✝✝✝[ወደ ኤፌሶን ሰዎች ምዕራፍ ፭፥፲፩፡፲፫]✝✝✝
“ፍሬም ከሌለው ከጨለማ ሥራ ጋር አትተባበሩ፥ ይልቁን ግለጡት እንጂ፥ እነርሱ በስውር ስለሚያደርጉት መናገር እንኳ ነውር ነውና፤ ሁሉ ግን በብርሃን ሲገለጥ ይታያል፤ የሚታየው ሁሉ ብርሃን ነውና።”
✝✝✝[የያዕቆብ መልእክት ምዕራፍ ፭፳]✝✝✝
“ኃጢአተኛን ከተሳሳተበት መንገድ የሚመልሰው ነፍሱን ከሞት እንዲያድን፥ የኃጢአትንም ብዛት እንዲሸፍን ይወቅ።”
✝✝✝[ትንቢተ ሕዝቅኤል ምዕራፍ ፫፥፲፰፡፲፱]✝✝✝
“እኔ ኃጢአተኛውን። በእርግጥ ትሞታለህ ባልሁት ጊዜ፥ አንተም ባታስጠነቅቀው ነፍሱም እንድትድን ከክፉ መንገዱ ይመለስ ዘንድ ለኃጢአተኛው አስጠንቅቀህ ባትነግረው፥ ያ ኃጢአተኛ በኃጢአት ይሞታል፤ ደሙን ግን ከእጅህ እፈልጋለሁ። ነገር ግን አንተ ኃጢአተኛውን ብታስጠነቅቅ እርሱም ከኃጢአቱና ከክፉ መንገዱ ባይመለስ፥ በኃጢአቱ ይሞታል፥ አንተ ግን ነፍስህን አድነሃል።”
💭 በስልክ ካሜራ የተቀረፀው ይህ ምስል የውቅሮ አማኑኤል ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን በቦምብ ሲደበደብ ያሳያል። ጥንታዊው ቤተክርስቲያም በታዋቂው የአጋንንት መሰባሰቢያ፤ ‘ነጋሽ (አል–ነጃሺ) መስጊድ‘ አቅራቢያ ባለ አንድ ኮረብታ ላይ ይገኛል።
ቀረፃውን ያደረገው ግለሰብ እንደገለጸው ቤተክርስቲያኑ ህዳር ፲፭ /፳፻፲፫ ዓ.ም (የነብያት ጾም መግቢያ ፥ ልክ በዚሁ ዕለት በግብጽም አንድ ቤተክርስቲያን ላይ መሀመዳውያኑ ጥቃት አድርሰው ነበር) ፤ በታንኮች በተተኮሰው ጥይት ተመታ። ቤተክርስቲያኑም፤ ግለሰቡ ታክሎ፤ ፲፯/17 ጊዜ ተመታ ፣ ግን ሁሉም ግባቸውን አልመቱም ፣ የተወሰኑት ወደ ኮረብታው አረፉ። ሰውዬው አክለውም ጥቃቱ የተከናወነው ከቅርብ ርቀት አይቼዋለሁ ባሉት የኤርትራ ጦር ነው ብለዋል። በቪዲዮው ውስጥ አንድ ድምጽ “መድኃኔ አለም አዲ ቄሾም እንዲሁ ተደብድቧል” የሚል ድምጽ ተሰምቷል።
ወራሪው ጦር ሆን ተብሎ የትግራይ ሃይማኖታዊ ቦታዎችን ዒላማ ማድረጉን ከጦር ከወንጀለኛው ጄነራል ብርሃኑ ቁራ ጁላ አፍ ሰምተነው ነበር። በማሪያም ደንገላት ቤተክርስቲያን፣ በውቅሮ ጨርቆስ እና በአክሱም ጽዮን ማሪያም ላይ የተደረጉት ጭፍጨፋዎች እንደሚያሳዩት እጅግ በጣም አሰቃቂ ግድያዎችም በአብያተ ክርስቲያናት ውስጥ መፈጸማቸውን ነው።
እንግዲህ ይታየን፤ ይህ ቪዲዮ የተቀረጸውና የተላከው ሕወሓቶች “በተንቤን ተራራ ዋሻዎች ተደብቀው ነበር” በተባለበት ወቅትና ፋሺስቶቹ የኦሮሞ አገዛዝ ወራሪዎች መቀሌን በሚቆጣጠሩበት ወቅት ነበር። ከአሁኑ ጋር ሲነፃፀር ያኔ በጣም ብዙ መረጃዎች ይወጡ ነበር። የሰማዕታት ስም ዝርዝር ሳይቀር።
ሕወሓት ወደ መቀሌ እንዲመለስ ከተደረገበት ዕለት አንስቶ ግን በኅዳር ጽዮን በአክሱም ጽዮን ቤተ ክርስቲያን ላይ የሉሲፈርን/ቻይናን ባንዲራ ሰቅለው እና “ምርኮኞች” ልደታቸውን በኬክና ማንጎ ጭማቂ ሲያከብሩ ከሚያሳዩት ቪዲዮዎች ሌላ ስለ አክሱም ጽዮንም ሆነ እንደ ቅዱስ አማኑኤል ስላሉት ጥንታውያን ዓብያተክርስቲያናትና ገዳማት ይዞታ ምንም የላኩት ቪዲዮ ወይም ያሳወቁት መረጃ የለም። ስለ ጽዮን ዝም ብለዋል! ለምን? አሁን መልሱን በደንብ የምናውቀው ይመስለኛል።
እስካሁን በአጥጋቢ መልስ ያጣሁለት አንድ ጥያቄ፤ እንዴት አንድ “ክርስቲያን ነኝ! ኢትዮጵያዊ ነኝ! ስለ ጽዮን ዝም አልልም!” የሚል ወገን ከአረብ፣ ከቱርክ፣ ከኢራን፣ ከሶማሌ እና ከቤን አሜር አህዛብ ጎን ተሰልፎ በክርስቲያን አባቶቹ፣ እናቶቹ፣ ወንድሞቹና እኅቶቹ ላይ፣ እንዲሁም በዓብያተ ክርስቲያናቱና ገዳማቱ ላይ ጥቃት ሊፈጽም ቻለ? የሚለው ጥያቄ ነው።
🔥 ግን የሁሉም ጊዜያቸው እያለቀ ነው፤ በቅዱሷ አክሱም ጽዮን ጭፍጨፋውን የፈጸመውን + የደገፈውን ሁሉ እግዚአብሔር በቅርቡ ይበቀለዋል! ዛሬ “ኢትዮጵያዊ ነኝ” ባይ ግብዝ ሁሉ ጥቁር ለብሶ ማልቀስ፣ መለመንና ይቅርታ መጠየቅ ነበረበት!
✞✞✞[የዮሐንስ ራእይ ምዕራፍ ፳፪፥፲፪]✞✞✞
“እነሆ፥ በቶሎ እመጣለሁ፥ ለእያንዳንዱም እንደ ሥራው መጠን እከፍል ዘንድ ዋጋዬ ከእኔ ጋር አለ።”
- ❖ አክሱም ጽዮንን የደፈረ ሰላም፣ ዕረፍትና እንቅልፍ የለውም✞
- ❖ ከዋልድባ ገዳም ፩ሺህ መነኮሳትን ዓምና ልከ በዚህ ጾመ ሑዳዴ ያባረረውንና ድርጊቱንም የደገፈውን ሁሉ እግዚአብሔር በቅርቡ ይበቀለዋል
- ❖ በደብረ አባይ ገዳም ጭፍጨፋውን የፈጸመውን + የደገፈውን ሁሉ እግዚአብሔር በቅርቡ ይበቀለዋል
- ❖ በደንገላት ቅድስት ማርያም ጭፍጨፋውን የፈጸመውን + የደገፈውን ሁሉ እግዚአብሔር በቅርቡ ይበቀለዋል
- ❖ በደብረ ዳሞ አቡነ አረጋዊ ጭፍጨፋውን የፈጸመውን + የደገፈውን ሁሉ እግዚአብሔር በቅርቡ ይበቀለዋል
- ❖ በውቅሮ አማኑኤል ጭፍጨፋውን የፈጸመውን + የደገፈውን ሁሉ እግዚአብሔር በቅርቡ ይበቀለዋል
- ❖ በዛላምበሳ ጨርቆስ ጭፍጨፋውን የፈጸመውን + የደገፈውን ሁሉ እግዚአብሔር በቅርቡ ይበቀለዋል
- ❖ በዛላምበሳ ጨርቆስ ጭፍጨፋውን የፈጸመውን + የደገፈውን ሁሉ እግዚአብሔር በቅርቡ ይበቀለዋል
✞ የድንግል ልጅ ስሞቹ ፦ ቃል፣ወልድ፣አማኑኤል፣ኢየሱስ, ክርስቶስ፣መድኃኔ አለም። ስሆኑ ትርጓመያቸውም፦
❖ #ቃልማለት፦ አንደቤት መናገርያ ማለት ስሆን ከ፫(3)ቱ አካላት አንዱ እግዚአብሔር #ወልድበህልውነት/በመሆን ግብሩ የ #አብእና የ #መንፈስቅዱስ ቃላቸው ስሆን የእግዚአብሔር ቃል ይባላል። ራእይ ፲፱፥፲፫ “በደም የታለሰ ልብስም ለብሶአል ስሙንም “ቃል እግዚአብሔር” አሉት። ቍላስ.፩፥፲፮ “በእርሱ ቃልነት እግዚአብሔር ሁሉን ፈጥሮአልና….”
❖ #ወልድማለት፦ ከ፫(3)ቱ አካላት ፩(1)ዱ ወልድ ስሆን ልጅ ማለት ነው የ #ወልድአካላዊ ግብሩ መወለድ ማለት ነው የ #አብየባሕርይ ልጅ ስለሆነ እግዚአብሔር ወልድ ይባላል። ገላ.፬፥፬+ዮሐ.ወ ፭፥፲፮+ማቴ ፫፥፲፯…
❖ #አማኑኤልማለት፦ እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ሆነ ማለት ነው። ማቴ ፩፥፳፫። ይህን በት.ኢሳ ፯፥፲፬ላይ ስሙን እናገኛለን። ይህ ማለት ከድንግል በተዋህደው ተዋህዶ አምላክ ሰው ሆነ ዮሐ.፲፥፲፬…….. ፩ኛ ቆሮ ፲፭፥፳፩አዳምን የመጀመርያው ሰው ይላል ክርስቶስን ደግሞ ሁለተኛው ሰው ይለዋል።
❖ #ኢየሱስማለት፦ መድኃኒት ማለት ነው ይህን መጽሐፍ ቅዱስም ይናገራል ሉቃስ ፪፥፲፩”እነሆ ዛሬ በዳዊት ከተማ መድኃኒት ተወልዶላችኃል” እንዳለ መልአኩ ለእረኞች….
❖ #ክርስቶስማለት፦ “ቅቡ /የተቀባ” ማለት ነው። በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስትያን እና በመሰሎቿ አብያተ ቤተክርስትያናት “የተዋሃደ” ተብሎ ይተረጉማል።
❖ #መድኃኒአለምማለት፦ የአለም መድኃኒት ማለት ነው። በእርሱ አለም ስለዳነ (በሞቱ አለምን ስላዳነ) መድኃኒአለም የአለም መድሃኒት እንለዋለን። ሉቃስ ፪፥፲፩ላይ እኔሆ ለሕዝብ ሁሉ የምሆን መድኃኒት እንዳላለ ሉቃስ፤ ዮሐ.ወ ፩፥፳፱ ላይ መጥምቁ ዮሐንስ “እነሆ የአለምን ኃጢአት የምያስወግድ የእግዚአብሔር በግ” እንዳለው እንደገና በሮሜ ፭፥፲፪፡፳፩ስናነብ በአንድ ሰው በአዳም ምክንያት ሞት ወደ አለም እንደመጣ ሁሉ በአንዱ በኢየሱስ ክርስቶስ ሞትም አለም እንደዳነ ይናገራል…………..
እኛ ኦርቶዶክሳዊያን በነዚህ ስሞች አምላካችን ጌታችንና መድኃኒታችንን እናከብረዋለን እንጠራዋለን እናመልከዋለን ። “ኢየሱስ ብቻ ስሙ ነው ሌሎችን ከየት አመጣችሁ ለምን ባለወልድ አማኑኤል መድሃኒአለም እያላቹ ትጠሩታላችሁ ኢየሱስ ማለት ብቻ እንጅ” የምሉ ወገኖቻችን አሉና እነዚህን ስሞችን እኛ ኦርቶዶክሶች ፈጥረንለት ሳይሆን መጽሐፍ ቅዱሱ እራሱ እንደምጠራው መገናዘብ ይገባናል። ለስም አጠራሩ ክብርና ምስጋና ይድረሰው የእኛ ጌታ የድንግል ማርያም ልጅ ጌታችን መድኅኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ። ክብር ለወለደችው ለድንግል!!!
______________