ቃጠሎ በአውሮፓ፣ ድርቅ በአረቢያ፣ አውሎ ነፋስ በአሜሪካ…እራሳቸው የመረጧቸውን የኢትዮጵያ ቀለማት ተመልከቱ…
ብዙ ሚሊየን አሜሪካውያን በሚቀጥሉት ቀናት ፍሎሪዳ ዙሪያ ባሉት ግዛቶች ከዚህ በፊት ያልገጠማቸውንና “ዶሪያን” የተባለ ቅጽል ስም የተሰጠውን ኃይለኛ አውሎ ነፋስ ተሸብረው በመጠባበቅ ላይ ናቸው። ፕሬዚደንት ዶላንድ ትራምፕ፦ “ኃይለኛ አውሎ ንፋስ እየመጣብን ነውና ተዘጋጁ፣ እነዘጋጅ!” በማለት ዜጎችን አስጠንቅቀዋል። እነዚህ አዎል ነፋሶች አሜሪካውያንን በየጊዜው ስለሚያሸብሩ፡ የአውሎ ነፋሶቹን ሰፌድ በኑክሌር ቦንብ ለመምታት እስከ ማሰብ ድረስ ፕሬዚደንት ትራምፕ ደርሰዋል።
ለነዋሪዎቹ ሰላሙን ያምጣላቸው፤ ግን ከእናንተ የበለጠ የኃያሎች ኃያል አለ፡ የሚነፍሰውን እስትንፋሱን አትችሉትምና ኢትዮጵያን ባትነኳት ይሻላችኋል!!!