[ኦሪት ዘፍጥረት ምዕራፍ ፬፥፰፡፲፩]
“ቃየልም ወንድሙን አቤልን። ና ወደ ሜዳ እንሂድ አለው። በሜዳም ሳሉ ቃየል በወንድሙ በአቤል ላይ ተነሣበት፥ ገደለውም። እግዚአብሔርም ቃየልን አለው። ወንድምህ አቤል ወዴት ነው? እርሱም አለ። አላውቅም፤ የወንድሜ ጠባቂው እኔ ነኝን? አለውም። ምን አደረግህ? የወንድምህ የደሙ ድምፅ ከምድር ወደ እኔ ይጮኻል። አሁንም የወንድምህን ደም ከእጅህ ለመቀበል አፍዋን በከፈተች በምድር ላይ አንተ የተረገምህ ነህ።”
ከዳግማዊ ግራኝ፣ ዳግማዊ ቃየል አህመድ አፍም ልክ የቃየልን ዓይነት አነጋገር በተደጋጋሚ በመስማት ላይ ነን፦
👉 “አንድ ስመኘው በቀለ የሚባል ሰው ሞተ…አልውቀውም እኮ…”
👉 “እኔ ቤተ ክርስቲያን አላቃጠልኩም: ካህናትን አልገደልኩም: ግፍ አልሰራሁም ስለዚህ ይቅርታ አልጠይቅም”
👉 “አላየሁም አልሰማሁም!” (ለገጣፎ ለይ የድሆች ቤት በጠራራ ፀሀይ በቡልዶዘር ሲፈራርስና ሲደረመስ)
👉 “እኔ የከተማ አስተዳዳሪ አይደለሁም”