናት እናት” የኾነውን ቀጥታ የግእዙን ቃላት መኾኑ ናቸው።

፰ኛ. «ግእዝ» የሚለው ቃል እራሱ አንደኛ፣ የመጀመሪያ ማለት ነው። የሰው ልጅ የመጀመሪያ የሆነው ቋንቋ አንደኛቢባል ይስማማዋል።

፱ኛ. የዚህ ቋንቋ የመጀመሪያው ተናጋሪ ሰው አዳም ነው። የዚህ ሰው ስም በቋንቋው ትርጉም ሊኖረው ይገባል። በግእዝ «አዳም» ማለት ያማረ ማለት ነው።

፲ኛ. ሌላው ነገር የግእዝ ፊደላት ከአምላክ የተገኙ ናቸው ለዚህም የአዳም ሶስተኛ ትውልድ የሆነው ሄኖስ በሰማይ ገበታ እንዳያቸው አባቶች ይናገራሉአማርኛ ቋንቋ ከግእዝ ያገኛቸውን በሙሉ ይዞ ሌሎች ፯ ፊደላትን በመጨመር ግእዝ ፳፮ ሲሆን አማርኛ ደግሞ ፴፫ ነው “ቨ”ን ሳይጨምር ማለት ነው፡፡

የግእዝን ፊደሎች ትርጉም ስንመለከት

ሀ፦ ብሂል ሀልዎቱ ለአብ እምቅድመ ዓለም ፥ የአብ አኗኗሩ ከዓለም በፊት ነው

ለ ፦ ብሂል ለብሰ ሥጋ እምድንግል ፥ ክርስቶስ ከድንግል ሥጋን ለበሰ

ሐ ፦ ብሂል ሐመ ወሞተ ፥ ስለኛ ታመመና ሞተ

መ፦ ብሂል መንክር ግብሩ ለእግዚአብሔር ፥ የእግዚአብሔር ሥራው ድንቅ ነው

ሠ ፦ ብሂል ሠረቀ በሥጋ ፥ በሥጋ ተገለጠ

ረ ፦ ብሂል ረግዓት ምድር በቃሉ ፥ ምድር በቃሉ ረጋች

ሰ ፦ ብሂል ሰብአ ኮነ እግዚእነ ፥ ጌታችን ሰው ሆነ

ቀ ፦ ብሂል ቀዳሚሁ ቃል ፥ ቃል መጀመሪያ ነበር

በ ፦ ብሂል በትሕትናሁ ወረደ ፥ ጌታችን በትሕትናው ወደኛ ወረደ

ተ ፦ ብሂል ተሰብአ ወተሰገወ ፥ ጌታችን ሰው ሆነ

ኀ ፦ ብሂል ኀያል እግዚአብሔር ፥ እግዚአብሔር ኀያል ነው

ነ ፦ ብሂል ነስአ ደዌነ ወጾረ ሕማመነ ፥ መከራችንን ያዘልን ሕመማችንን ተሸከመልን

አ ፦ ብሂል አእኵቶ ወእሴብሖ ለእግዚአብሔር ፥ እግዚአብሔርን ፈፅሜ አመሰግነዋለሁ

ከ ፦ ብሂል ከሃሊ እግዚአብሔር ፥ ጌታችን ቻይ ነው

ወ ፦ ብሂል ወረደ እምሰማይ ፥ ጌታ ከሰማይ ወረደ

ዐ ፦ ብሂል ዐርገ ሰማያተ ፥ ወደ ሰማይ ዐረገ

ዘ ፦ ብሂል ዘኵሎ ይእኅዝ እግዚአብሔር ፥ ጌታ ሁሉን የሚይዝ

የ ፦ ብሂል የማነ እግዚአብሔር ገብረት ኃይለ ፥ የጌታ ቀኝ እጅ ኃይልን ታደርጋለች

ገ ፦ ብሂል ገብረ ሰማያተ በጥበቡ ፥ ጌታ በጥበቡ ሰማያትን ሠራ

ጠ ፦ ብሂል ጣዕሙ ወታእምሩ ከመ ኄር እግዚአብሔር ፥ ጌታ ቸር እንደሆነ ቅመሱና ዕወቁ

ጰ ፦ ብሂል ጰራቅሊጦስ መንፈሰ ጽድቅ ፥ ጰራቅሊጦስ እውነተኛ መንፈስ ቅዱስ ነው

ጸ ፦ ብሂል ጸጋ ወክብር ተውህበ ለነ ፥ ጸጋ እና በረከት ተሰጠን

ፀ ፦ ብሂል ፀሐይ ጸልመት በጊዜ ስቅለቱ ለእግዚእነ ፥ ጌታ በተሰቀለ ጊዜ ፀሐይ ጨለመች

ፈ ፦ ብሂል ፈጠረ ሰማየ ወምድረ ፥ ጌታ ሰማይ እና ምድርን ፈጠረ

ፐ ፦ ብሂል ፓፓኤል ስሙ ለአምላክ ፥ ፓፓኤል የአምላክ ህቡዕ ስም

ትርጉማቸዉ ይሄን ይመስላል።

ስለዚህ ግእዝ የአዳም ቋንቋ ነው የሚለው መላምት የበለጠ ጥንካሬ አለው

______

Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

 
%d bloggers like this: