👉 ‘ከዚህም ነገር በኋላ ንጉሡ አርጤክስስ የአጋጋዊውን (ኦነጋዊውን) የሐመዳቱን (የአሕመድን) ልጅ ሐማን ከፍ ከፍ አደረገው’
በመጽሐፍ ቅዱስ የመጽሐፍ አስቴር ታሪክ ንግሥት አስቴር እና አጎቷ መርዶክዮስ ፤ ሐማ ተብሎ በሚጠራው ተንኮለኛ ፣ እብሪተኛና፣ ፀረ–አይሁድ/ፀረ–ሴማዊ በፋርስ ንጉሥ አርጤክስስ በተሾመ ባላባት ላይ ለአይሁድ ማንነታቸው እና ውርሻቸው እንዴት እንደቆሙ ይዘግባል፡፡
ከህንድ ጀምሮ እስከ ኢትዮጵያ ባሉ መቶ ሀያ ሰባት አገሮች ሲገዛ የነበረው የፋርስ ንጉሥ የአርጤክስስ ባሪያዎች ሁሉ ለሐማ ተደፍተው ይሰግዱ ነበር። አይሁዱ መርዶክዮስ ግን አልተደፋም፥ አልሰገደለትም። ታዲያ ሐማ መርዶክዮስ እንዳልተደፋለትና እንዳልሰገደለትም ባየ ጊዜ እጅግ ተቈጣ።። መርዶክዮስ እና አይሁድ ህዝቡ ስለ ሐማን ክብር፣ ቁመት እና ስልጣን ከሚያስቡት በላይ ሃይማኖታቸውን፣ እና እሴቶቻቸውን አብልጠው ስለሚወዱ ሐማ በጣም ይበሳጭ ነበር፡፡ ስለዚህ ሐማ በንጉሥ አርጤክስስ መንግሥት አገዛዝ ይኖሩ የነበሩትን አይሁዳውያኑን የመርዶክዮስን ሕዝብ ሁሉ ሊያጠፋቸው ወሰነ።
ንጉሥ አርጤክስስ ንግሥት አስቴርን ከልብ ይወዳት ነበር፤ ግን በፋርስ ስላደገች አይሁድ እንደሆነች አያውቅም ነበር፡፡ በተጨማሪም አሳዳጊዋ እና አይሁዳዊው አጎቷ መርዶክዮስ ንጉሡን ለመግደል እያሴሩ የነበሩትን ሁለት የንጉሡን ረዳቶች በማባረር የንጉሡን ሕይወት እንዳዳነውም ገና አላወቀም ነበር፡፡
ታሪኩን ለማሳጠር ፣ አስቴር በመጨረሻ ሐማ ማን/ምን እንደ ሆነና ምን እንዳቀደ ለንጉሥ አርጤክስስ ለመንገር እራሷን በቆራጥነት ማሳመን ነበረባት፡፡ እርሷም መርዶክዮስ ምናልባት ንግሥት የሆነችው “እንደዚህ ላለው ጊዜ” ሊሆን ይችላል ብሎ ስላሳመናት ይህን አደረገች፦
ሐማ የንጉሡን ሕይወት ያተረፈውን መርዶክዮስን ጨምሮ ሕዝቧን ሁሉ ለመግደል ቆርጦ እንደወጣ ለንጉሡ ደፍራ በተናገረች ጊዜ ወዲያውኑ ንጉሡ ወደ ሐማ በቁጣ ዞረበት፡፡ ብዙም ሳይቆይ ሐማ ለእርሱ የማይሰግደውን መርዶክዮስን ለመስቀል ሲል እራሱ በሠራው ግንድ ላይ እንዲሰቀል ንጉሡ ትዕዛዝ ሰጥቶ ሐማ እንዲሰቀል ተደረገ፡፡
ድንቁ የአስቴር ታሪክ አንዳንድ ትምህርቶችን ይጠቁመናል ፥ እንዲሁም አንዳንድ ትይዩዎችን ያሳየናል፡፡ ቆሻሻው ግራኝ አብዮት አህመድ እንኳን በአቅሙ ለእርሱ የማይሰግድሉተን ሁሉ አግቷቸዋል፣ ገደሏቸዋል፤ መጨረሻ የቀሩት ትግሬዎቹ ነበሩ፤ ስለዚህ ባጭር ጊዜ ውስጥ ፊቱን ወደእነርሱ አዞረ፤ ዘራቸውን ሁሉ ለማጥፋትም ዘመተ። መጨረሻው ምን ሊሆን እንደሚችል መጽሐፍ አስቴር ጠቁሞናል። ይህ የሉሲፈር አሽከር የእባብነት ቆዳ ቀይሮ ሕዝቡን ሊገዛ የተገሰለ ጨካኝ አላጋጭ ነውና እንደ ሐማ ክፉ አሟሟትን ይሞታል፤ ወደ ምድር ጥልቅም ይገባል።
[መጽሐፈ አስቴር ምዕራፍ ፫]
፩ ከዚህም ነገር በኋላ ንጉሡ አርጤክስስ የአጋጋዊውን የሐመዳቱን ልጅ ሐማን ከፍ ከፍ አደረገው፥ አከበረውም፥ ወንበሩንም ከእርሱ ጋር ከነበሩት አዛውንት ሁሉ በላይ አደረገለት።
፪ ንጉሡም ስለ እርሱ እንዲሁ አዝዞ ነበርና በንጉሡ በር ያሉት የንጉሡ ባሪያዎች ሁሉ ተደፍተው ለሐማ ይሰግዱ ነበር። መርዶክዮስ ግን አልተደፋም፥ አልሰገደለትም።
፫ በንጉሡም በር ያሉት የንጉሡ ባሪያዎች መርዶክዮስን። የንጉሡን ትእዛዝ ለምን ትተላለፋለህ? አሉት።
፬ ይህንም ዕለት ዕለት እየተናገሩ እርሱ ባልሰማቸው ጊዜ አይሁዳዊ እንደ ሆነ ነግሮአቸው ነበርና የመርዶክዮስ ነገር እንዴት እንደ ሆነ ያዩ ዘንድ ለሐማ ነገሩት።
፭ ሐማም መርዶክዮስ እንዳልተደፋለት እንዳልሰገደለትም ባየ ጊዜ እጅግ ተቈጣ።
፮ የመርዶክዮስን ወገን ነግረውት ነበርና በመርዶክዮስ ብቻ እጁን ይጭን ዘንድ በዓይኑ ተናቀ፤ ሐማም በአርጤክስስ መንግሥት ሁሉ የነበሩትን የመርዶክዮስን ሕዝብ አይሁድን ሁሉ ሊያጠፋ ፈለገ።
፯ በንጉሡም በአርጤክስስ በአሥራ ሁለተኛው ዓመት ከመጀመሪያው ወር ከኒሳን ጀምሮ በየዕለቱና በየወሩ እስከ አሥራ ሁለተኛው ወር እስከ አዳር ድረስ በሐማ ፊት ፉር የተባለውን ዕጣ ይጥሉ ነበር።
፰ ሐማም ንጉሡን አርጤክስስን። አንድ ሕዝብ በአሕዛብ መካከል በመንግሥትህ አገሮች ሁሉ ተበትነዋል፤ ሕጋቸውም ከሕዝቡ ሁሉ ሕግ የተለየ ነው፥ የንጉሡንም ሕግ አይጠብቁም፤ ንጉሡም ይተዋቸው ዘንድ አይገባውም።
፱ ንጉሡም ቢፈቅድ እንዲጠፉ ይጻፍ፤ እኔም ወደ ንጉሡ ግምጃ ቤት ያገቡት ዘንድ አሥር ሺህ መክሊት ብር የንጉሡን ሥራ በሚሠሩት እጅ እመዝናለሁ አለው።
፲ ንጉሡም ቀለበቱን ከእጁ አወለቀ፥ ለአይሁድም ጠላት ለአጋጋዊው ለሐመዳቱ ልጅ ለሐማ ሰጠው።
፲፩ ንጉሡም ሐማን። ደስ የሚያሰኝህን ነገር ታደርግባቸው ዘንድ ብሩም ሕዝቡም ለአንተ ተሰጥቶሃል አለው።
፲፪ በመጀመሪያውም ወር ከወሩም በአሥራ ሦስተኛው ቀን የንጉሡ ጸሐፊዎች ተጠሩ፤ ከህንድ ጀምሮ እስከ ኢትዮጵያ ድረስ ወዳሉ መቶ ሀያ ሰባት አገሮች፥ በየአገሩ ወዳሉ ሹማምትና አለቆች ወደ አሕዛብም ሁሉ ገዢዎች እንደ ቋንቋቸው በንጉሡ በአርጤክስስ ቃል ሐማ እንዳዘዘ ተጻፈ፥ በንጉሡም ቀለበት ታተመ።
፲፫ በአሥራ ሁለተኛው ወር በአዳር በአሥራ ሦስተኛው ቀን አይሁድን ሁሉ፥ ልጆችንና ሽማግሌዎችን፥ ሕፃናቶችንና ሴቶችን፥ በአንድ ቀን ያጠፉና ይገድሉ ዘንድ፥ ይደመስሱም ዘንድ፥ ምርኮአቸውንም ይዘርፉ ዘንድ ደብዳቤዎች በመልእክተኞች እጅ ወደ ንጉሡ አገሮች ሁሉ ተላኩ።
፲፬ በዚያም ቀን ይዘጋጁ ዘንድ የደብዳቤው ቅጅ በየአገሩ ላሉ አሕዛብ ሁሉ ታወጀ።
፲፭ መልእክተኞቹም በንጉሡ ትእዛዝ እየቸኰሉ ሄዱ፥ አዋጁም በሱሳ ግንብ ተነገረ። ንጉሡና ሐማ ሊጠጡ ተቀመጡ፤ ከተማይቱ ሱሳ ግን ተደናገጠች።
[መጽሐፈ አስቴር ምዕራፍ ፯]
፩ ንጉሡና ሐማም ከንግሥቲቱ ከአስቴር ጋር ለመጠጣት መጡ።
፪ በሁለተኛውም ቀን ንጉሡ በወይኑ ጠጅ ግብዣ ሳለ አስቴርን። ንግሥት አስቴር ሆይ፥ የምትለምኚኝ ምንድር ነው? ይሰጥሻል፤ የምትሺውስ ምንድር ነው? እስከ መንግሥቴ እኵሌታ እንኳ ቢሆን ይደረግልሻል አላት።
፫ ንግሥቲቱም አስቴር መልሳ። ንጉሥ ሆይ፥ በአንተ ዘንድ ሞገስ አግኝቼ እንደ ሆነ፥ ንጉሡንም ደስ ቢያሰኘው፥ ሕይወቴ በልመናዬ ሕዝቤም በመሻቴ ይሰጠኝ፤
፬ እኔና ሕዝቤ ለመጥፋትና ለመገደል ለመደምሰስም ተሸጠናልና። ባርያዎች ልንሆን ተሸጠን እንደ ሆነ ዝም ባልሁ ነበር፤ የሆነ ሆኖ ጠላቱ የንጉሡን ጉዳት ለማቅናት ባልቻለም ነበር አለች።
፭ ንጉሡም አርጤክስስ ንግሥቲቱን አስቴርን። ይህን ያደርግ ዘንድ በልቡ የደፈረ ማን ነው? እርሱስ ወዴት ነው? ብሎ ተናገራት።
፮ አስቴርም። ያ ጠላትና ባለጋራ ሰው ክፉው ሐማ ነው አለች። ሐማም በንጉሡና በንግሥቲቱ ፊት ደነገጠ።
፯ ንጉሡም ተቈጥቶ የወይን ጠጅ ከመጠጣቱ ተነሣ፥ ወደ ንጉሡም ቤት አታክልት ውስጥ ሄደ። ሐማም ከንጉሡ ዘንድ ክፉ ነገር እንደ ታሰበበት አይቶአልና ከንግሥቲቱ ከአስቴር ሕይወቱን ይለምን ዘንድ ቆመ።
፰ ንጉሡም ከቤቱ አታክልት ወደ ወይን ጠጁ ግብዣ ስፍራ ተመለሰ፤ ሐማም አስቴር ባለችበት አልጋ ላይ ወድቆ ነበር። ንጉሡም። ደግሞ በቤቴ በእኔ ፊት ንግሥቲቱን ይጋፋታልን? አለ። ይህም ቃል ከንጉሡ አፍ በወጣ ጊዜ የሐማን ፊት ሸፈኑት።
፱ በንጉሡም ፊት ካሉት ጃንደረቦች አንዱ ሐርቦና። እነሆ ሐማ ለንጉሡ በጎ ለተናገረው ለመርዶክዮስ ያሠራው ርዝመቱ አምሳ ክንድ የሆነው ግንድ በሐማን ቤት ተተክሎአል አለ። ንጉሡም። በእርሱ ላይ ስቀሉት አለ።
፲ ሐማንም ለመርዶክዮስ ባዘጋጀው ግንድ ላይ ሰቀሉት፤ በዚያም ጊዜ የንጉሡ ቍጣ በረደ።
_______________________
Like this:
Like Loading...