ከመደበኛ ወደ ኮንትራት በረራ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ኒው ኦርሊንስ መደበኛ በረራ የለውም። ዛሬ ግን አራት አውሮፕላኖች የከተማዋን አየር ማረፊያ ሞልተውት ታይተዋል። አየር መንገዱ ከመደበኛ በረራ ወደ ቻርተር/ኮንትራት በረራ ተሸጋግሯል ማለት ነው።
በደቡቡ ዩ.ኤስ.አሜሪካ ሉዊዚያና ግዛት የምትገኘዋ ኒው ኦርሊንስ በፈረንሳዮች የተቆረቆረች ሲሆን በአፍሪቃውያን የባርነት ንግድ ዘመን ከፍተኛ ሚና የተጫወተች ከተማ ናት። ከተማዋ መጀመሪያ የምትታወቀው በጃዝ ሙዚቃ ነበር፤ ቀስበቀስ ግን የስካር፣ የሽርሙጥና፣ የዕጽ ተገዢዎችና የግብረ–ሰዶማውያን መናኸሪያ ለመሆን በቅታለች። ለዚህም ይመስላል እ.አ.አ በ2005 ዓ.ም ከኢትዮጵያ ተራሮች የተነሳው ምስጢራዊ ነፋስ “ካትሪና” የተባለውን ኃይለኛ አውሎ ንፋስ ሠርቶ ኒው ኦርሊንስ ክፉኛ የመታት። 1400 ሰዎች ህይወታቸውን ሲያጡ በ90ቢሊየን ዶላር የሚገመት ንብረትም ወድሞ ነበር። ካትሪና – ኮሮና
በዛሬው ዕለት እንደታወቀው ኒው ኦርሊንስ በኮሮና ወረርሽ ከኒው ዮርክ ቀጥላ እየተጠቃች ያለች ከተማ ለመሆን በቅታለች።
ሆን ተብሎ ይመስላል፤ አየር መንገዳችንም ኮሮናን ተክትሎ መብረሩን ቀጥሏል። ይህ ለገንዘብ ብቻ ተብሎ የሚደረግ ነገር አይደለም፤ ከበስተጀርባው እጅግ በጣም ከፍተኛ ተንኮል አለ።