ምዕራባውያኑ ዔሳውያን እና ምስራቃውያኑ እስማኤላውያን ከጡት–ነካሾቹ ኢትዮጵያውያን ጋር በማበር በአገራችን እና በተዋሕዶ ክርስትና እምነት ላይ በጣም ትልቅ የሆነ ሤራ በመጠንሰስ ላይ ናቸው፤ ይህንንም አይደብቁትም፣ በግልጽ እየነገሩን ነው፦ የሉሲፈራውያኑ መጽሔት “Foreign Policy“ ሰሞኑን እባባዊ የሆኑ ጽሑፎችን በተከታታይ በማቅረብ ላይ ይገኛል። በዛሬው ዕለት „Don’t Let Ethiopia Become the Next Yugoslavia“ “ኢትዮጵያን የምትቀጥለው ዩጎዝላቪያ እንዳታደርጓት” በሚል ር ዕስ ሌላ የማታለያ ጽሑፍ ይዞ ቀርቧል። ይህ መጽሔት „Council on Foreign Relations“ በተሰኘው የኢሉሚናቲዎች ተቋም ነው የሚታተመው)።

ዩጎዝላቪያ ለመበታተን የበቃችው ኦርቶዶክስ ክርስቲያን የሆነችውን ሰርቢያን በማጥቃት ነበር። በአሜሪካና አውሮፓውያን ሤራ። ልክ አሁን ኦርቶዶክስ ሩሲያን ለመምታት በዩክሬይን እየጠነሰሱት እንዳለው ሤራ ማለት ነው። ባለፈው ገና ዋዜማ የዩክርየን ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ከእናቷ ከሩሲያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን በይፋ እንድትከፈል ተደርጓል። ያውም በገና ዋዜማ! ይህ ብዙ ያልተወራለት አሳዛኝ የታሪክ ክስተት ነበር።
በኢትዮጵያና ኤርትራም ይህን አይተናል፥ አይደል? ያው እንግዲህ ሉሲፈራውያኑ ላለፉት 50 ዓመታት የቀመሙትን ተንኮለኛ ሥራ በአገራችንም በማከናወን ላይ ናቸው። ሰሞኑን በይበልጥ የምናየው ነው!
ብዙዎቻችን እስካሁን በደንብ የተረዳነው አይመስለኝም፤ በትግርኛ ተናጋሪ ኢትዮጵያውያን ላይ እየተካሄደ ያለው የጥላቻ ዘመቻ ለተዋሕዶ ክርስትናችን የጀርባ አጥንት የሆነውን የአገራችንን ክፍል ለመምታት የታሰበ ዲያብሎሳዊ ሤራ ነው። ተዋሕዶ ነኝ የሚል ይህን በግልጽ ማየት ይኖርበታል። ዱሮ በጦርነትና ረሃብ በቀጥታ ተፈታተኑት፤ አሁን ደግሞ የራሳችንው ሰው እየተጠቀሙ ነው፤ የራሳችንን ፖለቲከኛ፣ የራሳችንን የቤተክርስቲያን አገልጋይ፣ የራሳችንን ፀሀፊና ጋዜጠኛ። ክርስቲያን ወገኖች ተጠንቀቁ! እንጠንቀቅ!
በተለይ በምዕራቡ ዓለም የምንገኝ ወገኖች፤ ከዛሬ ኅዳር ፯ እስከ ወሩ መጨረሻ ድረስ የዲያብሎስ ሠራዊት የክርስቶስ የሆነውን ሁሉ ከያቅጣጫው ያጠቃናል፤ ይህን የጨለማ ጊዜ ተግን በማድረግ በትምህርት ቤት፣ በሥራ ቦታ ወይም በመኖሪያ ቤቶች አካባቢ ቴክኖሎጂን በመጠቀም ጥቃት ለመፈጸም ይሻሉና ይህን አውቀን ለሌሊት ጸሎት እንዘጋጅ፣ ዳዊታችንን እንድገም። ዲያብሎስ ሥራው ሲነቃበት ካጠገባችን ይሸሻልና!
የሰይፈ ስላሴ ፀሎት ከክፉ ነገር ይጠብቀን!
እንኳን ለጥር ስላሴ በሰላም አደረሰን!
እ.አ.አ January 15, 2014 ዓ.ም ላይ በጦማሬ የቀረበ፦
በስመአብ ወወልድ ወመንፈሥ ቅዱስ፡ አሐዱ አምላክ፡ አሜን
“ዘመነ ስብከት” በታኅሣሥ ፰ እና በጥር ፲ ቀኖች መካከል ያሉት አራት የእሑድ ሰንበታት ከነሳምንታቶቻቸው፡ እያንዳንዳቸው በቅደም ተከተል፦
ተብለው የሚጠሩት ናቸው።
በእነዚህ ሰንበታትና ሳምንታት፦
እግዚአብሔር ወልድ በመንፈስ ቅዱስ ግብር በድንግል ማርያም ማሕፀን ተፀንሶ በፍጹም ሰውነት ከእርሷ ስለመወለዱ፡ የሰውነት አመጣጡም ለዓለሙ በደል ቤዛ ኾኖ የመሥዋዕትነት ዋጋን በመክፈል ፍጥረቱን ለማዳን ስለመኾኑ፡ “ኢየሱስ ክርስቶስ” በተባለበት ስሙም በምድር ላይ እየተመላለሰ፡ ከኃጢዓት በቀር እውነተኛውን ሰውኛ አኗኗር በመኖር ለሰው ልጆች ኹሉ ፍጹም አርአያነትን ስለማበርከቱ በነቢያት የተነገሩትን የእግዚአብሔርን ትንቢታዊ ቃላት በመጥቀስ ትምህርትና ምዕዳን (ምክር) ይሰጥባቸዋል፡ የተስፋ ዝማሬ ይሰማባችዋል፡ ስለሥጋዌ ምሥጢርም ይቅኔያት ማዕበል ይወርድባቸዋል።
እነዚህን አርእስት በመከተል “ፈኑ እዲክ እም አምርያም!..ፈኑ ብርሃነከ ወጽድቀከ…” ማለትም፡ “እጅህን ከሰማይ ላክ!.. ብርሃንህንና እውነትህን ላክ!” እያሉ የቀደሙት ሰዎች ወደፈጣሪያቸው ያቀርቡት የነበረው ያልተቋረጠ ልመና ተሰምቶላቸው፡ “እነ ውእቱ፡ ኖላዌ ‘ኔር!’” ማለትም ቸር ጠባቂ እኔ ነኝ!” የሚላቸውና “የእግዚአብሔር ቀኝ እጅ“፡ እውነተኛው የዓለም ብርሃን የተባለው ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እነሆ “ሰው ኾኖ በድንግል ማሕፀን ተፀነሰ ተወለደ እንደሰው በምድር ላይ ተመላለሰ!” በማለት በመንፈስ ወደኋላ ተመልሰን የነቢያትን የተስፋ ጉዞ ከፈጸምን በኋላ ከጥምቀቱ በዓል እንደርሳለን።
የጥር ሥላሴ
ከበዓለ ጥምቀት በፊት ግን ጥቂት ቀደም ብሎ፡ በጥር ፯ ቀን፡ “የጥር ሥላሴ” በዓል ይከበራል። ይህም የኾነው በታኅሣስ ፩ ቀን በሚውለው በየሱስ ክርስቶስ ትስብእት፡ ማለትም አምላክ ሰው ኾኖ በድንግል ማርያም ማሕፀን በመፀነሱ የእግዚአብሔር የአንድነቱና የሦስትነቱ ምሥጢር ስለተገለጸ፡ ስለታወቀና ስለተረዳ የምስጢረ ሥላሴና የምስጢረ ሥጋዌ ነገር በሰፊው እየተነገረ ትምህርቱ እንዲሰጥበት ምሥጢሩም እንዲፍታታበት ታስቦ ነው።
ምንጭ፦ “ኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያዊነት” ኹለተኛ መጽሓፍ
ለ አባታችን ንቡረ ንቡረ እድ ኤርምያስ ከበደ ወልደ ኢየሱስ፡ ነፍሳቸውን በገነት ያኑርልን! ኢትዮጵያ አንድ በጣም ትልቅ ታታሪ ሰው ነው ያጣችው! እንዴት እንደሚናፍቁኝ…
______
Like this:
Like Loading...